Anbesa Bank

Anbesa Bank LET'S GO FOR IT! Lion International Bank is dedicated to ensuring the satisfaction of its customers, both in their personal lives and business endeavors.

Our mission is to empower individuals and businesses to achieve their envisioned future. Recognizing that customers require more than just bank services, we focus on providing seamless banking experiences that remove barriers to success. Our commitment is to streamline banking processes, instill confidence in decision-making, and propel our customers towards progress. Lion International Bank S.C.

is one of the foremost private banks in Ethiopia. Founded in October 2006 and opened its doors for services in early January 2007, LIB made a marked shift in ownership as the company based its roots on a larger number of shareholders than any other Bank has had during its establishment year, and has become a pioneer for the Banks that came later.

Vacancy Announcements =======================Anbesa Bank  Invites competent and qualified candidates for the following p...
30/05/2026

Vacancy Announcements
=======================
Anbesa Bank Invites competent and qualified candidates for the following positions.

1. Branch Manager I
2. Sub Branch Manger
3. Resident Auditor
4. Senior Customer Service Officer I
5. Trainee Bank

Please visit the below link to our Websites for the details:
https://anbesabank.com/careers/
Deadline: June 03, 2026

#እንጀምረው

28/05/2026

አጋርፋ እና ነቀምቴ ቅርንጫፎቻችን አገልግሎት መስጠት ጀመሩ
===========================
ባንካችን ተደራሽነቱን ይበልጥ ለማጠናከር በኦሮሚያ ክልል አጋርፋ ከተማ 394ኛ፣ እንዲሁም ነቀምቴ ከተማ 395ኛ ቅርንጫፎቹን ከፍቶ አገልግሎት መስጠት መጀመሩን ስንገልጽ በደስታ ነው።

አንበሳ ባንክ
እንጀምረው!

#እንጀምረው

ውድ ደንበኞቻችን====================እንኳን ለ1447ኛው የዒድ አል አድሃ (አረፋ) በዓል በሠላም አደረሳችሁ እያለ መልካም ምኞቱን ይገልፃል። ዒድ ሙባረክ!አንበሳ ባንክእንጀምረው!...
27/05/2026

ውድ ደንበኞቻችን
====================
እንኳን ለ1447ኛው የዒድ አል አድሃ (አረፋ) በዓል በሠላም አደረሳችሁ እያለ መልካም ምኞቱን ይገልፃል።

ዒድ ሙባረክ!

አንበሳ ባንክ
እንጀምረው!

#እንጀምረው

እባክዎ ከአጭበርባሪዎች ይጠበቁ=========================ከባንክ አገልግሎቶች ጋር ተያይዞ በርካታ አጭበርባሪዎች ልዩ ልዩ የማዘናጊያ ዘዴዎችን በመጠቀም ገንዘብ እየሰረቁ ይገኛሉ፡...
25/05/2026

እባክዎ ከአጭበርባሪዎች ይጠበቁ
=========================
ከባንክ አገልግሎቶች ጋር ተያይዞ በርካታ አጭበርባሪዎች ልዩ ልዩ የማዘናጊያ ዘዴዎችን በመጠቀም ገንዘብ እየሰረቁ ይገኛሉ፡፡
በተለይም እነዚህ አስመሳይ አታላዮች ከባንክ የተደወለ በማስመሰል የፋይዳ መለያ ቁጥር ለማስተሳሰር፣ የሞባይል ባንክ አገልግሎት ለማስጀመር እና ሌሎችንም አገልግሎቶች ለማስተካከል በሚል ሀሰተኛ መረጃ በቀጥታ ወደ ደንበኞች የግል ስልክ በመደወል የደንበኞችን የይለፍ ቃል ወይም የአንድ ጊዜ የይለፍ ቃል (OTP) እየጠየቁ ምዝበራ ለመፈጸም ያለማቋረጥ ይጎተጉታሉ፡፡
ከዚህም ባለፈ በደንበኞች ማህበራዊ ገጾች ወይም ሌሎች መገናኛ ዘዴዎች "ገንዘብ ይላኩልኝ" የሚል መልዕክት በመላክ ደጋግ ደንበኞችን በማዘናጋት በውሸት መንገድ ገንዘብ ለማስላክ ተደጋጋሚ ሙከራ ያደርጋሉ፡፡
ስለዚህም ሁላችንም ራሳችንን ከአጭበርባሪዎች እንድንጠብቅ አንበሳ ባንክ አደራ እያለ ማንኛውንም ከላይ የተጠቀሱትን እና መሰል የማጭበርበሪያ መንገዶችን ፈጥነን እንድንነቃባቸው እና ማንኛውንም የሚስጥር ቁጥር ከማጋራት እንድንቆጠብ እንዲሁም ሳናረጋግጥ ገንዘብ እንዳናስተላልፍ መልዕክቱን ያቀርባል፡፡
ከዚሁ ጋር በተያያዘ ከአንበሳ ባንክ የተደወለ በማስመሰል ሊያታልሉ ለሚሞክሩ አጭበርባሪዎች ምላሽ ከመስጠት ወይም ከውሳኔ በፊት ወደ አንበሳ ባንክ ጥሪ ማዕከል 8803 በመደወል ወይም አቅራቢያዎ ወደሚገኝ ቅርንጫፍ በመቅረብ እውነታውን እንዲያረጋግጡ አንበሳ ባንክ በአክብሮት ለማስታወስ ይወዳል፡፡

