Solomon Eshete & Co.

Solomon Eshete & Co. We are a Chartered Certificated Accountants and Authorized Auditors in Ethiopia. We provide External

18/04/2026

የተጨማሪ እሴት ታክስ ደረሰኝ ሳያውቁ ጊዜው ካለፈብዎ ወይም ሲያሳውቁ በመሀል የረሱት ደረሰኝ ካለ ምን ማድረግ እንዳለብዎ ህጉ የሚለውን እናካፍልዎ?
በተጨማሪ እሴት ታክስ አዋጅ ቁጥር 1341/2016 እና በሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር 570/2017 መሠረት፣ የታክስ ደረሰኝን ለማስታወቅ ጊዜው ካለፈብዎት እንደ ጉዳዩ ዓይነት የሚከተሉትን እርምጃዎች መውሰድ ይችላሉ፦
1. የግብአት ታክስ ተቀናሽ (Input Tax Credit) ለማግኘት ከሆነ ደረሰኙን ያላሳወቁት ግዥ ፈጽመው የከፈሉትን ታክስ ለማቀናነስ (ለመቀነስ) ከሆነ፣ አዋጁ የጊዜ ገደብ ፈቅዶልዎታል። በአዋጁ አንቀጽ 29 ንዑስ አንቀጽ 7 መሠረት፣ በማናቸውም ምክንያት በአንድ የሂሳብ ጊዜ ውስጥ ተቀናሽ ሊደረግ የሚገባውን የታክስ መጠን (የግብአት ታክስ) ሳያሳውቁ የቀሩ እንደሆነ፣ ተቀናሽ ሊጠየቅበት ከሚገባው የሂሳብ ጊዜ መጨረሻ ጀምሮ ባሉት 12 ወራት ውስጥ በሚቀርብ ቀጣይ የታክስ ማስታወቂያ ላይ ደረሰኙን በማካተት ተቀናሽ እንዲደረግልዎ መጠየቅ ይችላሉ።
2. የሽያጭ (የውጤት ታክስ) ደረሰኝ ለማስታወቅ ከሆነ የሽያጭ ደረሰኝ መቁረጥ ወይም ማስታወቅ ዘግይተው ከሆነ፣ የታክስ ግዴታው ስለማይቀር ማስታወቂያውን በአፋጣኝ ማቅረብ ይኖርብዎታል። ማንኛውም የተመዘገበ ሰው ለእያንዳንዱ የሂሳብ ጊዜ የታክስ ማስታወቂያውን ወሩ በተጠናቀቀ በሚቀጥለው ወር የመጨረሻ ቀን ድረስ የማቅረብ ግዴታ አለበት። ይህ ጊዜ ካለፈ ግን የሚከተሉት ሁኔታዎች ይፈጠራሉ፦
• አስተዳደራዊ ቅጣት እና ወለድ፦ ታክስን በወቅቱ አለማሳወቅ ወይም ዘግይቶ መክፈል በታክስ አስተዳደር አዋጅ መሠረት የአስተዳደራዊ ቅጣት እና ወለድ ያስከትላል።
• የታክስ ባለሥልጣኑ ውሳኔ፦ የታክስ ባለሥልጣኑ ታክስ ሳይታወቅ በቆየበት ጊዜ ሁሉ የራሱን የታክስ ስሌት ውሳኔ (Assessment) ሊሰጥ ይችላል።
3. የታክስ ተመላሽ (Refund) ጥያቄ ካለዎት የተመዘገበው ሰው ተመላሽ ሊከፈለው በሚገባበት ጊዜ የታክስ ማስታወቂያ የማቅረብ ግዴታውን ካልተወጣ፣ የታክስ ባለሥልጣኑ ማስታወቂያው እስከሚቀርብ ድረስ ተመላሹ ገንዘብ ሳይከፈል እንዲቆይ ሊያደርግ ይችላል።
4. በኤሌክትሮኒክ ፊስካል መሣሪያ (EFD) የሚጠቀሙ ከሆነ መሣሪያው ባለመሥራቱ ምክንያት ግብይቱን በወቅቱ መመዝገብ ካልቻሉ፣ ሁኔታው በተፈጠረ በ24 ሰዓት ውስጥ ለታክስ ባለሥልጣኑ ማሳወቅ እና በእጅ የሚዘጋጅ የታክስ ደረሰኝ መስጠት ይኖርብዎታል። መሣሪያው ወደ ሥራ ሲመለስም ቀደም ብለው ያከናወኑትን ግብይት በመሣሪያው ውስጥ መመዝገብ ይኖርብዎታል።
በአጠቃላይ፣ የግብአት ታክስን (የግዥ ደረሰኝን) ለማስታወቅ የ12 ወራት የጊዜ ዕድል ቢኖርዎትም፣ የሽያጭ ደረሰኝን ግን ለቅጣት እና ለወለድ እንዳይዳረጉ በወቅቱ ማስታወቅ ተገቢ ነው።

11/02/2026

IFRS Implementation in Ethiopia
Why? When? Which Companies Apply Full IFRS vs IFRS for SMEs?
Ethiopia adopted International Financial Reporting Standards (IFRS) to modernize financial reporting and align with global best practices.
The implementation is supervised by the Accounting and Auditing Board of Ethiopia (AABE) under Financial Reporting Proclamation No. 847/2014.
Why IFRS?
✔ Improve transparency and comparability
✔ Strengthen investor confidence
✔ Enhance corporate governance
✔ Support capital market development
✔ Align Ethiopian companies with international reporting standards
IFRS allows Ethiopian businesses to present financial statements that are globally understandable and reliable.
Implementation Timeline
Standard
Deadline
Full IFRS
7 July 2023
IFRS for SMEs
7 July 2024
Who Applies Full IFRS?
Full IFRS applies to Public Interest Entities such as:
• Banks
• Insurance companies
• Financial institutions
• Government-owned enterprises
• Large share companies
These entities have public accountability and must comply with full IFRS Accounting Standards.
Who Applies IFRS for SMEs?
IFRS for SMEs applies to:
• Small and Medium-Sized Entities (SMEs)
• Private companies without public accountability
• Family-owned businesses meeting AABE criteria
This standard is simplified and more cost-effective than full IFRS.
Key Difference
Full IFRS → Detailed, comprehensive, suitable for large/public entities
IFRS for SMEs → Simplified framework for private SMEs
📞 Need IFRS or IFRS for SMEs Implementation or Audit Support?
If your company requires:
✔ First-time IFRS adoption (IFRS 1 transition)
✔ IFRS for SMEs conversion
✔ Financial statement preparation
✔ Audit under ISA
✔ AABE compliance advisory
Please contact:
Solomon Eshete Certified Audit Firm
Addis Ababa, Ethiopia
Email: [email protected]
Tel: +251 111111479

