እብናት - መቶ ፕሮጄክቶች

እብናት - መቶ ፕሮጄክቶች Etegie flour factory ; Teff ,sorghum and wheat flour production

11/09/2023
'' ማዕድን አዲስ የንጋት ተስፋ ለክልላችን !!''
23/06/2023

'' ማዕድን አዲስ የንጋት ተስፋ ለክልላችን !!''

''ስለ እብናት ልማት ዝም አልልም!!'' #ከአዲስ ዘመን- እብናት - አምድ ወርቅ -ሰቆጣ #ከደብረታቦር-እብናት-በለሳ- ዙሀሙሲት-አርባፀጓር - ሳህላ #ከሞጣ- እብናት-ሰቆጣ  #ከጎንደር -እ...
14/05/2023

''ስለ እብናት ልማት ዝም አልልም!!''
#ከአዲስ ዘመን- እብናት - አምድ ወርቅ -ሰቆጣ
#ከደብረታቦር-እብናት-በለሳ- ዙሀሙሲት-አርባፀጓር - ሳህላ
#ከሞጣ- እብናት-ሰቆጣ
#ከጎንደር -እብናት- ላሊበላ
ከዚህ በላይ የዘረዘርኳቸውን መስመሮች ከእብናት አንፃር ያለውን ትስስር አንድ በአንድ ለማየት እሞክራለሁ

@ከባህርዳር-አዲስ ዘመን- እብናት - አምድ ወርቅ -ሰቆጣ
እብናት ከክልሉ መዲና ከባህርዳር 122ኪ.ሜ ርቀት ቀጥታ መስመር ላይ ትገኛለች
ባህርዳር አለምአቀፍ ስታዲየም እና ኤርፖርትም አላት
ስፖርተኞች እና የሉዑካን ቡድኖች ከአንድ አለም አቀፍ ስታዲየም እስከ 120ኪ.ሜ ርቀት ድረስ ማረፊያ ወይም ሆቴል እንዲይዙ ይፈቅዳል ይህንንም ከግምት ውስጥ በማስገባት እብናት ባለኮከብ ሆቴሎችን ለመገንባት የቦታ ርክክብ ተደርጎ ቅድመ ግንባታ ላይ ትገኛለች
ነገር ግን ከባህር ዳር 120ኪ.ሜ ራዲየስ ብቸኛ የጠጠር መንገድ ያላት ወይም የአስፓልት መንገድ የሌላት ወረዳ ደግሞ እብናት ናት ???????
ከአዲስ ዘመን - እብናት - አምድ ወርቅ - ሰቆጣ መንገድ በ2ኛው የእድገትና ትራንስፎርሜሽን የእቅድ ምዕራፍ ይተገበራል ተብሎ በእቅድ ቢያዝም አስታዋሽ አቶ ቀርቷል
ሆኖም በለውጡ ምዕራፍ በአካባቢው ማህበረሰብ ጎስጓሽነት የ73 ኪ.ሜ የዲዛይን ስራ በአስቸኳይ (ከ3-6 ወር ) ተሰርቶ እንዲጠናቀቅ ታቅዶ በተለያየ ምክንያት ቢዘገይም መፅደቁን በበጎ ተመልክተን የኮንስትራክሽን ስራ ጨረታ መውጣቱን በተስፋ አንጋጠን በጉጉት ስንጠብቅ ብንቆይም እስካሁን ምንም አይነት ተግባራዊ እንቅስቃሴ አይታይም ??????

#ከደብረታቦ-እብናት-በለሳ-ዙሀሙሲት-አርባፀጓር ሳህላ
ከዞኑ መናገሻ ከተማ ደብረታቦር 38 ኪ.ሜ ርቀት ላይ የምትገኘው እብናት ከዞኑ ወረዳዎች በቅርበቷ ከአዲሷ ጉና በጌምድር ወረዳ ቀጥሎ በ2ኛ ደረጃ ላይ ትገኛለች ሆኖም ግን ከዞኑ ጋር በአስፓልት ያልተሳሰረች በዚህ ቅርበት የምትገኝ በቸኛዋ ወረዳ እብናት ብቻ ነች ???????
ይህ መስመር ደቡብ ጎንደር ዞንን ከማዕከላዊ ጎንደር በአቋራጭ መስመር የሚያገናኝ ነው
ከፍተኛ የሆነ የእንሰሳት ግብይት የሚፈፀመውም በዚሁ ቀጠና ነው
በትግል ወቅትም ፈጥኖ ደራሹ የዚሁ አካባቢ ማህበረሰብ ነው ። ትኩረት?????

#ከሞጣ- እብናት-ሰቆጣ
ይህ መስመር በፌደራል ደረጃ አስፓልት ሊሰራ ከታቀደ 10 አመት ያለፈው ቢሆንም ከሞጣ በጃራገዱ እስቴ ደብረታቦር ያለው ስራ ተጀምሮ አብዛኛው የአስፓልት ንጣፍ የለበሰና አባይ በረሃ አካባቢ ያለው መንገድ ግን ከቆረጣ ውጭ ሳይሰራለት በምን ምክንያት እንደቆመ ሳይታወቅ ተቋራጩ ማሽኖቹን ይዞ የወጣና ጥቂት የሚባለው ደግሞ አንዳቤት አካባቢ ተይዘው እንደቆሙ መረጃው አለን
በዚህ አጋጣሚ እብናት የአሰፓልት መንገድ ሊገባላት ነው ብለን ስንጠብቅ ከደብረታቦር - እብናት ያለው 38 ኪ.ሜ አጭር ጉዞ ከዲዛይኑም ስራ ውጭ ሆኖ ቀርቷል????
ጠቅላይ ሚኒስትሩም በርብ የመስኖ ውሃ ግድብ ግንባታ ፕሮጀክት ምርቃት መተው ከደብረታቦር- እብናት ያለው መስመር በቅርቡ አስፓልት መሆን እንዳለበት ቃል ገብተው ነበር ይህ ብቻ አይደለም ከርብ ግድብ ንፁህ የመጠጥ ውሃ እንዲሳብ ዶ/ር ኢ/ር ስለሽ በቀለ በደብዳቤም አሳውቀው ነበር ሁሉም የውሃ ሽታ ሆነው ቀርተዋል ???