📞 የአንባሳ ባንክ የጥሪ ማዕከል - 8803

አንበሳ ባንክ
እንጀምረው!

#እንጀምረው

11/05/2026

ጋንዲ እና አንፎ ቅርንጫፎቻችን አገልግሎት መስጠት ጀመሩ
===========================
ባንካችን ተደራሽነቱን ይበልጥ ለማጠናከር በአዲስ አበባ ከተማ ጋንዲ 392ኛ፣ እንዲሁም በኦሮሚያ ክልል ሸገር ከተማ አስተዳደር አንፎ 393ኛ ቅርንጫፎቹን ከፍቶ አገልግሎት መስጠት መጀመሩን ስንገልጽ በደስታ ነው።

አንበሳ ባንክ
እንጀምረው!

#እንጀምረው

ቀለል ባለ መንገድ ያስተሳስሩ=================የባንክ ሂሳብዎን ከፋይዳ ቁጥርዎ (FCN ወይም FAN ቁጥር) ጋር ቀለል ባለ መንገድ ያስተሳስሩሂሳብዎን በቀላሉ ከፋይዳ ጋር ለማስተሳሰ...
09/05/2026

ቀለል ባለ መንገድ ያስተሳስሩ
=================
የባንክ ሂሳብዎን ከፋይዳ ቁጥርዎ (FCN ወይም FAN ቁጥር) ጋር ቀለል ባለ መንገድ ያስተሳስሩ
ሂሳብዎን በቀላሉ ከፋይዳ ጋር ለማስተሳሰር ድረ ገጻችንን https://fayda.anbesabank.com/ ይጉብኙ ወይም በአቅራቢያዎ ወደሚገኝ የባንካችን ቅርንጫፍ ጎራ ይበሉ፡፡

እባክዎ ይህን ማስፈንጠሪያ ይጫኑ ፡ https://fayda.anbesabank.com/

አንበሳ ባንክ
እንጀምረው!

#እንጀምረው

አንበሳ ባንክ ከወለድ ነፃ የባንክ አገልግሎት የሼሪዓ አማካሪ ቦርድ አባላቱን አስተዋወቀ===============================አንበሳ ባንክ በሼሪዓ መርሆች ላይ ተመስርቶ የሚሰጠውን...
08/05/2026

አንበሳ ባንክ ከወለድ ነፃ የባንክ አገልግሎት የሼሪዓ አማካሪ ቦርድ አባላቱን አስተዋወቀ
===============================
አንበሳ ባንክ በሼሪዓ መርሆች ላይ ተመስርቶ የሚሰጠውን ከወለድ ነፃ የባንክ አገልግሎት የአስተዳደር ስርዓት የተደራጀ እንዲሆን እና አገልግሎቶቹ መሰረታዊ የሸሪዓ መርሆችን ያከበሩ እንዲሆኑ ለማስቻል የሼሪዓ አማካሪ ቦርድ ያቋቋመ ሲሆን የአማካሪ ቦርድ አባላቱን ከባንኩ የዲሬክተሮች ቦርድ እና የስራ አስፈጻሚ ቦርድ አባላት ጋር የማስተዋወቅ መርኃ ግብር ተካሂዷል፡፡

