Kokeb Sacco/ ኮከብ የገንዘብ ቁጠባና ብድር ዩንየን/

  • Home
  • Ethiopia
  • Injibara
  • Kokeb Sacco/ ኮከብ የገንዘብ ቁጠባና ብድር ዩንየን/

Kokeb Sacco/ ኮከብ የገንዘብ ቁጠባና ብድር ዩንየን/ Kokeb saving and credit cooperative union which is operating in Amhara national regional state , Awi

19/05/2026


​አድማስ ሁለገብ የገበሬዎች የህብረት ሥራ ማህበራት ዩኒየን ኃ/የተ/የግል ከዚህ በታች በተገለጸው ክፍት የሥራ መደብ ተወዳዳሪዎችን አወዳድሮ መቅጠር ይፈልጋል።

ስለሆነም መደቡ የሚጠይቀውን የትምህርት ዝግጅት የምታሟሉ ተወዳዳሪዎች ከታች እስከ ተጠቀሰው ቀን ድረስ መመዝገብ የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን።

18/05/2026

አዲስ ምዕራፍ የከፈተው የኀብረት ሥራ አዋጅ ማሻሻያ
******
የኅብረት ሥራ ማሻሻያ አዋጅ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በሙሉ ድምፅ መፅደቁ ለዘርፉ ታሪካዊ እመርታ ነው።

የማሻሻያ አዋጁ ኀብረት ሥራን ከለውጡ ጋር አብሮ የሚራመድ፣ ዘመኑን የዋጀ እና ሀገራዊ የልማት ተልዕኮዎችን የሚያሳካ ዘርፍ ለማድረግ ምቹ ሁኔታ የፈጠረ ነው።

ኀብረት ሥራን ከባህላዊ የማኅበር አስተሳሰብ ወደ ዘመናዊ የኢንቨስትመንትና የስራ ፈጠራ ተቋምነት የሚያሸጋግር አዲስ አቅጣጫ ያስቀመጠ ነው።

ማህበራቱ ከግሉ ዘርፍ ጋር በኢንቨስትመንት እንዲሰሩ፣ አደረጃጀታቸው እንዲጠናከር፣ በተማረ የሰው ኃይል እንዲመሩ እና የኦዲት ተደራሽነት እንዲያድግ የሚያስችል ነው።

በተለይም ማህበራት ከአባላት ውጭ ሼር እንዲሸጡ መፍቀዱ በዘርፉ ታሪካዊ ለውጥ ነው። ይህም ማህበራት ካፒታል ለማፍራት፣ ቴክኖሎጂ ለመጠቀም እና ተወዳዳሪ ቢዝነስ ለመገንባት አዲስ ዕድል ይፈጥራል።

አዲሱ አዋጅ ማህበራት በየትኛውም የሀገሪቱ ክፍሎች ቅርንጫፎች ከፍተው አገልግሎት መስጠት እንዲችሉ ሰፊ ዕድል ይፈጥሯል።

ይህም ማኅበራቱ ያጋጥማቸው የነበረው የስራ ቦታ ገደብ በማንሳት በነፃነትና በሰፊው እንዲንቀሳቀሱ የሚያስችል ነው።

እንዲሁም አዋጁ ሴቶች፣ ወጣቶች እና አካል ጉዳተኞች በራሳቸው እንዲደራጁ ከመፍቀዱ ባለፈ፣ በሌሎች ማህበራት ውስጥ በአመራር ደረጃ የተወሰነ ድርሻ እንዲኖራቸው መደንገጉ የተሳትፎ ፍትሕን የሚያጠናክር ነው።

ከዚህ በፊት በሕግ በግልጽ ያልተደነገጉ የኢንስፔክሽንና የሕግ ማስከበር ሥርዓቶችም በአዲሱ አዋጅ ተካተዋል።

በአጠቃላይ የተሻሻለው አዋጅ፦
🔹 የማህበራትን አደረጃጀትና አመራር ያጠናክራል
🔹 የፋይናንስ ተደራሽነትን ያሳድጋል
🔹 ከግሉ ዘርፍ ጋር የኢንቨስትመንት ትስስር ይፈጥራል
🔹የሴቶች፣ ወጣቶችና አካል ጉዳተኞች ፍትሀዊ ተሳትፎ ያጠናክራል
🔹 የኦዲትና የቁጥጥር ስርዓትን ዘመናዊ ያደርጋል
🔹 ግልፅነትንና ተጠያቂነትን ያጠናክራል
🔹 የአባላትን መብትና ጥቅም በሕግ ያስከብራል

ቀጣዩ ስራ የማስፈፀሚያ ደንብ ማፀደቅና ከወረቀት ወደ ተግባር በማውረድ የኀብረት ሥራ ማህበራት እውነተኛ አቅም እንዲገለጥ ማድረግ ነው።

ጠንካራ የሕግ ማዕቀፍ = በመርህ የሚመራ ኀብረት ሥራ = ጠንካራ ማኅበራዊ ኢኮኖሚ!

