Zemen Bank S.C.

Zemen Bank S.C. Whether you are working hard or out relaxing, We are at your service! Our Values include: Upholding the highest standards, being progressive and innovative.

Zemen Bank is a proudly Ethiopian, professional, dynamic, world-class and a totally customer financial institution. Our Personality is: To be challenging, spirited, provocative, ambitious and successful and to be friendly and courteous in all our relationships. To our Customers: We offer a professional partnership, trust and outstanding levels of service. Zemen Bank stands for innovation and excellence in everything we do.

ዘመን ባንክ ለኢትዮጵያ አየር መንገድ 80ኛ ዓመት መልካም ምኞቱን ገለጸ፡፡የኢትዮጵያ አየር መንገድ ለ80ኛ ዓመቱ በስኬት በመድረሱ በአቶ ደረጀ ዘበነ የዘመን ባንክ ዋና ሥራ አስፈጻሚ የተመራ...
03/06/2026

ዘመን ባንክ ለኢትዮጵያ አየር መንገድ 80ኛ ዓመት መልካም ምኞቱን ገለጸ፡፡

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ለ80ኛ ዓመቱ በስኬት በመድረሱ በአቶ ደረጀ ዘበነ የዘመን ባንክ ዋና ሥራ አስፈጻሚ የተመራው የከፍተኛ አመራር አባላት ልዑክ ግንቦት 25 ቀን 2018 ዓ.ም በአየር መንገዱ በመገኘት የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክታቸውን ገለጹ፡፡
አቶ ደረጀ ዘበነ በዚህ ወቅት ባስተላለፉት መልዕክት የሀገራችን ኩራት የሆነው አየር መንገድ አሠራሩና ተግዳሮቶችን ተቋቁሞ እዚህ ለመድረስ የተጓዘበት መንገድ በአርአያነት የሚጠቀስ መሆኑን ገልጸው፤ ተቋሙ እዚህ እንዲደርስ ትልቅ አስተዋጽኦ ላደረጉት ሁሉ ምስጋና አቅርበዋል፡፡ በተጨማሪም አየር መንገዱ ከዘመን ባንክ ጋር ስላለው ዘርፈ ብዙ የሥራ ግንኙነት አመስግነው፤ ለወደፊቱም ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አስታውቀዋል፡፡
አቶ መስፍን ጣሰው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ዋና ሥራ አስፈጻሚ በበኩላቸው ስለመልካም ምኞት መግለጫው አመስግነው፤ "እንኳን ደስ ያላችሁ ስላላችሁ እናመሰግናለን፡፡ ዘመን ባንክ አጋራችን ነው፤ ወደፊትም አብረን መሥራታችንን እንቀጥላለን" በማለት ተናግረዋል፡፡
#ዘመንባንክ

የዘመን ባንክ የትምህርት ቤት ክፍያ ስርዓት ወላጆች የትምህርት ቤቱን መለያ ኮድ በመጠቀም ክፍያ እንዲከፍሉ፤ የክፍያ ማረጋገጫ ደረሰኞችን እንዲያገኙ እንዲሁም ሪፖርቶች፣የቤትና የክፍል ሥራ፣ ...
02/06/2026

የዘመን ባንክ የትምህርት ቤት ክፍያ ስርዓት ወላጆች የትምህርት ቤቱን መለያ ኮድ በመጠቀም ክፍያ እንዲከፍሉ፤ የክፍያ ማረጋገጫ ደረሰኞችን እንዲያገኙ እንዲሁም ሪፖርቶች፣የቤትና የክፍል ሥራ፣ ተማሪዎች በክፍል ስለመገኘታቸውና መሰል ትምህርታዊ መረጃዎችን በስልኮቻቸው ወዲያው ካሉበት ቦታ ሆነው በማንኛውም ሰዓት ማግኘት ያስችላቸዋል፡፡
***
ቤተሰብ ይሁኑ :
Facebook: https://bit.ly/47Q7GeR
LinkedIn: https://bit.ly/3NmAmnE
X: https://bit.ly/48fi5AA
Instagram: https://bit.ly/3RmlUNP
YouTube: https://bit.ly/47U4sqI
Telegram: https://bit.ly/48fs1dE

***
#ዘመንባንክ

ዘመን ባንክ የአሰራር ሥርዓቱን ይበልጥ ለማዘመን ከኢትዮጵያ አርተፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት ጋር በቅርበት እንደሚሰራ ገለፀ፡፡ዘመን ባንክ የአሰራር ሥርዓቱን ይበልጥ ለማዘመን ከኢትዮጵያ ...
28/05/2026

