ANRS Bureau of Women, Youth & Social Affairs

ANRS Bureau  of Women, Youth & Social Affairs Bahir Dar Ethiopia

"7ኛው ጠቅላላ ምርጫ የአማራ ክልል ሕዝብ እና አመራሩ ወደ አዲስ የመንቃት ምዕራፍ የተሻገሩበት የልዩ ዘመን መክፈቻ ነው" ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመሥገን ጥሩነህ
05/06/2026

"7ኛው ጠቅላላ ምርጫ የአማራ ክልል ሕዝብ እና አመራሩ ወደ አዲስ የመንቃት ምዕራፍ የተሻገሩበት የልዩ ዘመን መክፈቻ ነው"

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመሥገን ጥሩነህ

የጎጅ ልማዳዊ ድርጊቶችን ለመከላከል ሁሉም ባለ ድርሻ አካላት ርብርብ ሊያደርግ እንደሚገባ ጥሪ ቀረበ።የጎንደር ከተማ አስተዳደር ሴቶች ህፃናትና ማህበራዊ ጉዳይ መምሪያ የጎጅ ልማዳዊ ድርጊት ...
05/06/2026

የጎጅ ልማዳዊ ድርጊቶችን ለመከላከል ሁሉም ባለ ድርሻ አካላት ርብርብ ሊያደርግ እንደሚገባ ጥሪ ቀረበ።

የጎንደር ከተማ አስተዳደር ሴቶች ህፃናትና ማህበራዊ ጉዳይ መምሪያ የጎጅ ልማዳዊ ድርጊት መከላከል ላይ ያተኮረ የምክክር መድረክ ከባለ ድርሻ አካላት ጋር አካሂዷል።

በሀገራችን የሚከሰቱ ጎጅ ባህላዊ ድርጊቶችን ለመከላከል የሚያግዙ ደንቦችንና ህጎች መኖራቸውን
በውይይት መድረኩ ላይ የተገኙት የጎንደር ከተማ አስተዳደር ፍትህ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ግርማ ጌታቸው ገልፀዋል።

የጎጅ ባህላዊ ድርጊቶችንና ህገ ወጥ የሰዎችን ዝውውር ለመከላከል ለህብረተሰቡ ግንዛቤ በመፍጠር ቤተሰቡንና ህብረተሰቡን እንዲጠብቅ ለማድረግ ሁሉም ባለ ድርሻ አካላት ኃላፊነቱን ሊወጣ እንደሚገባ አቶ ግርማ ተናግረዋል።

ጎጅ ባህላዊ ድርጊቶችን ለመከላከል በሚደረገው ጥረት ከግንዛቤ ፈጠራ ስራዎች ባሻገር የህግ ማስከበር ስራዎችንም ትኩረት መስጠት አስፈላጊ መሆኑን ገልፀዋል።

የጎንደር ከተማ አስተዳደር ከንቲባ የማህበራዊ ዘርፍ አማካሪ አቶ አወቀ ተፈራ በበኩላቸው በጎጅ ባህላዊ ድርጊቶች የሚከሰቱ ችግሮችን ለመከላከል የችግሩን መንስኤ በጥናትና ምርምር መለየትና የመከላከያ ስርዓት መዘርጋት አስፈላጊ መሆኑን ተናግረዋል።

የጎንደር ከተማ አስተዳደር ሴቶች ህፃናትና ማህበራዊ ጉዳይ መምሪያ ኃላፊ ወይዘሮ ሙሉቀን ጌታሁን ደግሞ የ በሴቶች ላይ የሚፈፀሙ ጥቃቶችን ለመከላከል የቅንጅት ስራዎችን ማጠናከር እንደሚገባ ገልፀዋል።

የሃይማኖት አባቶች በማስተማር የፍትህ ተቋማት ደግሞ ህግን በማስከበር የፆታዊ ጥቃትን በመከላከል ረገድ ሚናቸውን ሊወጡ እንደሚገባ ጠቁመዋል ።

በዕለቱ በክፍለ ከተሞች በአጋር ተቋማት የጎጅ ባህላዊ ድርጊቶችን ለመከላከል እየተከናወኑ ያሉ ስራዎች የእቅድ አፈፃፀም ሪፓርት በውይይት መድረኩ ላይ ቀርበዋል።