በገቢ ግብር የማሻሻያ አዋጅ ቁጥር 1395/2017 ማሻሻያ የተደረገባቸው ጉዳዮች   መግቢያ   ግብር የአንድ አገር ኢኮኖሚያዊ ሉዓላዊነት ከሚረጋገጥባቸው መንገዶች አንዱ ሲሆን መንግሥትም የዜ...
12/01/2026

በገቢ ግብር የማሻሻያ አዋጅ ቁጥር 1395/2017 ማሻሻያ የተደረገባቸው ጉዳዮች
መግቢያ
ግብር የአንድ አገር ኢኮኖሚያዊ ሉዓላዊነት ከሚረጋገጥባቸው መንገዶች አንዱ ሲሆን መንግሥትም የዜጎችን ኢኮኖሚያዊ፣ ማኅበራዊ እና ፖለቲካዊ እድገት በማረጋገጥ ረገድ ያለበትን ኃላፊነት ለመወጣት የሚያስፈልገውን ገቢ የሚያገኝበት ምንጭ ነው። የግብር ሕግ እንደማንኛውም ሌሎች ሕጎች ሁሉ ማኅበረሰቡ የደረሰበትን ሁለንተናዊ የእድገት ደረጃ ከግምት ባስገባ መልኩ ተቀርፆ በሥራ ላይ የሚውል እንደመሆኑ በየወቅቱ የሚኖሩ ማኅበራዊ፣ ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ሌሎች ለውጦችን ታሳቢ ባደረገ መልኩ መሻሻል ይኖርበታል።
የአገራችንም የግብር ሥርአት በየጊዜው የሚከሰቱ ለውጦችን ከግምት ባስገባ መልኩ የተለያዩ ማሻሻያዎችን በማድረግ አሁን ካለበት ደረጃ ደርሷል። በቅርቡ ማሻሻያ ከተደረገባቸው የግብር ሕግ አይነቶች አንዱ የገቢ ግብር አዋጅ ቁጥር 979/2008 ሲሆን በአዋጅ ቁጥር1395/2017 ማሻሻያ ተደርጎበታል። በዚህ አጭር ጽሑፍ የማሻሻያ አዋጁ ያካተታቸውን ዋና ዋና ጉዳዮች በአጭሩ እንዳስሳለን።
የማሻሻያ አዋጁ ያካተታቸው አዳዲስ ጉዳዮች
 ከመቀጠር፣ ከቤት ኪራይ፣ ከንግድ ሥራ እና ከዕድል ሙከራ የሚገኝ የገቢ ግብር
ከመቀጠር፣ ከኪራይ፣ ከንግድ ሥራ እና ከዕድል ሙከራ የሚገኝ የገቢ ግብር ምጣኔዎች በማሻሻያ አዋጁ ማሻሻያ ተደርጎባቸዋል፡፡ ይኸውም በቀድሞ የገቢ ግብር አዋጅ (አዋጅ ቁጥር 979/2008 አንቀፅ 11) ተደንግጎ የነበረው ከግብር ነፃ ከሚሆነው ከመቀጠር የሚገኝ ወርሃዊ ገቢ መጠን ጀምሮ እስከ ከፍተኛው የግብር ምጣኔ ድረስ ማሻሻያ ተደርጎበታል፡፡ በቀድሞው ሕግ ከገቢ ግብር ነፃ የሆነው እስከ ብር ስድስት መቶ (600) ያለ ገቢ የነበረ ሲሆን በማሻሻያ አዋጁ አንቀፅ 2(6) መሠረት እስከ ብር ሁለት ሺ (2,000) ድረስ ያለ ከመቀጠር የሚገኝ ወርሀዊ ገቢ ከግብር ነፃ እንዲሆን ተደርጓል። በተጨማሪም ከፍተኛው የማስከፈያ ምጣኔ የሆነው 35% ከአስር ሺ ዘጠኝ መቶ (10,900) ብር ወርሃዊ ገቢ ጀምሮ ይጣል የነበረ ሲሆን በማሻሻያ አዋጁ ግን ይሄው የ35% ምጣኔ ከአስራ አራት ሺ (14,000) ብር በላይ ወርሀዊ ገቢ ባላቸው ተቀጣሪዎች ላይ ብቻ የሚጣል ይሆናል።
ሌላው በአዋጅ ቁጥር 1395/2017 ማሻሻያ የተደረገው በኪራይ እና ንግድ ሥራ ገቢዎች ምጣኔ ላይ ነው። በቀድሞው የገቢ ግብር አዋጅ (አንቀፅ 14(2)) እና 19(2) መሠረት እስከ ብር ሰባት ሺ ሁለት መቶ (7,200) ድረስ ያሉ አመታዊ የኪራይ እና የንግድ ሥራ ገቢዎች ከግብር ነፃ የነበሩ ሲሆን ይኸው መጠን በማሻሻያ አዋጁ አንቀፅ 2(😎 እና 2(10) መሠረት ማስተካከያ ተደርጎበት ወደ ብር ሃያ አራት ሺ (24,000) አመታዊ የኪራይ እና የንግድ ሥራ ገቢ ከፍ እንዲል ተደርጓል። ከፍተኛው የ35% የግብር ምጣኔ የሚጣልበትን የኪራይ እና የንግድ ሥራ የገቢ መጠን በተመለከተ በማሻሻያ አዋጁ በቀድሞ አዋጅ ከነበረው ከብር አንድ መቶ ሰላሳ ሺ ስምንት መቶ (130,800) በላይ ከፍ በማድረግ ከብር አንድ መቶ ስልሳ ስምንት ሺ (168,000) በላይ አመታዊ ገቢ ላይ እንዲሆን ተደርጓል።
ሌላኛው ከግብር ምጣኔ አንፃር ለውጥ የተደረገው ከዕድል ሙከራ በሚገኙ ገቢዎች ላይ ነው። ቀደም ሲል ከዕድል ሙከራዎች ገቢ ያገኘ ሰው የገቢውን 15% (አስራ አምስት በመቶ) ግብር እንዲከፍል የሚደረግ ሲሆን (አዋጅ ቁጥር 979/2008 አንቀፅ 57(1)፤ በማሻሻያ አዋጁ አንቀጽ 2(22) መሰረት ከዕድል ጨዋታ ገቢ ያገኘ ሰው ከገቢው ላይ 20% (ሃያ በመቶ) ግብር መክፈል ይጠበቅበታል። ነገር ግን ይሄ የግብር መጠን በዕድል ሙከራ ከአንድ ሺ ብር በታች ባገኘ ሰው ላይ አይጣልም።
