የፌዴራል የመንግስት ግዥ አገልግሎት/Federal Public Procurement Service -PPS

  • Home
  • Ethiopia
  • Addis Ababa
  • የፌዴራል የመንግስት ግዥ አገልግሎት/Federal Public Procurement Service -PPS
Call Directions Website Contact the business

የፌዴራል የመንግስት ግዥ አገልግሎት/Federal Public Procurement Service -PPS Perform procurement of public organization common user items and nationally strategic utilities; render efficient and effective property disposal service;

የመንግስት ግዥ አገልግሎት በሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር 184/2002 ሐምሌ 2 ቀን 2002 ዓ.ም ሲቋቋም ዓላማዎቹ የመንግስት መስሪያ ቤቶች የሚጠቀሙባቸውን ተመሳሳይ ዕቃና አገልግሎቶች እንዲሁም አገራዊ ስትራቴጂካዊ ጠቀሜታ ያላቸው እቃዎችና አገልግሎቶች ከከፍተኛ ግዥ የሚገኘውን ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታ በሚያስገኝ ተመጣጣኝ ዋጋ፣ በተገቢው ጊዜና በተፈላጊው ጥራት እንዲቀርቡ ማስቻል፣በሽያጭ እንዲወገዱ ውሳኔ የተሰጠባቸውን የመንግስት መ/ቤቶች ንብረቶች በተቀላጠፈ አኳኋን በተመጣጣኝ ዋጋ እንዲወገዱ ማስቻል እና ለመንግስት የልማት ድርጅቶች በዕቃና አገልግሎት ግዥ እንዲሁም በንብረት ማስወገድ ረገድ እገዛ ማድረግ ናቸው፡፡

20/10/2026

ያገለገሉ ቁርጥራጭ ብረታ ብረቶች ሽያጭ ጨረታ ተከፈተ
*******
ዜና፡ አዲስ አበባ፡ ጥቅምት 10 ቀን 2019 ዓ.ም የመንግስት ግዥ አገልግሎት የ11 መ/ቤቶች ንብረት የሆኑ ያገለገሉ ቁርጥራጭ ብረታ ብረቶች በሽያጭ ለማስወገድ መስከረም 18 ቀን 2019 ዓ.ም በአዲስ ዘመን ጋዜጣ የሽያጭ ጨረታ ማስታወቂያ ማውጣቱ ይታወሳል፡
በዚህም መሰረት ጨረታው በትናንትናው ዕለት ከጠዋቱ 4፡15 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው እንዲሁም ሌሎች የሚመለከታቸው አካላት በተገኙበት በአገልግሎቱ አዳራሽ ተከፍቷል፡፡

የመንግስት ሠራተኞች መልካም ስብዕና ግንባታ ዙሪያ ስልጠና ተሰጠ ******************************ዜና፣ አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 07 ቀን 2019 ዓ.ም የመንግስት ግዥ አገልግሎት...
17/10/2026

የመንግስት ሠራተኞች መልካም ስብዕና ግንባታ ዙሪያ ስልጠና ተሰጠ
******************************
ዜና፣ አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 07 ቀን 2019 ዓ.ም የመንግስት ግዥ አገልግሎት የሠራተኞች መልካም ስብዕና እና ባህሪያዊ ብቃት ግንባታ ዙሪያ ስልጠና ተሰጠ።
ስልጠናው በዋናነት የአገልግሎቱ ሠራተኞች የሥነ-ምግባር ደንቦችን እንዲያከብሩ፣ ሕዝብን በታማኝነትና በቅንነት እንዲያገለግሉ እንዲሁም ተቋማዊ ሪፎርሞችን ስኬታማ እንዲያደርጉ ታስቦ መዘጋጀቱን በአገልግሎቱ የስራ አመራር ዋና ስራ አስፈፃሚ ኢቲሳ ደሜ (ዶ/ር) ገልፀዋል።
በመሆኑም የተሰጠው ስልጠና ለተቋም ብቻ ሳይሆን ለግል ሂወትም ጠቃሚ በመሆኑ ተግባራዊ ልናደርጋቸው ይገባል ብለዋል።
ስልጠናውን ከፌዴራል ሲቪል ሰርቪስ በመጡት ብርሀኑ አስፋው ( ዶ/ር ) የተሰጠ ሲሆን ፤ በአገልጋይነት ፣በጊዜ አጠቃቀም ፣ ተግባቦትና ተፅዕኖ መፍጠር ፣ መብቃትና መነሳሳት እንዲሁም ፈጠራ በሚሉ ርዕሰ ጉዳዮች ዙሪያ ሰፊ ገለፃ በማድረግ ግንዛቤ አስጨብጠዋል።
የተሰጠው ስልጠና ሰራተኞች ተገልጋዩን ህብረተሰብ በቅንነት እና በከፍተኛ የስነ ምግባር ዲሲፕሊን የማገልገል ባህላቸውን ይበልጥ እንዲያሳድጉና እንዲያጠናክሩ የሚያግዝ መሆኑን የስልጠናው ተሳታፊዎች ገልፀዋል።

