ጊዜ መረጃ

ጊዜ መረጃ ጊዜ መረጃ የሁል ጊዜ ምርጫዎ

19/05/2026
የታሪካዊው ፍልሚያ ይፋዊ ማብሰሪያ፡ ሴዶ ማርሻል አርት እና ጌታቸው መለሰ ስምምነት ላይ ደረሱ!በጉጉት ሲጠበቅ የነበረው የኢትዮጵያ MMA (ድብልቅ ማርሻል አርት) አዲስ ምዕራፍ ተከፈተ! ዛሬ...
14/05/2026

የታሪካዊው ፍልሚያ ይፋዊ ማብሰሪያ፡ ሴዶ ማርሻል አርት እና ጌታቸው መለሰ ስምምነት ላይ ደረሱ!

በጉጉት ሲጠበቅ የነበረው የኢትዮጵያ MMA (ድብልቅ ማርሻል አርት) አዲስ ምዕራፍ ተከፈተ! ዛሬ በተከናወነ ደማቅ ስነ-ስርዓት፣ ሴዶ ማርሻል አርት ከውድድር አዘጋጅ ጌታቸው መለሰ ጋር ውድድሩን በይፋ ለመቀበልና በክፍያ ዙሪያ የሚያጠነጥን የፊርማ ስነ-ስርዓት በስኬት አጠናቀዋል።

የውድድሩ አዘጋጅ ጌታቸው መለሰ ስምምነቱን ተከትሎ ባስተላለፉት አጭርና ግልጽ መልዕክት፦

The fight is On!" (ፍልሚያው ጀምሯል!) በማለት የውድድሩን መቃረብ አብስረዋል።

• ሴዶ ማርሻል አርት በውድድሩ ላይ ለመሳተፍ ሙሉ ዝግጁነቱን አረጋግጧል።

• በጥቅምና በክፍያ ስርአቱ ዙሪያ የጋራ መግባባት ላይ ተደርሷል።

• አዘጋጆቹና ተወዳዳሪዎቹ ወደ ቀጣዩ የዝግጅት ምዕራፍ ተሸጋግረዋል።

ይህ ታላቅ ፍልሚያ የሚካሄድበት ቀን በቅርቡ ይፋ ይደረጋል።

🐎 ጊዜ መረጃ

 #እናትነት ❤🥺   ልብ የሚነካ ትዕይንት 💔የዚች ላም ባለቤት ላሟ ለቀናት  መብላትና መጠጣት እንዳቆመች   ሁልጊዜም  መቆም የማይችል  አካል ጉዳተኛ ጥጃዋ አጠገብ እንዳለች አስተዋለ።ባለቤ...
14/04/2026

#እናትነት ❤🥺


ልብ የሚነካ ትዕይንት 💔

የዚች ላም ባለቤት ላሟ ለቀናት መብላትና መጠጣት እንዳቆመች ሁልጊዜም መቆም የማይችል አካል ጉዳተኛ ጥጃዋ አጠገብ እንዳለች አስተዋለ።

ባለቤቱም ፣ ጥጃውን በቀስታ በገመድ እና በዱላ አንስቶ እንዲቆም ረዳው።

መቆሙን የተመለከተችው ላም ልጇን ስላዳነላት ምስጋናዋን እና ደስታዋን እየገለፀች ይመስል ልብ የሚነካ ድምፅ እያሰማች ነበር

ጊዜ እያለፈ ሲሄድ ጥጃው ጥንካሬውን ማግኘት ጀመረ… ❣️
#እናትነት♥
Hijra Tube ኢስላማዊ ድህረ ገፅ

🐎 ጊዜ መረጃ

አርሰናል በሜዳው በቦርንማውዝ ተሸነፈ***********በ32ኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ አርሰናል በሜዳው በቦርንማውዝ 2 ለ 1 ተሸንፏል።በኤምሬትስ በተደረገው ጨዋታ ጁኒየር ክሩፒ እና...
11/04/2026

አርሰናል በሜዳው በቦርንማውዝ ተሸነፈ
***********

በ32ኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ አርሰናል በሜዳው በቦርንማውዝ 2 ለ 1 ተሸንፏል።