 የግብር ከፋይ ደረጃዎች
ሌላኛው በማሻሻያ አዋጁ ለውጥ ከተደረገባቸው ነጥቦች መካከል አንዱ የግብር ከፋይ ደረጃዎችን የተመለከተው ነው። በቀድሞው የገቢ ግብር አዋጅ 979/2008 አንቀፅ 3 መሠረት የደረጃ “ሀ”፣ “ለ” እና “ሐ” በሚል በሶስት የግብር ከፋይ ደረጃዎች ከፋፍሎ ያስቀመጣቸው ሲሆን ክፍፍሉም ጠቅላላ አመታዊ ገቢን ታሳቢ ያረገ ነው። በዚህም መሰረት ድርጅት ወይም ጠቅላላ አመታዊ ገቢው ብር አንድ ሚሊዮን (1,000,000) ወይም ከዚያ በላይ የሆነ ማንኛውም ሰው በደረጃ “ሀ” ስር የሚመደብ ሲሆን፣ ከብር አንድ ሚሊዮን (1,000,000) በታች እና ከብር አምስት መቶ ሺ (500,000) በላይ አመታዊ ገቢ ያላቸው (ድርጅቶችን ሳይጨምር) ደግሞ ደረጃ “ለ” ስር ይጠቃለላሉ። ድርጅትን ሳይጨምር አመታዊ ጠቅላላ ገቢው ከብር አምስት መቶ ሺ (500,000) በታች የሆኑ ግብር ከፋዮች በደረጃ “ሐ” ስር ይመደባሉ።
ነገር ግን በማሻሻያ አዋጁ አንቀፅ 2(2) መሠረት በሶስት ደረጃዎች የመክፈሉ ሂደት ቀርቶ የግብር ከፋዮች ደረጃ “ሀ” እና “ለ” በሚሉ ሁለት ደረጃዎች ብቻ እንዲከፈል ተደርጓል። ከአመታዊ ገቢ ምጣኔውም አንፃር ቀደም ሲል የነበረው እንዲሻሻል ተደርጎ በደረጃ “ሀ” ስር የሚወድቁ ግብር ከፋዮች ድርጅቶች ወይም ጠቅላላ አመታዊ ገቢያቸው ከብር ሁለት ሚሊዮን (2,000,000) እና በላይ የሆኑ ሌሎች ሰዎች ሲሆኑ ከዚህ መጠን በታች የሆነ ጠቅላላ አመታዊ ገቢ ያላቸው ሰዎች (ድርጅቶችን ሳይጨምር) በደረጃ “ለ” ስር እንዲመደቡ ተደርጓል።
 የገቢ ምንጭ (የታክስ መሰረት) ማስፋት
የገቢ ግብር ማሻሻያ አዋጁ በቀድሞው አዋጅ ያልነበረ አዲስ የግብር ምንጭ አካቶ የወጣ ነው። ይኸውም በማሻሻያ አዋጁ ላይ ከዲጂታል ይዘት ፈጠራ የሚገኝ ገቢም ግብር እንደሚከፈልበት በግልፅ ተደንግጓል። በገቢ ግብር የማሻሻያ አዋጅ አንቀፅ 2(1) መሰረት ከዲጂታል ይዘት ፈጠራ የሚገኝ ገቢ ማለት አንድ ግለሰብ ወይም ድርጅት የቪዲዮ ማጋሪያ አገልግልቶችን፣ የማኅበራዊ ሚዲያ መድረኮችን፣ የድምጽ ማስተላለፊያ (ፖድካስት) አገልግሎቶችን እና የቀጥታ ስርጭት መድረኮችን ጨምሮ በኦንላይን (በበይነ መረብ) መድረኮች ላይ ዲጂታል ይዘትን በመፍጠር እና በማሰራጨት የሚያገኘው ማንኛውም በገንዘብ ወይም በአይነት የሚገኝ ገቢ ነው። ይህም ከማስታወቂያዎች እና ስፖንሰርሺፖች፣ ከምርት ስም ስምምነቶች እና ድጋፎች፣ ከአጋርነት ግብይት እና የምርት ምደባዎች፣ ከደጋፊዎች አስተዋጽኦ፣ ከገንዘብ ስጦታዎች ወይም የብዙሃን የገንዘብ ማሰባሰብ (ክራውድ ፈንዲንግ)፣ ከአባልነት ክፍያዎች፣ ከዲጂታል ወይም ከአካላዊ ሸቀጦች ሽያጭ፣ ከማስተዋወቂያ እንቅስቃሴ ምትክ የተገኙ ዕቃዎች ወይም አገልግልቶች እና ተመሳሳይነት ያላቸው ሌሎች ክፍያዎችን ያካትታል፡፡ በዚህም መሠረት በኢትዮጵያ ነዋሪ ወይም ነዋሪ ያልሆነ ሰው በኢትዮጵያ ውስጥ የዲጂታል አገልግሎት በመስጠት ከሚያገኘው ገቢ 5% የማይበልጥ የገቢ ግብር እንደሚከፍል በአዋጅ አንቀጽ 2(17 ተደንግጓል)። የዲጂታል አገልግሎት ምንነትን በተመለከተ፣ የማስከፈያ ምጣኔ፣ የአከፋፈል ሁኔታ እና ሌሎች ተያያዥነት ዝርዝር ጉዳዮችን በተመለከተ የሚንስትሮች ምክር ቤት በሚያወጣው ደንብ መሠረት የሚወሰን ስለመሆኑ በማሻሻያ አዋጁ ተጠቅሷል።
ከዲጂታል ይዘት ፈጠራ ሥራው ትርፍ ለማግኘት ታስቦ በመደበኛነት የሚከናወን ከሆነ፣ ፈጣሪው ድርጅት ከሆነ፣ የሂሳብ መዝገብ የሚያዝ ከሆነ ወይም ከንግድ ጋር የተያያዙ ወጪዎች ተቀናሽ የሚደረጉለት ከሆነ የሚገኘው ገቢ እንደ ንግድ ሥራ ገቢ እንደሚቆጠር ከማሻሻያ አዋጁ አንቀጽ 2(11) መረዳ ይቻላል፡፡ ከእነዚህ ሁኔታዎች ውጭ ከዲጂታል ይዘት ፈጠራ የሚገኙ ገቢዎች እንደሌላ ገቢ ተቆጥረው በአዋጁ ሠንጠረዥ “መ” መሠረት ግብር የሚጣልባው ሲሆን ዝርዝር አፈፃፀሙም በሚኒስትሮች ምክር ቤት በሚወጣ ደንብ መሠረት የሚወሰን ይሆናል። ስለሆነም የዲጂታል ይዘት አመንጪዎች እንደማንኛውም ግብር ከፋይ ሁሉ መለያ ቁጥር የማውጣት፣ ገቢን የማስታወቅ እና ሌሎችም የታክስ ከፋዮች ግዴታዎች ይኖሩባቸዋል ማለት ነው።
