Commercial Bank of Ethiopia

Commercial Bank of Ethiopia The history of Commercial Bank of Ethiopia (CBE) dates back to the establishment of the State Bank of Ethiopia in 1942.
(846)

The Commercial Bank of Ethiopia, founded in 1942, is the nation's foremost bank and the first to introduce modern banking services, with over 1,971 branches and service outlets nationwide. CBE was legally established as a share company in 1963. Since then, it has been playing significant roles in the development of the country. Currently CBE has more than 41+ million account holders in its more th

an 1900 branches and the number of Mobile and Internet Banking users also reached more than 6 million and 39K. Active ATM card holders reached more than 8.8 million and 17 million CBE Birr users.

ማስተርካርድ ለዓለም አቀፍ ክፍያዎ!  ******* ወደ ውጭ ሀገራት ለሚያደርጉት ጉዞማስተርካርድዎን በሚቀርብዎት ቅርንጫፍ ይዘዙ፣የትም ሆነው ክፍያዎን በቀላሉ ይፈፅሙ!Experience Seam...
06/06/2026

ማስተርካርድ ለዓለም አቀፍ ክፍያዎ!
*******
ወደ ውጭ ሀገራት ለሚያደርጉት ጉዞ
ማስተርካርድዎን በሚቀርብዎት ቅርንጫፍ ይዘዙ፣
የትም ሆነው ክፍያዎን በቀላሉ ይፈፅሙ!

Experience Seamless Global Payments with Your CBE MasterCard!
*******
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ
ሁሌም የሚተማመኑበት ባንክ!

06/06/2026

ከዕለት ዕለት ሸመታዎ እስከ ትልልቅ ግብይትዎ
በሲቢኢ ፖስ!
****
በግብይት እና በአገልግሎት መስጫ ስፍራዎች ጥሬ ገንዘብ መያዝ ሳይጠበቅብዎ
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክን የክፍያ መፈፀሚያ ማሽኖች (ፖስ) በመጠቀም በቀን

👉 በመደበኛ ካርድዎ እስከ 500 ሺ ብር
👉 በጎልድ ካርድዎ እስከ 700 ሺ ብር
👉 በፕላቲኒየም ካርድዎ እስከ 1 ሚሊዮን ብር ግብይት መፈፀም ይችላሉ!

✅ ልብ ይበሉ፡

በካርድዎ ሲከፍሉ የፖስ ማሽኑ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ መሆኑን ያስተውሉ፤
የግብይት መጠኑ ሳይዘገይ ከሂሳብዎ ስለሚቀነስ፣ ቀሪ ሂሳብዎን በትክክል ያውቃሉ!
****
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ
ሁሌም የሚተማመኑበት ባንክ!

ተጨማሪ ጉርሻ ያግኙ! ****ውድ ደንበኞቻችን፡ከውጭ ሀገራት በ   ፣   ፣   ፣   ፣   ፣   ፣   ፣     ፣    ፣   እና   ዲጂታል የገንዘብ መላኪያ መተግበሪያዎች ገንዘብ ሲላክል...
06/06/2026

ተጨማሪ ጉርሻ ያግኙ!
****
ውድ ደንበኞቻችን፡

ከውጭ ሀገራት በ ፣ ፣ ፣ ፣ ፣ ፣ ፣ ፣ ፣ እና ዲጂታል የገንዘብ መላኪያ መተግበሪያዎች ገንዘብ ሲላክልዎ በእለታዊ የውጭ ምንዛሬ የመሸጫ ተመን ላይ ተጨማሪ 10 በመቶ ጉርሻ፤

እንዲሁም ከባንካችን ጋር በሚሠሩ ዓለም አቀፍ የሐዋላ አስተላላፊዎች በኩል ገንዘብ ሲላክልዎ በእለታዊ የውጭ ምንዛሬ የመሸጫ ተመን ላይ ተጨማሪ 9 በመቶ ጉርሻ የምናበረክትልዎ መሆኑን በደስታ እንገልፃለን!

