YEGNA Saving and Credit Cooperative Ltd

YEGNA Saving and Credit Cooperative Ltd Saving and credit cooperative

Vacancy Announcement
20/02/2026

Vacancy Announcement

17/02/2026

የቁጠባና ብድር ኀብረት ሥራ ማህበራት የፋይናንስ አገልግሎትን ወደ ማህበረሰቡ ደጃፍ የሚያደርሱ ተቋማት ናቸው
******
ቁጠባን በማሰባሰብ እና ተመጣጣኝ ብድር በመስጠት፣ የገንዘብ ቁጠባ እና ብድር ኅብረት ሥራ ማህበራት አባላትን ንግድ እንዲጀምሩ፣ እንዲያስፋፉ እና የቤተሰብ ኑሮአቸውን እንዲያሻሽሉ ይደግፋሉ::

ጠንካራ የቁጠባና ብድር ኀብረት ሥራ ማህበር ማለት አካታች ፋይናንስ፣ ደህንነቱ የተጠበቀ የአባላት ቁጠባ እና ጠንካራ የአካባቢ ኢኮኖሚ ግንባታ ማለት ነው።

በዚህ ረገድ በሀገራችን የበርካታ ዜጎችን ህይወት መቀየር የቻሉ በርካታ የገንዘብ ቁጠባ እና ብድር ኅብረት ሥራ ማህበራት ተፈጥረዋል፡፡

እስከ 2017 ዓ.ም በጀት ዓመት መጨረሻ በሀገራችን በአጠቃላይ ከ7.1 ሚሊዮን በላይ አባላት ያሏቸው 18,256 መሰረታዊ የገንዘብ ቁጠባ እና ብድር ኅብረት ሥራ ማህበራት፣ 124 ዩኒየኖች እና 2 ፌዴሬሽኖች በስራ ላይ ይገኛሉ፡፡

የቁጠባ መጠን በመሰረታዊ ማኅበራት 56.86 ቢሊዮን ብር፣ በዩኒየኖች 2.48 ቢሊዮን ብር፣ በፌዴሬሽኖች ደግሞ 19.2 ሚሊዮን ብር፣ በድምሩም 59.36 ቢሊዮን ብር ደርሷል፡፡

ከ14.6 ቢሊዮን ብር በላይ ካፒታል ማፍራትም ችለዋል፡፡

ጥር 30/2018 ዓ.ም" ህብረት ሥራ ከምርት እስከ ግብይት፣ከአምራች እስከ ሸማች" በሚል መሪ ቃል ሲካሄድ የቆየው  ኤግዚብሽን እና ባዛር  በዛሬው እለት ተጠናቀቀ።ከጥር 26-30/2018 ዓ...
07/02/2026

ጥር 30/2018 ዓ.ም

" ህብረት ሥራ ከምርት እስከ ግብይት፣ከአምራች እስከ ሸማች" በሚል መሪ ቃል ሲካሄድ የቆየው ኤግዚብሽን እና ባዛር በዛሬው እለት ተጠናቀቀ።

ከጥር 26-30/2018 ዓ.ም ድረስ በአዲስ አበባ ኤግዚቢሽን ማዕከል ሲካሄድ በቆየው ባዛር ላይ የፌደራልና የአዲስ አበባ ህብረት ስራ ኮምሽን ከፈተኛ አመራሮች በአካል በመገኘት ስለ ማህበሩ ገለፃ ተደርጎላቸዋል።

የኛ ቁጠባና ብድር ኃ/የተ/የህ/ስራ ማህበር ለአምስት ቀናት በቆየው ኤግዚብሽንና ባዛር ላይ አገልግሎቱን በሰፊው አስተዋዉቋል ።

05/02/2026
ዛሬም እንደቀጠለ ይገኛል ፡፡ከጥር 26-30 በኤግዚብሽን ማእከል  በድምቀት እየተካሄደ የሚገኘው 12 ተኛው የህብረት ስራ ኤግዚበሽን እና ባዛር ዛሬ ሁለተኛ ቀኑን ይዟል፡፡ የኛ ቁጠባና ብድር...
04/02/2026

ዛሬም እንደቀጠለ ይገኛል ፡፡ከጥር 26-30 በኤግዚብሽን ማእከል በድምቀት እየተካሄደ የሚገኘው 12 ተኛው የህብረት ስራ ኤግዚበሽን እና ባዛር ዛሬ ሁለተኛ ቀኑን ይዟል፡፡
የኛ ቁጠባና ብድር በቦታው በመገኘት ለተሳታፊዎች እራሱን እያስተዋወቀ ይገኛል፡፡
እርሶም ወደ ኤግዚቢሽን ማእከል መጥተው ይጎበኙ ያተርፉበታል፡፡ ስለየኛ መረጃ በመውሰድ አባል መሆን እና ቁጠባ መጀመር ይችላሉ፡፡

