Amu.

Amu. It's legally my fb page thank you all.

02/12/2023

ወልቀ መላኺ ኢሳያስ ኣፈ ወርቂ ንውዕሊ ፕሪቶርያ ቶኹሲ ደው ምባል ዕንቅፋት ኮይኑ ኣሎ።

ኮንግረስ ማን ጆን ጀምስ

ኣባል ኮንግረስ ኣሜሪካ ጆን ጀምስ ነዚ ዝበሉ ጉዳይ ኢትዮጵያ ኣመልኪቱ መፅበዓ ወይ ሓደጋታት ሃለዋት ፓሊሲ ኣሜሪካ ብዝብል ኣብ ዝተሳለጠ ዘተን ምድማፅን እዩ።

እቶም ኣባል ኮንግረስ ሰራዊት ውልቀ መላኺ ኢሳያስ ኣፈ ወርቂ ግዝኣት ትግራይ ብሓይሊ ወሪሩ ምሓዙን፣ ሰራዊት ኤርትራ ጃምላ ጨፍጫፍ ንፁሃት ተጋሩ፣ ፃታዊ ጥቕዓት ከምኡ እውን ጥሕሰት ሰብኣዊ መሰላትን ዘስካሕክሑ ግፍዕታት ኣብ ልዕሊ ተጋሩ ፈፂሙን እናፈፀመ ከምዝርከብን ኣብራህሪሆም።

25/11/2023

Shout out to my newest followers! Excited to have you onboard! Wedi Mhrey Mhrey, Aregawi Tesfay, Meron Haftu That you very much all.

24/11/2023

Shout out to my newest followers! Excited to have you onboard! Wedi Mhrey Mhrey, Aregawi Tesfay, Meron Haftu

09/06/2020

ስለተመለከታችሁን እናመሰግናለን ቪዲዮውን ሼር በማድረግ እናንተ ያገኛችሁትን እውቀት ለሌሎች አሳውቁ። ይህንን የአክሱም ቲዩብ ዝግጅት ዳውንሎድ አድርጎ ድጋሚ በሌላ ቻናል ላይ መጫን ...

09/06/2020

the satnael goal in ethiopia axum tube የአለም መጨረሻ ሰላም የሀገሬ ልጆች እንደምን አላችሁ ሀሳብ አስትያየታችሁን ስጡን እንዲሁም ሼር በማድረግ ይተባበሩን ፣ እናመስግናለን ቻናሉን ሰብስክራብ በማ...

13/04/2020

✝️⛪️✝️🌳🌻🌹ቃለ እግዝአብሔር ናብ ኩሉ ሕዝበ ክርስትያን ምእንቲ ክበጽሕን ከምኡውን ቋንቋ ትግርኛ ምእንቲ ክሰፍሕ share share share ብምግባር መንፈሳዊ ግዴታና ንዋጻእ።
''ተዛረብ ደአምበር ስቅ አይትበል።''ሓዋ.18፡9 🌴💐🌸✝️⛪️✝️⛪️✝️
✝️⛪️✝️⛪️✝️🌳🌹🌻So that the word of The Lord grow multiply and reach all the end of the earth, do your spiritual responsibility by sharing; so please share share share🌺🎄🌻✝️⛪️

10/04/2020

በስመአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!
"ሰሞነ ህማማት "
✔Please ✔share ✔

ነው?
ሰሙነ ሕማማት ለምን ይታሰባል?
የሚከለከሉ ና የሚፈቀዱ ነገሮች ምንድን ናቸው? ለምን?
ሰሙነ ሕማማትን ከሌሎች የዐቢይ ጾም ሳምንታት ልዩ የሚያደርገው ሥርዓት አለ፡፡ በኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ዐቢያተ ክርስቲያናት ሥርዓትና ደንብ መሠረት በሰሙነ ሕማማት ከጸሎተ ሐሙስ በስተቀር ቅዳሴ አይቀደስም፤ ስብሐተ ነግህ አይደርስም፤ ጸሎተ ፍትሐት አይጸለይም፤ ጸሎተ አስተሥርዮም አይደረግም፡፡ እንዲሁም ጥምቀተ ክርስትናም አይፈጸምም፡፡ ከላይ የተዘረዘሩት የቤተክርስቲያን ሥርዓቶች አስቀድሞ በዕለተ ሆሳዕና ይከናወናሉ፡፡
በተጨማሪም ማንኛውም ክብረ በዓል በዚህ ሳምንት ቢውል ከትንሣኤ በኋላ እንዲከበር ይተላለፋል፡፡ ይህ ብያኔ በኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ዐቢያተ ክርስቲያናት ዘንድ የጸና መንፈሳዊ ሥርዓት ነው፡፡