***
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ
ሁሌም የሚተማመኑበት ባንክ!

For more currency exchange rates:
https://combanketh.et/exchange-rates?srcPage=home


combanketh.et

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ለክቡራን የፌደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ዳኞች ፣ ለፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ዳኞች እና አቃብያነ ህግ በዲጂታል ባንኪንግ ስለሚፈፀሙ ወንጀሎች እና ወንጀሎቹን ለመከላ...
05/06/2026

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ለክቡራን የፌደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ዳኞች ፣ ለፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ዳኞች እና አቃብያነ ህግ በዲጂታል ባንኪንግ ስለሚፈፀሙ ወንጀሎች እና ወንጀሎቹን ለመከላከል እና ለመቆጣጠር በሚያስችሉ ሁኔታዎች ላይ የምክክር መድረክ አዘጋጅቷል
==================
ባንካችን ለፌደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት እና ለፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ዳኞች እና አቃብያነ ህግ በዲጂታል ባንኪንግ አገልግሎት ላይ የሚፈፀሙ የማጭበርበር ስልቶችንና ወንጀሎችን በጋራ ለመከላከል የሚያስችል የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ አዘጋጅቷል።

በመድረኩ ላይ የባንካችን ፕሬዚዳንት አቶ አቤ ሳኖን በመወከል ንግግር ያደረጉት የባንካችን የኮርፖሬት አገልግሎቶች ኤክስኪዩቲቭ ም/ፕሬዚዳንት አቶ ኤፍሬም መኩሪያ በአለም አቀፍ ደረጃ የባንክ ኢንደስትሪው ተቀያያሪና ፈጣን ለውጥ ባስመዘገበ ቁጥር በዘርፉ ላይ የሚያጋጥሙ የማጭበርበር ተግባራትና ወንጀሎችም እያደጉ መምጣታቸውን አንስተዋል።

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የዲጂታል ባንክ አገልግሎትም በፍጥነት እያደገ መምጣቱን አቶ ኤፍሬም ገልፀው በዚሁ ልክ በአገልግሎቱ ላይ የሚቃጡ ማጭበርበሮችና ወንጀሎችም እያደጉ በመሆኑ የመከላከል ስራ ለመስራት ከህግ ተርጎሚ አካላት ጋር በቅርበት መስራትና ስለአገልግሎቱ በቂ ግንዛቤ መስጠት አስፈላጊ መሆኑን ተናግረዋል።

የፌደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ፕሬዚዳንት ወ/ሮ ሌሊሴ ደሳለኝም የዲጂታል ባንኪንግ አገልግሎቶችን መጠቀም እጅግ አስፈላጊና የግድ እየሆነ ቢመጣም በዘርፉ የሚፈፀሙ ወንጀሎች ከሀብት ስርቆት ባለፈ በተቋማት ላይ ያለን እምነት፣የህግ የበላይነትንና የሀገርን ህልውናን ጥያቄ ውስጥ የሚከቱ እየሆኑ መምጣታቸውን ገልፀዋል።

እነዚህን ወንጀሎች ለመከላከል፣ ለመመርመርና ፍትሃዊ ዳኝነት ለመስጠትም የፍትህ አካላትና የፋይናንስ ተቋማት ተቀራርበው መስራትና በቂ ግንዛቤ መፈጠር እንዳለበት ወ/ሮ ሌሊሴ ገልፀዋል።

የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ፕሬዚዳንት አቶ ፉዓድ ኪያር በበኩላቸው በሀገረ መንግስት ግንባታ ውስጥ የህግ ተርጓሚው አካል ያለውን ሚና በማንሳት ሚናውን ለመወጣት የፋይናንስ አሰራርና ስርዓቶችን በውል መረዳት አስፈላጊ ነው ብለዋል።

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ያዘጋጀው የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክም ይህን የሚያጠናክር እንደሆነ ገልፀዋል።

በውጭ ሀገራት የሚኖሩ ደንበኞች የባንክ ሂሳብን ከፋይዳ መታወቂያ ጋር ማጣመርን በተመለከተ********የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ባወጣው መመሪያ መሠረት በዋና ዋና ከተሞች በሚገኙ የባንካችን ቅ...
05/06/2026

