Gole Saving and Credit Cooperative Union

Gole Saving and Credit Cooperative Union Gole saving and credit cooperative union establish in 2005 E.C

ጎል ኃ/የተወሰነ የህብረት ስራ ማህበራት የገንዘብ ቁጠባና ብድር ዩኒየን  የስራ ጊዜያቸዉን ያጠናቀቁ የቦርድ አመራሮችና በጠቅላላ ጉባኤ የተመረጡ አድስ የቦርድ አመራሮች  በዛሬዉ እለት የስራ...
04/01/2026

ጎል ኃ/የተወሰነ የህብረት ስራ ማህበራት የገንዘብ ቁጠባና ብድር ዩኒየን የስራ ጊዜያቸዉን ያጠናቀቁ የቦርድ አመራሮችና በጠቅላላ ጉባኤ የተመረጡ አድስ የቦርድ አመራሮች በዛሬዉ እለት የስራ ርክክብ አደረጉ፡፡ በርክክብ ስነ ስርአት ላይም የስራ ጊዜአቸዉን ያጠናቀቁ አመራሮች አድስ ለተመረጡ አመራሮች ሀሳብና አስተያየት የሰጡ ሲሆን ከነዚህም ዉስጥ የዩኒየኑ ቁጥጥር ኮሚቴ የነበሩት አቶ ሀይሌ ተስፍየ እኛ በነበርንበት ዘመን አንድ አይነት አስተሳሰብና አመለካከት በመያዝ ከቅጥር ሰራተኞች ጋር ሁነን ዩኒየኑን የተሻለ ደረጃ ላይ እንድደርስ በማድረግ ተሸላሚ አድርገናል፡፡እናንተም አድስ አመራሮች ዪኒየኑን ከዚህ የበለጠ ደረጃና ጠንካራ ተቋም እንድሆን የተጣለባችሁን ሀላፊነት እንድትወጡ ትልቅ የቤት ስራ ሰጥተናችኀል ብለዋል፡፡ሌሎች የቦርድ አመራሮችም ከዩኒየኑ አመራርነት ብንለቅም ለአድስ አመራሮች ከጎናቸዉ በመሆን ድጋፍ እንደሚያደርጉላቸዉ ሀሳብ ሰተዋል፡፡ አድስ ከተመረጡ አመራሮችም ዉስጥ የቦርድ ሰብሳቢ የሆኑት አቶ ዳዉድ ሙህየ የተሰጠንን የቤት ስራ ተቀብለን ህዝብ የጣለብንን ሀላፊነት በመወጣት ተቋሙን ዉጤታማ እናደርጋለን በማለት ሀሳብ በመስጠት የስራ ርክክብ አድርገዋል፡፡

ጎልኃ/የተወሰነ  የህብረት ስራ ማህበራት የገንዘብ ቁጠባና ብድር ዩኒየን 12ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤዉን አካሀደ፡፡ በጉባኤዉ ላይ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የአቀስታ ከተማ አስተዳደር ተቀዳሚ...
28/12/2025

