Wondimu Wolde Woimago

Wondimu Wolde Woimago To Provide Useful Economical,Social,Political &other informations to the society.

25/02/2026

የባሕር በር፡- የማይቀረው የትውልድ ድል!
********

ለኢትዮጵያ የባሕር በር ጥያቄ በታሪካዊ፣ ሕጋዊ እና ፖለቲካዊ ምክንያቶች የተገነባ ፅኑ ሀገራዊ አቋም ነው።

ኢትዮጵያ ለዘመናት የባሕር በር በማጣቷ ምክንያት በኢኮኖሚ፣ በዲፕሎማሲና በደኅንነት ረገድ እጅግ ከፍተኛ ዋጋ ስትከፍል ቆይታለች። ይህ የታሪክ ማነቆ ተፈትቶ ሀገራችን የሚገባትን ስፍራ የምትይዝበት ጊዜ አሁን ነው!

ለምን የባሕር በር የሕልውና ጥያቄ ሆነ?

ታሪካዊና ሕጋዊ መሰረት፦ ኢትዮጵያ የቀይ ባሕር ባለቤትና የቀጣናው የንግድ ማዕከል የነበረች የታሪክ ባለቤት ናት። ጥያቄዋም ከዓለም አቀፍ የሕግ መርሆዎችና ከጂኦ-ፖለቲካዊ እውነታዎች ጋር የተጣጣመ ፍትሐዊ ጥያቄ ነው።

የተከፈለው ከፍተኛ ዋጋ፦ ለዘመናት በወደብ ኪራይና በሎጂስቲክስ መስተጓጎል የፈሰሰው ቢሊዮኖች ዶላር የኢትዮጵያን እድገት የገደበ ትልቅ ሰንሰለት ሆኖ ቆይቷል። ይህ የሀብት ፍሰት ለትውልዱ ብልፅግና መዋል ነበረበት።

ሉዓላዊነትና ራስን መቻል፦ የባሕር በር እጦት ሀገራዊ ደኅንነታችንን ለሌሎች ፍላጎት ተጋላጭ አድርጎታል። ራሳችንን ችለን በሉዓላዊነት ለመቆም የራሳችን የባሕር መውጫ መኖሩ አማራጭ የሌለው ጉዳይ ነው።

የማይቀረው ስኬት፦ ኢትዮጵያ ይህንን ታሪካዊ ጥያቄ በእርግጠኝነት ታሳካዋለች! ይህ የዛሬው ትውልድ ትልቁ የቤት ሥራና የድል አክሊል ነው። ማነቆዎቻችንን ሰብረን፣ ከጎረቤቶቻችን ጋር በክብርና በጥቅም ተሳስረን የባሕር በር ባለቤት መሆናችን የማይታጠፍ የታሪክ ጉዞ ነው።

የነገዋ ኢትዮጵያ የባሕር በሯን ከፍታ፣ ልጆቿን መግባ፣ ዳግም ለዓለም የምታበራበት ጊዜ ቅርብ ነው!

Almighty God comfort all family‼️
07/10/2025

Almighty God comfort all family‼️

The funeral service for Ambassador Ayele Lire, Ambassador Extraordinary and Plenipotentiary of the Federal Democratic Republic of Ethiopia to the Republic of Cuba, who passed away on September 20, 2025, will be held tomorrow, Tuesday, October 7, 2025, at 3:00 p.m. at St. Joseph Church.

The Ministry of Foreign Affairs of the Federal Democratic Republic of Ethiopia once again expresses its profound sorrow over the passing of Ambassador Ayele Lire and extends its heartfelt condolences to his family, friends, and colleagues during this time of grief.