በውጭ ሀገራት የሚኖሩ ደንበኞች የባንክ ሂሳብን ከፋይዳ መታወቂያ ጋር ማጣመርን በተመለከተ
********
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ባወጣው መመሪያ መሠረት በዋና ዋና ከተሞች በሚገኙ የባንካችን ቅርንጫፎች የተከፈቱ የባንክ ሂሳቦች ባለቤቶች የሆኑና እስከ ግንቦት 6 ቀን 2018 ዓ.ም ከፋይዳ መታወቂያ ጋር ሳያጣምሩ የቀሩ ደንበኞች በቀጣይ እስኪያጣምሩ ሂሳባቸው በጊዜያዊነት እንዳይንቀሳቀስ መደረጉ ይታወቃል።

ከዚህ ጋር በተያያዘ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ መኖሪያቸውን ከኢትዮጵያ ውጭ ያደረጉ ደንበኞች የባንክ ሂሳባቸውን ከፋይዳ መታወቂያ ጋር ማጣመር ሳያስፈልጋቸው በጊዜያዊነት በልዩ ሁኔታ መስተናገድ የሚችሉበትን አሠራር ዘርግቷል።

በዚህ መሠረት ከዚህ በፊት ሂሳብ በሚከፍቱበት ወቅት የመኖሪያ አድራሻቸው ከኢትዮጵያ ውጭ እንደሆነ በባንካችን የመረጃ ቋት የተመዘገበ ማስረጃ ያቀረቡ ደንበኞች ሂሳብ ያልታገደ መሆኑን እያሳወቅን፤ በተለያየ ምክንያት ውጭ ሀገር እንደሚኖሩ በባንካችን የመረጃ ቋት ላይ ያላስመዘገቡ እና የባንክ ሂሳባቸው የታገደባቸው ደንበኞች ከዚህ በታች በተገለፀው አግባብ መስተናገድ የሚችሉ መሆኑን እንገልፃለን፡

1. ከኢትዮጵያ ውጭ መኖራቸውን የሚገልፅ ማስረጃ ለምሳሌ - የትምህርት ማስረጃ፣ የህክምና ማስረጃ፣ የውጭ ሀገር መንጃ ፈቃድ፣ ከውጭ ሀገር የተሰጠ ውክልና፣ የመኖሪያ ፈቃድ (የሎው ካርድ)፣ የሥራ ፈቃድ ወይም ሀገር ውስጥ እያሉ የተሰጠ ውክልና ሆኖ ነገር ግን ውክልናው ላይ ውጭ ሀገር መኖራቸውን የሚገልፅ ሀሳብ ካለ በህጋዊ መኪሎቻቸው አማካኝነት በማቅረብ እግዱን ማስለቀቅ ይችላሉ፤

2. ዲፕሎማቶች የዲፕሎማቲክ ማህበረሰብ መታወቂያቸውን በማሳየት ወይም ሂሳቡ የተከፈተው በዲፕሎማት መታወቂያ ከሆነ እግዱ ተነስቶላቸው ሂሳባቸውን ማንቀሳቀስ ይችላሉ፤

3. ደንበኛው በውጭ ሀገር እንደሚኖር የሚያረጋግጥ የኢሜይል መልእክት በኢምባሲ/ቆንስላ በኩል ከመጣ እግዱ በጊዜያዊነት ተነስቶላቸው መሰተናገድ ይችላሉ፤

4. በተጨማሪም ደንበኞች በውጭ ሀገር መኖራቸውን ሊያስረዱ የሚችሉ ማስረጃዎችን በቀጥታ የባንክ ሂሳቡ በተከፈተበት ቅርንጫፍ ሥራ አስኪያጅ የኢ-ሜል አድራሻ ወይም በዲያስፖራ ባንኪንግ ክፍል የኢ-ሜል አድራሻ [email protected] በመላክ እግዱን በጊዜያዊነት ማስነሳት ይችላሉ።
*****
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ
ሁሌም የሚተማመኑበት ባንክ!