ሕማምና ሞት የማይገዛው ጌታችንኢየሱስ ክርስቶስ የእኛን ሕማምና ሞትለራሱ በማድረግ በዚህ ሳምንትለእኛቤዛሆኗል፡፡‹ደዌያችንንተቀበለ፤ ሕማማችንንም ተሸከመ፤ ከዐመጸኞችምጋር ተቆጠረ፡፡እርሱግን ግፍን አላደረገም ተንኮልም ከክፉ አልተገኘበትም፡፡› (ኢሳ.42 4-12) ተብሎ እንተጻፈ፡፡ ምእመናን ክርስቶስ የተቀበለውን የእኛን ሕማም መሆኑን በማዘክር በሰሙነ ሕማማት ከማንኛውም የሥጋ ሥራ መታቀብ በዋዛ ፈዛዛ ባለመነጋገር፤ በሐዘን ልናከብረው ይገባል፤ ብድራትን የማያስቀረው አምላክም መተላለፋችንና በደላችንን በመደምሰስ የመንግሥቱ ወራሽ ያደርገናልና፡፡
ሰሙና ሕማማት እስከ አራተኛው ምዕተ ዓመት ድረስ ከጾሙ ተለይቶ ለብቻው ይከበር ነበር፡፡ በኋላ ግን በባሕረ ሐሳብ ቀመር መሠረት ጾሙም ሕማማቱም ትንሣኤውም ተያይዘው እንዲከበሩ ተደረገ፡፡ ምዕራባውያን ከአርባ ጾም ውስጥ የመጨረሻውን ሳምንት ሰሙና ሕማማት ያደርጉታል፡፡ የምሥራቃውያን /ኦሪየንታል/ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ዐቢያተ ክርስቲያናት የሆን ግን አርባውን ጾም ጨርሰን ከኒቆዲሞስ በኋላ ያለውን ተከታዩን አንድ ሳምንት ሰሙነ ሕማማት አድርገን እናከብራለን፡፡

"በህማማት የሚነሱ ጥያቄዎች እና መልሶቻቸው"
1. በህማማት ለምን መስቀል አንሳለምም ወይስ ለምን አናማትብም ?
የመስቀል ክብር እና ሐይል የታወቀው ጌታ በመስቀል ከተሰቀለ በሗላ ነው፡፡ በሰሞነ ህማማት ከሰኞ እስከ አርብ ያሉት ቀናት የአመተ ፍዳ መታሰቢያ ናቸው፡፡በነዚህ ዘመናት ሰዎች የመስቀልን አገልግሎት እንዳልጀመሩ ለማሳየት በሰሞነ ህማማት በቤተክርስቲያን ስርዓት መሰረት መስቀል መሳለምም ሆነ ማማተብ ስርዓት አይደለም፡፡ግን አነድ ሰዉ ተሳሰቶ ቢያማትብ ምንም በደልም ሐጢአትም አይሆንበትም።
2. በሰሞነ ህማማት ለምን አንሳሳምም?
ይሁዳ ጌታውን በመሳም አሳልፎ ሰጥቷል እኛ ግን እንደ ይሁዳ ክፋት ካለው መሳሳም መለየታችንን ለማስረዳት ከዚህም በተጨማሪ ሰላም በዘመነ ፍዳ እንዳልነበረ ለማሳየት በሰምነ ህማማት እስከ መሳሳም የደረሰ ጥብቅ ሰላምታ የለም፡፡
3. በሰሞነ ህማማት የማይደረጉ ሌሎች ነገሮች ምን ምን ናቸው? ማንኛውንም ለስጋ የሚያደሉ ተግባራትን መቀነስ እና ቢቻለን አብዛኛውን ጊዜያችንን የጌታን ህማም መከራ በማሰብ በፆም በፀሎት በስግደት ማሳለፍ ፤ቢቻል አመጋገባችንን ከወትሮው መቀነስ፤በትዳር ያሉ በፆም ወቅት በመኝታ ከመተዋወቅ መታቀብ አለባቸው፡፡
4.ታቦት ከመንበሩ አይነሳም ምንም የንግሰ በዓልም አይከበርም
5.ፍትሐት፣ክረሰትና የለም

