04/06/2026
"ሰኔ እና ሰኞ... አይግጠም"
ሰኔ እና ሰኞ አይግጠም የሚለው የቆየ የአባቶቻችን አባባል ዘንድሮም በ 2018 ዓ.ም. በአይናችን ልናየው በትክክል ገጥሟል። ሰኔ 1 ቀን ሰኞ ይውላሎል።
ከ 1979 ዓ.ም. ጀምሮ እስከ ዛሬ... በከፊል እንይ እስኪ..
1)1979 ዓ.ም. ( ዘመነ ማቲዎስ) በ1979 ዓ.ም. ሰኔ እና ሰኞ ሲገጥም አገሪቱ በከባድ ፈተና ውስጥ ነበረች የ1977ቱ ታላቁ ድርቅ መዘዝ እና በወቅቱ የነበረው የዝናብ እጥረት ተከስቶ ነበረ።
2) 1984 ዓ.ም.( ዘመነ ማርቆስ) በዚህ ወቅት ሰኔ እና ሰኞ በድጋሜ ገጠሙ። ህይ ዓመት የሽግግር ወቅት ቀውስ እንደነበረ የታሪክ መዛግብቶች በጥልቀት ያወሱናል። በዚህም ወቅት በመላው አገሪቱ ከፍተኛ የጸጥታ መደፍረስ ና ግጭት ነገሰ።
3) 1990 ዓ.ም. ( ዘመነ ማርቆስ) በዚህም ወቅት ሰኔ እና ሰኞ ሲገጥም በአገሪቱ ላይ ሊላ የደም ምዕራፍ ተከፈተ።በኢትዮጵያ እና በኤርትራ መካከል የተነሳው እጅግ አስከፊ የነበረው የባድሜ የድንበር ጦርነት በዚሁ አመት ፈነዳ።
4) 1997 ዓ.ም. ( ዘመነ ዮሐንስ) በ 1997 ላይ ደግሞ ታሪኩ ይበልጥ ልብ ሰባሪ ሆኗል።1997 ሰኔ እና ሰኞ ገጠመ። ያ ታዋቂው እና ውጥረት የበዛበት አገራዊ ምርጫ 97 የተካሄደው በዚህ ወቅት ነበር።
5) በ2007 ዓ.ም. (ዘመነ ዮሐንስ) ከ 10 ዓመታት በኋላ በ 2007 ዓ.ም. በድጋሜ በዘመነ ዮሐንስ ሰኔ እና ሰኞ ገጠሙ።
6) 2013 ዓ.ም. (ዘመነ ማርቆስ) በቅርብ ጊዜ ትውስታችን በሆነው በ 2013 ዓ.ም. ሰኔ እና ሰኞ በድጋሜ ገጠሙ። በዚህም ወቀት የጦርነት የጭንቀት የከበሮ ድምፅ የነበረ መሆኑን ሁላችንም እናስታውሳለን።
የታሪክ ፍሰት አያችሁ? አሁን ደግሞ ወደ ዘንድሮ እንምጣ። ዘንድሮ 2018 ዓ.ም. ነው።አመቱም ድጋሜ ዘመነ ማርቆስ ነው! ሰኔ እና ሰኞ ገጥመዋል። እንደ 1997ቱ, እና 2007ቱ ሁሉ:ዘንድሮም ሰኔ እና ሰኞ በዘመነ ማርቆስ ላይ መውደቃቸው ታዘባቸሁ? ታሪክ እራሱን ይደግማል? ወይንስ እኛ ካለፈው ተምረን ራሳችንን እና አገራችንን እንጠብቃለን? የዘንድሮው የሰኔ እና ሰኞ ገጠመኝ ለኢትዮጵያ ወጣቶች የጥንቃቄ የማስተዋል እና የሰላም ጊዜ ይሁንልን።
አባቶቻችን በምክንያት ነው > ያሉት አስተውሉ !
ፈጣሪ ኢትዮጵያንና ሕዝቦቿን ይጠብቅ!🇪🇹🇪🇹