ዘመን ባንክ የአሰራር ሥርዓቱን ይበልጥ ለማዘመን ከኢትዮጵያ አርተፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት ጋር በቅርበት እንደሚሰራ ገለፀ፡፡
ዘመን ባንክ የአሰራር ሥርዓቱን ይበልጥ ለማዘመን ከኢትዮጵያ አርተፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት ጋር በቅርበት እንደሚሰራ ተገለፀ፡፡ ይህ የተገለፀው የዘመን ባንክ ከፍተኛ የሥራ አመራሮች በኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት የሥራ ጉብኝት በማድረግ ከኢንስቲትዩቱ ጋር በጋራ ለመስራት የሚያስችላቸውን የመጀመሪያ ውይይት ባካሄዱበት ወቅት ነው፡፡
በዚህ ወቅት ኢንስቲትዩቱ የአርተፊሻል ኢንተለጀንስ ቴክኖሎጂን በመጠቀም ያበለፀጋቸውን የተለያዩ ሥርዓቶችና የሥራ እንቅስቃሴዎቹን በተመለከተ ለዘመን ባንክ አመራሮች ገለፃ ተደርጎላቸዋል፡፡ በተጨማሪም የዘመን ባንክ የሥራ ሐላፊዎች በኢንስቲትዩቱ የሚገኙትን የሮቦቲክስ ወርክሾፕ፣ የምርት ማሳያ ክፍልና የአርተፊሻል ኢንተለጀንስ ስታርትአፕ ማዕከልን ጎብኝተዋል፡፡
አቶ አስራት ታደሰ የዘመን ባንክ የሪቴይል ባንኪንግ ቺፍ ኦፊሰር በኢንስቲትዩቱ ተስፋ ሰጪ ሥራዎች በመሰራት ላይ እንደሚገኙ ገልፀው ባንኩ የአሰራር ሂደቱን ይበልጥ ለማዘመን ከኢንስቲትዩቱ ጋር በቅርበት እንደሚሰራ አስታውቀዋል፡፡ በተጨማሪም አቶ አስራት በኢንስቲትዩቱ የታቀፉ ስታርትአፖች ችግር ፈቺና በተለያዩ ዘርፎች በተግባር ላይ ሊውሉ የሚችሉ መፍትሄዎችን እየሰሩ መሆናቸውን ለመታዘብ መቻላቸውን ገልፀዋል፡፡
ዶ/ር ታዬ ግርማ የኢትዮጵያ አርተፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት ምክትል ዋና ዳይሬክተር ተቋሙ በተለያዩ ዘርፎች ሀገር በቀል የሆኑ የሰው ሠራሽ አስተውሎት መፍትሄዎችን ለማምጣት እያደረገ ያለውን ጥረት አብራርተዋል፡፡ የፋይናንስ ዘርፉን በዘመናዊ አሰራር ለመደገፍም ከባንኩ ጋር በቅርበት ለመስራት በኢንስቲትዩቱ በኩል ከፍተኛ ፍላጎትና ዝግጁነት መኖሩንም በውይይቱ ወቅት አረጋግጠዋል፡፡
#ዘመንባንክ

የተከበራችሁ ደንበኞቻችን፤ ከአጭበርባሪዎች ተጠንቀቁ!አጭበርባሪዎች የዘመን ባንክን ስምና አርማ ተጠቅመው ሀሰተኛ የማህበራዊ ሚዲያ በተለይም የቴሌግራም ገፆችን በመፍጠር ሀሰተኛ መልዕክቶችን በ...
26/05/2026

የተከበራችሁ ደንበኞቻችን፤
ከአጭበርባሪዎች ተጠንቀቁ!
አጭበርባሪዎች የዘመን ባንክን ስምና አርማ ተጠቅመው ሀሰተኛ የማህበራዊ ሚዲያ በተለይም የቴሌግራም ገፆችን በመፍጠር ሀሰተኛ መልዕክቶችን በማስተላለፍ ከደንበኞች ላይ የገንዘብ ስርቆት ለመፈፀም እየሞከሩ እንዳለ ደርሰንበታል፡፡ በመሆኑም ውድ ደንበኞቻችን ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን የጥንቃቄ መረጃዎች በመገንዘብ ሁሌም ጥንቃቄ እንድታደርጉ እንመክራለን::
•ዘመን ባንክ በቴሌግራም፣ በኢሜይልና በስልክ እንዲሁም በማንኛውም የማህበራዊ ትስስር ገፆች በመጠቀም ምስጢራዊነት ያለው መረጃ በጭራሽ አይጠይቅም።
•የእርስዎን የግል መረጃ ወይም የይለፍ ቃል የሚጠይቁ አጠራጣሪ የስልክ መልዕክቶች፣ ኢሜይል እና ከማይታወቁ ምንጮች የሚያገኟቸውን ማስፈንጠሪያዎች (Links) አይክፈቱ::
•መረጃ ለማግኘት ወደ 6500 በመደወል፤ የባንካችንን ቅርንጫፎች፣ እንዲሁም የባንካችንን ትክክለኛ የማህበራዊ ትስስር ገፆች ይጠቀሙ፤ ወይም በ [email protected] ያሳውቁን።
ዘመን ባንክ
የላቀ አገልግሎት ማዕከል!
#ዘመንባንክ