05/10/2025

የገጠር መሬት አስተዳደር፣ አጠቃቀምና የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ህገ-መንግስት
===================================
የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ህገ-መንግስት የገጠር መሬት ባለይዞታነትን መብት መሰረት በማድረግ አጅግ በርካታ ለሆኑ የንብረት መሰረታዊ መብቶች እውቅና የሰጠ ነው ፡፡ በአገራችን ለአመታት የገጠር መሬት አስተዳደርና አጠቃቀምን መሰረት በማድረግ እዚህም እዚያም ይነሱና ለግጭት መንስኤ በመሆን ዜጎች እርስ በርሳቸው ደም እንዲቃቡ ያደርጉ የነበሩትን ችግሮች በሚቀርፍ መንገድ መልስ የሰጠና በህዝብ ይሁንታ ያገኘ የፖሎቲካና የህግ ሰነድም ነው፡፡ የገጠር መሬትን መሰረት በማድረግ የተደነገጉትን ህገ-መንግስታዊ ድንጋጌዎችን በዝርዝር ሰናይ የህገ-መንግስቱ አንቀፅ 40(1) የግለ ንብረትን በማሰመልከት ዜጎች የግል ንብረት ባለቤትነት መብታቸው እንደሚከበርላቸውና ይህ መብት ሊገድብ የሚችለው ለህዝብ ጥቅም ሲባል ብቻ እንደሆነ ይደነግጋል፡፡ ስለሆነም ግለሰቦች በዚህ ግል ንብረት የመያዝና የመጠቀም መብት እንዳላቸው አፅንኦት በመስጠት የሌላን ዜጋ መብት እስካልተቃረኑ ድረስ የግል ንብረታቸውን ማለትም በመሬት ላይ የገነቡትን ወይም በጉልበታቸውና በገንዘባቸው የፈሩትን የመሸጥ፣ የማውረስ፣ ወይም በሌላ መንገድ ማስተላለፍ እንደሚችሉም ይደነግጋል፡፡ ከዚህ መገንዘብ የሚቻለው ዜጎች ንብረት የማፍራትና ከግዜ ወደ ግዜ በሚያሳዩት እድገት ተጠቃሚ የመሆን ዋስትና ያላቸው መሆኑን ተገንዝበው አገሪቱ ለተያያዘችው ፊጣንና ዘላቂ ልማት ሳይታክቱ እንዲሰሩ የሚያደርግ መሆኑን ነው፡፡ ይህ ህገ-መንግስታዊ የገጠር መሬት ባለይዞታነት መብት አርሶ አደሮች ከፊል አርብቶ አደሮችና አርብቶ አደሮች በየደረጃው የልማቱ ተጠቃሚ የመሆንን ስትራተጂ እውን ለማድረግ የሚያስችል የማአዝን ድንጋይ ነው፡፡ ቀጥሎ ያለው ድንገጌ ስለ ግለሰቦች፣ ቡዱኖችና የተለያዩ ማህበረ-ሰቦች በጋራ የንብረት ባለቤት ስለሚሆኑበትና እነዚህ በጉልበታቸው፣ በመፍጠር ችሎታቸው ወይም በካፒታላቸው ያፈሩት ተጨባጭነት ያለው ወይም ተጨባጭነት የሌለው ግን ደግም በገንዘብ ሊተመን የሚችል ዋጋ ያለው ንብረት ባለቤት መሆን እንደሚችሉ የሚደነግግ ሲሆን ከአንቀፅ 40 (2) መገንዘብ የሚቻለው የንብረት ባለቤትነት እንዴት እንደሚገኝ የሚደነግግ መሆኑ ነው፡፡ ከመሬት ባለቤትነት መብት አንፃር የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ህገ-መንግስት በሽግግር መንግስቱ ወቅት የግል ሃብት መሆን አለበት በሚሉ ወገኖችና የመንግስት እጅ መሆን አለበት በሚሉ ወገኖች መካከል የነበረውን የደራ ክርክር መቋጫ እንዲያገኝ በሚያስችል መልኩ “የገጠርም ሆነ የከተማ መሬትና የተፈጥሮ ሃብት ባለቤትነት መብት የመንግስትና የህዝብ ብቻ ነው፡፡ መሬት የማይሸጥ የማይለወጥ የኢትዮጵያ ብሄር ብሄረሰቦችና ህዝቦች የጋራ ንብረት ነው” በማለት የደነገገ በመሆኑ ለክርክሩ እልባት ሰጥቷል ብቻ ሳይሆን ከዚህ ባለፈም አሁን አገራችን እየተከተለችው ያለውን የልማት ፖሊሲና ስትራተጂ የገጠር መሬት በግል ሃብትነት በተያዘበት ኢኮኖምያዊ ማህበረ ሰብ ሊተገበር የማይቻል መሆኑ አሁን ያለንበት ሁኔታ በራሱ የሚያረጋግጠው ሐቅ ነው፡፡ ለዚህም በዋና ምክንያትነት ሊጠቀስ የሚችለው መሬት በግል ሃብትነት ይያዝ ቢባል ሰፊው አርሶ አደር ያለችውን መሬት እየሸጠ መሬት በጥቂት ባለሃብቶች እጅ እንዲገባ በማድረግ አርሶ አደሩና ሌላው የህበረተሰብ ክፍል የቀረችውን ጉልበቱ በርካሽ እየሸጠ ወደ ከፍ ድህነት እንዲገባ ከሚያደርገው በቀር ለስፊው አርሶ አደር