Debre Berhan International Investment & Finance Expo2024

Debre Berhan International Investment & Finance Expo2024 ኢንቨስትመንት የአገራዊ ኢኮኖሚ አብዮት መሣሪያ ነው!

14/11/2025
12/11/2025
11/11/2025
11/11/2025
ኢንዱስትሪዎች የአካባቢን ጥሬ ዕቃ በመጠቀም ተኪ ምርቶችን እያመረቱ ነው። ደብረብርሃን: ጥቅምት 18/2018 ዓ.ም (አሚኮ) የአካባቢን ጥሬ ዕቃ በመጠቀም ወደ ሥራ የገቡ ኢንዱስትሪዎች 8 ሚ...
29/10/2025

ኢንዱስትሪዎች የአካባቢን ጥሬ ዕቃ በመጠቀም ተኪ ምርቶችን እያመረቱ ነው።

ደብረብርሃን: ጥቅምት 18/2018 ዓ.ም (አሚኮ) የአካባቢን ጥሬ ዕቃ በመጠቀም ወደ ሥራ የገቡ ኢንዱስትሪዎች 8 ሚሊዮን ዶላር የሚያወጡ ተኪ ምርቶች ማምረታቸውን የደብረብርሃን ከተማ አሥተዳደር ኢንዱስትሪ እና ኢንቨስትመንት መምሪያ አስታውቋል።

ወደ ሥራ ከገቡ እና ተኪ ምርቶችን እያመረቱ ከሚገኙ ኢንዱስትሪዎች መካከል የአር ዜድ ኤክስ የጨርቃ ጨርቅ ፋብሪካ ይገኝበታል።

የአር ዜድ ኤክስ የጨርቃ ጨርቅ ፋብሪካ የንብረት ክፍል ኀላፊ አብርሃም ከተማ ፋብሪካው በርካታ የሀገር ውስጥ ጥሬ እቃዎችን በመጠቀም ኮምፎርት፣ አንሶላ እና የትራስ ልብሶችን እያመረተ እንደሚገኝ ተናግረዋል።

ፋብሪካው ያመረታቸውን ምርቶችም ለሀገር ውስጥ ገበያ እያቀረበ ነው ብለዋል።

ንብረትነቱ የአማራ ደን ኢንተር ፕራይዝ የኾነ ጥሬ ዕቃን በመጠቀም የሀገር ውስጥ ገበያን ለማርካት እየተሠራ መኾኑን የገለጹት ደግሞ የደብረ ብርሃን እንጨት ማቀነባበሪያ ፋብሪካ ኀላፊ ጌታቸው ይልማ ናቸው።

ጥራቱን የጠበቀ ምርት በማምረት ከግለሰብ እስከ ድርጅት ድረስ ቋሚ ደንበኞች እንዳሉ ያነሱት አቶ ጌታቸው ምርቱንም ለአካባቢው ነዋሪዎች እያቀረበ እንደኾነ አንስተዋል።

በደብረብርሃን ከተማ አሥተዳደር የሚገኙ የአካባቢን ጥሬ እቃ በመጠቀም ስምንት ኢንዱስትሪዎች ተኪ ምርት እያመረቱ እንደሚገኙ የከተማ አሥተዳደሩ ኢንዱስትሪ እና ኢንቨስትመንት መምሪያ ኀላፊ ብርሃን ገብረሕይወት ተናግረዋል።

የአካባቢን ጥሬ ዕቃ በመጠቀም ወደ ሥራ የገቡ ኢንዱስትሪዎች 8 ሚሊዮን ዶላር የሚያወጡ ተኪ ምርቶች ማምረታቸውን ነው ያብራሩት።

ወደ ሥራ ከገቡት ኢንዱስትሪዎች መካከል 4 ኢንዱስትሪዎች ምርታቸውን ለሀገር ውስጥ ገበያ ከማቅረብ ባለፈ ለውጭ ገበያ ማቅረብ መቻላቸውን ጠቁመዋል።

ከውጭ የሚገቡ ምርቶችን ለማስቀረት በከተማ አሥተዳደሩ የሚገኙ 74 የአካባቢ ጸጋዎችን በመለየት በትኩረት እየተሠራ መኾኑንም አመላክተዋል።

የሚመረቱ ምርቶች ለአካባቢው ነዋሪዎች በተመጣጣኝ ዋጋ ተደራሽ ለማድረግ በጥቃቅን እና አነስተኛ ኢንዱስትሪዎች፣ በኅብረት ሥራ ማኅበራት በኩል እንዲቀርብ እየተሠራ ነው ብለዋል።

በደብረብርሃን ከተማ አሥተዳደር በ2018 የመጀመሪያው ሩብ ዓመት 3 ነጥብ 4 ቢሊዮን ብር ያስመዘገቡ 46 ኢንዱስትሪዎችን ወደ ሥራ ለማስገባት እየተሠራ መኾኑንም አመልክተዋል።

ዘጋቢ፦ ስንታየሁ ኃይሉ

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

01/08/2025
10/03/2025
ከ2 ቢሊየን ብር በላይ በሆነ ካፒታል የተገነቡ ፋብሪካዎች  ተመረቁደብረብርሃን ፣ የካቲት 18/2017 ዓ/ም (ደብመኮ) በደብረ ብርሃን ከተማ በ2 ቢሊየን 130 ሚሊየን ካፒታል የተገነቡ 5ቱ...
25/02/2025

ከ2 ቢሊየን ብር በላይ በሆነ ካፒታል የተገነቡ ፋብሪካዎች ተመረቁ

ደብረብርሃን ፣ የካቲት 18/2017 ዓ/ም (ደብመኮ) በደብረ ብርሃን ከተማ በ2 ቢሊየን 130 ሚሊየን ካፒታል የተገነቡ 5ቱ ፋብሪካዎች ተመረቁ።

የኢፌደሪ የኢንዱስትሪ ሚኒስትር አቶ መላኩ አለበል ፣ የአማራ ክልል ዋና አፈጉባኤ ክብርት ፋንቱ ተስፋዬ፣ የአማራ ክልል ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ኀላፊ አቶ ይርጋ ሲሳይ፣ የአማራ ክልል ኢንዱስትሪ ኢንቨስትመንት ቢሮ ኀላፊ አቶ እንድሪስ አብዱ፣ የደብረ ብርሃን ከተማ ተቀዳሚ ከንቲባ አቶ በድሉ ውብሸት ተገኝተው መርቀዋል።

የተመረቁት ተሻለ አለባቸው ደስታ የፎም ምርት ውጤቶች ማምረቻ ፣ፍሮንቴር ኢንተርናሽናል ትሬዲንግ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር የጅብሰም ቦርድ ማምረቻ ፣ ሚሊዮን አለማየሁ ንጽህና መጠበቂያ -ኮስሞቲክስ ማምረቻ ፣በላይ ግዛው እንደሻው ምግብ ኮምፕሌክስ ማምረቻ ሲፋን ኔው ኢነርጅ ማኑፋክቸሪንግ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር የመኪና ባትሪ ማምረቻ ፋብሪካዎች ናቸው።

06/02/2025

Address

Addis Ababa
Debre Birhan

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Debre Berhan International Investment & Finance Expo2024 posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share