15/10/2026
19ኛው ብሔራዊ የሰንደቅ ዓላማ ቀን ተከበረ ፡፡አዲስ አበባ፡ጥቅምት 02 ቀን 2019 ዓ.ም 19ኛው ብሔራዊ የሰንደቅ ዓላማ ቀን “ሰንደቅ ዓላማችን ለብሔራዊ መግባባትና አንድነታችን!” በሚል ...
12/10/2026

19ኛው ብሔራዊ የሰንደቅ ዓላማ ቀን ተከበረ ፡፡
አዲስ አበባ፡ጥቅምት 02 ቀን 2019 ዓ.ም 19ኛው ብሔራዊ የሰንደቅ ዓላማ ቀን “ሰንደቅ ዓላማችን ለብሔራዊ መግባባትና አንድነታችን!” በሚል መሪ ቃል በደማቅ ሥነ-ሥርዓት ተከበረ።
በሥነ-ሥርዓቱ ላይ የመንግስት ግዥ አገልግሎት አመራርና ሠራተኞች ጨምሮ የብሔራዊ ስትራቴጅክ ሚኒስቴር እና የመንግስት ግዥና ንብረት ባለስልጣን አመራርና ሠራተኞች ታድመዋል ፡፡
ብሔራዊ የሰንደቅ ዓላማ ቀን በሕገ-መንግሥቱና በሚመለከታቸው ሕጎች መሠረት በየዓመቱ በጥቅምት ወር የመጀመሪያ ሳምንት ሰኞ በብሔራዊ ደረጃ ይከበራል።

በፌዴራል የመንግስት ግዥ አፈፃፀም መመሪያ እና በመንግስት የንብረት አስተዳደር መመሪያ ላይ ሲሰጥ የቆየው የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተጠናቀቀ ፡፡ አዲስ አበባ ፡ ጥቅምት ፡ 01/2019 ዓ....
11/10/2026

