25/01/2025
✨ አንድ ሚስት ባልዋን እሱ ዘንድ ተወዳጅ በሆነ ቅፅል ስም ልትጠራው ይገባል ይላሉ፡ ሸይኽ ዶ /ር ሱለይማን አር-ሩሀይሊ።
ኡሙ ደርዳእ ባስተላለፈችው ሀዲስ፡ ባለቤቷን አቡ ደርዳእን ሰይዲ/አለቃዬ ብላ ነው የጠራችው።
ከታዕብዮች ሚስት አንዷ፡ "እኛ ባሎቻችን ልክ እናንተ ባለስልጣኖችን እንደምታናግሩ እንጂ አናናግርም" ብላለች።
✨ ስለዚህ ባለቤቷ ዘንድ መከበርን፡ መወደድን የፈለገች ሴት ባልዋን፡ የኔ ውድ/የኔ ማር/ የኔ ጣፋጭ... እያለች በሚያስደስተው ቅፅል ስም ትጠራለች እንጂ፡ ስማ/አንተ.. እያለች አትጣራም።