ከፊል አርበቶ አደርና አርበቶ አደር የሚፈይደው ነገር አለመኖሩ ነው፡፡ እንደዚህ ያለ የልማት ዋስትና ያጣ አርሶ አደር ሆነ ሌላ የህብረተሰብ ክፍል ይዞ ፈጣንና ተከታታይነት ያለው ዘላቂ ልማትም ሆነ የምግብ ዋስትና ማረጋገጥ ፈፅሞ ሊታሰብ የሚችል አይደለም፡፡ በሌላም በኩል መንግስት ለሚያከሂደው ኢንቨስትመት መሬት ከአርሶ አደሩ እየገዛ ያከናውን ቢባልም መንግስት በግብርና በተለያዩ መንገዶች ያገኛትን ጥሪት አሟጦ ለልማት በማዋል ፈንታ በመሬት ግዠና ሽያጭ ገንዘቡ እንዲታጠር በማድረግ ኢንቨትመንትን የሚያቀጭጭ ሁኔታ ስለሚፈጥር ተመራጭ ኣይደለም ብቻ ሳይሆን የተሳሳተ የፖሊሲ አቅጣጫን ተከትሎ አገሪቱ በልማት፣ መልካም አስተዳደርና ዲሞክራሲ እጦት ወደ ባሰ ያለመረጋጋትና ስርዓት አልባነት እንድታመራ የሚያደርግ ፀረ-ሰላም አቅጣጫም ነው፡፡
ኢትዮጵያ የብዙ ብሄር ብሄረሰቦችና ህዝቦች አገር እንደመሆኗ መጠን የህዝቦቿ ኣኗኗርም የተለያየ ነው፡፡ ይህን የህዝቦቿ ብዝሀነት (divesity) ለማስተናገድ የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ህገ-መንግስት አንቀፅ 40(5) “የኢትዮጵያ ዘላኖች ለግጦሽ ሆነ ለእርሻ የሚጠቀሙበት መሬት በነፃ የማግኘት የመጠቀምና ከመሬታቸው ያለመፈናቀል መብት አላቸው ዝርዝር አፈፃፀሙ በህግ ይወሰናል” ሲል ይደነግጋል፡፡ ከዚህ መገንዘብ የሚቻለው ህገ-መንግስቱ በልማት ወደ ኋላ የቀሩ ብሄር ብሄረሰቦችና ህዝቦች ከአኗኗራቸው ጋር የሚሰማማ የመሬት አስተዳደር በመከተል የልማቱ ተሳታፊና ተጠቃሚ የሚሆኑበትን ሁኔታ የሚያመቻች መሆኑ ነው፡፡ ይህ ደግሞ በአርሶ አደርነት ቋሚ ቦታ ኑሯቸው የመሰረተ ልማት ተጠቃሚዎች እንዲሆኑ በማስቻልና በጋማ ከብት ዘመናዊ እርባታ ዘርፍ ስፊና ዘመናዊ የእንሰሳ እርሻ ልማት በመፍጠር አርብቶ አደሮቹ የልማቱ ተሳታፊና በየደርጃቸው ተጠቃሚ የሚሆኑበትን ሁኔታ ስለሚፈጥር ለገጠር ልማት ሰተራተጂው ግብ መምታት የበኩሉን አስተዋፅኦ ያበረክታል ብቻ ሳይሆን ዜጎች በፌደራሊዝም ስርዓት ማዕቀፍ በዘላቂነት አበረው አንዲኖሩ የሚያደርግም ነው ፡፡ በኢ.ፌ.ዲ.ሪ ህገ-መንግስት የመሬት ባለይዞታነት የሚገኘው በሁለት መንገድ እንደሆነና ይሄውም በነፃ ወይም በክፍያ ሊሆን እንደሚችል ይደነግጋል፡፡ ስለዚህ ጠቅላል ባለ መልኩ ሲታይ የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ህገ-መንግስት የገጠር መሬት የህዝብና የመንግስት እንዲሆን ማድረጉ ሰፊው አርሶ አደር፤ ከፊል አርብቶ አደር፤ አርብቶ አደርና በእርሻ ኢንቨስትመንት የሚሰማሩ ባለ ሃብቶች የገጠር መሬት በነፃ ወይም በክፍያ በማገኘት የባለይዞታነት መብት እንደሚያገኙና መንግስት የህዝብ ወኪል እንደመሆኑ መጠን መሬትን በህዝብ ስም እንዲያስተደደር የሚያስችለው ነው:: አሁን ባለው የገጠር መሬት አስተዳደርና አጠቃቀም መሬት የማይሸጥና የማይለወጥ የህዝብ ንብረት ሆኖ አንድ የገጠር መሬት ባለ ይዞታ አዋጅ ቁጥር 1161/2011 በሚደነግገው መስረት በቅድሚያ ተመጣጣኝ ከሳ ተከፍሎት ብቻ ሊለቅ እንደሚችል ከዚህ ውጭ ግን በህጋዊ መንገድ ያገኘውን የገጠር መሬት የማልማትና በፍሬው ተጠቃሚ የመሆን መብቱ በህገ መንግስቱና ይህን መሰረት በማድረግ በወጡ ሌሎች ህጎች የተረጋገጠ መብት ነው፡፡ ይህ ህገ-መንግስታዊ የገጠር መሬት ባለይዞታነት መብት የኢትዮጵያ ብሄር ብሄረሰቦችና ህዝቦች ዘላቂ ሰላም በማምጣት አንድ የኢኮኖሚ ማህበረሰብ የመፍጠርን አላማ መሰረት በማድረግ በህዝብ ይሁንታ ላይ የተመሰረተ በመሆኑ ሰፊውን አርሶ አደር ፣ ከፊል አርብቶ አደርና አርብቶ አደርን በየደረጃው ከድህነትና ኋላቀርነት ተላቆ የልማቱ ተጠቃሚ እንዲሆን በማስቻል ያለ ህገ-መንግስታዊ መርህ ነው፡፡