6.ሰላምታ ያለባቸው ጸሎቶች ለምሳሌ መልክዓ ቅድሳን አይጸለይም ከሱ ይልቅ መዝሙረ ዳዊት ውዳሴ ማርያም ግብረ ሕማማት እና መጽሐፈ ማሕያዊ የተባለ ብዙ ቃልኪዳን ያለው የጌታን መከራ የሚያወሳ መጽሐፈ ጸሎት
ይነበባሉ

ሰሙነ ሕማማት ለምን ይታሰባል?
ሰሙነ ሕማማትን ከሌሎች የዐቢይ ጾም ሳምንታት ልዩ የሚያደርገው ሥርዓት አለ፡፡ በኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ዐቢያተ ክርስቲያናት ሥርዓትና ደንብ መሠረት በሰሙነ ሕማማት ከጸሎተ ሐሙስ በስተቀር ቅዳሴ አይቀደስም፤ ስብሐተ ነግህ አይደርስም፤ ጸሎተ ፍትሐት አይጸለይም፤ ጸሎተ አስተሥርዮም አይደረግም፡፡ እንዲሁም ጥምቀተ ክርስትናም አይፈጸምም፡፡ ከላይ የተዘረዘሩት የቤተክርስቲያን ሥርዓቶች አስቀድሞ በዕለተ ሆሳዕና ይከናወናሉ፡፡
በተጨማሪም ማንኛውም ክብረ በዓል በዚህ ሳምንት ቢውል ከትንሣኤ በኋላ እንዲከበር ይተላለፋል፡፡ ይህ ብያኔ በኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ዐቢያተ ክርስቲያናት ዘንድ የጸና መንፈሳዊ ሥርዓት ነው፡፡

ሕማምና ሞት የማይገዛው ጌታችንኢየሱስ ክርስቶስ የእኛን ሕማምና ሞትለራሱ በማድረግ በዚህ ሳምንትለእኛቤዛሆኗል፡፡‹ደዌያችንንተቀበለ፤ ሕማማችንንም ተሸከመ፤ ከዐመጸኞችምጋር ተቆጠረ፡፡እርሱግን ግፍን አላደረገም ተንኮልም ከክፉ አልተገኘበትም፡፡› (ኢሳ.42 4-12) ተብሎ እንተጻፈ፡፡ ምእመናን ክርስቶስ የተቀበለውን የእኛን ሕማም መሆኑን በማዘክር በሰሙነ ሕማማት ከማንኛውም የሥጋ ሥራ መታቀብ በዋዛ ፈዛዛ ባለመነጋገር፤ በሐዘን ልናከብረው ይገባል፤ ብድራትን የማያስቀረው አምላክም መተላለፋችንና በደላችንን በመደምሰስ የመንግሥቱ ወራሽ ያደርገናልና፡፡
ሰሙና ሕማማት እስከ አራተኛው ምዕተ ዓመት ድረስ ከጾሙ ተለይቶ ለብቻው ይከበር ነበር፡፡ በኋላ ግን በባሕረ ሐሳብ ቀመር መሠረት ጾሙም ሕማማቱም ትንሣኤውም ተያይዘው እንዲከበሩ ተደረገ፡፡ ምዕራባውያን ከአርባ ጾም ውስጥ የመጨረሻውን ሳምንት ሰሙና ሕማማት ያደርጉታል፡፡ የምሥራቃውያን /ኦሪየንታል/ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ዐቢያተ ክርስቲያናት የሆን ግን አርባውን ጾም ጨርሰን ከኒቆዲሞስ በኋላ ያለውን ተከታዩን አንድ ሳምንት ሰሙነ ሕማማት አድርገን እናከብራለን፡፡