የሼሪዓ አማካሪ ቦርድ አባላቱ ሸይኽ አደም አብዱልቃድር - የትግራይ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዝደንት፣ ሸይኽ ሙባረክ መሐመድ አወል - የፌዴራል ሸሪዓ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት እና አቶ ኢብራሂም ዳውድ ሙዜይን - የፓን አፍሪካ የሸሪዓ አማካሪ ማህበር የምስራቅ አፍሪካ ተወካይ ሲሆኑ አባላቱ በእስልምና እምነት እና በሼሪዓ መርሆች ከፍተኛ ስፍራ ያለቸው፣ ከበሬታን እና አንቱታን ያተረፉ የኃይማኖች አባቶች ናቸው፡፡
የቦርድ አባላቱ የተመረጡት በእስልምና፣ በሸሪዓ ህግ፣ በሕግ ዳኝነት እንዲሁም ከወለድ ነፃ የባንክ አሰራር ዙሪያ ባላቸው ሰፊ ልምድ እና እውቀት መሰረት እንዲሁም በእስልምና ኃይማኖት ተቋማት ውስጥ ባላቸው ጠንካራ የአመራር ብቃት እና በማህበረሰቡ ዘንድ ባላቸው ከፍተኛ ተቀባይነት መሰረት መሆኑ በመርሃ ግብሩ ላይ ተገልጿል፡፡
አማካሪዎቹ የአንበሳ ባንክ ከወለድ ነፃ የባንክ አገልግሎቶች ከሸሪዓ መርሆዎች ጋር የተጣጣሙ፣ ግልፅ እና ታማኝ መሆናቸውን በመገምገም የተሻለ ሃሳብ የሚሰጡ ሲሆን ባንኩም ተወዳዳሪ እና ተገልጋዩን ህብረተሰብ የሚጠቅሙ አገልግሎቶችን ማቅረብ እንዲችል በማድረግ ከፍተኛ አስተዋጽዖ ይኖራቸዋል፡፡

አንበሳ ባንክ
እንጀምረው!

#እንጀምረው

06/05/2026

ወረታ፣ ለገጣፎ እና መቱ ቅርንጫፎቻችን አገልግሎት መስጠት ጀመሩ
===========================
ባንካችን ተደራሽነቱን ይበልጥ ለማጠናከር በአማራ ክልል ወረታ ከተማ 389ኛ፣ በኦሮሚያ ክልል ሸገር ከተማ አስተዳደር 390ኛ እንዲሁም በኦሮሚያ ክልል መቱ ከተማ 391ኛ ቅርንጫፎቹን ከፍቶ አገልግሎት መስጠት መጀመሩን ስንገልጽ በደስታ ነው።

አንበሳ ባንክ
እንጀምረው!

#እንጀምረው

በኩራት እንጀምረው!መልካም የአርበኞች ቀንአንበሳ ባንክእንጀምረው!   #እንጀምረው
05/05/2026

በኩራት እንጀምረው!

መልካም የአርበኞች ቀን

አንበሳ ባንክ
እንጀምረው!

#እንጀምረው

መልካም የላብአደሮች ቀንአንድ ላይ ሆነን እንጀምረው!አንበሳ ባንክ እንጀምረው!     #እንጀምረው
01/05/2026

መልካም የላብአደሮች ቀን
አንድ ላይ ሆነን እንጀምረው!

አንበሳ ባንክ
እንጀምረው!

#እንጀምረው

Address

Athlete Haile G/Selassie Avenue, Lex Plaza Bldg. Addis Ababa
Addis Ababa

Opening Hours

Monday 08:00 - 19:00
Tuesday 08:00 - 19:00
Wednesday 08:00 - 19:00
Thursday 08:00 - 19:00
Friday 08:00 - 19:00
Saturday 08:00 - 19:00

Telephone

+251116626000

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Anbesa Bank posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Anbesa Bank:

Share