መሪነት እና ስነልቦናዊ ተጽዕኖውእያንዳንዱ መሪ የሚከፍለው ስነልቦናዊ መስዋዕትነት እና በሚመራው ሰው ላይ የሚያሳድረው ተጽዕኖ ትልቅ ነው።መሪዎች የበታች ሰራተኞችን የሚያናግሩበት ቶን ትልቅ ...
22/09/2025

መሪነት እና ስነልቦናዊ ተጽዕኖው

እያንዳንዱ መሪ የሚከፍለው ስነልቦናዊ መስዋዕትነት እና በሚመራው ሰው ላይ የሚያሳድረው ተጽዕኖ ትልቅ ነው።

መሪዎች የበታች ሰራተኞችን የሚያናግሩበት ቶን ትልቅ ስነልቦናዊ ትርጉም አለው። ለምሳሌ፣ ቁጣቸው የሚያስፈራራና የሚያሸማቅቅ ከሆነ በሰራተኛው ላይ ፍርሃት እና በራስ መተማመን ማጣት ሊያስከትል ይችላል። ይህ ደግሞ የሰራተኛውን የሥራ ተነሳሽነትና ምርታማነት ይቀንሳል። በሌላ በኩል፣ አንድን ሰራተኛ ትከሻውን ነካ ነካ በማድረግ የሚያበረታቱ ከሆነ ግን የበለጠ እንዲተጋና እንዲበረታታ የሚያደርግ አዎንታዊ ስነልቦናዊ ሀይል ይፈጥራል። ይህ የሚያሳየው መሪዎች እንደ ምሳሌ በመሆን የሚሰጧቸው ትንንሽ ማበረታቻዎች እንኳን በሰራተኞቻቸው ላይ ምን ያህል አዎንታዊ ተጽዕኖ ሊኖራቸው እንደሚችል ነው።

መሪነት ቀላል ኃላፊነት አይደለም። በግለሰብ ደረጃ ብዙ መስዋዕትነት እና ፈተናዎችን የሚጠይቅ ነው። ይህንን ኃላፊነት የሚሸከሙ ሰዎች፣ ለጋራ ጥቅም ሲሉ ብዙ ዋጋ ይከፍላሉ።

🔹 መሪነት በግለሰብ ደረጃ ስቃይ ነው ነገር ግን ለመልካም ነገር ሲባል የሚከፈል ዋጋ ነው።
🔹 መሪነት ለጋራ ህልውናችን ስንል የሚከፈል መስዋዕትነት ነው።
🔹 ለጋራ እሴት ተብሎ እንደሚቃጠል ችቦ ነው።
🔹 መሪዎች መንገድ ጠራጊዎች ናቸው ይህም ዋጋ ሊያስከፍል የሚችል ነው።
🔹 መሪነት አካላዊና ስነልቦናዊ ሁኔታዎችን መሸከም መቻል ነው።
🔹 መሪዎች ለጋራ መነሳት ሲባል በግል መከራና ስቃይን የሚቀበሉ ናቸው።