 አማራጭ አነስተኛ ግብር
የገቢ ግብር ማሻሻያ አዋጅ ካካተታቸው አዳዲስ ጉዳዮች አንዱ አማራጭ አነስተኛ የግብር ሥርአት ነው። ግብር ከፋዮች ምንም አልሰራንም (ገቢ አላገኘንም) ወይም ስለከሰርን ግብር ልንከፈል አይገባም በማለት ማስታወቅ የተለመደ ነገር ሲሆን በሌላ በኩል ደግሞ ማናቸውም በንግድ ሥራ ላይ የተሰማራ ሰው ለአመታት በኪሳራ ሊቀጥል እንደማይችል ግልፅ ነው። ይህም ግብር ሳይከፍሉ ገቢ በሚያስገኝ ሥራ ላይ የተሰማሩ ሰዎች ሊኖሩ እንደሚችሉ ያስገንዘበናል። ከዚሁ መነሻ ከግብር ለመሸሽ ኪሳራ የሚያስታውቁ ትክክለኛውን ግብር እንዲከፍሉ፣ በትክክል ኪሳራ ያጋጠማቸው ደግሞ መክሰራቸው ሲረጋገጥ የከፈሉት ግብር እንዲካካስ ለማስቻል ሲባል አማራጭ አነስተኛ የግብር ሥርአት እንዲካተት ተደርጓል።
አማራጭ አነስተኛ የግብር ምጣኔን በተመለከተ በአዋጅ ቁጥር 1395/2017 አንቀፅ 2(11) መሠረት ማናቸውም ድርጅት ወይም ሰው ግብር በሚወሰንበት የግብር አመት ከሁሉም የንግድ ሥራ የገቢ ምንጮች ባገኘው ትርፍ ላይ ሊከፍል የሚገባው ግብር በዚሁ የግብር አመት ካገኘው ጠቅላላ ገቢ ከ2.5% (ከሁለት ነጥብ አምስት በመቶ) በታች ከሆነ በአዋጁ በተመለከተው የማስከፈያ ምጣኔ መሠረት አማራጭ አነስተኛ ግብር መክፈል እንደሚኖርበት ተደንግጓል።
 በጥሬ ገንዘብ የሚደረግ ግብይት ላይ የተደረገ ገደብ
ሌላኛው የተሻሻለው የገቢ ግብር አዋጅ ይዞት የመጣው ጉዳይ በጥሬ ገንዘቦች የሚደረጉ ግብይቶች ላይ ገደብ ማበጀት ነው። በጥሬ ገንዘብ የሚደረግ ግብይት ስለግብር ከፋዩ ግብይት በቂ መረጃ እንዳይኖር በማድረግ ለታክስ መሰወር ድርጊት በር ከፋች ይሆናል። ይህንንም ለመቀነስ እንዲያስችል ማናቸውም ግብር ከፋይ ወደ ባንክ ሂሳብ ገቢ በሚደረግ ቼክ፣ ወደ ባንክ ሂሳብ ገቢ በሚደረግ የባንክ ድራፍት፣ ከባንክ ሂሳብ ወደ ባንክ ሂሳብ ገንዘብ በማስተላለፍ ወይም በኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ፈቃድ በተሰጣቸው የክፍያ መፈጸሚያ መንገዶች ካልሆነ በስተቀር በአንድ ቀን ውስጥ ከአንድ ሰው ጋር በተደረገ ጠቅላላ ግብይት ወይም ከአንድ ግብይት ጋር በተያያዘ የሚፈጸም ክፍያ ወይም ከአንድ ሰው ጋር ከተፈጸመ አንድ ግብይት ወይም ተግባር ጋር የተያያዘ ክፍያ/ግብይቶች ከሃምሳ ሺ (50,000) ብር በላይ በጥሬ ገንዘብ መቀበል አይቻልም። ነገር ግን ይህ ገደብ በመንግሥት መስሪያ ቤቶች፣ በመንግሥት የልማት ድርጅቶች፣ በባንኮች እና በማይክሮ ፋይናንስ ድርጅቶች እንዲሁም የገንዘብ ሚኒስቴር በሚያወጣው መመሪያ መሠረት በተለዩ ሰዎች ወይም ድርጅቶች ላይ ተፈፃሚ እንደማይሆን ከማሻሻያ አዋጁ አንቀፅ 2(28) ድንጋጌ መረዳት ይቻላል።
ማጠቃለያ
በአጠቃላይ የገቢ ግብር ማሻሻያ አዋጅ ቁጥር 1395/2017 ከላይ የተጠቀሱትን ዋና ዋና ማሻሻያዎች ጨምሮ ገቢ ስለሚጣመርበት ሁኔታ፣ ግብር ቀደም ብሎ የሚከፈልበትን አሰራር እና ሌሎች ማሻሻያዎችን አካቶ ወደ ሥራ የገባ ሕግ ነው። ምንጭ የፍትሕ ሚኒስቴር
ታማኝ ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት የቢሮውን ማኅበራዊ ሚዲያ ማስፈንጠሪያ ይጠቀሙ እናመሰግናለን!!
ዌብሳይት:- aabof.com.et
ፌስቡክ:-https://www.facebook.com/aabof.gov.et?mibextid=ZbWKwL
ቴሌግራም:- https://t.me/AACABOFP
ዩቲዩብ:- youtube.com/channel/UCTPN7Re7T7tp_ekAhVuw2uA
ዋትሳፕ:-https://chat.whatsapp.com/FLSn12vRmsR9JsKUVDWxgtuuuu

