Commercial Bank of Ethiopia Trade Union

Commercial Bank of Ethiopia Trade Union ማኅበሩ የተመሠረተበት ዓመት :- ታኅሣስ 2 /1960 ዓ ም
የአባላት ብዛት:- ከ 35,000 በላይ

ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮችእንኳን ለ1447ኛዉ ኢድ አል-አድሃ (አረፋ) በዓል በሰላም አደረሳችሁ!*******  ኢድ ሙባረክ!የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሠራተኞች ማሕበርበአንድነት ለተሻለ...
26/05/2026

ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች
እንኳን ለ1447ኛዉ ኢድ አል-አድሃ (አረፋ) በዓል በሰላም አደረሳችሁ!
*******

ኢድ ሙባረክ!

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሠራተኞች ማሕበር
በአንድነት ለተሻለ ህይወት እንተጋለን!

Telegram https://t.me/CBETUOfficial
Facebook https://www.facebook.com/TradeUnion2018
Website https://cbetradeunion.org
ስልክ ቁጥር፡- +251111130294 / 0906570000

በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ምስራቅ ሪጅን ደማቅ ስፖርታዊ ፌስቲቫል ተካሄደ*****የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ምስራቅ ሪጅን መቀመጫ በሆነችዉ  አዳማ ከተማ “አብሮነታችን ለጤናችን እና ለባንካችን ስኬ...
25/05/2026

በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ምስራቅ ሪጅን ደማቅ ስፖርታዊ ፌስቲቫል ተካሄደ

*****

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ምስራቅ ሪጅን መቀመጫ በሆነችዉ አዳማ ከተማ “አብሮነታችን ለጤናችን እና ለባንካችን ስኬት “በሚል መሪ ቃል ግንቦት 16 ቀን 2018 ዓ.ም በሪጅኑ ስር በታቀፋ ዲስትሪክቶች ሠራተኞች በጋራ ተካሂዷል፡፡

‎በፌስትቫሉም የባንካችን ምስራቅ ሪጅን ምክትል ፕሬዝደንት አቶ መሃመድ ከዲሮ ፤ የአዳማ ከተማ ስፖርትና ወጣቶች ቢሮ ሃላፊ አቶ ፋፋ ገርማማ ፣ የባንካችን ዳይሬክቴሮች ቦርድ አባል አቶ ኦላኒ ሴቃታ ፣ የማህበራችን ፕሬዝደንት አቶ አበራ ጌታቸዉ ፣ የባንካችን ታለንት አኩዩዝሽን ዳይሬክተርና የዉስጥ ስፖርት የበላይ ጠባቂ ተወካይ አቶ ተካልኝ ቆርቻ እንዲሁም የሪጅን ዳይሬክተሮች እና የዲስትሪክት ዳይሬክተሮች ፣ አቶ ሰይፋ ይርዳዉ የዉስጥ ስፖርት ኮሚቴ ሰብሳቢ እና የዉስጥ ዉድድር ስፖርት ኮሚቴ አባላት ፣ የማህበራችን ስራ አስፈፃሚ እና ኦዲት ኮሚቴ አባላት እና የማሕበራችን ተጠሪ ፅ/ቤት ተወካዮች በተገኙበት ከባንካችን ሠራተኞች እና ቤተሰቦቻቸው ጋር በጋራ ስፖርታዊ እንቅስቃሴ በድምቀት ተከናዉኗል፡፡

በፌስትቫሉም ማስ ስፖርት ፣ የእግር ኳስ ግጥሚያ እንዲሁም 2.5 ኪ.ሜ የሩጫ ውድድር በህፃናት እና በአዋቂዎች በተሰየሙ ምድቦች ተካሄዶ በሩጫዉ ላሸነፉ አሸናፊዎች የሜዳሊያ እና የተሳትፎ የምስክር ወረቀት ከዕለቱ የክብር እንግዶች እጅ ተበርክቶላቸዋል፡፡

‎በመጨረሻም በአዳማ አበባ ቢቂላ ስታዲየም በተደረገ የወንዶች እግር ኳስ ጨዋታ አዳማ ዲስትሪክት አሰላ ዲስትሪክትን 2 ለ 1 በማሸነፍ የዋንጫ ተሸላሚ መሆን ችሏል፡፡

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሠራተኞች ማሕበር
በአንድነት ለተሻለ ህይወት እንተጋለን!