በአጠቃላይ መሪነት በጣም ውድ ነው❗

መሪዎች ተፅዕኖ አልባ ሊሆኑ አይችሉም፤ እያንዳንዱ መሪ መልካምም ሆነ መጥፎ አሻራውን ያሳርፋል። በዚህም መሰረት መሪነት በሚከተሉት ስድስት ባህሪያት ይገለጻል።

1. መሪዎቹ የሚመሩትን አሰራርና ስርዓት ወደፊት በከፍተኛ ፍጥነት እንዲራመድ ሊያደርጉት ይችላሉ። እነዚህ መሪዎች ያላቸውን ጥቂት ሀብት ለዓላማቸው ማሳኪያነት ይጠቀሙበታል።
2. ተራማጅ የሆኑ መሪዎች በዓላማ እና በታማኝነት የሚመሩ ናቸው።
3. መሪዎች የሀገርን ዕድል ፈንታ ሊቀይሩ ይችላሉ፤ ሀገር መንታ መንገድ ላይ በቆመችበት ወቅት ከችግር አውጥተው ህልውናን ያስቀጥላሉ።
4. ከወደቁበት የማይነሱ፣ የተሰጣቸውን ነገር ማስጠበቅ የማይችሉና ሰዎች ባሉበት እንዲቀሩ ሊያደርጉ ይችላሉ፤ ውስጥ ውስጡን የሚናድ ነገር ይገነባሉ፤ እነዚህ መሪዎች በሀገር ላይ ከፍተኛ ዋጋ ያስከፍላሉ።
5. ያለውን ነገር ተጠቅሞ መምራትና ውጤት ማምጣት የሚሳናቸው፣ ወደኋላ የሚጎትቱና እንድንሸራተት የሚያደርጉ መሪዎች አሉ።
6. የአፍራሽነት ሚና ያላቸው መሪዎች በሚመሩት ህዝብና ሀገር ላይ ከፍተኛ ውድቀትን ያስከትላሉ።

እነዚህ የመሪነት ባህሪያት በ2 መልኩ ይገለሉ ውጫዊ ምክንያቶች እና ውስጣዊ ምክንያቶች ናቸው።

መሪነት ትልቅ ዋጋ ያስከፍላል። መሪዎች ለሚያምኑበት ዓላማና ለሚመሩት ህዝብ ሲሉ የሚከተሉትን አራት ነገሮች መስዋዕት ያደርጋሉ።

🔻 ጊዜና ጉልበት: ለራሳቸው የሚሆን ጊዜን እና ጉልበትን ለጋራ ዓላማ አሳልፈው ይሰጣሉ።
🔻 ስሜት: የግል ስሜታቸውን ወደ ጎን በመተው ለጋራ ስኬት ይሰራሉ።
🔻 ሞራል: ከፍተኛ የሥነ-ልቦና ጫናዎችን እና ፈተናዎችን ይቋቋማሉ።
🔻 ሀብት (Resource): ያላቸውን ቁሳዊና መንፈሳዊ ሀብት ለሌሎች ይጠቀማሉ።

እውነተኛ መሪነት በግል የሚከፈል መስዋዕትነት እና ለጋራ ጥቅም የሚደረግ ልፋት ነው❗

መልካም አዲስ ዓመት ለኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያን በመላው አለም  ለምትገኙ ሁሉ ሰላም ለእናንተ ይሁን!🤝2018 ዓ/ም የሰላም፣የአንድነት፣የበረከትና የብልጽግና ዓመት ይሁንልን‼️
11/09/2025

መልካም አዲስ ዓመት ለኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያን በመላው አለም ለምትገኙ ሁሉ ሰላም ለእናንተ ይሁን!🤝
2018 ዓ/ም የሰላም፣የአንድነት፣የበረከትና የብልጽግና ዓመት ይሁንልን‼️

ለዘመናት ሲታመንበት የቆየውን የዓባይ ወንዝ ታሪክ በጥናታቸው የቀየሩት ተመራማሪ******ጣልያናዊው ፕሮፌሰር ክላውዲዮ ፋቼና በጂኦ-ሳይንስ የጥናት ዘርፍ ለበርካታ ዓመታት ምርምር ያደረጉ ምሁ...
05/09/2025