Elite Domain Hub@EliteDomainHub🌐 http://AABOF.COM – Short, versatile brandable domain for global business or tech. https://godaddy.com/forsale/aabof.com… :44 AM · Oct 13, 2025·12 Views

18/12/2025
HOW TO AUDIT A HOTEL BUSINESS1. UNDERSTAND Nature THE OF THE HOTEL BUSINESS Before beginning the audit, understand the h...
22/11/2025

HOW TO AUDIT A HOTEL BUSINESS

1. UNDERSTAND Nature THE OF THE HOTEL BUSINESS

Before beginning the audit, understand the hotel’s structure:

🏨 Number of rooms and categories (standard, deluxe, suite, etc.)
🏨 Ancillary services: bar, restaurant, laundry, event hall, car hire, pool, spa
🏨 Pricing structure: room rates, discounts, commissions
🏨 Staff strength and departments
🏨 Payment methods: cash, POS, transfer, online booking platforms

2. START WITH A PRELIMINARY RISK ASSESSMENT

Identify common risk areas such as:

🏨Revenue leakage from unrecorded room bookings or bar sales
🏨Cash theft by front desk or bar staff
🏨Ghost staff on payroll
🏨Suppliers' overbilling
🏨Unauthorized complimentary services
🏨No stock-taking or stock shrinkage

Ask:
🏨Is the hotel owner actively involved?
🏨Is there an accounting system in place (manual or digital like QuickBooks)?
🏨Are there internal controls (daily reports, stock cards, POS vs cash reconciliations)?

3. ROOM REVENUE AUDIT
This is usually the major income stream.

Steps:
🏨Get the room occupancy report for your audit period.
🏨Get the room rate card (official prices).
🏨Reconcile rooms booked × rate = Expected revenue.
🏨Compare with actual revenue recorded.
🏨Verify discounts, complimentary, or free rooms — ensure they were authorized.
🏨Trace bookings from source: logbook, booking platforms (e.g., Booking.com, Jumia Travel), or front desk system.

Red Flags:
🏨Rooms showing occupied but no matching payment.
🏨Manual logbook that doesn’t reconcile with cash collected.
🏨Frequent ‘complimentary’ rooms with no written authorization.

4. RESTAURANT & BAR SALES AUDIT
Food & beverage can leak significantly if not controlled.

Steps:
🏨Check daily sales summary reports.
🏨Compare with POS or manual sales records.
🏨Confirm menu prices are consistent and adhered to.
🏨Reconcile stock movement (e.g., crates of drinks in vs sold).
🏨Watch out for "cash sales not remitted" or "unrecorded direct sales."

Tip: Use stock cards for popular items (e.g., beer, spirits, bottled water, rice, chicken, oil).

Red Flags:
🏨Frequent stock-outs with low sales reported.
🏨Bar staff bypassing POS.
🏨Multiple refunds or voided transactions.

5. EVENT HALL & OTHER SERVICES AUDIT

Review:
🏨Booking register
🏨Receipts issued
🏨Deposit and balance payments
🏨Event hall agreements
Compare expected vs actual income.

6. EXPENSES AUDIT
Common issues: inflated expenses, fictitious purchases, or personal expenses disguised as business costs.

Steps:
🏨Review all expenses for the period.
🏨Check supporting documents: invoices, receipts.
🏨Match purchases to suppliers.
For recurrent expenses (e.g., diesel, foodstuffs), test for reasonableness.
Identify cash withdrawals and trace use.

Red Flags:
🏨No receipts for large cash expenses.
🏨Staff using personal vendors for kickbacks.
🏨Repeated diesel purchases without generator log.