በሰሙነ ህማማት ከሰኞ እስከ ቅዳሜ
የተከናወኑትን ተግባራት
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
† #ሰኞ
~~~
ጌታችን ከቢታንያ ሲወጣ ተራበ ቅጠል ያለባትን
በለስ ከሩቁ አይቶ በለሲቱን ቀረባት ነገር ግን
ከቅጠል በቀር ምንም አልተገኘባትም ከአሁን
ጀምሮ ማንም ከ አንች ፍሬን አይብላ ብሎ
እረገማት በለስ የተባሉ እስራኤላዊያን ናቸዉ፡፡..............
† #ማክሰኞ
~~~
ሻጮች እና ለዋጮችን ከቤተ
መቅደስ ባሶጣ ጊዜ ይኼንን በማን ኃይል
እንዳደረገዉ የአይሁድ መምህራን ጠይቀዉት
ነበር ማቴ 21-23
ስለሆነም የጥያቄ ቀን ይባላል፡፡..............
† #ረቡዕ
~~~
ምክረ አይሁድ ይባላል ምክንያቱም የአይሁድ
ሊቃነ ካህናት እና ጸሐፍት ጌታን እንዴት መያዝ
እንዳለባቸዉ ምክር ያጠናቀቁበት ቀን በመሆኑ..............
† #ሐሙስ
~~~
በቤተ ክርስቲያን የተለያየ
ስያሜዎች ያሏቸዉ በርካታ ድርጊቶች
የተፈጸሙበት ነዉ፡፡
|ጸሎተ ሐሙስ ይባላል፡
መድኃኒዓለም ክርስቶስ አይሁድ መጥተዉ
እስኪይዙት
ድረስ ሲጸልይ ያደረበት ነዉና ጸሎተ ሐሙስ
ተባለ
|ሕጽበተ ሐሙስ ይባላል፡-
ጌታችን በዚህ ዕለት የደቀ መዛሙርቱን እግር
ጎንበስ
ብሎ በታላቅ ትህትና አጥቧልና
|የሚስጢር ቀን ይባላል፡-
ከሰባቱ ምስጢራት አንዱ የሆነዉን ምስጢረ
ቁርባን በዚህ ዕለት ተመስርቷልና
|የሐዲስ ኪዳን ሐሙስ ይባላል፡-
ምክንያቱም የ ኦሪት መስዋዕት የሆነዉ
የእንስሳት ደም ማብቃቱን ገልጦ ለድህነተ
ዓለም ራሱን የተወደደ መስዋዕት አድርጎ
ያቀረበበት ዕለት በመሆኑ
|የነፃነት ሐሙስ ይባላል፡-
ምክንያቱም ለኃጢአትና ለዲያብሎስ ባርያ
መሆኑ ማብቃቱና የሰዉ ልጅ ያጣዉን ክብር
መልሶ ማግኘቱ የተረጋገጠበት ቀን
ስ� #ዓርብ ፡-
~~~
ጌታችን ከ ጲላጦስ አደባባይ እስከ ሊጦስጥራ
የተንገላታበት ለአዳምና ለልጆቹ በምልዕልተ
መስቀል ለሞት እራሱን አሳልፎ የሰጠበት ቀን
ነዉ፡፡..............
† #ቅዳሜ ፡-
~~~
|በዚች ዕለት የጌታችን መከራ
በማሰብ በጾም ታስባ ስለምትዉል ቅዳም
ሥዑር ወይም የተሻረችዉ ቅዳሜ
ትባላለች፡፡
|ካህናቱም ለምዕመናን ለምለም ቄጤማን
የሚያድሉበት ዕለት ስለሆነ ለምለም ቅዳሜም
ትባላለች፡፡
|እንደዚሁም ልዑል
እግዚአብሔር በዚህ ቀን 22ቱን ስነ ፍጥረታት
ፈጥሮ ከስራዉ ያረፈበት ዕለት በመሆኑ ቅ/
ቅዳሜ ይባላል፡፡
ከህማሙ ከመከራው በረከት ያሳፈን!!
በሰሙነ ሕማማት የሚፈጸሙ ሥርዓቶች