ጎልኃ/የተወሰነ የህብረት ስራ ማህበራት የገንዘብ ቁጠባና ብድር ዩኒየን 12ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤዉን አካሀደ፡፡ በጉባኤዉ ላይ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የአቀስታ ከተማ አስተዳደር ተቀዳሚ ከንቲባ አቶ ብርሀን ሽመልስ ጎል ዩኒየን በአጭር ጊዜ ተቋቁም ለዉጥ ያመጣ ዩኒየን ሲሆን ህብረት ስራ ማህበራት ለሀገር ኢኮኖሚ እድገት ወሳኝ ናቸዉ ብለዋል፡፡ ከንቲባዉ አያይዘዉም አባል መሠረታዊ ማህበራት ጠንካራና ተወዳዳሪ ተቋም በመገባት የአባሎቻቸዉን ችግር በመፍታት እንደ ሀገር የልማት የድርሻቸዉን መወጣት እንዳለባቸዉ አሳስበዋል፡፡ በጉባኤዉም የደቡብ ወሎ ዞን ህ/ስራ ፅ/ቤት ሀላፊ፡ቡድን መሪና ባለሙያዎች ፡የተንታ ወሪዳ፡የመቅደላ ወረዳ፡የከላላ ወረዳ፡የለጋምቦ ወረዳ፡የአቀስታ ከተማ ና የጊምባከተማ አስተዳደር ከንቲባዎች፡አስተዳዳረዎች፡ፅ/ቤት ሀላፊዎች፡ አጋር አካላትና የጠቅላላ ጉባኤ አባላት ተገኝተዋል ፡፡ በጉባኤዉም፡-
1.የ2017 አፈፃፀም ሪፖርት
2.የ2018 እቅድ
3.የስራ ጊዜአቸዉ የደረሱ አመራሮችን ማተካካት
4.የተሻለ አፈፃፀም ያላቸዉን ወረዳዎች፡የዩኒየን ቅርንጫፍ ፅ/ቤና አባል መሠረታዊ ማሀበራትን በመሸለም እዉቅና ተሰጥቷል፡፡በመጫረሻም የለጋምቦ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ አልየ ይመር ዩኒየኑ በክልል ደረጃ በ2017 አ.ም በነበረዉ አፈፃፀም 1ኛ በመዉጣት ዋንጫ ያመጣ ሲሆን ዘንድሮም የበለጠ ሰርተን ደረጃችንን ይዘን ማስጠበቅ አለብን በማለት ተልእኮ በመስጠት ጉባኤዉ ተጠቃሏል፡፡

15/02/2025
ጎል ሃ/የተወሰነ የህብረት ስራ ማህበራት የገ/ቁ/ብ/ዩኒዬን የጸጥታ ችግሩ  መጠነኛ በሆነባቸው  የአባል መሰረታዊ የገ/ቁ/ብድር ህብረት ስራ ማህበራት ሰብሳቢዎች /ሊቀመንበሮችና/ሒሳብ ሰራተኞ...
15/02/2025

ጎል ሃ/የተወሰነ የህብረት ስራ ማህበራት የገ/ቁ/ብ/ዩኒዬን የጸጥታ ችግሩ መጠነኛ በሆነባቸው የአባል መሰረታዊ የገ/ቁ/ብድር ህብረት ስራ ማህበራት ሰብሳቢዎች /ሊቀመንበሮችና/ሒሳብ ሰራተኞችን በሁለት አዳራሽ ለሁለት ቀን የሚቆይ ስልጠና ዛሬ ጀምሮ እየሰጠ ይገኛል

በጎል የገንዘብ ቁጠባና ብድር ዩኒየን እና ከአመልድ ኢትዮጵያ ጋር በጥምረት የሚመራው የጅምላ የወጣቶች ስራ ስምሪት በንብ ማነብ ፕሮግራም (ማኢኤኤ) የብድር ስርጭትና አከፋፈል ሂደቶች ላይ ያ...
09/02/2025