7. PAYROLL & STAFF AUDIT

Steps:
🏨 Obtain payroll list and compare with actual staff on ground.
🏨 Match payments to bank statements or salary vouchers.
🏨Watch for ghost workers, double payments, or inflated salaries.
🏨 Check for proper deductions (PAYE, pensions).

Red Flags:
🏨Ex-staff still being paid.
🏨Cash salary payments with no records.

8. STOCKAND INVENTORY AUDIT
Stock issues are very common especially in the kitchen and bar.

What you should do:
🏨Take physical stock count of major items: drinks, food, toiletries, linen.
🏨Compare with purchase records.
🏨Look for discrepancies in kitchen ingredient usage vs meals sold.

Red Flags:
🏨Stewards/kitchen staff taking stock home.
🏨No proper record of food items or laundry stock.

9. CASH AND BANK RECONCILIATION

Match income from sales with:
🏨Bank deposits
🏨POS settlements
🏨Cash in hand
Do daily reconciliations to spot gaps.

Red Flags:
🏨Delayed banking of cash.
🏨POS payments not hitting the hotel account.
🏨Staff collecting transfers to personal accounts.

10. REVIEW of INTERNAL CONTROLS

Ask:
🏨Is there a segregation of duties (e.g., cashier ≠ accountant)?
🏨Are daily cash reports prepared?
🏨Is stock counted and signed off regularly?
🏨Is there CCTV monitoring at key points (e.g., reception, bar, store)?

Recommendations:
🏨Introduce shift handover reports.
🏨Use POS and accounting software for transparency.
🏨Train staff on fraud risks.

Kindly share this post if you found it valuable. 😊

To your continuous success,

Whether you’re looking for hotels, homes, or vacation rentals, you’ll always find the guaranteed best price. Browse our 2,563,380 accommodations in over 85,000 destinations.

12/11/2025
በኢትዮጵያ ፍ/ር ሕግ መሠረት የውል መፍረስ (invalidations) እና ውል መሠረዝ(Cancelation ) የዳኝነት ጥያቄ እና መሠረታዊ ሀሳቦች  ጠበቃና የህግ አማካሪ ፋንታሁን ደለለው 0...
12/11/2025

በኢትዮጵያ ፍ/ር ሕግ መሠረት የውል መፍረስ (invalidations) እና ውል መሠረዝ(Cancelation ) የዳኝነት ጥያቄ እና መሠረታዊ ሀሳቦች

ጠበቃና የህግ አማካሪ ፋንታሁን ደለለው 0929101037/0983337690
መግቢያ
| በፍ/ር ህጋችን የውል ግዴታ ቀሪ የሚሆኑባቸው የተለያዩ መንገዶች ሲኖሩ ከእነዚህም ሁለቱ የሆኑትን ውል መፍረስ እና ውል መሠረዝን በተመለከተ ምን ማለት እንደሆኑ፣ መሠረታዊ ልዩነታቸውን እና አንድነታቸውን በመለየት ግንዛቤ ለማስጨበጥ እንሞክራለን።

1. የውል አመሰራረት(Establishment of contract)...
ውል በሁለት ተዋዋይ ወገኖች መካከል በገዛ ፍቃዳቸው ማንም ሳያስገድዳቸው ለመዋዋል በህግ ችሎታ በተሰጣቸው ሰወች(በህግ እና በተፈጥሮ) መካከል የህጉን ውለታ በሚጠይቀው መንገድ ተገቢውን ህጋዊ የፎርም አቀራረጽ በመከተል ህጋዊ እና ሊፈጸም በሚችል መልኩ ስምምነት ሊደረግ የሚችል ነው። የፍ/ር ህግ 1676

2. ውል የሚካሄድባቸው ዘዴዎች(means of contract agreement) ...
ውል በዋናነት በጹሁፍ ወይም በቃል ሊደረግ የሚችል ሲሆን እዚህ ላይ ሊታሰብ የሚገባው ነገር ግን ውሉ ሊደረግ የሚችልበትን መንገድ የውሉ አቀራረጽ በህጉ ልዩ ፎርም ሊከተል የሚገባ መሆኑን ህጉ ሲያስገድድ ተዋዋይ ወገኖች የግድ ያንን በህግ የተጣለባቸውን ስረአት ሊከተሉ ያስፈልጋል።

3. ውል መሠረዝ(cancelation of contract) የፍ/ህግ 1808 ፥1815/1/፥1817/1/ እና 2 ....
በተዋዋይ ወገኖች መካከል የተደረጉ የሚጸኑ ውሎች በተዋዋይ ወገኖች መካከል እንደ ህግ ተደርጎ ሊቆጠር የሚችል መሆኑን በፍ/ር ህግ ቁጥር 1731 ላይ ተደንጎግ የተቀመጠ ነው። ይሁን እንጂ በውል አለመፈጸም ወይም አፈጻጸም ችግር ምክንያት በአንድኛው ተዋዋይ የአፈጻጸም ቸልተኝነት ወይም ጉድለት ምክንያት በሌላይኛው ወገን ላይ በመዘግየት ወይም ከውሉ ስምምነት ውጭ አካሄድ ምክንያት የከፋ ውጤት እየተከተለበት ስለመሆኑ ሲረዳ የውል ይሰረዝልኝ ጥያቄ በፍ/ር ህግ ቁጥር 1771 መሠረት ሊያቀርብ ይችላል። ይህን ተከትሎ የውል መሠረዝ ስረአት ሊፈጸም ይችላል ማለት ነው።

ከዚህ የምንረዳው ውልን በሚጸና መንገድ ተዋዋይ ወገኖች ካደረጉ በኋላ በውሉ አፈጻጸም ጉድለት ምክንያት ውሉ ቀሪ የሚሆንበት መንገድ ሲሆን በዚህ ምክንያት በውሉ አፈጻጸም ችግር ምክንያት ተጎጂ ነኝ ውሉ ሊሰረዝ ይገባል የሚለው አካል ዳኝነት ስልጣን ባለው ፍርድ ቤት በመጠየቅ ውሉ እንዲሰረዝለት መጠየቅ ይችላል።