Telegram https://t.me/CBETUOfficial
Facebook https://www.facebook.com/TradeUnion2018
Website https://cbetradeunion.org
ስልክ ቁጥር፡- 0906570000 ዘወትር በሥራ ሰዓት ይደዉሉ

በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ደቡባዊ ሪጅን እና ምዕራብ ሪጅን  ደማቅ ስፖርታዊ ፌስቲቫል ተካሄደ*********ስፖርታዊ ፌስቲቫሉ “አብሮነታችን ለጤናችን እና ለባንካችን ስኬት “በሚል መሪ ቃል በባ...
19/05/2026

በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ደቡባዊ ሪጅን እና ምዕራብ ሪጅን ደማቅ ስፖርታዊ ፌስቲቫል ተካሄደ
*********

ስፖርታዊ ፌስቲቫሉ “አብሮነታችን ለጤናችን እና ለባንካችን ስኬት “በሚል መሪ ቃል በባንካችን ደቡባዊ ሪጅን መቀመጫ በሆነችዉ ሐዋሳ ከተማ እንዲሁም የባንካችን የምዕራብ ሪጅን መቀመጫ በሆነችዉ ጅማ ከተማ ግንቦት 9 ቀን 2018 ዓ.ም በየሪጅኖቹ ስር በታቀፉ ዲስትሪክቶች፣ ሠራተኞች እና የሠራተኞቹ ቤተሰቦቻቸዉ በተገኙበት በድምቀት ተካሂዷል፡፡

በዕለቱም የባንካችን ደቡባዊ ሪጅን ምክትል ፕሬዝደንት አቶ ፍፁም አላሎ እንዲሁም የምዕራብ ሪጅን ምክትል ፕሬዝዳንት ተወካይ አቶ ቶሌራ ፀጋዬ ፤ የሁለቱ ሪጅን ዲስትሪክት ዳይሬክተሮች፣ የማህበራችን ስራ አስፈፃሚዎች ፤ የሰራተኞች ስፖርት ዉድድር አዘጋጅ ኮሚቴዎች እንዲሁም የማሕበራችን ተጠሪ ፅ/ቤት ተወካዮች ተገኝተዉ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡

በፌስትቫሉም የማስ ስፖርት፣ ሩጫ ፣ ገመድ ጉተታ፣ እግር ኳስ እና ሌሎችም ስፖርቶች የተከናወኑ ሲሆን ለአሸናፊዎች የዋንጫ፣ የሜዳሊያ እና የተሳትፎ የምስክር ወረቀት ከእለቱ የክብር እንግዶች እጅ ተበርክቶላቸዋል፡፡

የስፖርት ፌስትቫሉ በቀጣይም በምስራቅ ሪጅን መቀመጫ በሆነችዉ አዳማ ከተማ በደማቅ ሁኔታ የሚከናወን ይሆናል፡፡

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሠራተኞች ማሕበር
በአንድነት ለተሻለ ህይወት እንተጋለን!

Telegram https://t.me/CBETUOfficial
Facebook https://www.facebook.com/TradeUnion2018
Website https://cbetradeunion.org
ስልክ ቁጥር፡- +251111130294 / 0906570000 ዘወትር በሥራ ሰዓት ይደዉሉ፡፡

የቅርንጫፍ ጉብኝት ተካሄደ፡፡************የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሠራተኞች ማሕበር የተጠሪ ፅ/ቤት እና የዋና መስሪያ ቤት ተወካዮች የበጀት ዓመቱን ሁለተኛ ዙር የቅርንጫፍ እና የስራ ክ...
18/05/2026

የቅርንጫፍ ጉብኝት ተካሄደ፡፡

************

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሠራተኞች ማሕበር የተጠሪ ፅ/ቤት እና የዋና መስሪያ ቤት ተወካዮች የበጀት ዓመቱን ሁለተኛ ዙር የቅርንጫፍ እና የስራ ክፍሎች ጉብኝት (የመስክ ምልከታ) ከግንቦት 3 እስከ ግንቦት 8 ቀን 2018 ዓ.ም ድረስ ያካሄዱ ሲሆን በጉብኝቱም ከአባል ሠራተኞች እንዲሁም ከስራ መሪዎች ጋር ሰፊ ዉይይት ተደርጓል።

