Ethiopian Insurance Corporation የኢትዮጵያ መድን ድርጅት

Call Directions Website Contact the business

Ethiopian Insurance Corporation የኢትዮጵያ መድን ድርጅት Ethiopian Insurance Corporation (EIC) was established in 1976 by proclamation No.68/1975. The Corpor

25/08/2026

ለመላው የእስልምና ዕምነት ተከታዮች
እንኳን ለመውሊድ በዓል በሰላም አደረሳችሁ!

በዓሉ የሰላም እና የደስታ እንዲሆንላችሁ እንመኛለን!

አስተማማኝ አጋርዎ
የኢትዮጵያ መድን ድርጅት!

21/08/2026

የኢትዮጵያ መድን ድርጅትን በራስዎ አገላለጽ እንዴት ይገልጹታል?

በየስራ ሀላፊዎቻችንን እናስተዋውቅዎ ዝግጅታችን ክፍል 3፣ የማርኬቲንግ እና ኮርፖሬት ኮሙኒኬሽን ዳይሬክተር የሆኑት ወ/ሮ ሲያዴ ሰለሞን ስለ ኢትዮጵያ መድን ድርጅት ያላቸውን ግላዊ እይታ፣ ድርጅቱ ለእሳቸው ያለውን ትርጉም እና ተቋሙን እንዴት እንደሚገልጹት በአጭሩ አካፍለውናል!

ቪዲዮውን በመመልከት ሙሉ ውይይቱን ይከታተሉ።

የኢትዮጵያ መድን ድርጅት አስተማማኝ አጋርዎ!

#የስራሀላፊዎቻችንንይተዋወቁ #ኢመድ50 #አመራር

How would you describe EIC in your own words?

In Episode 3 of Meet Our Leaders, SIYADE SOLOMON, Director of Marketing & Corporate Communications, shares a personal perspective on EIC, reflecting on what the Corporation means to her and how she experiences it.

🎬 Watch the episode and hear the conversation for yourself.
Ethiopian Insurance Corporation
Your Reliable Partner.

አስቸኳይ የጨረታ ማስታወቂያ 📢የኢትዮጵያ መድን ድርጅት ተሽከርካሪዎችን፣ የተሽከርካሪ አካላትን፣ ጋቢናዎችን እና የተለያዩ ቁሳቁሶችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል።በጨረታው መሳተፍ ...
20/08/2026

አስቸኳይ የጨረታ ማስታወቂያ 📢
የኢትዮጵያ መድን ድርጅት ተሽከርካሪዎችን፣ የተሽከርካሪ አካላትን፣ ጋቢናዎችን እና የተለያዩ ቁሳቁሶችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል።
በጨረታው መሳተፍ የምትፈልጉ ተወዳዳሪዎች ሙሉ መረጃውን እና የጨረታ ማስከበሪያ (CPO) ዝርዝሩን በተያያዘው ምስል ላይ መመልከት ትችላላችሁ።
📞 ለበለጠ መረጃ፡ 011439-25-89 / 011439-25-45
hashtag

#የኢትዮጵያመድንድርጅት
#የጨረታማስታወቂያ



ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለደብረታቦር (ቡሄ) በዓል በሰላም አደረሳችሁ!የቡሄን በዓል ከወዳጅ ዘመዶችዎ ጋር በደስታና በሰላም ሲያከብሩ፣ ህይወትዎን እና ንብረትዎን በ...
19/08/2026

ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለደብረታቦር (ቡሄ) በዓል በሰላም አደረሳችሁ!

የቡሄን በዓል ከወዳጅ ዘመዶችዎ ጋር በደስታና በሰላም ሲያከብሩ፣ ህይወትዎን እና ንብረትዎን በኢትዮጵያ መድን ድርጅት የዋስትና ሽፋን በማስጠበቅ ለቤተሰብዎ አስተማማኝ የደህንነት ስጦታ ያበርክቱ።

መልካም በዓል!

#የኢትዮጵያመድንድርጅት
#አስተማማኝአጋርዎ

18/08/2026

#አስተማማኝአጋርዎ
#የኢትዮጵያመድንድርጅት
#50ዓመታትየታመነ

12/08/2026

እያንዳንዱ የካሳ ጥያቄ ጀርባ ታሪክ አለ፤ ከእያንዳንዱ ታሪክ ጀርባ ደግሞ ሰው አለ!

