New Business Bticoin plc for ethiopia

New Business Bticoin plc for ethiopia Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from New Business Bticoin plc for ethiopia, Finance, Addis Ababa.

05/02/2019
04/02/2019

BITCOIN :
Bitcoin.What !! ቢትኮይን. !!!!!! ምን?

ለኢንርኔት ዓለም የተዘጋጀ እና ከየትኛውም ሀገር መንግሥት ጋር ግንኙነት የሌለው ሲሆን ይህ ቢትኮይንገንዘብም ሊገኝ የሚችለው እርሱኑ በጥሬ ገንዘብ በመግዛት፣ ለምርት/አገልግሎት በክፍያ መልክ በመቀበል ወይም mine በማድረግ ነው።

በዚህ ገንዘብ አማካኝነት የተከናወኑ ልውውጦችን ትክክለኛነት በኮምፒውተር በታገዘ የCryptography ስሌት አማካኝነት የማረጋገጥ ስራ Mining ይባላል።

ይህን ሥራ ለሚሰሩ ሰዎች ሲስተሙ አዲስ ቢትኮይን እያተመ ይከፍላቸዋል። አዲስ ቢትኮይኖች የሚታተሙትም በዚህ መንገድ ብቻ ነው።

Mining ለዚሁ ተብለው የተዘጋጁ ልዩ ኮምፒውተሮችን እና ከፍተኛ የሆነ የኤሌክትሪክ ፍጆታ የሚፈልግ ስራ ሲሆን አፍሪካ ጨምሮ በተለያዩ የዓለማችን ክፍሎች ይህንን ስራ በመስራት ሲስተሙ የከፈላቸወን ቢትኮይን ወደ ሀገራቸው ጥሬ ገንዘብ እየቀየሩ በማስቀመጥ ስራ ላይ የተሰማሩ በርካታ ድርጅቶች እና ግለሰቦች አሉ። ለሚሸጡት ምርት ወይም አገልግሎት በቢትኮይን የሚፈፀምን ክፍያ የሚቀበሉ በርካታ የምግብ ቤቶች፣ የህግ አገልግሎት ሰጪዎች፣ አምራቾች ... ወዘተ ስላሉም ለነዚህ ነጋዴዎች በቢትኮይን የተቀበሉትን ክፍያ ፕሮሰስ አድርገው ወደ ጥሬ ገንዘብ በመቀየር ወደ ባንክ ሒሳባቸው ገቢ የማድረግ ስራ ብቻ የሚሰሩ ድርጅቶች አሉ። የመጀመሪያው ዲጅታል ገንዘብ በመሆኑ እና በዚሁ ጽሁፍ ለሚነሱ ተዛማጅ ሀሳቦች መነሻ በመሆኑ መረጥነው እንጂ በአሁኑ ጊዜ በዚሁ ጽንሰ ሀሳብ ተመሳሳይ አገልግሎት የሚሰጡ ከ 1500 በላይ ዲጂታል ገንዘቦች አሉ።

በኢንተርኔት የሚፈጸም ገቢ እና ወጪ ምን ያህል ያስተማምናል?

ግብይት በሚያያደርጉ ሁለት ወገኖች መካከል መተማመን ሳይኖር ሲቀር የገቢና ወጪ ክፍያዎችን ትክክለኛነት የሚያረጋግጥ ሶስተኛ ወገን ያስፈልጋል። የባንኮች አንጀራ የተመሰረተው በዚሁ የሦስተኛ ወገንነት ሚና ላይ ነው። የCypherpunks አመለካከት ደግሞ ይህ የሶስተኛ ወገንነት ሚና በጥቂት ኃያላኖች እጅ መወደቅ ሳያስፈልገው በየትኛውም ቦታ ሥራውን ለመስራት ፍቃደኛ በሆኑ ሰዎች አማካኝነት (decentralized ሆኖ) መከናወን ነው ያለበት መሆንም ይችላል በሚል መነሻ ነው ቢትኮይንን የወለደው።

በቢትኮይን የሚፈጸሙ ክፍያዎች ትክክለኛነት የሚረጋገጠው በMining እንደመሆኑ የዚህን የገንዘብ ዝውውርና የማረጋገጡን ሂደት እዚህጋ በድጋሚ ማንሳት ይጠበቅብናል።