1.ስግደት:-በሰሙነ ሕማማት 41 ጊዜ ኪርያላይሶን 12 ጊዜ አቡነ ዘበሰማያት እየተዜመ እጅግ አብዝቶ ይሰገዳል::
2. ጸሎት:- በሰሙነ ሕማማት ከ24 ሰዓት ውስጥ 10 የጸሎትና የንባብ ሰዓታት ይገኛሉ እነዚህም ከጠዋቱ 1 ሰዓት; 3ሰዓት; 6ሰዓት; 9ሰዓት; 11ሰዓት እንዲሁም ከምሽቱ 1 ሰዓት; 3ሰዓት; 6ሰዓት; 9ሰዓት; 11ሰዓት ናቸው::
በነዚህም ሰዓታት የጌታን ስቃይ ለማዘከር መዝሙረ ዳዊትና ግብረ ሕማማት ድርሳነ ማኅያዊ አብዝተው ይጸለያሉ::
3.ጾም:-በሰሙነ ሕማማት ብዙ አዝማደ መባልዕት /አዘውትረን የምንመገባቸው ምግቦች/ አይበሉም:: በዚህም ሳምንት እስከ ምሽቱ አንድ ሰዓት እንድንጾም; ይኸውም ቆሎ;ዳቦ;ወኃና ጨው ብቻ እንደታዘዙ በግብረ ሕማማት ላይ ተጽፎ ይገኛል::
4.አለመሳሳም:-አይሁድ ጌታችንን ለመስቀል እየተንሾካሾኩ ስለተመካከሩና ይሁዳ ጌታችንን በመሳም አሳልፎ ስለሰጠው መሳሳም አይፈቀድም:: መስቀልም በዘመነ ኦሪት የወንጀለኛ መቅጫ የእርግማን ምልክት ስለ ነበር ጌታችን በክቡር ደሙ ቀድሶ የድል አርማ እስኪያደርግልን ድረስ አንሳለመውም ገላ. 3:13 ማቴ.10:38 ማቴ. 26:29
5.አክፍሎት:-እመቤታችን; ያዕቆብና ዮሐንስ የጌታችን ትንሳኤ ሳናይ እህልና ውኃ አንቀምስም ብለው እስከ ትንሳኤው መቆየታቸውን በማሰብ የሚጾም ነው::
6.ጉልባን:-ከባቄላ ከስንዴ ከገብስ የሚዘጋጅ በጸሎተ ሐሙስ ዕለት የሚበላ ንፍሮ ሲሆን ትውፊቱም የስቅለቱ ሐዘን መግለጫ ነው::
7.ጥብጠባ:-ይህ ምዕመናን በሰሙነ ሕማማት የፈጸሟቸውን ኃጢአቶች ለካህን እየተናዘዙ በወይራ ቅጠል ቸብቸብ እየተደረጉ ስግደት የሚቀበሉበት ነው:: ይህም የጌታ ምሳሌ ነው::
8.ቄጠማ:-ጌታችን ብርሃነ ትንሳኤዉን እንደገለጠልን የምናስብበት ሲሆን የእሾህ አክሊል በመድፋቱ ምሳሌም በራሳችን ላይ እናስረዋለን::

እንበለ ደዌ ወሕማም እንበለ ጻማ ወድካም
ያብጽሐነ ያብጽሕክሙ ለብርሃነ ትንሳኤሁ እግዚአብሔር በፍስሐ ወበሰላም::

10/04/2020

✍Corona virus update የ24_ሰዓት_የኮሮና_ቫይረስ_ስርጭትና_አጠቃላይ_ኬዝ ///share
ሐሙስ ሚያዚያ 01-2012 እስከ ጠዋቱ 3:00
────────
♨በጠቅላላ የኮሮና ቫይረስ ያጠቃቸዉ 1,518,927 ደርሰዋል
♨በአጠቃላይ የሟቾች ቁጥር 88,516 ሆኗል
♨በጠቅላላ ከቫይረሱ ያገገሙትም 330,697 ሆነዋል
♨በአጠቃላይ አሁን ቫይረሱ ያለባቸው ሰዎች 1,099,714 ናቸው
♨በአጠቃላይ በአሳሳቢ ደረጃ የሚገኙትም 48,087 ሰዎች ናቸው