“የሥራ ኃላፊዎቻችንን እናስተዋውቅዎ በሁለተኛ ክፍሉ የካሳ ዳይሬክተራችንን ወ/ሮ አስሚያ ገብረ ጊዮርጊስን ይዞላችሁ ቀርቧል።

ወ/ሮ አስሚያ በዳይሬክቶሬቱ ያሳለፉትን የሙያ ጉዞ፣ በሥራ አጋጣሚ ያጋጠሟቸውን ልብ የሚነኩ ታሪኮች እና በእለት ተእለት አገልግሎታችን የሚገጥሙ መልካም የደንበኞች ትዝታዎችን ያካፍሉናል!
……………………………………………………………………………..

Behind every insurance claim there is a story. Behind every story there is a person!

In Episode 2 of Meet Our Leaders, Mrs. Asmiya G/Giorgis, Claims Director at EIC, reflects on her journey in the claims directorate. She shares the defining moments, heartfelt customer experiences, and real stories that drive our mission every day!

07/08/2026

Meet Our Leaders!

We're excited to launch Meet Our Leaders, a new series introducing the professionals behind Ethiopian Insurance Corporation and the work they do every day.

In the first episode, Jalene Hailu, Reinsurance Director, shares insights into the role of reinsurance in the insurance industry, answering common questions and explaining how it supports coverage for large and complex risks.

Watch the conversation to learn more about the role reinsurance plays behind the scenes.


……………………………………………………………………….

የስራ ሀላፊዎቻችንን እናስተዋውቅዎ!

የኢትዮጵያ መድን ድርጅት ባለሙያዎችን እና እለት እለት የሚያከናውኑትን ሥራዎች የሚያስተዋውቅ የስራ ሀላፊዎቻችንን እናስተዋውቅዎ! የተሰኘ አዲስ ዝግጅታችንን የጀመርን ሲሆን በመጀመሪያው ክፍል የጠለፋ ኢንሹራንስ ዳይሬክተር የሆኑት ወ/ሮ ጃሌኔ ሃይሉ፤የጠለፋ ኢንሹራንስ በኢንሹራንስ ኢንዱስትሪ ውስጥ ያለውን ሚና በማብራራት እና በየጊዜው በደንበኞች ለሚጠየቁ ጥያቄዎች ምላሽ በመስጠት ያደረጉትን ቆይታ ይከታተሉ፡፡

#መሪዎቻችንንይወቁ #የጠለፋዋስትና #ኢንሹራንስ #የኢትዮጵያመድንድርጅት

23/07/2026

ለህልምዎ መከታ
ለቤተሰብዎ ደህንነት አሌኝታ
ለንግድ ለንብረትዎ ብርቱ መተማመኛ በመሆን በያሉበት ተደራሽ ሆነን ፈጣኑን የመድን አገልግሎት ማቅረባችንን ቀጥለናል

ይምጡ እና ይጎብኙን በአገልግሎታችን ጥራት ይረካሉ!

#አስተማማኝአጋርዎ
#የኢትዮጵያመድንድርጅት

ከሪፎርም ወደ አዲስ የስኬት ምዕራፍ! 18.6 ቢሊዮን ብር | 40% እድገትበኢትዮጵያ ኢንሹራንስ ኢንዱስትሪ ውስጥ ከፍተኛውን የገበያ ድርሻ የያዘው እና በተቋማዊ ሪፎርም፣ የለውጥ እና የልህቀ...
20/07/2026

ከሪፎርም ወደ አዲስ የስኬት ምዕራፍ!

18.6 ቢሊዮን ብር | 40% እድገት

በኢትዮጵያ ኢንሹራንስ ኢንዱስትሪ ውስጥ ከፍተኛውን የገበያ ድርሻ የያዘው እና በተቋማዊ ሪፎርም፣ የለውጥ እና የልህቀት ግስጋሴ ላይ ያለው የኢትዮጵያ መድን ድርጅት ፣ በ2018 በጀት ዓመት 18.6 ቢሊዮን ብር የዓረቦን ገቢ በመሰብሰብ እና ከባለፈው ዓመት የ 40% እድገት በማስመዝገብ አዲስ የስኬት ምዕራፍ ከፍቷል።
ከተሰበሰበው 18.6 ቢሊዮን ብር ውስጥ 18.08 ቢሊዮን ብር ከጠቅላላ ኢንሹራንስ፣ 531.4 ሚሊዮን ብር ከህይወት ኢንሹራንስ፣ እንዲሁም 24.8 ሚሊዮን ብር ከተካፉል አገልግሎት የተገኘ ነው

ይህ ስኬት የቁጥሮች ስብስብ ብቻ ሳይሆን፤ በሪፎርም የተጠናከረ አሠራር፣ የደንበኞቻችን የማይናወጥ እምነት፣ከሪፎርሙ ራዕይ ጋር በመቆም ለለውጥ ቁርጠኛ ሆነው የሰሩ ሠራተኞቻችን ትጋት እና የአጋሮቻችን ድጋፍ ያፈራው ውጤት ነውና ለዚህ ታሪካዊ ስኬት አስተዋጽኦ ላበረከቱ ደንበኞቻችን፣ ሠራተኞቻችን፣ አጋሮቻችን እና ሁሉም ባለድርሻ አካላት ከልብ እናመሰግናለን።

