04/08/2025
ወጋገን ባንክ ከሁለት ዓለም አቀፍ ባንኮች ጋር ስምምነት በመፈፀም የ85 ሚሊዮን ዶላር የዓለም አቀፍ ንግድ ፋይናንስ ዋስትና ማግኘቱን በደስታ ያበስራል
ሐምሌ 28 ቀን 2017 ዓ.ም
ወጋገን ባንክ ከአፍሪካ ቀጠናዊ የኢንቨስትመንት እና የልማት ፋይናንስ ቡድን (TDB) እና የአፍሪካ ኢምፖርት ኤክስፖርት ባንክ ጋር በፈፀመው ስምምነት በድምሩ የ85 ሚሊዮን ዶላር የዓለም አቀፍ ንግድ ፋይናንስ ዋስትና ማግኘቱን ይፋ ያደርጋል፡፡
የተፈፀመው ስምምነት ወጋገን ባንክ ከዓለም አቀፍ ባንኮች ጋር ያለውን ስትራቴጂክ አጋርነት በማጠናከር በዓለም አቀፍ ንግድ ግብይት ዙሪያ ለሚያቀርበው የሌተር ኦፍ ክሬዲት እንዲሁም ከገቢ እና ከወጪ ንግድ ጋር ለተያያዙ ሰነዶች ዋስትና የመስጠት አቅሙን በማጠናከር ለበርካታ ደንበኞች አገልግሎቱን ተደራሽ ማድረግ የሚያስችለው ይሆናል፡፡
በተጨማሪም በወጋገን ባንክ እና በተጠቀሱት ባንኮች መካከል የተፈፀመው የፋይናንስ ዋስትና ስምምነት ባንኩ ለረጅም ዓመታት ከበርካታ ዓለም አቀፍ ባንኮች ጋር በመስራት ያካበተው በጠንካራ መተማመን ላይ የተመሰረት የስራ ግንኙነት መገለጫ ሲሆን በቀጣይም ከሌሎች ዓለም አቀፍ ባንኮች ጋር ተመሳሳይ የስራ ግንኙነት የመመስረት እድል የሚፈጥርለት ይሆናል፡፡
Wegagen Bank Secures 85 Million USD International Trade Finance Guarantee Facility
August 04, 2025
Wegagen Bank has secured access to an international trade finance guarantee facility amounting to 85 million USD following agreements made with the Eastern and Southern African Trade and Development Bank (TDB) and the African Export-Import Bank (Afreximbank).
The agreement further reinforces Wegagen Bank’s strategic partnerships with global financial institutions and enhances its capacity to provide Letter of Credit (L/C) confirmation, while also expanding its ability to offer guarantees for various import and export-related documentary services. This advancement positions the Bank to deliver more accessible, reliable, and efficient trade finance solutions to a wider range of clients.
Furthermore, the trade finance guarantee agreement between Wegagen Bank and the aforementioned global financial institutions stands as a testament to the Bank’s longstanding, enduring, and collaborative relationships with reputable international banks. Moreover, such agreement positions Wegagen Bank to extend its network of partnerships with more global financial institutions and solidify its presence in the international trade finance landscape.