Hijra-Bank logiya sultan qali mirac luddi

Hijra-Bank logiya sultan qali mirac luddi Hijra Bank logia

24/12/2025
29/10/2024
29/06/2023

Watch, follow, and discover more trending content.

17/09/2022

# # #✍አስገራሚ ቂሷ❗️

ዒሻእ ሰላት ተሰግዶ ጥቂት ደቂቃዎች እንዳለፉ አንድ ወጣት ከወደ ውጭ በኩል ይጮህና የመስጅዱን ጀማዓ ይጠራል። ሰዉ ግር ብሎ ልጁን ተከትሎ ሲወጣ አንድ እድሜው 20 የማይሞላ ልጅ ባቡር ገጭቶት አካሉን ለሁለት ከፍሎታል (ሱብሀን አላህ) ግን ሩሁ አልወጣችም ሊሞት ጣር ላይ ነበር በዚህ ሁኔታ ላይ ሳለ ከተሰበሰቡት አንዱ ጎንበስ ብሎ የልጁን ጭንቅላት በእግሩ ላይ አስቀመጠው።
"ላ ኢላሀ ኢለላህ በል... ላ ኢላሀ ኢለላህ በል"
ይለውም ጀመር... ልጁ ሩሁ ልትወጣ ጥድፊያ ላይ ናት ይፈራገጣል...እናም የአሏህ ተውፊቅ ሆነና
ልጁ " ላ ኢላሀ ኢለላህ ሙሀመዱን ረሱሉላህ" እንዳለ ሰውነቱ ቀዘቀዘ ትንፋሹ ዳግም ላይመለስ ተቋረጠ ነፍሱም ወደ ፈጣሪዋ አመራች።
(ኢና ሊላሂ ወኢና ኢለይሂ ራጂዑን)

ተባብረው ልጁን ሰዎች ወደሚበዙበት አካባቢ ወሰዱት ቤተሰቡን ለማፈላለግ... ሌሊቱ ጨለማማ ነበር ጽልመቱ ያስፈራል ብርሀናማ ቦታ ሆነው ልጁን የሚገልፁ ነገሮችን ልብሶቹን በመጠቀም ቤተሰቡን ያፈላልጉ ጀመር... ድንገት በቦታው ከነበሩት አንዱ የአስክሬኑን እጅ ይዞ ፦"ይህ ልጅ ክርስቲያን ነው አንገቱ ላይ መስቀል ይኸው..." እያለ ጮኸ።

ሁሉም ግራ ተጋባ "ይህ ልጅ በተውሂድ ነው የሞተው ታድያ እኛው በሙስሊሞች መቃብር እንቅበረው ወይስ ለቤተሰቦቹ አስረክበን በክርስቲያኖች መቃብር ይቅበሩት?" እያሉ ይወያዩ ጀመር..

ቤተስቦቹ ጋ ለመውሰድ ይወስኑና ተሸክመውት በእንባ ወደ ቤተሰቦቹ ጉዞ ጀመሩ። ልጁ መስጅድ አካባቢ ስለሞተ አስክሬኑን ያጀቡት ሁሉም ሙስሊሞች ነበሩ። ተሸክመውት ከአከባቢው ሲደርሱ አባቱም የልጁን ማረፍ ሰምቶ ሲገሰግስ አገኙት አባትየውም ሲያያቸው ተንሰቅስቆ ያለቅስ ጀመር (እንዴት አያልቅስ ተስፋ ይሆነኛል፣ ረዳት ይሆነኛል፣ መመኪያ ይሆነኛል ብሎ የሚጠብቀው ልጁ ከሰዎች ትከሻ ላይ ተጭኖ ሲመጣለት...)
ልጁን አቅፎ አምርሮ ያለቅሳል...

ይህ ሁሉ ሙስሊም ልጁን ተሸክሞ መምጣቱ ያስገረመው አባት እያለቀሰ ለተሰበሰበው ሰው እንዲህ አላቸው፦ "ይህን ስነግራችሁ በህፍረት ነው... ልጄ እንዲያው ቁርአን መስማት ይወዳል። አዎ ልጄ በርግጥ ክርስቲያን ነው ነገር ግን የሙስሊሞችን ቁርአን መስማት ይወዳል።
ዘወትር ክፍሉ ስገባ ኢርፎን/earphone ከጆሮው አያለሁ... "ምንድነው የምትሰማው?" ስለው
"ዘፈን ነው"ይለኛል። ከጆሮው ነቅዬ ሳዳምጥ ግን ቁርአን ነው።

በጣምም እቆጣው ነበር ይሄን መስማት ካልተውክ እገድልሀለሁ እያልኩ ሁሌም አስጠነቅቀውም ነበር... "ባባ እኔን መግደል አትችልም ቁርአን መስማትም አትከልክለኝ" ይለኝ ነበር..