ለዘመናት ሲታመንበት የቆየውን የዓባይ ወንዝ ታሪክ በጥናታቸው የቀየሩት ተመራማሪ
******

ጣልያናዊው ፕሮፌሰር ክላውዲዮ ፋቼና በጂኦ-ሳይንስ የጥናት ዘርፍ ለበርካታ ዓመታት ምርምር ያደረጉ ምሁር ናቸው።

በጂኦ-ሳይንስ ዘርፍ ያዘጋጇቸው ከ300 በላይ የምርምር ውጤቶች እና ፅሁፎችንም በዓለም አቀፍ ደረጃ በሚታወቁ መጽሔቶች ላይ ማሳተም ችለዋል ፕሮፌሰር ክላውዲዮ።

ለበርካታ ዩኒቨርስቲዎች እንደማጣቀሻ ሆኖ እያገለገ የሚገኝ የመሬት ቅርፊት እና የተራሮች አፈጣጠርን የሚተነትን የምርምር ፅሁፍም ከሌሎች ምሁራን ጋር ሆነው ለሕትመት አብቅተዋል።

የፕሮፌሰር ክላውዲዮ የጥናት እና የምርምር ፅሁፎች ከፍተኛ ተጽዕኖ መፍጠር የቻሉ ሲሆን፤ በተለያዩ ወቅቶች ባቀረቧቸው ጥናቶች በርካታ ዓለም አቀፍ ሽልማቶችን እና እውቅናዎችን አግኝተዋል።

እኚህ ምሁር ካደረጓቸው ታላላቅ የምርምር ውጤቶች መካከል ከዓመታት በፊት በላይቭ ሳይንስ መፅሄት ላይ ያሳተሙት የምርምር ውጤት ይገኝበታል።

ፕሮፌሰሩ በጂኦ-ሳይንስ ዘርፍ የታላላቅ ምሁራን እና ተመራማሪዎችን የጥናት ውጤቶች ይፋ በሚያደርገው ታዋቂው መፅሄት ላይ አቅርበውት የነበረው ጥናት ለዓመታት ሲታመንበት የቆየውን ሃሳብም ያስቀየረ ነው።

የጥናት ውጤታቸውም የዓባይ ወንዝ የዛሬ 30 ሚሊየን ዓመት ገደማ እንደተፈጠረ ያስረዳል።

የዘርፉ ምሁራን የዓባይ ወንዝ ዕድሜ እስከ ስድስት ሚሊየን ዓመታት እንደሚሆን ለዘመናት ሲያምኑበት የቆየውን መላምት የቀየረው የፕሮፌሰር ክላውዲዮ ጥናት፤ ዓባይ ከኢትዮጵያ ተራሮች መፍለቅ እና መፍሰስ የጀመረው ከ30 ሚሊየን ዓመታት በፊት እንደሆነ የሚያስረዳ ውጤት ሆኗል።

ዛሬ ታሪክ ተለውጧል ፤ ከኢትዮጵያ ተራሮች እና አለቶች እኩል ተፈጥሮ ለ30 ሚሊዮን ዓመታት ሲፈስ የኖረው ዓባይ አሁን ማረፊያ አግኝቷል።

በዋሲሁን ተስፋዬ

ለአቶ ማሞ ምህረቱ ሽኝት ተደርገላቸውዛሬ ነሐሴ 29/2017 ዓ/ም. በገንዘብ ሚንስቴር ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ በተገኙበት የማክሮ ኢኮኖሚ ኮሚቴው ለብሔራዊ ባንክ ገዥ ለነ...
04/09/2025

ለአቶ ማሞ ምህረቱ ሽኝት ተደርገላቸው

ዛሬ ነሐሴ 29/2017 ዓ/ም. በገንዘብ ሚንስቴር ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ በተገኙበት የማክሮ ኢኮኖሚ ኮሚቴው ለብሔራዊ ባንክ ገዥ ለነበሩት አቶ ማሞ ምህረቱ የሰንብት ሥነ ሥርዓት አካሂዷል፡፡

በዚህ ልዩ ፕሮግራም አቶ ማሞ በተለይም መንግስት በቅርብ ግዚያት የወሰዳቸውን ታሪካዊና ውጤታማ የኢኮኖሚ ሪፎርም ላይ በብሔራዊ ባንክ ገዥነትና የማክሮ ኢኮኖሚ ኮሚቴ አባልነት ላበረከቱት አስተዋፅኦ ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ምስጋና አቅርበው በቀጣይ በአለም ዓቀፍ ደረጃ ለሚጠብቃቸው የስራ ኃላፊነት በብቃት እንደሚወጡ በመተማመን መልካም ምኞታቸውን ገልጸዋል፡፡

