Tana cosacou

Tana cosacou ይህ የጣና ኃ.የተወሰነ የህብረት ስራ ማህበራት የገንዘብ ቁጠ?

ሚያዚያ 02 ፡2015ዓ.ምጣና ዩኒዬን የ9ወር የስራ አፈጻጸም ገመገመ፣ በትላንትናው እለት የዩኒዬኑ የስራ አመራር ቦርድ አባላት፣የቁጥጥር ኮሚቴዎችና ባለሙያወች በተገኙበት የሦስተኛው ሩብ አመ...
10/04/2023

ሚያዚያ 02 ፡2015ዓ.ም
ጣና ዩኒዬን የ9ወር የስራ አፈጻጸም ገመገመ፣ በትላንትናው እለት የዩኒዬኑ የስራ አመራር ቦርድ አባላት፣የቁጥጥር ኮሚቴዎችና ባለሙያወች በተገኙበት የሦስተኛው ሩብ አመት ስራ ተገምግሟል። የሁሉም ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ስራ አስኪያጆች ሪፖርት አቅርበዋል፣በቀረበው ሪፖርትም ላይ በዘጠኝ ወራት የተከናወኑ የዋና ዋና ተግባራት አፈጻጸም በጥንካሬና በድክመት ተከፋፍሎ ታይቷል።ባለሙያው እና ማኔጅመንቱ እንዲሁም የቦርድ አመራሩ በድክመት የተቀመጡትን ተግባራት በሚቀጥሉት ሦስት ወራት ሙሉ በሙሉ ቀርፎ የበጀት አመቱን እቅድ 100% እንዲዘጋ መልዕክት ተላልፏል።
www.facebook.com/tanacooprativeunion
በሌላ በኩል ሁሉም የቁጠባና ብድር እንዲሁም የሂሳብ ባለሙያወች በተመደቡበት ወረዳ የሚገኙ አባል ማህበራትን በማጠናከር ለአመራርና ቅጥር ሰራተኛ ስልጠና በመስጠትና የሂሳብ አሰራራቸውን አሻሽለው በህግና በመመሪያው መሰረት እየሰሩ አባሎቻቸው የሚተማመኑባቸው ዘላቂ የኅብረት ስራ ማህበራት እንዲሆኑ የበኩላቸውን መወጣት እንደሚጠበቅባቸው ለባለሙያወች የቤት ስራ ተሰጥቷል።
www.facebook.com/tana.4361

The activities that make savings and credit unions different from other similar associations are set with the activities...
17/03/2023

The activities that make savings and credit unions different from other similar associations are set with the activities of financial and financial activities. If finances are not managed systematically and properly, or if they cannot be explained, it can cause widespread problems for the associations. Savings and credit unions are based on savings and contributions from members.
Associations' assets can be distributed as loans, dividends or as a source of income.
Savings, financial loans from management bodies and money kept in the form of trust (Management's loan) member's lot registered as a loan by the association, undistributed profit, money kept together, and the direct release is displayed. All these are the of the association.
The association provides credit services to members and similar associations based on the above-mentioned resources. This is money for loan servicing as a source of income for the association. For loan money, the money must be returned to the association at the time of repayment. However, due to various reasons and cases of excess treatment, the amount spent for loan service may be collected in full.
At this time were created.
is also following this process as it is important to take precautions before disbursing loans to prevent arrears. we are working together with various partners in every district and kebele to make the arrears due to various reasons.