በኤምሬትስ በተደረገው ጨዋታ ጁኒየር ክሩፒ እና አሌክስ ስኮት የቦርንማውዝን ግቦች አስቆጥረዋል።

ቪክቶር ዮኬሬስ በፍጹም ቅጣት ምት የአርሰናልን አንድ ግብ አስቆጥሯል።

አርሰናል ከ4 ተከታታይ የሊጉ ጨዋታዎች በኋላ የተሸነፈ ሲሆን ከተከታዩ ማንችስተር ሲቲ ያለውን የነጥብ ልዩነት ወደ 12 የሚያሰፋበትን አጋጣሚ ሳይጠቀምበት ቀርቷል።

ቦርንማውዝ በፕሪሚየር ሊጉ ለ12ኛ ተከታታይ ጨዋታ ሳይሸነፍ የወጣበት ሆኗል።

አሁን ሁለት ተስተካካይ ጨዋታ በሚቀረው ማንችስተር ሲቲ እና በአርሰናል መካከል ያለው የነጥብ ልዩነት 9 ብቻ ነው።

🐎 ጊዜ መረጃ

ምሳችሁን እና እራታችሁን ይዛችሁ ኑ - ሚኬል አርቴታ***************የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ከሁለት ሳምንት ረፍት በኋላ ዛሬ በሚደረግ አንድ ጨዋታ ይመለሳል። የሊጉ መሪ አርሰናል ቀ...
10/04/2026

ምሳችሁን እና እራታችሁን ይዛችሁ ኑ - ሚኬል አርቴታ
***************

የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ከሁለት ሳምንት ረፍት በኋላ ዛሬ በሚደረግ አንድ ጨዋታ ይመለሳል። የሊጉ መሪ አርሰናል ቀን 8 ሰዓት ከ30 ላይ በኤምሬትስ ከቦርንማውዝ ይጫወታል።

ከማንችስተር ሲቲ በዘጠኝ ነጥብ ርቆ እየመራ የሚገኘው አርሰናል የነገውን ጨዋታ ካሸነፈ ሲቲ እሁድ ከቼልሲ እስኪጫወት ልዩነቱን ወደ 12 የሚያሰፋ ይሆናል።

ስፔናዊው አሰልጣኝ ሚኬል አርቴታ ጨዋታውን በተመለከተ በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ለደጋፊዎቹ መልዕክት አስተላልፏል።

በኤምሬትስ ከቦርንማውዝ የሚደረገው ጨዋታ ከየትኛውም ጊዜ በላይ ወሳኝ መሆኑን የገለጸው አሰልጣኙ፣ የመድፈኞቹን ደጋፊዎች "በጠዋት ተነሱ፣ ቁርሳችሁን ቀድማችሁ ብሉ፣ ምሳችሁን እና እራታችሁን ይዛችሁ ወደ ስታዲየም ኑ ይሄ ለእኛ ትልቅ ታሪክ የምንሰራበት ቀን ሊሆን ይገባል" በማለት መልዕክቱን አስተላልፏል።

በነገው ጨዋታ ጉዳት ላይ የነበረው ኤቤሬቺ ኤዜ ለመርሀ ግብሩ ዝግጁ መሆኑን አሰልጣኙ ይፋ አድርጓል። የቡካዮ ሳካ፣ ማርቲን ኦዴጋርድ፣ ዩሪየን ቲምበር እና ሪካርዶ ካላፊዮሪ ጉዳይ ገና የሚታይ መሆኑን አርቴታ ተናግሯል።

በሁለት ሳምንት ውስጥ ከሁለት ዋንጫዎች ወጪ የሆነው አርሰናል ከሁለት ተከታታይ ጨዋታዎች ሽንፈት በኋላ በሻምፒዮንስ ሊግ ስፖርቲንግ ሊዝበንን ማሸነፉም ይታወሳል።

🐎 ጊዜ መረጃ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ  (ዶ/ር) የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ዓመታዊ የአፈፃፀም ሪፖርት ገመገሙ********************ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ  (ዶ/ር) ዛሬ ...
07/04/2026

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ዓመታዊ የአፈፃፀም ሪፖርት ገመገሙ
********************

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ዛሬ ጠዋት የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ዓመታዊ የአፈፃፀም ሪፖርትን ገምግመዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝዳንት ሌ/ጄኔራል ታደሰ ወረደ አመታዊ የአፈፃፀም ሪፖርት ቀርቦላቸው በውጤቶቹ ላይ ግምገማ እና ውይይት መደረጉንም የጠቅላይ ሚኒስትር ፅ/ቤት አስታውቋል።

🐎 ጊዜ መረጃ

8 ዓመት ሞላቸው!በዚች ሰዓት፣ በዚች ቀን ነበርመጋቢት 24 ቀን 2010 ዓ.ም. የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ወደ ስልጣን የመጡት።ባለፉት 8 ዓመታት ኢትዮጵያን እንዴት ...
02/04/2026

8 ዓመት ሞላቸው!