በጎል የገንዘብ ቁጠባና ብድር ዩኒየን እና ከአመልድ ኢትዮጵያ ጋር በጥምረት የሚመራው የጅምላ የወጣቶች ስራ ስምሪት በንብ ማነብ ፕሮግራም (ማኢኤኤ) የብድር ስርጭትና አከፋፈል ሂደቶች ላይ ያተኮረ የምክክር መድረክ በመቅደላ ወረዳ ከወሪዳ ቴክኒክ ኮሚቴና ከቀበሌ ከመጡ አጋር አጋር አካላት አካሂዷል፡፡
ዩኒየኑም ከ50 ሚሊዩን ብር በላይ በ ወረዳዉ በፕሮግራሙ ለተመረጡ 4 ቀበሌዎች ስርጭት ለማድረግ እየሰራ ይገኛል ፡፡ዩኒየኑና ፕሮግራሙ በጋራ በመሆን ለወጣት ሴቶች እና ወንዶች የስራ እድል የማመቻቸት አላማ አፅንዖት ሰጥተው 80% ያህሉ ዕድሎች ያተኮሩላቸው በሴቶች ላይ ከፍተኛ ትኩረት ተሰጥቶታል። በተጨማሪም፣ 10% የሚሆኑት እድሎች ለአካል ጉዳተኞች እና ለሌሎች ተጋላጭ ቡድኖች የተመደቡ ናቸው። በክልሉ ያለውን የስራ አጥነት ችግር ለመቅረፍ እና ኢኮኖሚያዊ ልማትን ለማጎልበት ከMaYEA ፕሮግራም ጋር ዩኒየኑ በጋራ ለመስራት ቁርጠኛ መሆኑን አሳዉቋል፡፡። በመድረኩ ብድሩን ለማሰራጨትና ለማስመለስ ከማን ምን ይጠበቃል የሚለዉን ገለፃ የዩኒየኑ ቁጠባ ብድርና የመድህን ዋስትና ክፍል ሃላፊ አቶ ብርሀን በቀለ ማብራሪያ ከሰጡ በኀላ በብድር ስርጭትና አመላለሱ ዙሪያ መግባባት ላይ ተደርሷል።
በመጨረሻም የደቡብ ወሎ ዞን ህብረት ስ/ማ/ማስ/ ፅ/ቤት ፍይናንስ ቡድን መሪ አቶ ደረጀ መንግስቱ ለፕሮግራሙ ስኬት ጎል የገንዘብ ቁጠባና ብድር ዩኒየን ያለውን ወሳኝ ሚና እና ተሳታፊዎቹ የመርሃ ግብሩ የንብ ማነብ ተግባራትን ለማጎልበት፣ ለምርቶች እሴት ለመጨመር እና ለምግብ ዋስትና፣ ለተሻሻለ ኑሮ እና ለአካባቢ ዘላቂነት ዩኒየኑ የበኩሉን አስተዋፅኦ ለማድረግ ያለውን አቅም ተናግረዉ በተነሱት ሀሳብ ላይ ማጠቃለያም ሰጥተዋል።

ጎል ሃ/የተወሰነ የኅ/ስራ ማኅበራት የገ/ቁ/ብድር ዩኒዬን በ25/0512015 ዓ.ም በዋናው ጽ/ቤት በስራ ክልሉ የሚገኙትን የቀበሌ የኅብረት ስራ አደራጅ ባለሙያዎች፤ የወረዳዎች የኅብረት ስራ...
02/02/2023

ጎል ሃ/የተወሰነ የኅ/ስራ ማኅበራት የገ/ቁ/ብድር ዩኒዬን በ25/0512015 ዓ.ም በዋናው ጽ/ቤት በስራ ክልሉ የሚገኙትን የቀበሌ የኅብረት ስራ አደራጅ ባለሙያዎች፤ የወረዳዎች የኅብረት ስራ ጽ/ቤት ሀላፊዎችና ሁሉም የቡድን መሪዎች፤ የዩኒዬኑ የቅ/ስራ አስኪያጆችና ከዞን ኅብረት ስራ ቡድን መሪ እንድሁም አቻ ዬኒዬኖች በተገኙበት የምክክር መድረክ አካሒዷል።
በምክክር መድረኩም የቀረቡ ሪፖርቶች
1. ዩኒዬኑ ከምስረታ እስካሁን የሰራቸው ስራዎችና የደረሰበት
2. የ2015 ዓ.ም የሁለተኛ ሩብ አመት እቅድ ክንውን አፈጻጸም
3. አጠረ ያለ የማጠናከሪያ ማንዋል ትግበራ ስልጠና የቀረቡ ሲሆን በነዚህም ሀሳቦች ላይ በጥልቀት ውይይት ተካሒዶባቸዋል።
በመጨረሻም ከላይ እስከ ታች ያለነው የኅብረት ስራ ቤተሰቦች በጋራ በመስራት የኅብረት ስራ ችግሮችን መቅረፍ እንዳለብንና ወደ ዩኒዬኑ የማይቆጥቡ መሰረታዊ ማህበራት ቁጠባቸውን ማምጣት እንዳለባቸውና ዪኒዬኑም ለአባለት የተሻለ ብድርና ድጋፍ ማድረግ እንደለበት ፣ በሁሉም ወረዳዎች ምንም አይነት ይሁን ውዝፍ ብድር መገኘት እንደለለበት ተስማምተን ስራዎችን ቀጣይም ተገናኝተን እንደምንገመግም በመግባባት ስብሰባው/ምክክሩ ተጠናቋል።