1)ውዝፍ ብድሮችን ዜሮ ማድረስ፤
2) የዩኒዬኑ አፈጻጸም መለካት
#------------------------------ #-------------------------------
የገንዘብ ቁጠባና ብድር ኅብረት ስራ ማህበራት ከሌሎች መሰል ማህበራት ለየት የሚያደርጋቸው ተግባራት በሆኑ ተግባራት ጋር የተገናኘ ነው።ፋይናንስ በስርዓትና በአግባቡ ካልተመራ ወይም ማስረዳደር ካልተቻለ ማህበራቱ ላይ ሰፊ #ቀውስ ሊያስከትል ይችላል። የገንዘብ ቁጠባና ብድር ኅብረት ስራ ማህበራት ሃብት መሰረት የሚያደርገው አብዛኛውን ከአባላት ከሚሰበሰብ ቁጠባና ከዕጣ ካፒታል ነው።
የማህበራት ሃብት በእዳና በካፒታል ወይም በሀብት ምንጭነት አጠቃቀም ተብሎ ሊከፈል ይችላል። ቁጠባ፣ከአበዳሪ አካላት የተገኘ ብድር እና በአደራ መልክ የተቀመጠ ገንዘብ(የአስተዳድሩልኝ ብድር) በማህበሩ በእዳነት የሚመዘገብ ሲሆን፣የአባላት ዕጣ፣ያልተከፋፈለ ትርፍ፣በመጠባበቂያነት የተቀመጠ ገንዘብ፣በስጦታ የተገኘ ደግሞ በካፒታል መልክ ይታያል። እነዚህ ሁሉ የማህበሩ ናቸው።
ማህበሩ ለአባሉና ለመሰል ማህበር የብድር አገልግሎት የሚሰጠው ከላይ ከተጠቀሱት የሃብት ምንጮች ነው።ለማህበሩ ዋነኛው የገቢ ምንጭ ይህ ለብድር አገልግሎት የዋለው ገንዘብ ነው።ለብድር የዋለው ገንዘብ በመመለሻ ጊዜው ወደ ማህበሩ መመለስ ያለባቸው ለዚሁ ነው።
ሆኖም ግን በተለያዩ ምክንያቶችና ከአቅም በላይ በሆኑ አጋጣሚወች ለብድር አገልግሎት የወጣው ገንዘብ ሙሉ በሙሉ ላይሰበሰብ ይችላል። በዚህ ጊዜ ውዝፍ ብድር ተፈጠረ እንላለን።
ውዝፍ ብድር እንዳይፈጠር ብድር ከመሰራጨቱ በፊት ቅድመ ጥንቃቄ ማድረግ ወሳኝ በመሆኑ ይህንን ሂደት እየተከተለ ይገኛል።ከዚህ በተለያዩ ወረዳወች በልዩ ልዩ ምክንያቶች የተፈጠረውን ውዝፍ ብድር #ዜሮ ለማድረግ በየወረዳውና በየቀበሌው ከተለያዩ አጋር አካላት ጋር በጋራ በመሆን የማስመለስ ስራ እየሰራ ይገኛል።
------------------------- #---------------------------
ሌላው የሀብት ምንጭ የሚሆነው የማህበሩ ካፒታል አቅምን ማጎልበት ሥራ ነው።ለዚህም የአባላት ቁጥር በየጊዜው የማሳደግ ተግባር ወሳኝና ወደ ጎን ሊተው የማይቻል ስራ ነው።ይህንን ተግባር ለማከናወን ማህበሩ አስተማማኝ የፋይናንስ አሰራር ስርዓት ላይ መቆም አስተማማኝ የካፒታል አቋም ላይ ማህበሩ መገኘት በአባላትና በማህበሩ ደንበኞች መካከል አሜኔታን ይፈጥራል።በአካባቢው ካሉ ከሌሎች የፋይናንስ ተቋሞች ጋር ሲነጻጸር ልቆ እንዲገኝ ያስችለዋል።
ለዚህ ደግሞ ማህበሩ በየጊዜው አፈጻጸሙን መገምገም፣ያለበትን ደረጃ መለየትና ማወቅ አለበት ። የፋይናንስ መገምገሚያ መለኪያ በየወሩ እያዘጋጀ ዩኒዬኑ ያለበትን አቋም በመለካት ይገመግማል።

27/06/2015ዓ.ም የዩኒዬኑ የስራ አመራር ቦርድ ሰብሳቢ፣የቁጥጥር ኮሚቴ የማኔጅመንት አባላትና ባለሙያወች በተገኙበት የሰባት ወር የእቅድ ክንውን አፈጻጸም ግምገማ ተካሂዷል።የፋይናንስ። የ...
07/03/2023