እዚህ ላይ ጠያቂው ወሉን ተገዶ ሌላይኛው ወገን ከሚፈጽም ይልቅ መሠረዙ ምክንያታዊ እና ውጤታማ ስለመሆኑ ተገቢወውን ጥናት ሊያደርግ ያስፈልጋል። የፌ/ጠ/ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት 248670 ይመልከቱት።

4. ውል መፍረስ(invalidation) የፍ/ር ህግ 1815/1/ 1817(
ውል ከመሠረቱ አራት በውል ውስጥ መካተት የሚገባቸውን መሠረታዊ ነገሮች በሟሟላት ሊመሠረት የሚገባ እንደሆነ በህግ ቁጥር 1676 ላይ የተቀመጠ ነው።

እነዚህ
4.1 ፈቃድ ሲሆን ...
ይህ ያለ ማንም አሰገዳጅነት ተዋዋይ ወገኖች ነጻ ሆነው ስምምነት የሚፈጽሙበት ነው።

4.2 የህግ ችሎታ ...
:- ይህ ተዋዋይ ወገኖች ውልን ለመዋዋል የሚያስችል ስልጣን ሊኖራቸው የሚችል መሆኑን የሚያሳይ ሲሆን በእድሜ ለምሳሌ ከ18 በላይ መሆኑ በህግ በተለየ ሁኔታ ካልተደነገገ በቀር እድሜ 18 እና ከዚያ በላይ መሆኑ፣ይህን ለማድረግ የህግ ወይም የፍርድ ክልከላ የሌለበት ስለመሆኑ በአጠቃላይ ይህን የውል ስምምነት ለማድረግ በህግ ሙሉ ስልጣን ያለው ስለመሆኑ ሊረጋገጥ የሚገባ ነው።

4.3.የውለታው ጉዳይ(Subject matter) ...
ይህ የውለታው ጉዳይ ፍሬ ነገሩ ሲሆን ይህም ህጋዊ እና ሊፈጸም የሚችል መሆን አለበት።

4.4. የውሉ አቀራረጽ(form) ...
የፍ/ህግ ቁጥር 1808(2) ሲሆን ህጉ የተለየ የውል አቀራረጽ ፣ በውለታው ጉዳይ የተነሳ እንዲደረግ ባዘዘ ጊዜ ያንን የውል አቀራረጽ ወይም ፎርም ተዋዋይ ሊከተሉ የሚገባ ነው።
ወደ እዚህ አርእስ ዋና ነጥብ ስንመጣ ከእነዚህ መሠረታዊ ነጥቦች የተነሳ ውሉ ቀሪ እንዲሆን የሚያበቃውን ጉድለት የተፈጸመበት እንደሆነ የውል መፍረስ ስረአት ጥያቄ የሚከተል እና የሚፈጸም ይሆናል።

5. መሠረታዊ አንድነታቸው...
ሁለቱም ውሉ ቀሪ የሚሆኑበት ስረአቶች ሲሆኑ ይህም ሲሆን ወደ ነበሩበት የሚመለሱበት ነው። እንዲሁም ሁለቱም የይርጋ ጊዜያቸው ይለያይ እንጂ በይርጋ ቀሪ ሊሆኑ የሚችሉ ነው። የውል ይሠረዝልኝ ጥያቄ በአስር አመት በፍ/ር ህግ ቁጥር 1845 መሠረት የሚቀርብ ሲሆን እንደ የውል ልዩ ባህርያት ደግሞ የራሳቸው የይርጋ ጊዜ ተቀምጧል።

6. ውሉ ህገወጥ ከሆነስ...
ውሉ ህገወጥ ከሆነ ከጅምሩ ውል እንዳልነበረ የሚታሰብ ሲሆን ከውል ይፍረስልኝ ወይም ይሰረዝልኝ ጥያቄ ይልቅ ተዋዋዩ ወገን በተሳሳተ ህገወጥ በሆነ ውል ምክንያት ያጣውን የተወሰደበትን ኪሳራ ገንዘብ ንብረት ወይም ሌላ መብት ከውል ውጭ እንዲመለስለት መጠየቅ ነው።

7. ህጉ ከሚጠይቀው የውል አቀራረጽ(ፎርም) ውጭ ከሆነስ...
እንዲህም በሆነ ጊዜ ህጉ የሚጠይቀውን ፎርማሊቲ ያላሟላ በመሆኑና ይህም ከህጉ አለማ ውጭ ህግ ያልተከተለ በመሆኑ ውል እንደተደረገ (Void) የሚያስቆጥረው ባለመሆኑ በዚህ ምክንያት ተገጂ የሆነ አካል ውልን መሠረት አድርጎ ሳይሆን ከውል ውጭ የተወሰደበት፣የተገዳው ነገር ካለ እንዲመለስ ወይም እንዲካስ የመጠየቅ መብት አለው።

8. ሲጠቃላል...
የውል መፍረስና መሰረስ ባህርያት የውል ግዴታን ቀሪ የሚያደርጉ ሲሆን የውል መፈረስ መሠረታዊ የውል አመሠራረቶች ላይ ሊሟሉ የሚገባቸው ነጥቦች ባለመሟላታቸው የተነሳ የሚከሰት ሲሆን ውል መሠረዝ በተዋዋይ ወገኖች መካከል የሚጸና ውል ከተደረገ በኋላ ከአፈጻጸም ጉድለት የሚከሰት ነው።

ፋንታሁን ደለለው ( ጠበቃና የህግ አማካሪ)
https://www.facebook.com

🇪🇹 Ethiopia’s New Income Tax Amendment – Proclamation No. 1395/2017Ethiopia has made important changes to the Income Tax...
26/10/2025

🇪🇹 Ethiopia’s New Income Tax Amendment – Proclamation No. 1395/2017

Ethiopia has made important changes to the Income Tax law (Proclamation 979/2016).
The new amendment 1395/2017 started in July 2025.