♨በአሜሪካ እንደተለመደው በ24 ሰዓት በርካታ ሰው የሞተባት ቀዳሚዋ ሀገር ሆናለች (+1,940) ያስተናገደችው አዲስ ኬዝም +31,935 ነው። በአሜሪካ ጠቅላላ የሟቾች ቁጥር
ክስፔን በልጧል።
──────────────────
♨ብሪታኒያ በ24 ሰዓት ውስጥ በርካታ ሰው የሞተባት 2ኛዋ ሀገር ነች (+938) የአዲስ ተጠቂዎች ቁጥር +5,491 ሆኗል።
──────────────────
♨ስፔን ባለፉት 24 ሰዓት በርካታ ሰው የሞተባት 3ኛዋ ሀገር ነች (+747) ያገኘችው አዲስ ኬዝም +6,278 ነው።
─────────────────
♨በጣልያን ባለፉት 24 ሰዓት +542 ሰዎች ሲሞቱባት ተጨማሪ +3,836 አዲስ ኬዝ ማግኘቷን ሪፖርት አድርጋለች።
──────────────────
♨ፈረንሳይ በ24 ሰዓት በርካታ ሰው የሞተባት 5ኛዋ ሀገር ነች (+541) ፣ እንዲሁም +3,881 አዲስ ኬዝም አለባት።
─────────────────
♨ጀርመን በ24 ሰዓት ውስጥ +333 ሞት እና +5,633 አዲስ ኬዝ እንዳላት ታውቋል። አጠቃላይ ኬዟ 113,296 ሆኖ 4ኛ ላይ ስትቀመጥ ከሌሎች አንፃር የሟቾች ቁጥር አነስተኛ
ነው (2,349)
─────────────────
♨ቤልጅየም ባለፉት 24 ሰዓት በርካታ ሰው የሞተባት 7ኛዋ ሀገር ነች (+205) ተጨማሪ +1,209 አዲስ ኬዝ አስተናግዳለች።
────────────────
♨ኔዘርላንድ ባለፉት 24 ሰዓት በርካታ ሰው የሞተባት 8ኛ ዋ ሀገር ነች (+147) አዳዲስ ኬዝ +969 ሆኗል።
─────────────────
♨ብራዚል 24 ሰዓት በርካታ ሰው የሞተባት 9ኛዋ ሀገር ነች (+134) እንዲሁም ከላቲን አሜሪካ ሀገራት በርካታ የቫይረሱ ኬዝ ያለባት ሀገር ነች (16,188) በጠቅላላው
ያስተናገደችው ሞትም 820 ደርሷል።
──────────────────
♨በኢራን ባለፉት 24 ሰዓት በርካታ ሰው የሞተባት 10ኛ ሀገር ነች (+121) ያስተናገደችው አዲስ ኬዝም +1,997 ነው።
──────────────────
♨ቻይና ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ 2 ሰው የሞተባት ሲሆን 62 አዳስ ኬዝ እንዳላትም ሪፖርት ተደርጓል
──────────────────
♨በስዊድን በ24 ሰዓት 96 ሞትና 726 አዲስ ኬዝ
♨በቱርክ በ24 ሰዓት 87 ሞትና +4,117 አዲስ ኬዝ
♨በካናዳ በ24 ሰዓት +46 ሞትና +1,540 አዲስ ኬዝ
♨በስዊዘርላንድ በ24 ሰዓት 74 ሞትና +1,027 አዲስ ኬዝ
♨በደቡብ ኮሪያ በ24 ሰዓት 130 ሞትና 303 አዲስ ኬዝ
♨በህንድ በ24 ሰዓት 18 ሞትና +565
አዲስ ኬዝ
♨በራሺያ በ24 ሰዓት 5 ሞትና +1,175 አዲስ ኬዝ
♨በአውስትራሊያ በ24 ሰዓት 1 ሞትና 64 አዲስ ኬዝ
♨በጃፓን በ24 ሰዓት 1 ሞትና 410 አዲስ ኬዝ
──────────────────
♨በአህጉራችን ከፍተኛ ኬዝ ያለባት ደቡብ አፍሪካ ባለፉት 24 ሰዓት 96 አዲስ ኬዝና 5 ሞት ያስተናገደች ሲሆን በጠቅላላው 1,845 ኬዝና 18 ሞት አለባት።
─────────────────
♨አልጄሪያ በ24 ሰዓት ውስጥ ብቻ 12 ሰው ሲሞትባት 104 አዲስ ኬዝም አስተናግዳለች። አጠቃላይ 205 ሰው ሲሞትባት በአፍሪካ ከፍተኛው ነው።
─────────────────
♨ግብፅ ባለፉት 24 ሰዓት +110 አዳዲስ ኬዝ እና 9 ተጨማሪ ሞት የተገኘባት ሲሆን በጠቅላላው 103 ሞት አስተናግዳለች።
──────────────────
♨ሞሮኮ በ24 ሰዓት ውስጥ +91 የኮሮና ቫይረስ ኬዝ ያገኘችና 3 ተጨማሪ የሞት ሪፖርትም አላት። ጠቅላላ 93 ሰው ሞቶባታል።
♨በባህሬን በ24 ሰዓት +12 አዲስ ኬዝ ተመዝግቧል
♨በኳታር በ24 ሰዓት +153 አዲስ ኬዝ ተመዝግቧል
♨በሊባኖስ በ24 ሰዓት +28 አዲስ ኬዝ ተመዝግቧል
♨ኩዌት በ24 ሰዓት 112 አዲስ ኬዝ አስተናግዳለች
♨በካሜሮን በ24 ሰዓት +45 አዲስ ኬዝና 1 ሞት
♨ቱኒዚያ በ24 ሰዓት 1 ሞትና +5 አዲስ ኬዝ
♨በቡርኪናፋሶ በ24 ሰዓት +30 አዲስ ኬዝና 4 ሞት
♨በጋና በ24 ሰዓት 1 ሞትና 26 አዲስ ኬዝ
♨በማሊ በ24 ሰዓት 2 ሞትና 3 አዲስ ኬዝ
♨በላይቤሪያ በ24 ሰዓት 1 ሞትና 17 አዲስ ኬዝ
♨ሶማሌ ለሀገራ የመጀመሪያ የሆነ ሞት ትላንት አስመዝግባለች
♨ዚምቧቡዌ በ24 ሰዓት 1 ሞት አስመዝግባለች
♨በኬንያም በ24 ሰዓት 7 አዲስ ኬዝ ተገኝቷል
♨በጅቡቲ ትላንት ብቻ 45 አዲስ ኬዝ የተገኘ ሲሆን በጠቅላላው 135 የቫይረሱ ኬዝ አለባት
♨በርካታ የኮሮና ቫይረስ ኬዝ ያስተናገዱ ሀገራት