27/06/2015ዓ.ም የዩኒዬኑ የስራ አመራር ቦርድ ሰብሳቢ፣የቁጥጥር ኮሚቴ የማኔጅመንት አባላትና ባለሙያወች በተገኙበት የሰባት ወር የእቅድ ክንውን አፈጻጸም ግምገማ ተካሂዷል።
የፋይናንስ። የቁጠባና ብድር ክፍል ኃላፊወች በበጀት አመቱ በ7ወራት የተከናወኑ ዋና ዋና ተግባራት አፈጻጸማቸው በአምስቱ ቅርንጫፍ ጽ/ቤቶች ምን ይመስላል የሚለውን ለታዳሚወች ካቀረቡ በኋላ በዩኒዬኑ የስራ አመራር ቦርድ ሰብሳቢና በዩኒዬኑ ዋና ስራ አስኪያጅ መሪነት ሰፋ ያለ ውይይት ሲካሄድ ቆይቷል።
በዛሬው ውይይት.....
በዋናነት አባል ማህበራትን በመደገፍ፣በመከታተልና በማጠናከር በየወረዳው ሞዴል የሆኑ ኅብረት ስራ ማህበራትን መፍጠር ዘላቂ አስተማማኝ የፋይናንስ ተቋም ሁነን መገኘት አለብን በሚል ነጥብ የጋራ ውይይት ተደርጓል።
በተጨማሪም.....
ከአባላት በቁጠባ ከሚሰበሰቡ ገንዘቦችና ከተለያዩ መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች በሚገኝ የተዘዋዋሪ ብድር ለአባል ማህበራት ይሰራጫል ተብሎ በተያዘው እቅድ መሰረት እንዲሁም አባላት በጠየቁት ጥያቄ መሰረት የብድር ጥያቄ ያቀረበው ማህበር እየተገመገመ ብድሩ እየተሰራጨ እንደሚገኝ ተጠቁሟል። ይሁን እንጅ የብድር ስርጭቱ የአባላትን ፍላጎት ማርካት እንዲችል ሁሉም የቁጠባና ብድር ባለሙያወች በየወረዳው ያሉ አባል ማህበራት ቁጠባ እንዳያቆራርጡ፣ ከሰብል ሽያጭ የሚገኘውን ገንዘብ በዩኒዬኑ ላይ በመቆጠብ ተጠቃሚ እንዲሆኑ ግንዛቤ መፍጠር እንደሚጠበቅባቸው መልዕክት ተላልፏል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ...
ለአባል ማህበራት ብድር በሚሰራጭበት ወቅት ተበዳሪወች አስተማማኝ የብድር ዋስትና በማቅረብና ህጋዊ የሆነ የብድር ውል እንዲይዙ በማድረግ ብድሩ እንዲሰራጭ ክትትልና ቁጥጥር በማድረግ ከተሰራጨ በኋላም ብድሩ ለታለመለት አላማ እንዲውል እንዲሁም በመመለሻ ጊዜው በአግባቡ እንዲመልሱ ባለሙያው የቅርብ ክትትልና ድጋፍ በማድረግ ውዝፍ ዝድር ከመፈጠሩ በፊት ቅድሚያ ጥንቃቄ ማድረግ እንደሚገባ በውይይቱ ላይ ተነስቷል።

በመጨረሻም.....

ዛሬ የቀረበውን የስራ አፈጻጸም ሪፖርት መነሻ በማድረግ በቀሪ ወራቶች በበጀት አመቱ የተያዘውን እቅድ ሙሉ በሙሉ ፈጽሞ ለመገኘት ሁሉም ባለድርሻ አካላት የበኩላቸውን በመወጣት ለዩኒዬኑ ስራ መሳካት በጎ አሻራቸውን እንዲያስቀምጡ የቀጣይ አቅጣጫ በማስቀመጥ ስብሰባው ተጠናቋል።
ጣና የህዝብ ባንክ!!!