22/05/2026

ዘመን ባንክ የኤሌክትሪክ ሞተር ብስክሌት የባትሪ ስዋፒንግ ቴክኖሎጂን በመጠቀም በኢትዮጵያ የመጀመሪያው ባንክ ሆነ፡፡

ዘመን ባንክ በዶዳይ ኩባንያ የቀረበውን የኤሌክትሪክ ሞተር ብስክሌት የባትሪ መቀየሪያ (Swapping) ቴክኖሎጂ በመጠቀም በኢትዮጵያ የመጀመሪያው ባንክ ሆነ፡፡
የባትሪ ስዋፒንግ ቴክኖሎጂ የኤሌክትሪክ ሞተር ብስክሌት ተጠቃሚ ባትሪው በሚያልቅበት ጊዜ ወደ ስዋፒንግ ጣቢያ በመውሰድ ባትሪ በፍጥነት መቀየር ያስችለዋል። ይህ ሂደት የመጠበቂያ ጊዜን በእጅጉ በመቀነስ የሥራ ቅልጥፍናን ከማሻሻሉም በላይ የኤሌክትሪክ መጓጓዣ ቴክኖሎጂን እጅግ ቀላል በማድረግ ማህበረሰቡ እንዲጠቀመው ያበረታታል።
ይህ እርምጃ ዘመን ባንክ ለአካባቢ ጥበቃ፣ ማህበራዊና መልካም አስተዳደር (ESG) መርሆዎች ያለውን ጠንካራ ቁርጠኝነት ያሳያል፣ በተለይም የአረንጓዴ መጓጓዣን በመደገፍ የካርቦን ልቀትን ለመቀነስ በሚደረገው ጥረት ውስጥ በኢትዮጵያ የፋይናንስ ዘርፍ የበኩሉን እየተወጣ ይገኛል፡፡
ዘመን ባንክ በኢትዮጵያ የባንክ ዘርፍ ውስጥ ከምስረታው ጊዜ ጀምሮ አዳዲስ ሃሳቦችንና አገልግሎቶችን በቴክኖሎጂ በተደገፈ ሁኔታ በመጠቀም ቀዳሚ ተቋም ነው፡፡ የኤሌክትሪክ ሞተር ብስክሌት የባትሪ ስዋፒንግ ቴክኖሎጂን በመጠቀም የመጀመሪያው ባንክ መሆኑም ይህንን የሚያጠናክረው ነው፡፡
#ዘመንባንክ

ዘመን ባንክ እና የአውሮፓ ኢንቨስትመንት ባንክ በአረንጓዴ ፋይናንስ ትብብራቸውን አጠናከሩየአውሮፓ ኢንቨስትመንት ባንክ እና ዘመን ባንክ የአረንጓዴ የፋይናንስ ሥርዓት ቴክኒካል ድጋፍ ፕሮግራም...
20/05/2026

ዘመን ባንክ እና የአውሮፓ ኢንቨስትመንት ባንክ በአረንጓዴ ፋይናንስ ትብብራቸውን አጠናከሩ
የአውሮፓ ኢንቨስትመንት ባንክ እና ዘመን ባንክ የአረንጓዴ የፋይናንስ ሥርዓት ቴክኒካል ድጋፍ ፕሮግራም አጋርነታቸውን ለማጠናከር ተስማሙ፡፡
በመጋቢት 2016 ዓ.ም. በይፋ የተጀመረው ይህ የትብብር ፕሮጀክት የዘመን ባንክን በአየር ንብረትና ተያያዥ የአደጋ አስተዳደርና በአረንጓዴ ፋይናንስ ዘርፍ ያለውን አቅም ለማጠናከር ያለመ ሲሆን ሁለቱም ወገኖች ትብብሩ እንደሚቀጥል አረጋግጠዋል፡፡
በፕሮግራሙ ማዕቀፍ ዘመን ባንክ በአውሮፓ ኢንቨስትመንት ድጋፍ ከዲኤአይ ግሎባል ጋር በመተባበር በየፋይናንስ ሪፖርት በሁሉም አገሮች ከሚተገበሩ ተመሳሳይ መስፈርቶች አንፃር ያሉ ክፍተቶችንና የአየር ንብረት የአደጋ ተጋላጭነትን ለመለየት የሚያስችሉ የሽግግር ዕቅድ ዝግጅትና የአረንጓዴ ፋይናንስ ስትራቴጂ ማበልፀግን ጨምሮ የተለያዩ ጥናቶችና የአሰልጣኞች ስልጠና ተከናውነዋል፡፡
የማጠናቀቂያ ውይይቱ የዘመን ባንክ የዳይሬክተሮች ቦርድ ምክትል ሰብሳቢ ዶ/ር ሰዋለ አባተ ፣ የዳይሬክተሮች ቦርድ አባላት፣ ከፍተኛ የሥራ ሐላፊዎች፣ የአውሮፓ ኢንቨስትመንት ባንክ የኢትዮጵያና የአፍሪካ ህብረት ቢሮ ኃላፊ ሌይላ ትራዎሬን ጨምሮ የባንኩና የዲኤአይ ተወካዮች በተገኙበት ግንቦት 12 ቀን 2018 ዓ.ም. ተካሂዷል።
በወቅቱም የትብብሩን ስኬታማነት በማስመልከት ዘመን ባንክ ለአውሮፓ ኢንቨስትመንት ባንክና ለዲኤአይ አማካሪዎች የምስጋና የምስክር ወረቀት አበርክቷል።
#ዘመንባንክ