በፌዴራል የመንግስት ግዥ አፈፃፀም መመሪያ እና በመንግስት የንብረት አስተዳደር መመሪያ ላይ ሲሰጥ የቆየው የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተጠናቀቀ ፡፡
አዲስ አበባ ፡ ጥቅምት ፡ 01/2019 ዓ.ም የመንግስት ግዥ አገልግሎት በፌዴራል መንግስት የግዥ አፈጻጸም መመሪያ ቁጥር 1073/2017 እና በፌዴራል መንግስት የንብረት አስተዳደር መመሪያ ቁጥር 1095/2017 ዙሪያ ሲሰጥ የቆየው የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተጠናቋል ።
በስልጠናው ከመመሪያዎቹ ባሻገር ዓመታዊ የግዥ ዕቅድን በኤሌክትሮኒክ መንግሥት ግዥ ሥርዓት (e-GP) ማዘጋጀት እና የሚወገዱ ንብረቶችን በኤሌክትሮኒክስ የመንግስት ንብረት ማስወገድ ዘዴ ( e-GD) ማስወገድ በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ሰፊ ገለፃ እና ውይይት ተካሂዷል ።
በተጨማሪም የማዕከል ግዥ አፈፃፀም በግዥ መሪ ስራ አስፈፃሚ በአቶ ወርቁ ገዛኸኝ ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል ።
በአገልግሎቱ የስራ አመራር ዋና ስራ አስፈፃሚ ኢቲሳ ደሜ (ዶ/ር) በውይይቱ ማጠቃለያ ላይ እንደተናገሩት ስልጠናው በዋናነት አዲሱን የመንግሥት ግዥ አፈፃፀም መመሪያ በተግባር በተሟላ መልኩ ለመተግበር የሚያስችል ግንዛቤ በማዳበር፣ በግዥ ሂደት ላይ የተሻለ አፈፃፀም ለማምጣት እንዲሁም ፤ የመንግስትን ሀብትና ንብረት ከብክነት በመጠበቅ እና በቴክኖሎጂ (e-GP) የታገዘ በማድረግ ቀልጣፋ የህዝብ አገልግሎት ለመስጠት ታስቦ መዘጋጀቱን ገልፀዋል።
በመሆኑም በቀጣይ ተመሰሳይ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠናዎች በዙር እንደሚቀጥሉ አስገንዝበዋል ።
ለ3 ተከታታይ ቀናት የተካሄደው የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና በአውሮፓ ህብረት በተገኘ የገንዘብ ድጋፍ የተዘጋጀ ሲሆን ፤ ከአገልግሎቱ የሚመለከታቸው የስራ ክፍሎችን ጨምሮ ከፌዴራል ባለበጀት መ/ቤቶች ተሳትፈዋል።

ወ/ሮ ትዕግስት ፍስሐ እና አቶ ፍቃዱ ሆረታ  የገንዘብ ሚኒስቴር ሚኒስትር  ዴኤታ ሆነው በመሾማቸው የመንግስት ግዥ አገልግሎት  የተሰማውን ደስታ እየገለፀ ፤ መልካም የስራ ጊዜ እንዲሆንላቸው...
11/10/2026

ወ/ሮ ትዕግስት ፍስሐ እና አቶ ፍቃዱ ሆረታ የገንዘብ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ሆነው በመሾማቸው የመንግስት ግዥ አገልግሎት የተሰማውን ደስታ እየገለፀ ፤
መልካም የስራ ጊዜ እንዲሆንላቸው አገልግሎቱ መልካም ምኞቱን ይገልፃል።

በፌዴራል መንግስት የንብረት አስተዳደር መመሪያ ላይ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና እየተሰጠ ይገኛል ። መስከረም 30:2019 ዓ.ም የመንግስት ግዥ አገልግሎት በፌዴራል መንግስት የንብረት አስተዳ...
10/10/2026

በፌዴራል መንግስት የንብረት አስተዳደር መመሪያ ላይ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና እየተሰጠ ይገኛል ።
መስከረም 30:2019 ዓ.ም የመንግስት ግዥ አገልግሎት በፌዴራል መንግስት የንብረት አስተዳደር መመሪያ ቁጥር 1095/2017 ላይ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና በመስጠት ላይ ነው ።
የመንግስት ንብረት አስተዳደር ግልጽ፣ ውጤታማ፣ ተጠያቂነት የሰፈነበት እና በቴክኖሎጂ የታገዘ እንዲሆን በማድረግ ፤ የመንግስትን ንብረት በጥንቃቄ የመያዝ፣ የመጠቀም፣ የመቆጣጠር እና አገልግሎቱ ሲያበቃ በወቅቱና በተገቢው መንገድ እንዲወገዱ ለማስቻል፤ የመንግስት ንብረት አስተዳደር መመሪያ መውጣቱ ይታወቃል ።
በመሆኑም በአገልግሎቱ የሚገኙ እና ጉዳዩ የሚመለከታቸው ባለሙያዎች በመመሪያው ላይ ግለፅነት ለመፍጠር እና የተቋሙ ንብረቶችን በእቅድ ለመምራት እና ለአገልግሎት ለማዋል እንዲሁም የሚወገዱ ንብረቶችን በኤሌክትሮኒክስ የመንግስት ንብረት ማስወገድ ዘዴ ( e-GD) ማስወገድ በሚቻልበት ዙሪያ ግንዛቤ ለመፍጠር ስልጠናው መዘጋጀቱን በመድረኩ ተገልጿል ።
የግንዛቤ ማስጨበጫው በአውሮፓ ህብረት በተገኘ የገንዘብ ድጋፍ የተዘጋጀ ሲሆን ፤ ከመንግስት ግዥና ንብረት ባለስልጣን በመጡ ባለሙያዎች እየተሰጠ ይገኛል ።