በውይይቱ ላይ የሴቶች ጥቃት ፣ ግግ ማስፈልፈል፣ ህገ ወጥ የሰዎች ዝውውርን መከላከል፣ የሴቶች የጉልበት ብዝበዛ፣የአደንዛዥ ዕፅ ተጠቃሚዎችን በመከላከል ረገድ የተሰሩ ስራዎች በቀረቡት ሪፓርቶች ተመላክተዋል።

ከጎንደር ዩኒቨርስቲ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የአንድ ማዕከል አገልግሎት አስተባባሪ አቶ ዋኘው ሰጤ ደግሞ በአንድ ማዕከል አገልግሎት ተጠቃሚ የሆኑ የህብረተሰብ ክፍሎችን ለማገዝ የፍትህ ተቋማት እያደረጉት ያለው የህግ ድጋፍ የሚያበረታታ መሆኑን ተናግረዋል።

የኢዮሪካ የበጎ አድራጎት ድርጅ ት አስተባባሪ
ወይዘሮ ፅጌማሪያም ፈንታው በበኩሏቸው በየትኛውም ቦታ ላይ ሴቶች ተጋላጭነት የመጨመር አዝማሚያ እያሳዬ መሆኑን ሃሳባቸውን አካፍለዋል።

የውይይቱ ተሳታፊዎች በበኩላቸው የጎጅ ባህላዊ ድርጊቶችን ለመከላከል መሰረታዊ ችግሮች ተቀናጅቶ መፍታት ፣ በወጣቱ ላይ በትኩረት መስራት ፣ የጎጅ ባህላዊ ድርጊት መከላከል ስራዎችን መስራት፣ ህብረተሰቡ ላይ የሚስተዋለውን የሞራልና መልካም እሴቶች መሸርሸርን መልሶ መገንባት እንደሚገባ አስተያየታቸውን ገልፀዋል።

ጎጅ ባህላዊ ድርጊቶቾን ለመከላከል በትኩረት መስራት ይኖርብናል ያሉት አስተያየት ሰጭዎቹ በአጥፊዎቾ ላይ ህጋዊ ርምጃ መወሰድ ፣ ለፍትህ ተቋማት ተገቢውን ማስረጃ በማቅረብ ለፍትህ ስርዓቱ አጋዥ መሆን ይጠበቅብናል ብለዋል።

በውይይቱ የሃይማኖትት አባቶች ፣የማህበራዊ ዘርፍ አመራሮች ፣የፀጥታ አካላት ፣መንግስትታዊ ያልሆኑ ድርጅት ተወካዮችና የመምሪያ ኃላፊዎች ተሳትፈዋል።

ጎንደር ከተማ ኮሙኒኬሽን

የባህርዳር ከተማ አስተዳደር ሴቶች ወጣቶችና ማህበራዊ ጉዳይ መምሪያ ለወጣት አደረጃጀቶች የሊደር ሽፕ ስልጠና ተሰጠ።ስልጠናውን አስመልክቶ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የባህር ዳር ከተማ አስተዳ...
05/06/2026

የባህርዳር ከተማ አስተዳደር ሴቶች ወጣቶችና ማህበራዊ ጉዳይ መምሪያ ለወጣት አደረጃጀቶች የሊደር ሽፕ ስልጠና ተሰጠ።

ስልጠናውን አስመልክቶ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የባህር ዳር ከተማ አስተዳደር ሴቶች ወጣቶችና ማህበራዊ ጉዳይ መምሪያ የወጣቶች አደረጃጀት ስብዕና ልማት ቡድን መሪ በሆኑት በወ/ሮ ሁሉአገርሽ አቻምየለህ ያስጀመሩት ሲሆን ወጣቶች የመሪነት ጥበብ እውቀት እንዲኖራቸው እና በስልጠናው ያገኙትን እውቀት ለሚመሩት ወጣት ለማስተላለለፍ እንዲችሉ ይህ የስልጠና ፕሮግራም መዘጋጀቱን አብራርተዎል።

ስልጠናውን ከማህበረ ህይወት በመጡት በአቶ ጌታለም አይቸው አማካኝነት በመሰጠት ላይ ሲሆን ለወጣት አደረጃጀቶች በሊደር ሽፕ ዙርያ የአመራር ጥበብ ማለት ምን ማለት እንደሆነ ፣ እይታ ማለት ምን ማለት እንደሆነ ፣ የእይታ ትርጉምና ወሳኝነት ፣ የእይታ ክፍተት እንዲሁም በአመለካከት ዙሪያ በሚሉት ርዕሰ ጉዳዬች ላይ ሰፊ ስልጠና ተሰጥቶል።

