16/03/2021
የገንዘብ ቁጠባና ብድር ህብረት ስራ ማህበራት የፋይናንስ ተደራሽነትን በማፋጠን ወደር የለሽ ሞተር ከመሆናቸውም ባለፈ የድህነትን ተራራ መናድ የሚቻልባቸው መሳሪያዎች ናቸው:: በመሆኑም የነጻነት ፋና የገንዘብ ቁጠባና ብድር ኃ.የተወ ህብረት ስራ ዩኒየን ይህንን በመገንዘብ ማህበራት ለተቋቋሙለት አላማ ሚናቸው በአግባቡ እንዲወጡ 3 ቅርንጫፎችን በመክፈት ለአባል ማህበራት የቁጠባ፡ የብድር፡ አነስተኛ የህይወት መድን ኢንሹራንስ፡ የሰብል ኢንሹራንስ፡ የስልጠና፡ የክትትል እና ድጋፍ እንዲሁም የህትመት አገልግሎት እየሰጠ ቢገኝም የሚመለከተው መንግስታዊም ይሁን መንግስታዊ ያልሆነ ባለድርሻ አካል እነዚህን መሳሪያዎች በመደገፍና በማጠናከር ማህበራት ሚናቸውን በተገቢው እንዲወጡ እንዲያግዝ እና የማህበራት ልምድ በማስፋፋት የድርሻቸውን እንዲወጡ ጥሪያችን እናቀርባለን፡፡
ጊዜው ለተደራጁት ነው!!!!!!!