ከአምስት አስርት ዓመታት በፊት የጀመረው የእምነት ጉዞ፣ ዛሬ በውጤት ፤ ወደፊትም በልህቀት እና ደንበኛን ማዕከል ባደረገ አገልግሎት ይቀጥላል።
hashtag
#አስተማማኝአጋርዎ #የኢትዮጵያመድንድርጅት
#ሪፎርም

ጉብኝት ለውጤታማነት! ጉብኝት ለጠንካራ አጋርነት!በከፍተኛ የለውጥ ስትራተጂ እና የእድገት ጎዳና ላይ የሚገኘው የኢትዮጵያ መድን ድርጅት ዋና ሥራ አስፈፃሚ ክቡር አቶ አቤል ታደሰ እና የድርጅ...
15/07/2026

ጉብኝት ለውጤታማነት! ጉብኝት ለጠንካራ አጋርነት!

በከፍተኛ የለውጥ ስትራተጂ እና የእድገት ጎዳና ላይ የሚገኘው የኢትዮጵያ መድን ድርጅት ዋና ሥራ አስፈፃሚ ክቡር አቶ አቤል ታደሰ እና የድርጅቱ ስራ አመራሮች ኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግ ዋና መስሪያ ቤት በመገኘት ውጤታማ ጉብኝት አደረጉ፡፡

በጉብኝቱ ወቅት ክቡር አቶ አቤል ታደሰ፣ የልማት ድርጅቶችን በባለቤትነት የሚያስተዳድረው የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግን በአሁኑ ወቅት በታላቅ ተሀድሶ ውስጥ የሚገኘውን እና ለህብረተሰቡ የተሟላ የመድን ሽፋን በመስጠት የሃገሪቱን የኢኮኖሚ እንቅስቃሴ እንዳይስተጓጎል በማስቻል የበኩሉን አስተዋጽዖ በማበርከት ላይ ላለው የኢትዮጵያ መድን ድርጅት ለውጥ እና እድገት እያደረገ ላለው እገዛ እና ክትትል አመስግነው በቀጣይም የኢ.መ.ድ አመራርና ሰራተኞች ከቀድሞ በበለጠ ለሃገራችን እድገት በመትጋት በኢኮኖሚ እድገት ላይ ጉልህ አሻራ ለማሳረፍ ቁርጠኛ እንደሆኑ ተናግረዋል፡፡

የኢትዮያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ክቡር ዶ/ር ብሩክ ታዬም በበኩላቸው የኢትዮያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግ የአፍሪካ ትልቁ የመንግስት የሀብት ፈንድ በመሆኑ ተበታትነው የነበሩ በርካታ የመንግስት የልማት ድርጅቶችን በአንድ ማዕከል በማሰባሰብ በዘመናዊ መንገድ የሚያስተዳድር ስትራቴጂካዊ ተቋም መሆኑን ገልጸው ሀገር አቀፍ ኢኮኖሚያዊ እድገትን ለማረጋገጥ አዳዲስና ከፍተኛ ተፅዕኖ የሚፈጥሩ እንደኢትዮጵያ መድን ድርጅት ያሉ በፋይናንሱ ዘርፍ ግዙፍ እና ጠንካራ ሚና የሚጫወቱትን ተቋማትን በቅርብ በመከታተል ትርፋማነታቸውንና ዘላቂነታቸውን ማረጋገጥ ለሃገር እድገት እጅግ ወሳኝ እንደሆነ አውስተው ለወደፊቱም ለኢትዮጵያ መድን ድርጅት አስፈላጊውን እገዛ እያደረጉ እንደሚቀጥሉ አሳስበዋል፡፡

#ስኬቶቻችንንእየዘከርንየወደፊቱንእንቀይሳለን
#አስተማማኝአጋርዎ

Address

Churchel
Addis Ababa
2545

Opening Hours

Monday 08:00 - 16:00
Tuesday 08:00 - 16:00
Wednesday 08:00 - 16:00
Thursday 08:00 - 16:00
Friday 08:00 - 16:00
Saturday 08:00 - 00:00

Telephone

+251115512400

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Ethiopian Insurance Corporation የኢትዮጵያ መድን ድርጅት posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Ethiopian Insurance Corporation የኢትዮጵያ መድን ድርጅት:

Shortcuts

Share