ግንቦት /2018 ዓ.ም

ከባህርዳር ከተማ አስተዳደር ሴቶች ወጣቶችና ማህበራዊ ጉዳይ መምሪያ፤

ፕላን ኢንተርናሽናል ከUNHCR እና RRS ጋር በመተባበር የተለያዩ ጉዳት ላለባቸው ተማሪዎች የድጋፍ ቁሳቁሶች አበረከተፕላን ኢንተርናሽናል በUNHCR እና RRS ትብብር በገንዳውሃ ከተማ አስ...
05/06/2026

ፕላን ኢንተርናሽናል ከUNHCR እና RRS ጋር በመተባበር የተለያዩ ጉዳት ላለባቸው ተማሪዎች የድጋፍ ቁሳቁሶች አበረከተ

ፕላን ኢንተርናሽናል በUNHCR እና RRS ትብብር በገንዳውሃ ከተማ አስተዳደር ስር ለሚገኙ የተለያዩ አካል ጉዳት ላለባቸው ተማሪዎች የመማሪያና የድጋፍ ቁሳቁሶችን በይፋ አስረክቧል።
የተደረገው ድጋፍ ከፊል መስማት ለተሳናቸው፣ አይነ ስውራን እና የእንቅስቃሴ ችግር ላለባቸው ተማሪዎች የሚያገለግሉ ክራንች፣ ዊልቸር እና ሌሎች የድጋፍ ቁሳቁሶችን ያካተተ ሲሆን፣ ተማሪዎቹ በእኩል ዕድል ትምህርታቸውን እንዲከታተሉና በትምህርት ቤት ውስጥ ያሉ ተግዳሮቶችን እንዲቀንሱ የሚያግዝ ነው።

በድጋፉ ስነ-ስርዓት ላይ የገንዳ ውሃ ከተማ ትምህርት ጽሕፈት ቤት ሀላፊ አቶ በየነ አዳነ ተገኝተው ባደረጉት ንግግር፣ ፕላን ኢንተርናሽናል፣ UNHCR እና RRS ለተማሪዎቹ ያደረጉትን ድጋፍ ከፍተኛ ምስጋና በመግለጽ፣ ይህ ድጋፍ አካል ጉዳተኛ ተማሪዎች በትምህርታቸው ላይ በሚያጋጥሟቸው ችግሮች ላይ ጉልህ መፍትሔ እንደሚያመጣ ገልጸዋል።
በተጨማሪም የሁሉንም ተማሪዎች ተሳትፎ የሚያረጋግጥ አካታች ትምህርት ለመገንባት የተቋማቱ ድጋፍ ቀጣይነት እንዲኖረው ጥሪ አቅርበዋል።

የተደረገው ድጋፍ ማንኛውም ተማሪ በአካል ጉዳቱ ምክንያት ከትምህርት እንዳይገለል የሚያግዝ ሲሆን፣ የትምህርት እኩልነትን፣ ተደራሽነትን እና ማህበራዊ አካታችነትን ለማጠናከር የሚያበረክት እርምጃ መሆኑ ተጠቅሷል።

“ሁሉም ልጆች ያለ ልዩነት የመማር መብት አላቸው፤ የተደረገው ድጋፍም ይህንን መብት በተግባር ለማረጋገጥ የተወሰደ ጠቃሚ እርምጃ ነው።” ተብሏል።

ምንጭ፤- ከምዕራብ ጎንደር ሴቶች ወጣቶችና ማህበራዊ ጉዳይ መምሪያ

05/06/2026

ለዛሬዎቹ ህጻናት ፍቅርና በጎነትን እናውርስ !