በዚች ሰዓት፣
በዚች ቀን ነበር

መጋቢት 24 ቀን 2010 ዓ.ም. የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ወደ ስልጣን የመጡት።

ባለፉት 8 ዓመታት ኢትዮጵያን እንዴት መሯት?

የአመራር ዘመናቸውን እንዴት ትገመግሙታላችሁ?

ሀሳባችሁን አካፍሉን ?

🐎 ጊዜ መረጃ

"የምቀኝነት መጨረሻ - በዱባይ የተፈፀመው የጓደኛ ክህደት ታሪክ 👇በስደት ዓለም አብሮ መብላትና መጠጣት፣ መረዳዳት የተለመደ ቢሆንም፤ አንዳንዴ ግን ቅርብ ያልነው ሰው የጥፋታችን ምክንያት ሊ...
01/04/2026

"የምቀኝነት መጨረሻ - በዱባይ የተፈፀመው የጓደኛ ክህደት ታሪክ 👇

በስደት ዓለም አብሮ መብላትና መጠጣት፣ መረዳዳት የተለመደ ቢሆንም፤ አንዳንዴ ግን ቅርብ ያልነው ሰው የጥፋታችን ምክንያት ሊሆን ይችላል። ዛሬ በዱባይ የተፈፀመ እውነተኛና አሳዛኝ የክህደት ታሪክ እናያለን።

ክስተቱ፦

በዱባይ በቤት ሰራተኝነት የምትሰራው መሰረት (ስሟ የተቀየረ) ለረጅም ዓመታት በቆጠበችው 70,000 ድርሃም (ከ1.5 ሚሊዮን ብር በላይ) በአዲስ አበባ ቤት ለመግዛት ትዘጋጃለች። ይህንን የደስታ ዜና በቅርብ ለምታውቃትና አብራት ለምትሰራው ጓደኛዋ ታካፍላለች። ጓደኛዋ ግን በደስታ ፋንታ በውስጧ ምቀኝነት አደረባት።

ወንጀሉ፦

ጓደኛዋ መሰረት ገንዘቡን ወደ ኢትዮጵያ በህገ-ወጥ መንገድ (ሁዋላ) እንድትልክ ታባብላታለች። "የማውቀው ሰው አለ፣ የተሻለ ተመን ይሰጥሻል" በማለት ወደ አንድ ገለልተኛ ቦታ ትወስዳታለች። እዚያም ከደረሱ በኋላ ጓደኛዋ አስቀድማ ካዘጋጀቻቸው ግብረ-አበሮቿ ጋር በመሆን በመሰረት ላይ ድብደባ ፈጽመው ገንዘቡን በሙሉ ዘርፈው ለሞት አፋፍ ላይ ጥለዋት ይሰወራሉ።

ፍርዱ፦

መሰረት በታምር በሕይወት ተርፋ ለፖሊስ በሰጠችው ጥቆማ መሰረት፣ ዱባይ ፖሊስ ባደረገው ከፍተኛ ክትትል ጓደኛዋና ግብረ-አበሮቿ ከሳምንት በኋላ እጅ ከፍንጅ ተያዙ።

ዋናዋ ወንጀለኛ (ጓደኛዋ)፦ በከባድ ዝርፊያና በሰው ሕይወት ላይ አደጋ በማድረስ የ 15 ዓመት ጽኑ እስራት ተፈርዶባታል።

ግብረ-አበሮች፦ እያንዳንዳቸው የ 10 ዓመት እስራት ተፈርዶባቸዋል።

ተጨማሪ፦ ከእስራት በኋላ ሁሉም ከሀገር እንዲባረሩ (Deportation) ተወስኖባቸዋል።

ትምህርቱ፦

በስደት ዓለም የድካማችሁን ውጤት ለምታምኑት ሰው እንኳ ቢሆን በሚስጥር መያዝን ልመዱ። ገንዘብ ስትልኩ በባንክ ብቻ እንዲሆን ይመከራል።