ከመጀመሪያ የንግድ ጅማሬዎ እስከ ትልቅ ህልምዎ ድረስ፣ ዘመን ባንክ እንደፍላጎትዎ በሚዘጋጁ የባንክ አገልግሎቶች፣የብድር አይነቶች፣ ተለዋዋጭ የባንክ ሂሳቦችና የባለሙያ ምክር አገልግሎቶችን በ...
16/05/2026

ከመጀመሪያ የንግድ ጅማሬዎ እስከ ትልቅ ህልምዎ ድረስ፣ ዘመን ባንክ እንደፍላጎትዎ በሚዘጋጁ የባንክ አገልግሎቶች፣የብድር አይነቶች፣ ተለዋዋጭ የባንክ ሂሳቦችና የባለሙያ ምክር አገልግሎቶችን በመስጠት የንግድ ጉዞዎን በእያንዳንዱ እርምጃዎ ይደግፋል፡፡
***
ቤተሰብ ይሁኑ :
LinkedIn: https://bit.ly/3NmAmnE
X: https://bit.ly/48fi5AA
Instagram: https://bit.ly/3RmlUNP
YouTube: https://bit.ly/47U4sqI
Telegram: https://bit.l
Facebook: https://bit.ly/47Q7GeR
***
#ዘመንባንክ

ለተከበራችሁ ደንበኞቻችን፤የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ባወጣው መመሪያ አዲስ አበባንና ሐረሪ ክልልን ጨምሮ በ27 ዋና ዋና ከተሞች የሚገኙ የባንካችን ደንበኞች እስከ ግንቦት 6 ቀን 2018 ዓ.ም...
14/05/2026

ለተከበራችሁ ደንበኞቻችን፤
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ባወጣው መመሪያ አዲስ አበባንና ሐረሪ ክልልን ጨምሮ በ27 ዋና ዋና ከተሞች የሚገኙ የባንካችን ደንበኞች እስከ ግንቦት 6 ቀን 2018 ዓ.ም ድረስ ሂሳባቸውን ከፋይዳ ቁጥር (ብሔራዊ መታወቂያ) ጋር ማስተሳሰር እንዳለባቸው አስገንዝቧል። በተጨማሪም በተቀሩት የሀገራችን ክፍሎች የሚገኙ ደንበኞች እስከ ሰኔ 30 ቀን 2018 ዓ.ም ድረስ ማጠናቀቅ እንደሚኖርባቸው አስታውቋል፡፡
እርስዎም እስካሁን ድረስ የፋይዳ ቁጥርዎን ከዘመን ባንክ ሂሳብ ቁጥርዎ ጋር ካላስተሳሰሩ ከተጠቀሰው ቀን በፊት ካሉበት ሆነው ይህንን ማስፈንጠሪያ https://fayda.zemenbank.com/ በመጠቀም ወይም ወደሚቀርብዎት የዘመን ባንክ ቅርንጫፍ በመሄድ ሂሳብዎን ከፋይዳ ጋር እንዲያስተሳስሩ በአክብሮት እንጠይቅዎታለን። ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት በ6500 ይደውሉልን፡፡
ስለ ትብብርዎ እናመሰግናለን።
ዘመን ባንክ፤
የላቀ አገልግሎት ማዕከል!
#ዘመንባንክ

Address

Senga Tera Ras Abebe Aregay Street
Addis Ababa
1212

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Zemen Bank S.C. posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Zemen Bank S.C.:

Share