Here are the main changes everyone should know:-

1) Digital business tax – Income from online services (like YouTube, apps, websites, cloud, and streaming) will now be taxed in Ethiopia.
2)Minimum tax – Even if a business shows a loss, it must pay 2.5 % of annual sales as minimum tax.
3) Cash rule – Any payment over 50,000 birr made in cash cannot be used as an expense for tax purposes.

4) Higher withholding taxes –
• Dividend = 15 %
• Interest = 10 %
• Undistributed profit = 15 %
• Repatriated profit = 15 %

5) Purchase tax (WHT) – Local withholding tax increased from 2 % to 3 %.
Starts from 10,000 birr for services and 20,000 birr for goods.

6) Salary tax updated – The first 2,000 birr per month is now tax-free, and new salary brackets apply.

7) Foreign companies – A foreign business working in Ethiopia for more than 91 days in 12 months is now taxable.

8) Group companies – Dividends between related companies (same owner ≥ 50 %) are now tax-free.

Solomon Eshete FCCA
Principal – Solomon Eshete Certified Audit Firm
“Helping Ethiopian businesses stay compliant and informed.”

17/09/2025

Can 2025 Tax Law Apply to 2017? No!

Business owners often ask: “Can Proclamation 1395/2025 be used for 2017 taxes?” The answer is NO. Here’s why:

Law Timing Matters: The 2025 law starts from July 2025. It cannot change past years.

2017 Law Applies: For 2017, only Proclamation 979/2016 rules are valid.

2.5% Sales Tax: The 2025 rule cannot be applied retroactively. The tax authority cannot charge 2.5% sales tax for 2017 transactions.

Bottom line: Always follow the law that was in effect during the tax period. Past taxes cannot be changed by new laws.

22/08/2025

ለግንዛቤዎት!
========
ግብር ከፋይ በሀሰተኛ ደረሰኞች እንዳይጭበረበር ሊያከናውነው የሚገባ የጥንቃቄ ተግባራት
#የሚፈጽማቸውን ማናቸውም ግዥዎች የግብር ከፋዩ ስም፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር፣ ብሔራዊ መታወቂያ ትክክል መሆኑን በማረጋገጥ ከታወቀ የንግድ አድራሻ ግብይት መፈጸሙን ማረጋገጥ ፤
#አቅራቢው ወይም ሻጭ ግብር ከፋይ መለያ ቁጥር በመጠቀም ከንግድ በይነ መረብ https://etrade.gov.et/ ለሚጸመው ግዥ የንግድ ምዝገባና ፈቃድ መኖሩንና የታደሰ መሆኑን ማረጋገጥ የግብይት ደረሰኙ በተገለጸው አድራሻ ከግብር ከፋዩ ወይም ህጋዊ ተወካዩ በቀጥታ በአድራሻው በመገኘት መቀበል ፤
#ግብር ከፋዩ ክፍያ ከመፈጸሙ በፊት ለግብይቱ የተሰጠው የሽያጭ መመዝገቢያ ማሽን ደረሰኝ ህጋዊ እና ስራ ላይ ያለ ስለመሆኑ የማሽኑን መለያ ቁጥር/MRC/ በመጠቀም TASS http://www.erca.gov.et:8001/tass/ ሥርዓት ውስጥ በማስገባት በማረጋገጥ ክፍያውን መፈጸም
#ግብር ከፋዩ ክፍያ ከመፈጸሙ በፊት ለግብይቱ የተሰጠው የማንዋል ደረሰኝ ከሆነ ህጋዊ እና ስራ ላይ ያለ ግብር ከፋይ ስለመሆኑ የደረሰኙን መለያ ቁጥር/QR CODE/ በመጠቀም በማስገባት እና በማረጋገጥ ክፍያውን መፈጸም ፤
#የሚፈጽማቸውን ማናቸውንም የግዥዎች በህግ ከተገደበው የገንዘብ መጠን በላይ ሲሆን ክፍያውን ከላይ በተገለጸው የአቅራቢ ስም በተከፈተ የባንክ ሂሳብ በማስላለፍ ማስረጃ መያዝ፤
#በቋሚነት የሚፈጽማቸው የግብይት ውሎች አቅራቢው ቢያንስ የታደሰ ፍቃድ ያለው፣ ከ2 ወር ላልበለጠ ጊዜ ታክሱን ያላሳወቀ መሆኑን እና በተገለጸው አድራሻ የሚገኝ መሆኑን ማስረጃ በማረጋገጥ ውል መፈጸም ከውል በፊት ግብር ከፋዩ የአቅራቢውን ሕጋዊነት ለማረጋገጥ የሚያቀርባቸው ጥያቄውን ለግብር አወሳሰን እና ታክስ መረጃ ሥራ ክፍል በማቅረብ ማስረጃ መያዝ ፤
#ከውል በኃላ አቅራቢው ታክስ ግዴታው እየተወጣ መሆኑን በየወሩ በማረጋገጥ ቀጣይ ግብይት ወይም ክፍያ መፈጸም ይኖርበታል፡፡ ግዴታውን እየተወጣ ካልሆነ ለባለስልጣኑ ማሳወቅ ፤
#ከላይ በዝርዝር የተገለጹ ቅድመ ጥንቃቄዎችን በማሞላት የተፈጸመ ግብይት ቢሆንም ሻጭ ግብር ከፋዩ ግዴታውን ሳይወጣ ከተገኘ ግብር ከፋዩ አድራሻውን እና ሌሎች ግብር ከፋዩን የሚመለከቱ መረጃዎች እና ማስረጃዎች በመስጠት በመጠቆም መተበባር ፤

21/08/2025

Address

Addis Ababa
31003

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Solomon Eshete & Co. posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Solomon Eshete & Co.:

Share