ራስዎን ከአጭበርባሪዎች ለመከላከል ይህን ያድርጉ!  ******•  ከባንክ ነው በሚል የሚደርስዎትን የስልክ ጥሪ ትክክለኛነት ወደ ባንካችን ቅርንጫፍ በመሄድ ወይም ወደ 951 በመደወል ሳያረጋ...
05/06/2026

ራስዎን ከአጭበርባሪዎች ለመከላከል ይህን ያድርጉ!
******
• ከባንክ ነው በሚል የሚደርስዎትን የስልክ ጥሪ ትክክለኛነት ወደ ባንካችን ቅርንጫፍ በመሄድ ወይም ወደ 951 በመደወል ሳያረጋግጡ ምንም ዓይነት እርምጃ አይውሰዱ፣
• የባንክ መረጃዎን በስልክ ለማንም አይስጡ፣
• የባንኩን መተግበሪያዎች (Apps) ከ Play Store እና App Store ብቻ አውርደው ይጠቀሙ፣
• የዲጂታል የባንክ አገልግሎት የሚስጥር ቁጥርዎን ለማንም አያሳውቁ፤ ሞባይል ስልክዎ ላይ ወይም ማንኛውም ነገር ላይ አይፃፉ፣ ጠንካራ የሚስጥር ቁጥር ይጠቀሙ፣
• ከማህበራዊ ሚዲያ ጓደኛ የሚመጣን የእርዳታ ጥሪ በጥንቃቄ ይፈትሹ፣
• በሌላ ሰው ተጠልፈው ሊሆን ይችላል እና በዲጂታል የመልእክት መለዋወጫ ዘዴዎች ከሚያውቁት ሰውም ቢሆን የሚደርስዎትን የገንዘብ ላክልኝ ጥያቄ ስልክ ደውለው ሳያረጋግጡ ምላሽ አይስጡ፣
• ከማይታወቁ ምንጮች የሚያገኟቸውን ማስፈንጠሪያዎች (Links) አይክፈቱ፣
• መረጃ ለማግኘት የባንካችንን ቅርንጫፎች፣ ወደ 951 በመደወል እና ትክክለኛ የባንካችንን የማህበራዊ ትስስር ገፆች ይጠቀሙ፡፡
*******
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ
ሁሌም የሚተማመኑበት ባንክ!

ሀገርዎ ላይ ንብረት እንዲያፈሩ እናግዝዎት! **********በውጭ ሀገራት የምትኖሩ ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ሀገርዎ ላይ ንብረት እንዲያፈሩ እኛ እናግዝዎታለን!!እርስዎ ከ10...
05/06/2026

ሀገርዎ ላይ ንብረት እንዲያፈሩ እናግዝዎት!
**********
በውጭ ሀገራት የምትኖሩ ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ሀገርዎ ላይ ንብረት እንዲያፈሩ እኛ እናግዝዎታለን!!

እርስዎ ከ10 እስከ 70 በመቶ ሲቆጥቡ፣ እኛ ቀሪውን

• ለቤት መግዣ/ መሥሪያ
• ለአውቶሞቢል መግዣ
• ለግል ጉዳይ
• ለኢንቨስትመንት
በረዥም ጊዜ በተመጣጣኝ ወለድ እናበድርዎታለን!

የዳያስፖራ የቤት መግዣ/መሥሪያ ብድር ቁጠባ ሂሳብ በ unite.et መተግበሪያ፣
ባሉበት ሀገር በሚገኝ የኢትዮጵያ ኢምባሲ በኩል፣ አሊያም
ሀገር ቤት ባለ ህጋዊ ወኪልዎ አማካኝነት መክፈት ይችላሉ!