On 27/06/2015, an evaluation of the performance of the seven-month plan was conducted in the presence of the members of the union's executive board, management members of the control committee and experts.
After the officials of the finance, savings and loan department presented to the audience what the performance of the main activities in the 7 months of the fiscal year was like in the five branch offices, a wide discussion was held under the leadership of the chairman of the management board of the union and the general manager of the union.
In today's conversation.....
There was a joint discussion on the point that we should be a sustainable and reliable financial institution by supporting, monitoring and strengthening member associations and creating model cooperatives in each district.
in addition.....
According to the plan that indirect loans from members' savings and various non-governmental organizations will be distributed to the member associations, and based on the questions asked by the members, it is indicated that the loan is being distributed by the association that submitted the loan request. However, a message has been sent that all the savings and loan experts in each district should create awareness so that the member associations in every district do not cut down on savings, so that the money from the sale of crops can be saved and benefited by the union.
Meanwhile...
During the distribution of loans to member associations, the borrowers should be provided with a reliable loan guarantee and have a legal loan contract.
Finally.....
Based on the work performance report presented today, the meeting was concluded by setting a direction for all the stakeholders to do their part and leave a good mark for the success of the work of the Union in the remaining months of the budget year.
Tana Public Bank!!!
www.facebook.com/tanacooprativeunion
www.facebook.com/tana.4361

ጣና ዩኒየን
Tana cosacou

ተቋማት ጋር የሚለያዩባቸው ዋነኛ ምክንያቶች፦ #1.የህዝብ ተቋማት ናቸው፤ #2.አባላት ከማህበሩ ላይ ባለቤትም ተገልጋይም ነው #3.በአርሶ አደሩ ደጃፍ ስር የሚገኙ ተቋም ናቸው #4.እያንዳን...
27/02/2023

ተቋማት ጋር የሚለያዩባቸው ዋነኛ ምክንያቶች፦
#1.የህዝብ ተቋማት ናቸው፤
#2.አባላት ከማህበሩ ላይ ባለቤትም ተገልጋይም ነው
#3.በአርሶ አደሩ ደጃፍ ስር የሚገኙ ተቋም ናቸው
#4.እያንዳንዱ ውሳኔ በአባላት ድምጽ የተመሠረተ ነው
#5.የቁጠባ ወለድና የብድር ወለድ በአባላት ድምጽ ይወሰናል
#6. ለአባላት አገልግሎት ሰጭ እንጅ ለትርፍ የተቋቋሙ አይደሉም
#7.ማህበሩ የሚያተርፈው ትርፍ መልሶ በትርፍ ክፍፍል መርህ መሰረት ለአባላት እንዳላቸው የዕጣ መጠን መሰረት ይከፋፈላል
#8. ለአባላት ብድር የሚሰጡትን አባላት በወሰኑት የብድር ወለድ መሰረት ነው
#9.የሚመሩት ወይም የሚተዳደሩት በአባላት ብቻ ነው
#10.አባላት በገ/ቁ/ብ/ኅ/ስ/ማህበርት ባለቤትም ተገልጋይም ናቸው፤
#11. ብድር በተለይ አነስተኛ ገቢ ላለው ማህበረሰብ የሚሰጡ ናቸው፤
#12.የገ/ቁ/ብ/ኅ/ስ/ማህበራት የህዝብ ባንክ ናቸው!!