በጎንደር ከተማ አስተዳደር ግብርና መምሪያ ለነፍሰ ጡር እና ለአጥቢ እናቶች የስርዓተ ምግብ ስልጠና ሰጠ።በጎንደር ከተማ አስተዳደር ግብርና መምሪያ በሰቆጣ ቃል ኪዳን ፕሮግራም አማካኝነት በም...
04/06/2026

በጎንደር ከተማ አስተዳደር ግብርና መምሪያ ለነፍሰ ጡር እና ለአጥቢ እናቶች የስርዓተ ምግብ ስልጠና ሰጠ።

በጎንደር ከተማ አስተዳደር ግብርና መምሪያ በሰቆጣ ቃል ኪዳን ፕሮግራም አማካኝነት በምግብና በስርዓተ ምግብ ጽንሰ ሀሳብ ዙሪያ ለነፍሰ ጡር እና ለአጥቢ እናቶች ስልጠና ሰጥቷል።

የጎንደር ከተማ ግብርና መምሪያ የምግብና የስርዓተ ምግብ ቴክኖሎጂ ባለሙያ አቶ ደግፍ ዘውዱ እንደገለጹት፣ ስልጠናው እናቶች በስርዓተ ምግብ ዙሪያ በቂ ግንዛቤ እንዲኖራቸው እና የተመጣጠነ ምግብ በመመገብ ጤናማና አምራች ዜጋ ለመፍጠር ያለመ መሆኑን ገልጸዋል።

ያልተመጣጠነ ምግብ የስነ-ምግብ እጥረትን እና የሕፃናት እድገት መቀንጨርንና መቀጨጭን ሊያስከትል እንደሚችል ጠቁመዋል።

ተመጣጣኝ ምግብ አመጋገብ፣ በእናቶችና በሕፃናት ጤና ላይ የስርዓተ ምግብ ያለው አስፈላጊነት፣ ከአካባቢ ሀብት በመጠቀም የተለያዩ የምግብ አይነቶችን ማዘጋጀት እና የቤተሰብ ምግብ ደህንነትን ማሻሻል በሚቻልባቸው መንገዶች ላይ ግንዛቤ እንደተፈጠረላቸው ገልጸዋል ።

ህፃናትን ለ1000 ቀናት የተመጣጠነ ምግብ እንዲያገኙ እናቶች ከነብሰጡር ጀምሮ የተመጣጠነ ም ግብ መመገብ እንዳለባቸዉ ጠቅሰዉ ከተወለዱ ሁለት ዓመት እስኪሞላቸዉ እናቶች ህፃናትን የተመጣጠነ ምግብ መመገብ እንደሚገባቸዉ ተናግረዋል፡፡

ስልጠናው የእናቶችንና የሕፃናትን የምግብ ይዘት ለማሻሻል፣ የስነ-ምግብ እጥረትን ለመቀነስ እና ጤናማ ትውልድ ለመፍጠር ያለመ መሆኑ አቶ ደግፍ ተናግረዋል ።

የስልጠናው ተሳታፊ እናቶችም ከስልጠናው ያገኙትን እውቀት በተግባር በመተግበር የቤተሰባቸውን የምግብ ሁኔታ ለማሻሻል እንደሚሰሩ ገልጸዋል።

ምንጭ:- ጎንደር ከተማ አስተዳደር ሴቶች፣ ወጣቶችና ማህበራዊ ጉዳይ መምሪያ

የክረምቱን መግባት ተከትሎ ከሚከሰት የወባ በሽታ ጥንቃቄ ማድረግ ይገባል። ወቅቱን መገንዘብ እና ተገቢውን ቅድመ ጥንቃቄ ማድረግ እጅግ መሠረታዊ ነገር ነው። ሞቃታማው ወራት አልፎ ቅዝቃዜ ከሚ...
04/06/2026

የክረምቱን መግባት ተከትሎ ከሚከሰት የወባ በሽታ ጥንቃቄ ማድረግ ይገባል።

ወቅቱን መገንዘብ እና ተገቢውን ቅድመ ጥንቃቄ ማድረግ እጅግ መሠረታዊ ነገር ነው። ሞቃታማው ወራት አልፎ ቅዝቃዜ ከሚተካበት ወራት ልንደርስ ጫፍ ላይ እንገኛለን። ይህ ወቅት ታዲያ ጥንቃቄ የሚፈልግ ጊዜ ነው።

በተለይም ለሰው ልጅ የጤና ጠንቅ የኾነችው ወባ አምራቹን በስፋት ልታጠቃ የምትችልበት ምቹ አጋጣሚ የሚፈጠርበትም ጊዜ ነው። በባሕር ዳር ከተማ አንዳንድ አካባቢዎች ዜጎች በወባ ተጠቅተው በጤና ጣቢያዎች መገኘት ጀምረዋል።