አገልግሎቱን በሲቢኢ ኑር ከወለድ ነፃ የባንክ አገልግሎትም ማግኘት ይቻላል።

ለበለጠ መረጃ
ለኮንቬንሽናል- https://combanketh.et/cbe-for-you/diaspora-accounts
ከወለድ ነፃ ተጠቃሚዎች- https://combanketh.et/cbe-for-you/cbenoor-diaspora-accounts

****
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ
ሁሌም የሚተማመኑበት ባንክ!

05/06/2026

ለተሻለ ነገ...
የሲቢኢ ኑር የትምህርት ቁጠባ ሂሳብ
***********
የርስዎንም ሆነ የልጆችዎን የከፍተኛ ትምህርት ወጪ ለመሸፈን
የትምህርት ቁጠባ ሒሳብ ተጠቃሚ ይሁኑ!

በወዲዓህ ወይም
በሙዷራባህ (70 በመቶ ትርፍ የሚያጋራ) አማራጮች
ሂሳቡን መክፈት ይችላሉ!

ጁምዓ ሙባረክ!
********
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ
ሁሌም የሚተማመኑበት ባንክ!

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እና የኢትዮጵያ አየር መንገድ  አዲስ የቪዛ ዓለም አቀፍ የቅድመ ክፍያ ካርድ ይፋ አደረጉ**** ማምሻውን በስካይ ላይት ሆቴል በተዘጋጀ መርሀ ግብር የኢትዮጵያ ንግድ ...
04/06/2026

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እና የኢትዮጵያ አየር መንገድ አዲስ የቪዛ ዓለም አቀፍ የቅድመ ክፍያ ካርድ ይፋ አደረጉ
****
ማምሻውን በስካይ ላይት ሆቴል በተዘጋጀ መርሀ ግብር የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እና የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከቪዛ ኩባንያ ጋር በመተባበር ይፋ ያደረጉት የክፍያ ካርድ ደንበኞች በውጭ ሀገራት ቆይታቸው በቀላሉ ክፍያ እንዲፈጽሙ የሚያስችል ነው።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ የሼባ ማይልስ አባላት የሆኑ መንገደኞች በሚደርሱበት ማንኛውም የዓለም መዳረሻ ካርዱን በሽያጭ መፈጸሚያ ማሽን (POS) ወይም ለኦንላይን ግብይት በሚጠቀሙበት ጊዜ ተጨማሪ የጉዞ ማይል ሽልማት እንደሚያስገኝላቸው ታውቋል፡፡

በመርሐ ግብሩ ላይ በመገኘት ንግግር ያደረጉት የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የኮርፖሬት አገልግሎቶች ኤክዝኪዩቲቭ ምክትል ፕሬዚደንት አቶ ኤፍሬም መኩሪያ ባንኩ አዳዲስ የዲጂታል አገልግሎቶችን በማቅረብ እና በማስተዋወቅ የደንበኞቹን ፍላጎት ለማሟላት ጠንክሮ እየሰራ ነው ብለዋል።

ዛሬ በይፋ የተጀመረው ዓለም አቀፍ የቪዛ ካርድ አገልግሎት የባንካችን እና የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ አብሮ የማደግ ፍላጎት አንድ ማረጋገጫ ነው ሲሉ አቶ ኤፍሬም ተናግረዋል።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ የንግድ ዘርፍ ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ ለማ ያዴቻ በበኩላቸው አዲስ የተጀመረው የቪዛ ካርድ አገልግሎት ለሼባ ማይልስ አባል ደንበኞች ዓለም አቀፍ የክፍያ አገልግሎቶችን ከመስጠት ባሻገር ተጨማሪ ጥቅሞችን እንደሚያስገኝ ተናግረውል።

በቪዛ የምስራቅ አፍሪካ ክላስተር ኃላፊ እና በኢትዮጵያ ሥራ አስኪያጅ የሆኑት አቶ ያሬድ እንዳለ የሀገር ኩራት የሆኑት ሁለቱ ተቋማት የሚያደርጉት ትብብር የደንበኞችን ፍላጎት የሚያሟላ እና የሥራውን ጥራት ወደ ከፍተኛ ደረጃ የሚያሸጋግር መሆኑን ተናግረዋል።

Address

Ras Desta Damtew St, P.O.Box 255
Addis Ababa
+251 11 300 0000

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Commercial Bank of Ethiopia posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Commercial Bank of Ethiopia:

Share