09/05/2026
የኢትዮጵያ ጤና መድኅን አገልግሎት የ9 ወራት የዕቅድ አፈጻጸሙን ገመገመ
01/09/2018 ኢጤመአ
የኢትዮጵያ ጤና መድኅን አገልግሎት የ2018 በጀት ዓመት የዘጠኝ ወራት የሥራ አፈጻጸም ሪፖርትን አስመልክቶ ከመላው ሠራተኞቹ ጋር የውይይት መድረክ አካሄደ። በውይይቱ ላይ የአገልግሎቱ ዋና ዳይሬክተር አቶ ተስፋየ ወርቁ ተገኝተው የሥራ መመሪያና ንግግር ያደረጉ ሲሆን፣ ተቋሙ በዘጠኝ ወራት ውስጥ ያስመዘገባቸው አበይት ድሎችና ያጋጠሙ ተግዳሮቶች በዝርዝር ተናግረዋል።
አሁን አለንበት ደረጃ ለመድረስ የተመቻቹ ነገሮችም የመኖራቸውን ያክል ውጣ ውርዶች ነበሩ ያሉት አቶ ተስፋየ የቀጣዮቹ ቀሪ ወራቶች እስካሁን ያልተሰሩ ተግባራት የሚከናወኑበትና የ2019 በጀት አመት የዝግጅትት ስራዎችም በመኖራቸው በትኩረት ሊሰራ ይገባል ብለዋል።
የዕቅድ አፈጻጸሙን ሪፖርት ያቀረቡት የአገልግሎት የስራ አመራር ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ከፍያለው ሞቲ፣ተቋሙ በዘጠኝ ወራት ውስጥ የማኅበረሰብ አቀፍ ጤና መድኅን (CBHI) ሽፋን በከፍተኛ ደረጃ ማሳደግ መቻሉንና በአገር አቀፍ ደረጃ የወረዳ ሽፋኑን 96% መድረሱን ገልጸውው፣የአባላቱን ቁጥር 15 ሚሊዮን በማድረስ አጠቃላይ ተጠቃሚዎችን ወደ 69 ሚሊዮን ማደጉን ይፋ አድርገዋል።
የአባላትን መረጃ በዘመናዊ መንገድ ለመያዝ የሚያስችል የዲጂታል ሲስተም በትግበራ ላይ ሲሆን፣ ከ650 በላይ ወረዳዎች መረጃዎቻቸውን ወደ ሲስተሙ አስገብተዋል። በተጨማሪም የማኅበራዊ ጤና መድኅን (SHI) ትግበራን ለማሳለጥ አዲስ ሲስተም ለምቶ ወደ ሥራ መግባቱም ተወስቷል
በአገር አቀፍ ደረጃ ሁሉን አቀፍ የጤና መድኅን ሽፋን ለማሳደግ በ17 የሀገሪቱ ክፍሎች ከሚገኙ የማህበረሰብ ራዲዮ ጣቢያዎች ጋር በመቀናጀት ሳምንታዊ ፕሮግራሞች መጀመራቸው እና ከኢትዮጵያ ራዲዮ ጋር በመተባበር በመካከለኛው ሞገድ (MW) መደበኛ የአየር ሰዓት ተረክቦ ስራ መጀመሩን የገለጸው ሪፖርቱ፣
እንደ ኢቢሲ፣ ፋና እና ኢዜአ ካሉ ግዙፍ የሚዲያ ተቋማት ጋር በመተባበር ከ55 ጊዜ በላይ ዘገባዎች እንዲተላለፉ መደረጉና በከፍተኛ አመራሮች በተሰጠ ጋዜጣዊ መግለጫ የ16 የሚዲያ ተቋማትን ሽፋን ማገኝቱ ተነግሯል።
ለዓመታት ሲጠበቅ የነበረው የማኅበራዊ ጤና መድኅን ሥርዓት ባሳለፍነው ከጥር 1 ቀን 2018 ዓ.ም ተጀምሮ የጤናው ዘርፍ የመንግሥት ሠራተኞችና ቤተሰቦቻቸው ወደ ሥርዓቱ እንዲገቡ መደረጉም ተነግሯል
አገልግሎት መስሪያ ቤቱ ከአባላት መዋጮና ከተለያዩ ድጎማዎች በአጠቃላይ ከ17 ቢሊዮን ብር በላይ መሰብሰብ መቻሉን ገልጾ፣የመክፈል አቅም ለሌላቸው ዜጎች የሚሰጠው የጥቅል ድጎማ ሙሉ በሙሉ ለወረዳዎች የተላለፈ ሲሆን፣ መጠኑም 2.9 ቢሊዮን ብር መሆኑ አስታውሷል።
በሆስፒታሎች የሚሰጠውን የህክምና አገልግሎት ጥራት ለማረጋገጥ የክሊኒካል ኦዲት ሥራዎች መከናወናቸውና ከመንግሥት የሪፎርም ሥራዎች ጋር ተያይዞ የሠራተኞች የብቃት ምዘናና የደመወዝ ስኬል ማሻሻያ ተግባራዊ መደረጋቸው የአገልግሎት አሰጣጥን ለማሻሻልና የሠራተኛውን አቅም ለመገንባት የትሰሩ ተግባራት መሆናቸውን በሪፖርቱ አመላክቷል
በክልል ደረጃ የሚፈለገው የከፍተኛ አመራር ድጋፍ አናሳ መሆን፣ ከሥራው ስፋት ጋር የሚመጥን አደረጃጀት አለመፈጠርና በጤና ተቋማት የሚሰጠው የሕክምና አገልግሎት የጥራት ችግር፣ ደካማ የመረጃ ልውውጥና የጥራት ቁጥጥር ሥርዓት፣ እንዲሁም የሥራ እንቅስቃሴን የሚያደናቅፍ የተሽከርካሪ እጥረት የስራ መሰናክሎች ነበሩ ያለው በሪፖርቱ ቀርብዋል፡፡
የሪፎርም ተግባራትን ማጠናከር፣ለቀጣይ ሦስት ዓመታት የሚሆን አዲስ የኢንቨስትመንት ስትራቴጂክ ዕቅድ ማዘጋጀት፣የፌደራል ፑል የሚመሰረትበትን ሁኔታ በማመቻቸት የፋይናንስ መሰረቱን ማጠናከርና የክሌም ማኔጅመንትን እና የፋይናንስ ኦዲትን ማጠናከር፣ እንዲሁም አሰራርን በዲጂታል ቴክኖሎጂ የታገዘ ማድረግ በትኩረት ሊሰራባቸው የታቀዱ ጉዳዮች ናቸው ብሏል"Youtube: https://www.youtube.com/-HealthInsurance
Website: www.ehis.gov.et
Twitter: http://twitter.com/service4E
Facebook: https://web.facebook.com/EthioHIS/
Telegram: https://t.me/buuu1lTelegram: https://t.me/buu
X (formerly Twitter) (https://twitter.com/service4E)
Ethiopia Health Insurance Service () / X