የገንዘብ ቁጠባና ብድር ኅብረት ስራ ማህበራት ለ አርሶ አደሩ አለኝታ ናቸው!!
ጣና የኅብረት ስራ ማህበራት የገንዘብ ቁጠባና ብድር ዩኒዬን!!
www.facebook.com/tanacooprativeunion
www.facebook.com/tana.4361

-------------------------  ----------------------------- #1. የኅብረት ሥራ ማኅበራት አባልነት በማኅበራቱ አገልግሎት ለመጠቀም ለሚፈልጉናየአባልነት ግዴታዎች...
18/02/2023

------------------------- -----------------------------
#1. የኅብረት ሥራ ማኅበራት አባልነት በማኅበራቱ አገልግሎት ለመጠቀም ለሚፈልጉና
የአባልነት ግዴታዎችን ለመቀበል ፈቃደኛ ለሆኑ ሰዎች ሁሉ በጾታ፣ በማኅበራዊ አቋም፣ በዘር፣ በፖለቲካ አመለካከት፣ በአካል ጉዳተኝነት ወይም በሃይማኖት ልዩነት ሳይደረግ ለሁሉም ክፍት የሆኑ ተቋሞች ናቸው።
#2. የኅብረት ሥራ ማኅበራት ፖሊሲ በማውጣትና ውሳኔዎችን በማስተላለፍ የነቃ
ተሳትፎ በሚያደርጉ አባላት የሚመሩ ዲሞክራሲያዊ ድርጅቶች ናቸውናቸው።በተጨማሪ እያንዳንዱ አባል እኩል ድምጽ አላቸው።
#3. ትርፍ ላይ ለመጠባበቂያ እና ለሌሎች አገልግሎቶች ተቀንሶ ከተቀመጠ በኋላ አባላት
ከኅብረት ሥራ ማህበሩ በገዙት ዕጣ መጠን እና ባደረጉት ተሣትፎ መሠረት ቀሪው ትርፍ የሚከፋፈልባቸው ተቋማት ናቸው።
#4. ኅብረት ሥራ ማኅበራት ከሌሎች አካላት ጋር መንግሥትንም ጨምሮ ስምምነት የሚያደርጉት ወይም ከኅብረት ሥራ ማኅበራቸው ውጭ ከሚገኝ ምንጭ ገንዘብ በመበደር ካፒታላቸውን ማሳደግ የሚችሉት የአባላት ዲሞክራሲያዊ ቁጥጥርን በሚያረጋግጥ፣ የኅብረት ሥራ ማኅበራቸውን የራስ በራስ ማስተዳዳር መብት በሚጠብቅ እንዲሁም የራስ አገዝ ባህሪውን
በማይነካ ሁኔታ ነው።
#5. የኅብረት ሥራ ማኅበራት አባላት፣ ተመራጮች፣ ሥራ አስኪያጅ እና ሠራተኞች
ለኅብረት ሥራ ማኅበራቸው ዕድገት ተገቢውን አስተዋጽኦ እንዲያበረክቱ ትምህርትና ሥልጠና እንዲያገኙ ያደርጋሉ፤ ስለ ኅብረት ሥራ ማኅበራት ምንነትና ጥቅም ለሕዝቡ በተለይም ለወጣቱ ያስተዋውቃሉ፡፡
#6. በአካባቢ፣ በሀገር አቀፍ፣ በአህጉር አቀፍ እና በዓለም አቀፍ ደረጃ ከሚገኙ የኅብረት ሥራ ማህበራት መዋቅሮች ጋር በመተባበር የኅብረት ሥራ ማህበራት እንቅስቃሴን በማጠናከር አባሎቻቸውን በሚገባየሚያገለግሉ ተቋማት ናቸው።
#7. ኅብረት ሥራ ማኅበር አባሎቻቸው ባፀደቋቸው ፖሊሲዎች አማካኝነት በአካባቢያቸው
ላለው ኅብረተሰብ ዘላቂ ልማት ለማምጣት የሚያስችል ተግባር የሚያከናውኑ ተቋማት ናቸው።
ምንጭ፡የኅብረት ስራ ማህበራት መርሆች
www.facebook.com/tana.4361
www.facebook.com/tanacooprativeunion

16/05/2015ዓ.ምጣና ኃ/የተ የኅብረት ስራ ማህበራት የገንዘብ ቁጠባና ብድር ዩኒዬን 15ኛ አመት 11መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤውን ነዛሬው እለት እያካሄደ ይገኛል፣በጉባኤው ላይ ከክልል፣ከዞንና...
24/01/2023