አንድ ተጠቃሚ ኮምፒውተሩ ወይም ሞባይሉ ላይ ባለው Wallet ውስጥ በጥሬ ገንዘብ ገዝቶም ይሁን በክፍያነት ተቀብሎ ያገኛቸውን ቢትኮይን ያስቀምጣል። ክፍያ ሊፈጽምለት የፈለገውን ሰው የWallet አድራሻ ኮምፒውተሩ ወይም ሞባይሉ ላይ በመጻፍ Send የምትለዋን በመጫን ይልካል። በዚህ መልኩ ዲጂታል ገንዘብን በመጠቀም የሚፈጸም ክፍያ የሚመዘገበው አንድ መዝገብ (ledger) ላይ ሲሆን ከዚህ የሚመነጩ ክፍያዎችን ትክክለኛነት በማረጋገጥ ጥቅም ለማግኘት በመላው ዓለም ልዩ የMining ኮምፒውተራቸውን ይዘው የሚሰሩ የዚሁ መዝገብ ግልባጭ ስላላቸው ትራንዛክሽኑ መፈጸሙ ወዲያው መዝገባቸው ላይ ይታያቸዋል። እዚህ ጋ 'ማረጋገጥ' የምንለው ለክፍያ የዋለው ገንዘብ ከዚህ ቀደም ከፋዩ ለሌላ ክፍያ የተጠቀመው (double spent) አለመሆኑን እና ከፋዩ እየከፈለ ያለው በርግጥም ከቦርሳው ያለውን እና የራሱ የሆነን ገንዘብ መሆኑን እርግጠኛ ሆኖ መመስከርን ነው። ይህ የማረጋገጥ ስራ ጥብቅ የሆነ የCryptography ሕግን እንዲከተል በሲስተሙ የሚገደድ በመሆኑ በማረጋገጥ ሥራ ላይ የተሰማሩ ሰዎች ለግል ጥቅማቸው ሲሉ ሊያጭበረብሩ የሚችሉበት ምንም አይነት እድል የለም። ይህ ሂደት በአማካይ ከ10 እስከ 30 ደቂቃ ይፈጃል። ክፍያው ተረጋገጠ የሚባለው ሥራውን ከሚሰሩ ወገኖች በቅድሚያ የተቀመጠለትን የማረጋገጫ ስሌት በትክክለኛ መንገድ ሰርቶ በማጠናቀቅ ውጤት ሲያስረክብ ነው። ቀድሞ ውጤት ያስገኘው አረጋጋጭ ትራንዛክሽኑ የተፈፀመ ጊዜ ለማረጋገጫ ይከፈላል ተብሎ የተገለፀው የቢትኮይን መጠን ሲከፈለው ሌሎቹ አረጋጋጮች ደግሞ ቀድሞ ባረጋገጠው ወገን መረጃ መሰረት የየራሳቸውን ሌጀር እንዲያስተካክሉ (Update እንዲያደርጉ) ይገደዳሉ።

በባንክ ቋንቋ ስናስቀምጠው Mining በቢትኮይን ለሚፈጸም ግብይት data center ነው። ሆኖም በማዕከል የተቀመጠ እና በአንድ ተቋም ቁጥጥር ሥር ያለ ሳይሆን በመላው አለም የተሰራጨ እና በተሳታፊ ወገኖች ሙሉ ዕይታ ሥር ሆኖ የሚንቀሳቀስ አስተማማኝነቱም ማንም ሊያስታቸው በማይችሉ የሒሣብ አልጎሪዝሞች አማካኝነት የተረጋገጠ እንጂ በሰራተኞች ታማኝነት ላይ ያልተመሰረተ ነው። ይህ የዲጂታል ገንዘብ የመቆጣጠሪያ ስልት ዕውን እንዲሆን ያስቻለው ቴክኖሎጂ Blockchain ተብሎ ይጠራል።

ቢትኮይን በአፍሪካ ያለው ተቀባይነት ምን ያህል ነው?