በባሕር ዳር ከተማ አሥተዳደር ጤና መምሪያ የኅብረተሰብ ጤና አደጋዎች መከላከያ እና መቆጣጠሪያ አሥተባባሪ ይዘንጋው መኮንን በክረምት መግቢያ እና መውጫ ላይ ያሉ ጊዜያቶችን ሰዎች ጥንቃቄ ማድረግ ካልቻሉ በወባ መጠቃታቸው አይቀሬ ይኾናል ይላሉ።

አሁን ላይ በከተማው በወባ የመጠቃት ሁኔታ በየሳምነቱ እየጨመረ መሄዱን ከጤና ጣቢያዎች የሚደርሰው መረጃ እየጠቆመ እንደሚገኝም ተናግረዋል።
ከተማ አሥተዳደሩ ቀድሞ ወባን ለመከላከል ቅድሚያ ተጠቂ ናቸው ላላቸው እና አቅማቸው አነስተኛ ለኾኑ 26 ሺህ ዜጎች አጎበር ማሰራጨቱን ጠቁመው ሰዎች በተገቢ መንገድ እንዲጠቀሙበትም አስገንዝበዋል።

አጎበር ያላገኙ የከተማዋ ነዋሪዎችም ለበሽታው ትኩረት በመስጠት ከዚህ በፊት የተሠራጨውን በሚገባ ጥቅም ላይ የማዋል እና መግዛት የሚችሉ ደግሞ ገዝተው በመጠቀም ጥንቃቄ እንዲያደርጉ ነው አስተባባሪው የመከሩት።

ከተማ አሥተዳደሩ የዜጎችን ጤና መጠበቅ ቅድሚያ የሚሰጠው ተግባር ነው የሚሉት አሥተባባሪው የአርብ ጠንካራ እጆች በሚል የጽዳት ዘመቻ ሲያካሂድ መቆየቱን ገልጸዋል። ኅብረተሰቡ ከጥቅሙ አንጻር ተረድቶ በሚገባው ልክ እየተረባረበ ባለመኾኑ እንዲሳተፍ ነው ያስገነዘቡት።
ወባን ለመከላከል ዋነኛው ሥራ የአካባቢ ጽዳት እንደኾነ ጠቁመው ለሥራው ትኩረት እንዲሰጥም ነው ያስረዱት።

በባሕር ዳር ከተማ አሁን ላይ በወባ የመጠቃት አዝማሚያ እያሳዩ ያሉት ቀበሌ 11 (ዓባይ ማዶ)፣ መሸንቲ እና በላይ ዘለቀ ክፍለ ከተማ መኾናቸውን ለአብነት አንስተዋል። ለጊዜው እነዚህ አካባቢዎች ይበልጥ ትኩረት እንደሚሹ ነው ያብራሩት።
ሌሎች አካባቢዎችም ወቅቱ ለወባ ምቹ የኾነ ጊዜ መኾኑን በመረዳት ጥንቃቄ ማድረግ ይገባቸዋል ነው ያሉት።

በከተማዋ 10 ጤና ጣቢያዎች፣ 11 ጤና ኬላዎች፣ እና 3 ሆስፒታሎች ኅብረተሰቡን እያገለገሉ ስለመኾኑ የጠቆሙት አስተባባሪው ተቋሞቹ ለወባ ለካርድ ክፍያ ካልኾነ በስተቀር መድኃኒት በነጻ በመኾኑ ትኩሳት ሲኖር በፍጥነት ወደ ሕክምና መሄድ ይገባል ነው ያሉት። በጤና ተቋሞቹም በቂ የኾነ መድኃኒት ስለመኖሩም ነው ያስረዱት።

አምራች እና ለሀገር ወሳኝ የኾነው ኃይል በወባ እንዳይጎዳ ግን ጥንቃቄ ማድረግ እና ግንዛቤ መፍጠር እንደሚገባም ነው የጠቆሙት።

ከአማራ ኮሙኒኬሽን ቢሮ

04/06/2026

”የአካል ጉዳተኞችን ተሳትፎ ማረጋገጥ የሁላችንም ሀላፊነት ነው !!”