ጥር 26/2018 ዓ.ም" ህብረት ሥራ ከምርት እስከ ግብይት፣ከአምራች እስከ ሸማች" በሚል መሪ ቃል የተዘጋጀው  ኤግዚብሽን እና ባዛር  በይፉ ተከፈተ።የኛ ቁጠባና ብድር ኃ/የተ/የህ/ስራ ማህ...
03/02/2026

ጥር 26/2018 ዓ.ም

" ህብረት ሥራ ከምርት እስከ ግብይት፣ከአምራች እስከ ሸማች" በሚል መሪ ቃል የተዘጋጀው ኤግዚብሽን እና ባዛር በይፉ ተከፈተ።
የኛ ቁጠባና ብድር ኃ/የተ/የህ/ስራ ማህበር በኤግዚብሽኑ ላይ እየተሳተፈ ይገኛል።

ከጥር 26-30/2018 ዓ.ም ድረስ በአዲስ አበባ ኤግዚቢሽን ማዕከል ለህዝብ ክፍት ሆኖ የሚቆይ ሲሆን መግቢያ ነፃ መሆኑን ከአዘጋጆች ለማወቅ ተችሏል።

ጥር 25/2018 ዓ.ምየኛ ቁጠባና ብድር ኃ/የተ/የህ/ስራ ማህበር " ኅብረት ሥራ ከምርት እስከ ግብይት፣ ከአምራች እስከ ሸማች” በሚል መሪ ቃል በተዘጋጀው  ሲምፖዚየም፣ ኤግዚብሽን እና ባዛ...
02/02/2026

ጥር 25/2018 ዓ.ም

የኛ ቁጠባና ብድር ኃ/የተ/የህ/ስራ ማህበር " ኅብረት ሥራ ከምርት እስከ ግብይት፣ ከአምራች እስከ ሸማች” በሚል መሪ ቃል በተዘጋጀው ሲምፖዚየም፣ ኤግዚብሽን እና ባዛር ላይ መሳተፍ ጀመረ።
ከመላው አገሪቱ የተመረጡ የህብረት ስራ ማህበራት እየተሳተፉ የሚገኙ ሲሆን የኛ ቁጠባና ብድርም ከድሬዳዋ ተሞክሮውን ለማቅረብ አራት አባላትን የያዘ የማህበሩ የቦርድ አመራሮችና ሰራተኞች አዲስ አበባ
ተገኝተዋል።
በዛሬው እለት ጥር 25 በዓድዋ ሙዚየም እየተካሄደ በሚገኘው ሲምፖዚየም ላይ እየተሳተፈ የሚገኝ ሲሆን ከጥር 26-30/2018 ዓ.ም ድረስ ደግሞ በኤግዚቢሽን ማዕከል ኤግዚቢሽንና ባዛር ተሳታፊ እንደሚሆን ለማወቅ ተችሏል።

የ2018 ዓ.ም የኅብረት ሥራ ኤግዚቢሽን፣ ባዛር እና ሲምፖዚየም በማስመልከት ጋዜጣዊ መግለጫ ተሰጠ*****ዛሬ፣ በኢትዮጵያ ኅብረት ሥራ ኮሚሽን ለ12ኛ ጊዜ፣ በአዲስ አበባ ኅብረት ሥራ ኮሚሽ...
29/01/2026

የ2018 ዓ.ም የኅብረት ሥራ ኤግዚቢሽን፣ ባዛር እና ሲምፖዚየም በማስመልከት ጋዜጣዊ መግለጫ ተሰጠ
*****
ዛሬ፣ በኢትዮጵያ ኅብረት ሥራ ኮሚሽን ለ12ኛ ጊዜ፣ በአዲስ አበባ ኅብረት ሥራ ኮሚሽን ደግሞ ለ5ኛ ጊዜ የተዘጋጀውን የኅብረት ሥራ ኤግዚቢሽን ባዛር እና ሲምፖዚየም በማስመልከት ጋዜጣዊ መግለጫ ተሰጥቷል፡፡

በመግለጫውም በአሁኑ ወቅትም የተለያዩ አገልግሎቶችን የሚሰጡ ከ89 ሺህ በላይ መሰረታዊ የኅብረት ሥራ ማህበራት ከ25 ሚሊዮን በላይ ዜጎችንም በአባልነት በማቀፍ አገልግሎት በመስጠት ላይ መሆናቸው የተጠቆመ ሲሆን፣ በተጨማሪም በሀገር አቀፍ ደረጃ 435 የኅብረት ሥራ ዩኒየኖች እና 4 ፌዴሬሽኖች እንደሚገኙ ተጠቁሟል፡፡

እነዚህ ኀብረት ሥራ ማህበራትም የገጠር ምርትን ከከተማ ግብይት፣ አምራችን ከሸማች ጋር በቀጥታ በማገናኘት አካታች ኢኮኖሚያዊ እድገትና ማህበራዊ ፍትሃዊነት ለማረጋገጥ ወሳኝ ሚና እየተጫወቱ መሆኑን የኢትዮጵያ ኅብረት ሥራ ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር አቶ ሺሰማ ገ/ስላሴ ገልጸዋል፡፡