#ከጎንደር -እብናት- ላሊበላ
ይህ መስመር ከፍተኛ የቱሪስት መደረሻ የሆኑ ሁለት ታሪካዊ ከተሞችን ያስተሳስራል
ከአይና ቡግና -ቆብ- መቀጣዋ ያለው የጠጠር መንገድ ጥርጊያ ለዚህ አካባቢ መልካም ዜና ነው ሆኖም ከመቀጣዋ እብናት የሚገነባው መንገድ በሁለት ቀበሌዎችና በወቅቱ አመራሮች አለመግባባት ሳይሰራ ቆይቷል በዚህ አመት በሰለማያ በኩል ሊሰራ የዲዛይን ስራው እየተከናወነ ነው
ከጎንደር ላሊበላ በአዲስ ዘመን ወረታ ጋይንት ጋሸና ላሊበላ ያለውን እረጅምና አሰልች ጉዞ በማስቀረት ከጎንደር እብናት ላሊበላ አቋራጩን መስመር በመጠቀም በአስፓልት መሰራት ቢቻል ጥቅሙ ዘርፈ ብዙ ሲሆን የህዝቡን ድካምና እንግልት ደግሞ ያስቀራል የአካባቢውን እምቅ ሀብትም መጠቀም ይቻላል ። ትኩረት???
በኢትዮጵያ በቀጣዩ 10 ዓመት የልማት እቅድ ሁሉንም ወረዳ ከወረዳ በአስፓልት ለማስተሳሰር እቅድ ተይዟል ይሁን እንጅ በአሁኑ ነባራዊ ሁኔታ ከክልሉም ሆነ ከዞኑ ጋር ያልተሳሰረች ወረዳና ከተማ ደግሞ እብናት ነች ???????
በአጠቃላይ
ለአንዲት ሀገር ፈጣን ልማትና እድገት መሰረተ ልማት የአንበሳውን ድርሻ ይወስዳል
ሰላምና መሰረተልማት ከኢንቨስትመንት ጋር ያላቸው ትስስር ቀጥታ ወይም የአንድ ሳንቲም ሁለት ገፅታ ናቸው
ሰላማችን በታወከ ጊዜ ህልውናችን አደጋላይ በወደቀ ስዓት እንደ ንብ ተመን ተከዜ ላይ ታድመን ያቅማችን ዘምተን አካባቢያችን አላስደፈርንም
መሰረተ ልማታችን በተለይ የአስፓልት መንገዳችን ግን ከአቅማችን በላይ ሆኖ ይኸው ዛሬም የህዝባችን ስቃይና እንግልት እየተመለከትን እኛም የገፈቱ ቀማሽ ሆነን አልቃሽና አስለቃሽ ሆነናል
እብናት የታሪክ መዛግብት ያለባት ከተቆረቆረችም 112 ዓመት ያስቆጠረች እድሜ ጠገብ ከተማ ነች
ከ750 ዓመት በላይ ያስቆጠሩ እነ ሰይኮ ኪዳነ ምህረት ና አምስትያ ገዳም ደግሞ የአካባቢው ጌጦችና በረከቶች ናቸው
ወፍጦማ ዋሻ ፣ ባዶ ገደል ፣ ደምጎርስና ድርኳዜ ደግሞ ተጨማሪ መስህቦቻችን ናቸው
አካባቢው በእንሰሳት ምርቱ የታወቀ ሲሆን ከጠጁና ከማሩማ ያልቀመሰ የለም
እጣንና ሙጫው እንዲሁም ገና ያልተነካው የማዕድን ፀጋዎች
የሰሊጥ፣ የማሾና የቦለቄ ምርቱ የውጭ ምንዛሬ ማስገኛ አማራጮች ናቸው
ሁሉን አብቃይ የሆነው አፈሯ፣ አየሯና ምልካዓ ምድሯ ለኑሮ ተስማሚ ለኢንቨስትመንትም ተመራጭ ያደርጋታል
ስለሆነም የሚመለከተው አካል የህዝባችን እንግልት የአካባቢውን የመልማት ፍላጎትና ፍትሀዊ ተጠቃሚነት በውል ተመልክቶ ምላሽ እንዲሰጠን ስንል እንጠይቃለን ።
ትኩረት ለእብናትና አካባቢው !!!
06/09/2015 ዓ.ም

ከአሰፋ ወንድሙ የፌስቡክ ገፅ ላይ የተወሰደ

Good Job
14/05/2023

Good Job

18/01/2023
30/12/2022
እብናት ላይ ኢንቨስት ያድርጉ
14/12/2022

እብናት ላይ ኢንቨስት ያድርጉ

Address

Wogagen
Ebbenat

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when እብናት - መቶ ፕሮጄክቶች posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to እብናት - መቶ ፕሮጄክቶች:

Share