ቢትኮይን በመግዛትና መሸጥ ግብይት ብዛት፤ ቢትኮይንን መሰረት አድርገው አዳዲስ ብቅ ብቅ ባሉ የስራ ፈጠራዎች ብዛት፤ እንዲሁም በጋራ በመሰባሰብ በጉዳዩ ዙሪያ በሚደረጉ እንቅስቃሴዎች ብዛት ጋና፣ ኬንያ፣ ናይጄሪያ እና ደቡብ አፍሪካ መሪ ናቸው። ዝምባብዌ እና ቦትስዋናም በዚሁ ተግባር የተሰማሩ ጥቂት የማይባሉ ዜጎች አሉዋቸው።

ቢትኮይን በዓለም አቀፍ ገበያ ከሚሸጥበት ዋጋ ይልቅ በአፍሪካ የሚሸጥበት እና የሚለወጥበት ዋጋ የ45 በመቶ ብልጫ አለው። ለዚህም ለምክንያት የሚጠከሱት አቅርቦት ከፍላጎት ያነሰ መሆኑ፣ የአፍሪካ ባንኮች የውጭ ምንዛሬ አቅም አናሳ መሆን፣ ወደ አፍሪካ ምርት የሚልኩ ላኪዎች ክፍያን በቢትኮይን ለመቀበል ፈቃደኛ መሆን፣ ከውጪ የሚመጣ ካፒታል እና እርዳታም ጭምር በቢትኮይን እየሆነ መምጣት (ለምሳሌ ያህል Save the Childern እና American Red Cross እርዳታ በቢትኮይን ይቀበላሉ) እንዲሁም በአህጉሪቱ ያለው የኤሌክትሪክ ሀይል እጥረት በ mining ሥራ ቢትኮይን የሚገኝበትን እድል ማጥበቡ ዋና ዋናዎቹ ናቸው። ሥራ አጥነት እና የመግዛት አቅማቸው በየጊዜው የሚቀንስ የአፍሪካ ሀገራት ገንዘቦችም ዜጎች ቢትኮይን በመግዛትና በመሸጥ ገቢ ለማግኘት የሚፈልጉ እንደሆኑና ያገኙትንም ገቢ በቢትኮይን ለማስቀመጥ እንዲመርጡ ምክንያት እንደሆነም ይነገራል።

በሌላ በኩል ሲታይ የአፍሪካ የፋይናንስ ዘርፍ የቁጥጥር ደንብ ከጠቀስናቸው አዳዲስ ሥራዎች እኩል ሊራመድ አልቻለም።

አውሮፖን የተመለከትን እንደሆነ ግን ከትልልቅ ዓለምአቀፍ የፋይናንስ ተቋማት መካከል JP Morgan እና Goldman Sachs የሥራቸውን ቅልጥፍና ለማሳደግ የሚያስችል የBlockchain ቴክኖሎጂ ለማመቻቸት በጋራ እየሰሩ መሆኑን ያገኘነው መረጃ ያስረዳል።

የAWS Mining ማንነት እና ጥቅሞቹ

AWS Mining በስድኒ አውስትራሊያ ዋና መስሪያ ቤቱ አድርጎ በ 2015 እኤአ የተቋቋመ የMining ስራ የሚሰራ ተቋም ሲሆን ሁለቱን አመታት ማለትም 2015 እና 2016 በራሱ ቻይና በተከላቸው የ Mining ፋርሞች ሲሰራ ቆይቶ ከ May, 2017 ጀምሮ በአዉስትራሊያ የስራ ፍቃድ በማውጣት የኤክስቼንጅ እና የአፍሊዬት ፕሮግራሙን ጨምሮ ማንኛውም የዓለም ህዝብ ተሳታፊ እና ተደራሽ የሚያደርግ እንዲሁም በማንኛውም የእድሜ፣ የኢኮኖሚ እና የቴክኒካል እውቀት ላሉ ተጠቃሚ የሚያደርግ ቢትኮይን Mining ሥራ ለ400 ቀናት በሚገዛ ኮንትራት ክፍት አድርጎ እየሰራ የሚገኝ ነው።

Address

Addis Ababa
GC

Telephone

+251937705147

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when New Business Bticoin plc for ethiopia posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share

Category