16/05/2015ዓ.ም
ጣና ኃ/የተ የኅብረት ስራ ማህበራት የገንዘብ ቁጠባና ብድር ዩኒዬን 15ኛ አመት 11መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤውን ነዛሬው እለት እያካሄደ ይገኛል፣
በጉባኤው ላይ ከክልል፣ከዞንና ከወረዳ ኅ/ስራ ማ/ማ/ተ/ጽ/ቤት ጥሪ የተደረገላቸው ኃላፊዎችና በሁሉም ወረዳ የሚገኘ የዩኒዬኑ አባል ማህበራት አመራሮች ፣የስራ አመራር ቦርዶችና ቁጥጥር ኮሚቴዎች እንዲሁም የዩኒዬኑ ባለሙያዎች እና ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተሳታፊ ሁነዋል፣

የዛሬው ጉባኤ ከሌሎች ጉባኤወች ለየት የሚያደርገው ዩኒዬኑ የቦታ ባለቤት ከሆነበት ማግስት በመሆኑ ነው፣

ከዛሬው ጉባኤ ምን ይጠበቃል ?
፨ የስራ አመራር ቦርድ ሪፖርት ይቀርባል
፨የቁጥጥር ኮሚቴ ሪፖርት ያቀርባል
፨የዋና ዋናቭተግባራት አፈጻጸም ይቀርባል
፨በክክል ኦዲተሮች የ2013/14ኦዲት ሪፕርት ይቀባል
፨ የ2014/15 እቅድ ይቀርባል በመጨረሻም በተያዘው መርሃግብር መሰረት የእውቅናና ሽልማት ዝግጅት ይኖራል ተብሎ ይጠበቅበታል!!

13/05/2015ዓ.ምከብዙ እልህ አስጨራሽ ትግል እና ድካም በኋላ ጣና ዩኒዬን የቦታ ባለቤት መሆን ችሏል። ይህንንም ደስታ የጠቅላላ ጉባኤው ተወካዮች በተገኙበት በድምቀት አክብሯል። ለዚህ ስ...
21/01/2023

13/05/2015ዓ.ም
ከብዙ እልህ አስጨራሽ ትግል እና ድካም በኋላ ጣና ዩኒዬን የቦታ ባለቤት መሆን ችሏል። ይህንንም ደስታ የጠቅላላ ጉባኤው ተወካዮች በተገኙበት በድምቀት አክብሯል። ለዚህ ስራ መሳካት ከፍተኛ አስተዋዖ ላደረጉት አካላት በተለይ ለዩኒዬኑ ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ በላቸው ጥላሁን ትልቅ ምስጋና ይገባቸዋል በማለት የስራ አመራር ቦርድ ሰብሳቢ የሆኑት አቶ አዱኛ አመራና የቦርዱ አባል አቶ ይዘንጋው ዋለልኝ ውይይቱን በምስጋና ክፍተውታል።
--------------------------------------------------------------
በዛሬው እለት ሁሉም የጠቅላላ ጉባኤ ተወካዮችና ፣የስራ አመራር ቦርድ፣ የቁጥጥር ኮሚቴወችና ጥሪ የተደረገላቸው የማህበራት አመራሮች በተገኙበት በዚሁ ፕሮግራም ላይ ከቦታ ማግኘት ደስታ ማብሰር አልፎም በተለያዩ አጀንዳዮች ላይ ውይይት ተደርጓል።
በውይይቱ ላይ ከተነሱ ሃሳቦች መካከል ዩኒዬኑ ባገኘው በዚሁ ቦታ ላይ ለኅብረት ስራ ማህበራት የምርምር እና ስልጠና ማዕከል በመገንባት ዩኒዬኑ መሰረታዊ ማህበራት ከገቡበት ውድቀት መታደግ እንዳለበት ተገልጿል። በተጨማሪም ዩኒዬኑ ባቀፋቸው ወረዳወች የሚገኙ ማህበራት ያጋጠማቸውን ችግሮች በመለየት ሁሉም ባለድርሻ አካላት ዘላቂ የሆነ መፍትሔ ማስቀመጥ እንደሚገባውም ተገልጿል።
በዛሬው ውይይት ለዩኒዬኑ ከዚህ መድረስ ደከመኝ ሰለቸኝ ሳይሉ ትልቅ ተጋድሎ ሲያደርጉ ለቆዩት አመራሮችና አጋር አካላት ምስጋና ቀርቦላቸዋል። ከነዚህም መካከል የቀድሞው የክልል ኅ/ስራ ማ/ማ/ተ/ጽ/ቤት ባለሙያ በአሁኑ ሰዓት የቀንዲል የገ/ቁ/ብ/ኅ/ስራ ማህበር ሰብሳቢ የሆኑት አቶ አሞኘ ፣ የቀድሞው የጣና ዩኒዬን የስራ አመራር ቦርድ ሰብሳቢ አባ ታደሠ፣ እንዲሁም ኅብረት ስራ ማህበራትን እንደ ልጆቹ ለሚወዳቸው፣ለሚያውቃቸውና በትልቅ የኃላፊነት ስሜት እያገለገሉ ለሚገኙት ስመ ጥር እና አንጋፋ አመራር በአሁኑ ሰዓት ደግሞ ለጣና ዩኒዬን የቁጥጥር ኮሚቴ ሰብሳቢ በመሆን እያገለገለ ለሚገኘው ለአባ አስቻለ አይናለም የምስጋና የምስክር ወረቀት ተበርክቶላቸዋል።
በመጨረሻም የዩኒዬኑ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ የፊታችን ማክሰኞ እንደሚካሄድ ተገልጾ ውይይቱ ተጠናቋል።
ጣና የህዝብ ባንክ!!