11/05/2026
11/05/2026
11/05/2026
በአገው ግምጃቤት ከተማ በ 2018 ዓ/ም የቤት መስሪየ ቦታ የተሰጣቸው 78 መሰረታዊ ማህበራት ዩንየናችን ከ 91 ሚሊየን በላይ ብድር በማመቻቸት ካሳ እንዲከፍሉ እና የቦታ ባለቤት እንዲሆኑ ...
11/05/2026

በአገው ግምጃቤት ከተማ በ 2018 ዓ/ም የቤት መስሪየ ቦታ የተሰጣቸው 78 መሰረታዊ ማህበራት ዩንየናችን ከ 91 ሚሊየን በላይ ብድር በማመቻቸት ካሳ እንዲከፍሉ እና የቦታ ባለቤት እንዲሆኑ ያደረገ ሲሆን ዛሬ በዩንየኑ አዳራሽ የብሄረሰቡ ዋና አስተዳዳሪ እና ከፍተኛ የዞንና የወረዳ አመራሮች በተገኙበት የእጣ ማውጣት እና ቦታ የማስተላለፍ ስነ ስርአት እየተከናወነ ይገኛል !

ኮከብ ዩንየን በጓጉሳ ሽኩዳድ ወረዳ ህብረት ስራ ማህበራት ማደራጃ ጽ/ቤት በበጀት አመቱ የተከናወኑ የጋራ ተግባራትን የሚመለከታቸው የህብረት ስራ ቤተሰቦች በተገኙበት በመገምገም ላይ ነው!
05/05/2026

ኮከብ ዩንየን በጓጉሳ ሽኩዳድ ወረዳ ህብረት ስራ ማህበራት ማደራጃ ጽ/ቤት በበጀት አመቱ የተከናወኑ የጋራ ተግባራትን የሚመለከታቸው የህብረት ስራ ቤተሰቦች በተገኙበት በመገምገም ላይ ነው!

ኮከብ ዩንየን በ 2018 በጀት አመት በአገው ግምጃቤት ከተማ  ቦታ ለመውሰድ የተመለመሉ 78 የመሰረታዊ የቤት ግንባታ እና አከባቢ ልማት ማህበር አመራሮች ጋር በካሳ አከፋፈል እና ቤት ግንባ...
04/04/2026

ኮከብ ዩንየን በ 2018 በጀት አመት በአገው ግምጃቤት ከተማ ቦታ ለመውሰድ የተመለመሉ 78 የመሰረታዊ የቤት ግንባታ እና አከባቢ ልማት ማህበር አመራሮች ጋር በካሳ አከፋፈል እና ቤት ግንባታ ዙሪያ ውይይት በማድረግ አቅጣጫዎችን አስቀምጧል!

04/04/2026

ኮከብ ዩንየን በዛሬው እለት ከ ከአንከሻ ጓጉሳ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ
ከግ/ቤት ከተማ ከንቲባ
ከከተማ አስተዳደሩ መሬት አስተዳደር ሀላፊ
ከወረዳው መሬት አስተዳደር ሀላፊ
ከወረዳው የህብረት ስራ ማደራጃጃ ሃላፊ
ከዩንየን ስራ አስኪያጅ የብድር የስራ ሂደት እና ፋይናንስ የስራ ሂደት ሃላፊዎች ጋር በካሳ አከፋፈል ዙሪያ ውይይት አድርጎ በአሰራሮች ዙሪያ አቅጣጫ በማስቀመጥ ዛሬ 8:00 ለማህበር አመራሮች እንዲገለጽ ወስኗል !

ግምጃ ቤት
03/04/2026

ግምጃ ቤት

Address

Injibara

Telephone

+251582240468

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Kokeb Sacco/ ኮከብ የገንዘብ ቁጠባና ብድር ዩንየን/ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Kokeb Sacco/ ኮከብ የገንዘብ ቁጠባና ብድር ዩንየን/:

Share

Category