ምስል በ የፈጠረ


🐎 ጊዜ መረጃ

"እሺ የልጄን አጽም እንኳ አሳዩኝ!" — የሀና አባት ልብ የሚነካ ጥሪጉርሻ ፔጅን የምትከታተሉ የመንግሥት አካላትና የሚመለከታችሁ ሁሉ፣ ጉዳዩን ትኩረት ስጡት 🙏ሳውዲ/ኢትዮጵያ— የአንድ ልጅ ...
01/04/2026

"እሺ የልጄን አጽም እንኳ አሳዩኝ!" — የሀና አባት ልብ የሚነካ ጥሪ

ጉርሻ ፔጅን የምትከታተሉ የመንግሥት አካላትና የሚመለከታችሁ ሁሉ፣ ጉዳዩን ትኩረት ስጡት 🙏

ሳውዲ/ኢትዮጵያ— የአንድ ልጅ እናት የሆነችውና በሳውዲ አረቢያ በረሃዎች ውስጥ ደብዛዋ የጠፋው ወጣት ሀና ጉዳይ፣ አሁን ላይ እጅግ አሳዛኝ ምዕራፍ ላይ ደርሷል።

የሀና አባት በታነቀ ድምፅና በእንባ ሆነው ያሰሙት አዲስ የድምፅ መረጃ፣ የቤተሰቡን ስቃይ እና የደላሎችን ጭካኔ ቁልጭ አድርጎ የሚያሳይ ሆኗል።

በድምፅ መረጃው ላይ እንደሚሰማው፣ የሀና አባት ልጃቸው መሞቷን በውሸት በደላሎች ከተነገራቸው በኋላ የሚከተሉትን ልብ ሰባሪ ቃላት ተናግረዋል፦

*ሌላ ወሬ አልፈልግም፤ እሺ እውነት ከሆነ የልጄን አጽም እንኳ ቢሆን አሳዩኝ!"በማለት ልጃቸውን በክብር ለመቅበር ያላቸውን የመጨረሻ ምኞት ገልጸዋል።

* በአካል ሄጄ ቀብሯን ማየት እፈልጋለሁ" ያሉት አባቷ፣ ደላሎቹ ስለ ልጃቸው ሁኔታ የሚሰጡት መረጃ እርስ በርሱ የሚጋጭና ቤተሰቡን ለከፋ ስቃይ የሚዳርግ መሆኑን ገልጸዋል።

የሀና አባት እንደሚሉት፣ ደላሎቹ የልጃቸውን አጽም ለማሳየት ቃል ቢገቡም፣ በተደጋጋሚ ቀጠሮ በማጠፍና በማስፈራራት ቤተሰቡን እያሰቃዩ ይገኛሉ።

ይህ ድርጊት ደላሎች በሰው ሕይወት ከመነገድ ባለፈ፣ የቤተሰብን ሥነ-ልቦናዊ ሰላም ለማደፍረስ ምን ያህል እንደሚጨክኑ ማሳያ ሆኗል።

በመሆኑም፦

1. መንግሥት እና ኤምባሲው የሀና አባት ለቀረቡት ጥያቄ ምላሽ እንዲያገኙ እና የልጃቸው እጣ ፈንታ በሕጋዊ መንገድ እንዲጣራ ግፊት እንዲያደርጉ በአክብሮት እንጠይቃለን።

2. ደላሎች ለሕግ ይቅረቡ በንጹሐን ዜጎች ሕይወት እና በቤተሰብ ስሜት ላይ የሚቀልዱ ሕገ-ወጥ አዘዋዋሪዎች በአፋጣኝ ተለይተው ለሕግ እንዲቀርቡ ዘመቻችንን እንቀጥላለን።

ድምፅ እንሁንላቸው! ይህን አሳዛኝ የአባት ድምፅ እና መረጃ በማጋራት፣ ጉዳዩ ለሚመለከታቸው አካላት እንዲደርስና ፍትሕ እንዲሰፍን የበኩላችንን እንወጣ።

ይህ መረጃ ለብዙዎች እንዲደርስ ና ሀሳቡ ፊስቡክ ላይ በደንብ እንዲሸራሸር Like፣ Share እና Comment::

በማድረግ ተባበሩን።

🐎 ጊዜ መረጃ

በአዲስ አበባ "የተባበሩት" አካባቢ በደረሰ የትራፊክ አደጋ የሰው ሕይወት አለፈ::አዲስ አበባ መጋቢት 23 ቀን 2018 ዓ.ም ዛሬ ረፋድ ላይ በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ልዩ ስሙ "የተባበሩት አ...
01/04/2026