በፌዴራል የመንግስት ግዥ አፈፃፀም መመሪያ ላይ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና እየተሰጠ ነው፡፡ አዲስ አበባ ፡ መስከረም 30/2019 ዓ.ም  የመንግስት ግዥ አገልግሎት በፌዴራል መንግስት የግዥ ...
10/10/2026

በፌዴራል የመንግስት ግዥ አፈፃፀም መመሪያ ላይ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና እየተሰጠ ነው፡፡
አዲስ አበባ ፡ መስከረም 30/2019 ዓ.ም የመንግስት ግዥ አገልግሎት በፌዴራል መንግስት የግዥ አፈጻጸም መመሪያ ቁጥር 1073/2017 ያተኮረ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና እየሰጠ ይገኛል ።
የግንዛቤ ማስጨበጫው በአውሮፓ ህብረት በተገኘ የገንዘብ ድጋፍ የተዘጋጀ ሲሆን ፤ የስልጠናው ዋና ዓላማ የመንግሥት ፋይናንስና ግዥ አሰራርን ግልጽ፣ ቀልጣፋ፣ እና ተጠያቂነት የሰፈነበት ለማድረግ እና በተለይም አዲሱ መመሪያ የኤሌክትሮኒክ መንግሥት ግዥ ሥርዓትን (e-GP) ጨምሮ በርካታ ማሻሻያዎችን ያካተተ በመሆኑ፣ በእሱ ላይ ግልፀኝነት ለመፍጠር መሆኑን በአገልግሎቱ የግዥ መሪ ስራ አስፈፃሚ አቶ ወርቁ ገዛኸኝ ገልፀዋል ።
ስልጠናው ከመንግስት ግዥና ንብረት ባለስልጣን በመጡ ባለሙያዎች እየተሰጠ ሲሆን ፤ የመንግስት ግዥ መርሆዎችና ዓላማዎች ፣ የግዥ ዘዴዎችና መረጣ ፣ በአጽዳቂ ኮሚቴ ተግባርና ኃላፊነት ፣በጨረታ ስነ ስርዓት ፣ በውል አስተዳደር እንዲሁም ዓመታዊ የግዥ ዕቅድን በኤሌክትሮኒክ መንግሥት ግዥ ሥርዓትን (e-GP) ማዘጋጀት በሚሉ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ትኩረት በማድረግ እየተሰጠ ይገኛል ።
በስልጠናው ከአገልግሎቱ ጉዳዩ የሚመለከታቸው ባለሙያዎችን ጨምሮ ከተቋሙ ጋር የስራ ግንኙነት ያላቸው የፌደራል ባለበጀት መ/ቤት የግዥ ባለሙያዎች ተሳታፊ ሆነዋል ።

ዶ/ር ፍፁም አሠፋ  የገንዘብ ሚኒስቴር ሚኒስትር ሆነው በመሾማቸው የመንግስት ግዥ አገልግሎት  የተሰማውን ደስታ ይገልፃል ።መልካም የስራ ጊዜ እንዲሆንላቸውም አገልግሎቱ መልካም ምኞቱን ከወዲ...
08/10/2026

ዶ/ር ፍፁም አሠፋ የገንዘብ ሚኒስቴር ሚኒስትር ሆነው በመሾማቸው የመንግስት ግዥ አገልግሎት የተሰማውን ደስታ ይገልፃል ።
መልካም የስራ ጊዜ እንዲሆንላቸውም አገልግሎቱ መልካም ምኞቱን ከወዲሁ ይገልፃል ።

26/09/2026

Address

Addis Ababa
Addis Ababa

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when የፌዴራል የመንግስት ግዥ አገልግሎት/Federal Public Procurement Service -PPS posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to የፌዴራል የመንግስት ግዥ አገልግሎት/Federal Public Procurement Service -PPS:

Shortcuts

Share