አንድ ልብ ለትውልድ የህፃናት የሴቶች እና የአረጋዊያን መርጃ ድርጅት ከባህርዳር ከተማ አስተዳደር ሴቶች ወጣቶችና ማህበራዊ ጉዳይ መምሪያ ጋር በመተባበር ከ100 ሽህ ብር በላይ የሚያወጣ የን...
04/06/2026

አንድ ልብ ለትውልድ የህፃናት የሴቶች እና የአረጋዊያን መርጃ ድርጅት ከባህርዳር ከተማ አስተዳደር ሴቶች ወጣቶችና ማህበራዊ ጉዳይ መምሪያ ጋር በመተባበር ከ100 ሽህ ብር በላይ የሚያወጣ የንጽህና መጠበቂያ ቁሳቁስ በግዮን 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ለሚማሩ110 ሴት ተማሪዎች ለ2 ዓመት የሚጠቀሙበት የንጽህና መጠበቂያ ድጋፍ ተደረገ ።

አንድ ልብ ለትውልድ የህፃናት የሴቶች እና የአረጋዊያን መርጃ ድርጅት በስሩ ካሉ10 ፕሮጀክቶች መካከል እኔም ለእህቴ የተሰኘው ፕሮጀክት አንዱ ሲሆን ይህ ፕሮጀክት በዋናነት ትኩረት አድርጎ የሚሰራው በማረሚያ ተቋማት፣ በጦርነት እና በተፈጥሮ አደጋ ለተጎዱ ሴት እህቶቻችን የንጽህና መጠበቂያ ድጋፍ ማድርግና በንጽህና መጠበቂያ መግዣ እጦት ምክንያት ትምህርት የሚያቋርጡ ሴት እህቶቻችን ያለ ምንም ችግር ትምህርታቸውን እንዲማሩ ጥራቱን የጠበቀ የንጽህና መጠበቂያ ድጋፍ ማድረግ ዋና ተግባሩ መሆኑን የገለፁት የአንድ ልብ ለትውልድ የህፃናት የሴቶች እና የአረጋዊያን መርጃ ድርጅት መስራች እና ዳይሬክተር ወ/ሮ ማራናታ ተክለሰንበት ሲሆኑ ይህንንም ድጋፍ ላለፍት 10 ዓመታት ለበርካታ ሴት እህቶቻችን ያለእረፍት ማገልገላቸውን ገለፀዋል።

በቀጣይም ፕሮጀክቱ በባህር ዳር ከተማ በርካታ የድጋፍ ስራዎችን እንደሚሰራና የተጀመርውም ድጋፍ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ተገልጿል ።

ግንቦት 2018 ዓ.ም ባህርዳር


ምንጭ፤- ከባህርዳር ከተማ አስተዳደር ሴቶች ወጣቶችና ማህበራዊ ጉዳይ መምሪያ

7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ሰላማዊ ሆኖ በመጠናቀቁ እንኳን ደስ አለን - የኢትዮጵያ ፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤትየኢትዮጵያ ፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ሰላማዊ ሆኖ ...
03/06/2026

7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ሰላማዊ ሆኖ በመጠናቀቁ እንኳን ደስ አለን - የኢትዮጵያ ፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት

የኢትዮጵያ ፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ሰላማዊ ሆኖ በመጠናቀቁ የተሰማውን ደስታ ለመላው የኢትዮጵያ ሕዝብ ገልጿል።

የፖለቲካ ፓርቲዎች፣ የፀጥታ ኃይል አካላት እንዲሁም ሕዝቡ እና ሌሎች ባለድርሻ አካላት በሙሉ ምርጫው በሰላም እንዲጠናቀቅ ለተወጡት ሀገራዊ ኃላፊነት እና ላሳዩት ፅናትም ምክር ቤቱ ያለውን ምስጋና እና አድናቆት ገልጿል።

ምክር ቤቱ በመግለጫው፣ “ልዩነቶቻችንን እና ችግሮቻችንን በዴሞክራሲያዊ መንገድ በመፈታት በምርጫው የታየውን ሰላም በማስቀጠል የበኩላችንን ሚና እንወጣ፤ ለሀገራችን ዘላቂ ሰላም በጋራ እንቁም” ሲል ጥሪውን አቅርቧል።

አማራ ኮሙኒኬሽን

Address

Amhara National Reginal State
Bahir Dar
1238

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when ANRS Bureau of Women, Youth & Social Affairs posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share