🇺🇸 አሜሪካ☞ 435,128
🇪🇸 ስፔን☞ 148,220
🇮🇹 ጣልያን☞139,422
🇩🇪 ጀርመን☞ 113,236
🇫🇷 ፈረንሳይ ☞112,950
🇨🇳 ቻይና☞ 81,865
🇮🇷 ኢሪን☞64,586

♨በኮሮና ቫይረስ ብዙ ሰው የሞተባቸው ሀገራት
🇮🇹 ጣልያን ☞17,665
🇺🇸 አሜሪካ ☞14,795
🇪🇸 ስፔን ☞14,792
🇫🇷 ፈረንሳይ☞10 ,869
🇬🇧 ብሪታኒያ ☞7,097
🇮🇷 ኢሪን ☞3,993
🇨🇳 ቻይና ☞3,335

♨በርካታ ዜጎች ያገገሙላቸው ሀገራት
🇨🇳 ቻይና ☞77,167
🇪🇸 ስፔን ☞48,021
🇩🇪 ጀርመን☞ 46,300
🇮🇹 ጣልያን☞22,837
🇮🇷 ኢሪን ☞29,812

ምንጭ፡ ወርልዶሜትር

✔መረጃውን ከወደዱት ለወዳጅዎ እንዲደርስ ሼር ያርጉት
✔አቀራረባችን ላይ አስተያየት ካሎት ኮሜንት

Address

Mekelle
MOM

Telephone

+251996880918

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Amu. posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share