05/08/2025

ኢንተርኔትን ስንጠቀም ልንጠነቀቅ የሚገቡን 10 ጉዳዮች

1. የግል መረጃችንን ከማጋራት መቆጠብ፤

2. የምናውቃቸውን ሰዎች ብቻ ማነጋገር

3. በኦንላይን ብቻ የምናውቃቸውን ሰዎች ከፍተኛ እምነት አለመጣል፤

4. የጓደኝነት ጥያቄን በአካል ከምናውቃቸው ሰዎች ብቻ እንቀበል፤

5. ሁልጊዜ ስለምንለጥፈው ነገር በጥንቃቄ ደጋግሞ ማንበብ

6. በሁሉም የማህበራዊ ሚዲያ መለያዎች ላይ የግላዊነት(privacy 🔏) መጠበቂያዎችን መጠቀም፤

7. ሁሉም ሰው በኦንላይን እሱ እንደሆነ የሚነግረን ሁሉ እውነት አድርጎ አለመቀበል፤

8. ተገቢ ያልሆነ ይዘትን ሲያጋጥመን ወዲያውኑ ሪፖርት እናድርግ፤

9. ከጓደኞቻችን እና ከቤተሰባችን ጋር ስንመለከታቸው ምቾት የሚሰጡንን ምስሎች ብቻ ማጋራት፤

10. የይለፍ ቃላችንን በፍጹም ከማጋራት መቆጠብ፤

02/08/2025
30/07/2025

ጥንቆላ በህግ አምስት አመት ያስቀጣል።

ማታለል ሆን ብሎ ሰውን በማጭበርበር ዋጋ ያለውን ነገር በአብዛኛው የገንዘብ ጥቅምን ለማግኘት የሚፈፀም ተግባር ነው፡፡ ይህ ዓይነቱ ተግባር የሕዝብን እምነት በመጠቀምም ይፈጸማል፡፡

በዚህ መልኩ ሰዎችን ያታለለ አካል ተገቢ እና ተመጣጣኝ ቅጣት የሚያገኝ ይሆናል፡፡

ማንም ሰው ለራሱ ሀብት ለማግኘት አስቦ መንፈስ እጠራልሃለሁ፣ ጋኔን እስብልሃለሁ፣ ደንቃራ እጥልልሃለሁ፣ እጠነቁልልሃለሁ፣ ዕድልህን እነግርሃለሁ፣ ነገርን እገልፅልሃለሁ፣

ኮከብህን እቆጥርልሃለሁ፣ ህልምን እፈታልሃለሁ፣ የወደፊት ዕድልህን አውቅልሃለሁ፣ ወስጥ እጅህን አነብልሃለሁ፣ ከሞተ ሰው ጋር አነጋግርሃለሁ በማለት ወይም በሰው እምነት ያለአግባብ መገልገል በሚያስችል በማናቸውም ሌላ መንገድ ሰውን ያታለለ እንደሆነ በወንጀል ሕጉ ይቀጣል፡፡

የግል አቤቱታ ሲቀርብበት አፈፃፀሙ በደንብ መተላለፍ ድንጋጌዎች የሚያስቀጣ ካልሆነ (ቀላል ካልሆነ) በቀር በመቀጮ ወይም የተደጋገመ ወንጀል በፈፀመ ጊዜ በቀላል እስራት ወይም ነገሩ ከባድ ሲሆን ከአምስት ዓመት በማይበልጥ እስራት እንደሚያስቀጣ የወንጀል ሕጉ እንቀፅ 700 ይደነግጋል፡፡

[በየትኛውም መስክ ሞዴል ባለሙያ ለመሆን!...........🖊😎]************************************************በሥነ ምግባር፣ በሥራ አፈጻጸም፣ በማህበራዊ እሴቶች...
24/07/2025

[በየትኛውም መስክ ሞዴል ባለሙያ ለመሆን!...........🖊😎]
************************************************
በሥነ ምግባር፣ በሥራ አፈጻጸም፣ በማህበራዊ እሴቶች ትግበራ እና ሌሎች ተያያዥ ጉዳዮች ላይ ሞዴል ባለሙያ ለመሆን ከፈለጉ፣ እራስዎን በየጊዜው ማሻሻል እና ትክክለኛውን የአስተሳሰብና የሥራ መንገድ መከተል ያስፈልግዎታል።