በሀገራችን እየተከናወነ ካለው የኀብረት ሥራ ማህበራት የሪፎርም አጀንዳ ጋር ተያይዞም፣ ኀብረት ሥራ ማህበራት ከባህላዊ አሠራር ወጥተው የአዲሱ ትውልድ ኀብረት ሥራ መገለጫ የሆኑ ገበያ ተኮር፣ ተወዳዳሪ፣ ተጠያቂና ዘላቂ የቢዝነስ ተቋማት እንዲሆኑ ቀጣይነት ያለው ስራ እየተሰራ ይገኛል ያሉ ሲሆን፣ በሪፎርሙ ኀብረት ሥራ ማህበራት ከምርት እስከ ግብይት ባለው ሁሉን አቀፍ የእሴት ሰንሰለት ውስጥ ምርትን በብዛትና በጥራት እንዲያቀርቡ ጥረት እየተደረገ ነው ብለዋል።

በዚህም ከ98 ከመቶ በላይ በግብርና ግብዓት አቅርቦት እንዲሁም በከተሞች የምርት አቅርቦትና ግብይት በተሰራው ስራም በሀገር አቀፍ ደረጃ 378 ኀብረት ሥራ ማህበራት ከ1400 በላይ በሚሆኑ የቅዳሜ እና እሁድ ገበያዎች በንቃት በመሳተፍ የገበያ ዋጋን በማረጋጋትና የዋጋ ግሽበትን በመከላከል የበኩላቸውን ሚና እየተጫወቱ እንደሆነ ጠቁመዋል::

ዘንድሮም በኢትዮጵያ ኅብረት ሥራ ኮሚሽን ለ12ኛ ጊዜ፣ በአዲስ አበባ ኅብረት ሥራ ኮሚሽን ደግሞ ለ5ኛ ጊዜ የተዘጋጀው የኅብረት ሥራ ኤግዚቢሽን ባዛር እና ሲምፖዚየምም የኅብረት ሥራ ማኅበራትን አቅም በመገንባት፣ ምርት እና አገልግሎት በማስተዋወቅ፣ የገበያ መዳረሻ በማስፋት፣ ዘላቂነት ያለው የገበያ ትስስር በመፍጠር እና የገበያ ዋጋ በማረጋጋት ሂደት ውስጥ ትልቅ ሚና ይጫወታል ብለዋል፡፡

በዘነድሮው ኤግዚቢሽን እና ባዛር ከ360 በላይ ኅብረት ሥራ ማህበራት የሚሳተፉ ሲሆን ከ300 ሚሊዮን ብር በላይ የቀጥታ ግብይት እና የገበያ ትስስር ይፈጣራል ተብሎ እንደሚጠበቅ ጠቁመዋል፡፡

የአዲስ አበባ ኅብረት ሥራ ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር አቶ ተጫነ አዱኛ በበኩላቸው በዘነድሮው ኤግዚቢሽን እና ባዛር ከ80 ሺህ በላይ የከተማው ነዋሪ ይሳተፋል ተብሎ እንደሚጠበቅ ጠቁመው፣ ባጠቃላይ በአዲስ አበባ ከተማ ደረጃ 164 ኅብረት ሥራ ማህበራት ይሳተፋሉ ብለዋል፡፡

ዘንድሮ በኢትዮጵያ ኅብረት ሥራ ኮሚሽን ለ12ኛ ጊዜ፣ በአዲስ አበባ ኅብረት ሥራ ኮሚሽን ደግሞ ለ5ኛ ጊዜ የተዘጋጀው የኅብረት ሥራ ኤግዚቢሽን ባዛር እና ሲምፖዚየም፣ ሲምፖዚየሙ ጥር 25 በአድዋ ሙዚም አዳራሽ፣ ኤግዚቢሽን እና ባዛሩ ደግሞ ከጥር 26 እስከ 30 በአዲስ አበባ ኤግዚቢሽን ማእከል እንደሚዘጋጅ ተጠቁሟል፡፡

28/01/2026
Vacancy Announcement 📢 📢 📢Yegna SACCO’sThrive Together
17/01/2026

Vacancy Announcement 📢 📢 📢
Yegna SACCO’s
Thrive Together

Address

Dire Dawa

Opening Hours

Monday 08:00 - 12:00
14:30 - 17:30
Tuesday 08:00 - 12:00
14:30 - 17:30
Wednesday 08:00 - 12:00
14:30 - 17:30
Thursday 08:00 - 12:00
14:30 - 17:30
Friday 08:00 - 12:00
14:30 - 17:30
Saturday 08:00 - 12:00

Telephone

+251921666444

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when YEGNA Saving and Credit Cooperative Ltd posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to YEGNA Saving and Credit Cooperative Ltd:

Share