ጎል ሃ/የተወሰነ የገ/ቁ/ብ/ህ/ስ/ማ/ዩነዬን በቀን 22/01/2015 ዓ.ም የአራቱም ወረዳ አባል ህብረት ስራ ማህበራት እና የአደራጅ ተቋሙ ሀላፊና የቡድን መሪዎች እንድሁም የዞንና ሌሎች ተ...
03/10/2022

ጎል ሃ/የተወሰነ የገ/ቁ/ብ/ህ/ስ/ማ/ዩነዬን በቀን 22/01/2015 ዓ.ም የአራቱም ወረዳ አባል ህብረት ስራ ማህበራት እና የአደራጅ ተቋሙ ሀላፊና የቡድን መሪዎች እንድሁም የዞንና ሌሎች ተጋባዠ እንግዶች በተገኙበት ጠቅላላ ጉባኤውን አካሒዷል።
ዩኒዬኑ በ2014 በጀት ዓመት ያከናወናቸው እቅድ ክንውን አቅርቦ የተሻለ አፈጻጸም ያመጡ ወረዳዎችና መሰረታዊ ማህበራትን እውቅና ሰጥቷል
ዩኒዬኒ ያሳለፍናቸው ወራቶች አስቸጋሪና ለስሩ ጥሩ ባይሆኑም በአደራጅ ተቋሙ ትብብር በዩኒዬኑ ሰራኞችና በቦርዱ አመራር ጥረት የተሻለ ውጤት ማስመዝገብ ችሏል በዚህ በጀት ዓመት የተሻለ ትርፍ ማስመዝገብ የተቻለበትና አባል መሰረታዊ ማህበራትንም ጭምር የብድር ተጠቃሚ ያደረገበት አመት መሆኑንም የአባል መሰረታዊ ማህበራት ምስክርነታቸውን ሰጥተዋል።
ዩኒዬኑ የመሰረተበት ዕድሜ አጭር ቢሆንም አመርቂ ውጤቶችን እያዝመዘገበ የሚገኝ ተቋም ሁኗል ሲመሰረት በ394,000 መነሻ ካፒታል ስራ የጀመረው በ2014 በጀት ዓመት በኦድት በተረጋገጠው አጠቃላይ ሀብቱ ከ106 ሚሊዮን ብር በላይ እንደደረሰ ከኦድት ሪፖርት ለመስማት ችለናል።
በመጨረሻም የ2015 በጀት ዓመት የቀረቡለትን እቅዶች ጠቅላላ ጉባኤው በሙሉ ድምጽና እንሰራዋለን በሚል ወኔ በሙሉ ድምጽ አጽድቋል።

Address

Akesta

Opening Hours

Monday 02:30 - 11:30
Tuesday 02:30 - 11:30
Wednesday 02:30 - 11:30
Thursday 02:30 - 23:30
Friday 14:30 - 23:30

Telephone

+251331140287

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Gole Saving and Credit Cooperative Union posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share