ዋና ዋናዎቹን ነጥቦች ከዚህ በታች እንመልከት፦

1. በማንኛውም ሁኔታ እውነትን ይናገሩ፤ ለገቡት ቃል ይኑሩ፤ ከማንኛውም ሙስናና ብልሹ አሰራር ይራቁ፤ ግልጽነትንም ያበረታቱ።

2. በዘር፣ በፆታ፣ በሃይማኖት፣ በፖለቲካ አመለካከት ወይም በማንኛውም ልዩነትን ከግምት ውስጥ ሳያስገቡ ሁሉንም ሰው በእኩልነት ያገልግሉ።

3. ለሥራዎ እና ለውሳኔዎችዎ ሙሉ ኀላፊነት ይውሰዱ። ስህተት ሲፈጠር ኀላፊነቱን ተቀብለው ለማረም ይትጉ።

4. የሰዎችን እና የድርጅትን ሚስጥሮች በአግባቡ ይጠብቁ።

5. በሙያዎ ያሉ አዳዲስ እውቀቶችን እና ቴክኖሎጂዎችን ለመማር ሁልጊዜ ይትጉ። ስልጠናዎችን ይውሰዱ፣ መጽሐፍትን ያንብቡ እና በዘርፉ ከሚገኙ የሙያው አባቶች ይማሩ።

6. ሥራዎን በጥራት ያከናውኑ። የሚጠበቅብዎትን ብቻ ሳይሆን ከዚያ በላይ ለመስራት ይጣሩ።

7. ሥራዎን በጥሩ ሁኔታ ለማከናወን ጊዜዎን በትክክል ያቅዱና ይጠቀሙ።

8. ለችግሮች ዘላቂና የተሻሉ መፍትሄዎችን ለመስጠት አዳዲስ ሀሳቦችን ያመንጩ። ባሉበት አይርገጡ፤ የተሻሉ አሰራሮችን ይፈልጉ።

9. ከህዝቡ ጋር ለመነጋገር እና ችግሮቻቸውን ለማዳመጥ ቀለል ብለው ይቅረቡ። ከህዝብ ጋር አብረው ለመስራት ይትጉ፤ ህዝብን የመፍተሔ አካልም ያድርጉ፡፡

10. የሰዎችን ችግር ለመረዳት ይሞክሩ። ለእያንዳንዱ ሰው ችግር ትኩረት በመስጠት ለመርዳት ይጣሩ።

11. ከሥራ ባልደረቦችዎ፣ ከሌሎች ተቋማት እና ከማህበረሰቡ አባላት ጋር በጋራ ለመስራት ይጣሩ። የቡድን ስራን ያበረታቱ።

12. በሚያደርጉት ነገር ሁሉ ለሌሎች አርዓያ ይሁኑ። የእርስዎ መልካም ስነ ምግባር እና የስራ አፈጻጸም ሌሎች እንዲከተሉ ያነሳሳል።

13. ህግና ደንብ ያክብሩ። ህግን የሚያስከብር እና ከህግ በላይ ማንም እንደሌለ የሚያምን ባለሙያ ይሁኑ።

14. የእራስዎን ጥንካሬዎችና ድክመቶች ይወቁ። ድክመቶችዎን ለማስተካከል በየጊዜው ይስሩባቸው።

15. የሥራ ጫናንና ጭንቀትን በአግባቡ መቆጣጠርን ይማሩ። ይህ ለጤናዎ እና ለስራ አፈጻጸምዎ ወሳኝ ነው።

16. ሁልጊዜም አዎንታዊ አመለካከትን ያንፀባርቁ። ችግሮችን እንደ ዕድል ይመልከቷቸው።

17. ሌሎችን ባለሙያዎች በተገቢው መልኩ ለማረም፣ አዎንታዊ ትችት ለማቅረብ እና ለማብቃት ይስሩ፡፡ ይህ ለእርስዎም ይሁን ለባለሙያዎች በአጠቃላይ ለተቋምና ለህዝብ ዕድገት ወሳኝ ነው፡፡

እነዚህን መርሆች በተግባር ላይ በማዋል፣ በሙያዎ የሚከበር፣ በህዝብ ዘንድ ተወዳጅና አድናቆትን የሚያተርፍ ሞዴል ባለሙያ መሆን ይችላሉ።
********************************************
ለአስተማሪ ነገሮች ገፃችንን
👉Like
👉Follow&Share ያድርጉ!
ለአስተሳሰብ ለውጥ እንታገላለን!

Address

Hossana

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Wondimu Wolde Woimago posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Wondimu Wolde Woimago:

Share