በቦታው ያሉት ሁሉ እየተያዩ ይለቃቀሱ ነበር።
"ልጅህ እኮ በሸሀዳ ነው የሞተው" ብለው ሲነግሩት...ያ የልጁ መሞት ቅስሙን የሰበረው አባት ያ የልጁን ሬሳ አቅፎ ቁጭ ያለው አባት
እንባውን እያረገፈ ልጁን በስስት እያየ እንዲህ አለ፦

"ልጄ በመሰከረው ነገር እኔም እመሰክራለሁ ከአሏህ ሌላ አምላክ እንደሌለ ሙሀመድም የአላህ መልዕክተኛ እንደሆኑ እመስክራለሁ"

ከዚያም ሁሉም ጀማዓ ጀናዛውን ይዘው ወደ ሙስሊሞች መቃብር "ላ ኢላሀ ኢለላህ... ላ ኢላሀ ኢለላህ.... ላ ኢላሀ ኢለላህ" እያሉ አጅበው ወስደው ቀበሩት።

❤️❤️👇ሙስሊም ሆኖ ኖሮ በኩፍር መሞትም አለና ካፊር ሆኖ ኖሮ በተውሂድ መሞትም አለና "አሏህ ኻቲማችንን ያሳምርልን"❤️❤️

ምንጭ፦ ﻫﻨﺎ ﺃﺑﻨﺎﺀ ﻋﺎﺋﺸﺔ ﺃﻡ ﺍﻟﻤﺆﻣﻨﻴﻦ

HB's Strategic Management briefing for Head Office Staff ሂጅራ ባንክ ያዘጋጀውን የአምስት ዓመት ስትራቴጂ ሠነድ ለዋና መስሪያ ቤት ሰራተኞች እያቀረበ ይገኛል...
11/08/2022

HB's Strategic Management briefing for Head Office Staff

ሂጅራ ባንክ ያዘጋጀውን የአምስት ዓመት ስትራቴጂ ሠነድ ለዋና መስሪያ ቤት ሰራተኞች እያቀረበ ይገኛል።
# # # # # # # # # # # # # # # # # # # # # # # # # # # # #

ሂጅራ ባንክ ባንኩን በቀጣይ አምስት ዓመት ተወዳዳሪና ውጤታማ ሊያደርግ የሚችለውን ስትራቴጂ የቀየሰ ሲሆን የባንኩ ከፍተኛ አመራሮች ሁሉንም ሰራተኞችና ባለድርሻ አካላትን በአግባቡ በማሳተፍ ስትራቴጂው በታቀደው አግባብ ግቡን እንዲመታ አስፈላጊውን ጥረት ያደርጋሉ።

ሂጅራ ባንክ በሽራተን አዲስ እየተካሄደ ባለው 'ከወለድ ነፃ የፋይናንስና የኢኮኖሚ ጉባኤ' ላይ እየተሳተፈ ይገኛል።ሂጅራ ባንክ ጉዞ ወደ ብሩህ ተስፋ! # # # # # # # # # # # # #...
11/08/2022

ሂጅራ ባንክ በሽራተን አዲስ እየተካሄደ ባለው 'ከወለድ ነፃ የፋይናንስና የኢኮኖሚ ጉባኤ' ላይ እየተሳተፈ ይገኛል።

ሂጅራ ባንክ ጉዞ ወደ ብሩህ ተስፋ!
# # # # # # # # # # # # # # # # # # # # # # # # # # # # # #

በዛሬው እለት የፈይናንስ ዘርፍን ከዳያስፖራው ማህበረሰብ ጋር ለማስተዋወቅ እና በባንኮች አገልግሎት ዳያስፖራው ተሳታፊ እና ተጠቃሚ እንዲሆን የሚያስችል በሽራተን አዲስ ሆቴል ከወለድ ነጻ የፋይናስና የኢኮኖሚ ጉባኤ እየተካሄደ ይገኛል። ሂጅራ ባንክ ይህንን ጉባኤ ስፖንሰር በማድረጉ ላቅ ያለ ደስታ ይሰማዋል፡፡

Hijra banki 2021/22 mizaaniyyat sanatal fayyale abnisso tuybulleeh tan ludditteh lakqoh acwaa kee mamaxxaga mattacooh su...
11/08/2022

Hijra banki 2021/22 mizaaniyyat sanatal fayyale abnisso tuybulleeh tan ludditteh lakqoh acwaa kee mamaxxaga mattacooh sumqatih warkat yeceem kinnuuk olompiya - najaashi luddi mizaaniyyat sanatih ellacabol fayyale gadda gaaboyseemih taagah kaah ekraaroom daga fayyale abnisso abteeh 1-heele caddooy jimma - abba jifar fayyalw caddoh gadda gaaboysak 2-heelw caddooy markaato bilak luddi fayyale caddooy 3-heele caddooy logiya sultan qali mirac luddi fayyale gadda gaaboysak 4-heele caddooy chagni - racmaan luddu sanatal yeceen ekraaro aracat haak 2 - heele caddooy Desse - arraagaw luddi kaah yeceen ekraaro aracat haak 3- heele caddoh yewqen. Acwa taddiirak ossotinah luddi taamah saqoltih namma ayroh Leadership aydakaakan yeceenim kee mamaxxaga sumqatih acwa keenih yeceeh.

Address

Logya

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Hijra-Bank logiya sultan qali mirac luddi posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Hijra-Bank logiya sultan qali mirac luddi:

Share