www.facebook.com/tanacooprativeunion

29/12/2022
ጣና በስኬት ጎዳናዩኒዬኑ የ15አመት ጉዞ ስኬቶች አሃዛዊ መግለጫ...በቅርብ ቀን በፌስቡክ አድራሻችን ይጠብቁንየfacebook ገጻችን  ላይክ በማድረግ እና ለሌሎች በማጋራት አብሮነታችሁን አሳ...
07/12/2022

ጣና በስኬት ጎዳና

ዩኒዬኑ የ15አመት ጉዞ ስኬቶች አሃዛዊ መግለጫ...
በቅርብ ቀን በፌስቡክ አድራሻችን ይጠብቁን

የfacebook ገጻችን ላይክ በማድረግ እና ለሌሎች በማጋራት አብሮነታችሁን አሳዩን፤

www.facebook.com/tana.4361
www.facebook.com/tanacooprativeunion

10/11/2022

ጣና በልማቱ ጎዳና...
የአባል የህብረት ስራ ማኀበራትና አባሎቻቸዉ ማኀበረ-ኢኮኖሚያዊ ችግሮች ፈጥኖ ለመፍታት፣የመስራት አቅምና ብቃት ለማሳደግና ተደራሽ አካባቢያዊ የፋይናንስ አገልግሎት ለመስጠት ዩኒዬኑ የጀመረውን አገልግሎት በመጠንና በሽፋን ለማስፋት እያንዳንዱ አባል ማህበራት በመደገፍ ዉጤታማ ለማድረግ ከመቸውም በላይ እቅድ ነድፎ ወደ ስራ የገባ ተቋም ነው።
#ጣናዩኒዬን
ይህንን ተግባሩን ከግብ ለማድረስ ከራሱ አልፎ አባል መሰረታዊ ማህበራት በተማረ የሰው ኃይል እንዲመራ ባለሙያወችን ቀጥሮ በማሰራት ላይ ይገኛል።
www.facebook.com/tanacooprativeunion
www.facebook.com/tana.4361

Address

11. 5880712283118, 37. 38224383683539
Bahir Dar
6000

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Tana cosacou posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Tana cosacou:

Share