በአዲስ አበባ "የተባበሩት" አካባቢ በደረሰ የትራፊክ አደጋ የሰው ሕይወት አለፈ::

አዲስ አበባ መጋቢት 23 ቀን 2018 ዓ.ም ዛሬ ረፋድ ላይ በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ልዩ ስሙ "የተባበሩት አደባባይ" ተብሎ በሚጠራው አካባቢ በደረሰ አስከፊ የትራፊክ አደጋ የአንድ ሰው ሕይወት ሲያልፍ፣ በሦስት ሰዎች ላይ ደግሞ ከባድ የአካል ጉዳት መድረሱን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታውቋል።

እንደ ፖሊስ መረጃ ከሆነ አደጋው የተከሰተው ዛሬ ረፋድ 1፡00 ሰዓት ገደማ ነው። ከ"አቤም" ወደ "የተባበሩት" አቅጣጫ ቁልቁለት ሲጓዝ የነበረ የሠሌዳ ቁጥሩ ኮድ 3A-41968 አ/አ የሆነ የ"አልያንስ" የሕዝብ ማመላለሻ አውቶቡስ መቆጣጠር በማቃቱ አደጋውን አድርሷል።

አውቶቡሱ ከአያት ወደ ሲ.ኤም.ሲ አቅጣጫ ሲጓዙ በነበሩ ሁለት ተሽከርካሪዎች ላይ ጉዳት አድርሷል፦

* የሠሌዳ ቁጥሩ ኮድ 3-35090 አ/አ በሆነ የፒካፕ ተሽከርካሪ።

* የሠሌዳ ቁጥሩ ኮድ 3B-57071 አ/አ በሆነ "ቪትዝ" መኪና።

አውቶቡሱ ተሽከርካሪዎቹን ከገጨ በኋላ አደባባዩ ላይ በመውጣት ሊገለበጥ መቻሉ ተገልጿል።

* በወቅቱ የፒካፕ መኪናውን ሲያሽከረክር የነበረው ግለሰብ ሕይወት ወዲያውኑ አልፏል።

* በፒካፕ መኪናው ውስጥ ተሳፍረው የነበሩ ሁለት ሴት ተማሪዎች (የ7ኛ እና የ5ኛ ክፍል) እንዲሁም የቪትዝ መኪናው አሽከርካሪ ላይ ከባድ የአካል ጉዳት ደርሷል።

ተጎጂዎቹ በአሁኑ ወቅት በሕክምና ተቋም ክትትል እየተደረገላቸው እንደሚገኝ ታውቋል።

አሽከርካሪዎች የመንገዱን አቀማመጥና ሁኔታ ከግምት ውስጥ በማስገባት፣ ተሽከርካሪን መቆጣጠር በሚያስችል ፍጥነትና ጥንቃቄ ሊያሽከረክሩ እንደሚገባ የአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ አሳስቧል።

የአዲስ አበባ ፖሊስ ለሟች ቤተሰቦች መጽናናትን፣ ለተጎጂዎች ደግሞ ፈጣን ማገገምን ተመኝቷል።

Via የአዲስ አበባ ፖሊስ

🐎 ጊዜ መረጃ

እናት ልጁን መግረፍ እማይችልበት ግዜይህች ልጅ እናቷ ልትገርፋት ስትሞክርእናቷን አሯሩጣ በመያዝ በጭካኔ ደጋግማ ትደበድባታለችምንም አይነት አለመግባባት ወይም ችግር ቢኖር እንኳ፣ በወላጅ ላይ...
30/03/2026

እናት ልጁን መግረፍ እማይችልበት ግዜ
ይህች ልጅ እናቷ ልትገርፋት ስትሞክር
እናቷን አሯሩጣ በመያዝ በጭካኔ ደጋግማ ትደበድባታለች
ምንም አይነት አለመግባባት ወይም ችግር ቢኖር እንኳ፣ በወላጅ ላይ አይደለም እጅን አንስቶ መደባደብ ይቅርና መልስም አይሰጥም
​ድርጊቱን የፈጸመችው ልጅ ተገቢውን ምክር ወይም የህግ እርምት ማግኘት ይኖርባታል።

🐎 ጊዜ መረጃ

Address

Addis Ababa

Telephone

+251913702222

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when ጊዜ መረጃ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share