Telegram https://t.me/CBETUOfficial
Facebook https://www.facebook.com/TradeUnion2018
Website https://cbetradeunion.org
ስልክ ቁጥር፡- +251111130294 / 0906570000 ዘወትር በሥራ ሰዓት ይደዉሉ፡፡

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሻምፒዮን ሆኗል! ===============በ2018 የኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪሚየር ሊግ የመጨረሻ ሳምንት ጨዋታ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ኢትዮ ኤሌክትሪክን በእሙሽ ዳንኤል እ...
17/05/2026

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሻምፒዮን ሆኗል!
===============
በ2018 የኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪሚየር ሊግ የመጨረሻ ሳምንት ጨዋታ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ኢትዮ ኤሌክትሪክን በእሙሽ ዳንኤል እና በረድዔት አስረሳኸኝ ግቦች 2–0 በማሸነፍ በተከታታይ ለ6ኛ ጊዜ እንዲሁም በአጠቃላይ ለ9ኛ ጊዜ የኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪሚየር ሊግ ሻምፒዮን ሆኗል።

እንኳን ደስ አላችሁ እንኳን ደስ አለን!

16/05/2026
በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሰሜን ሪጅን ደማቅ ስፖርታዊ ፌስቲቫል ተካሄደ********በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሰሜን ሪጅን መቀመጫ በሆነችዉ በዉቢቷ ባህር ዳር ከተማ ግንቦት 2 ቀን 2018 ዓ.ም ...
12/05/2026

በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሰሜን ሪጅን ደማቅ ስፖርታዊ ፌስቲቫል ተካሄደ

********

በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሰሜን ሪጅን መቀመጫ በሆነችዉ በዉቢቷ ባህር ዳር ከተማ ግንቦት 2 ቀን 2018 ዓ.ም ታላቅ ስፖርታዊ ፌስትቫል የተካሄደ ሲሆን በፌስትቫሉም በሪጅኑ በሚገኙ ሠራተኞች መካከል የእግር ኳስ፣ የሩጫ እና የማስ ስፖርት እንቅስቃሴ በድምቀት ተከናዉኗል፡፡

የባንካችን የሰሜን ሪጅን ምክትል ፕሬዝዳንት አቶ ሳሙኤል ተስፋሁነኝ በፌስትቫሉ ላይ በመገኘት በባህር ዳር ከተማ ላይ ለመጀመሪያ ጊዜ በተደረገዉ የስፖርት ፈስቲቫል አዘጋጅ ኮሚቴዉ እና ለታዳሚዎች ምስጋና አቅርበዉ ጤናማ እና ዉጤታማ አንድ የባንክ ማህበረሰብ ለመገንባት ባንካችን በተለያየ ደረጃ ስፖርታዊ እንቅስቃሴዎች እንዲኖሩ በሰፊዉ እየሰራበት ነዉ ብለዋል፡፡

የባህር ዳር ዲስትሪክት ዳይሬክተር አቶ ደመዜ ባልቤ በበኩላቸዉ ፌስቲቫሉ ጤንነታችን ከመጠበቅ ባሻገር የባንካችን ሰራተኞች እና የሰራተኛ ቤተሰቦችን በማገናኘት እና በማስተዋወቅ የአብሮነት ፣ የትብብር መንፈስ ለመፍጠር ከፍተኛ ሚና እንዳለዉ እና ለባንካችን ዉጤታማነት የሚያበረክተዉ አስተዋጽዎ ከፍተኛ በመሆኑ ወደፊት ፌስቲቫሉ በተጠናከረ መልኩ መቀጠል እንዲችል በጋራ መሰራት እንደሚኖርበት ገልጸዋል።

የባህርዳር ከተማ አስተዳደር ባህል እና ስፖርት መምሪያ ሃላፊ በመልክታቸዉ ስፖርታዊ እንቅስቃሴ የተሟላ ጤና ከማስገኘቱ ባሻገር ስራችንን በተቀላጠፈ መልኩ በከፍተኛ የስነ ልቦና ዝግጅት እንድናከናዉን ያግዛል ሲሉ ገልጸዋል።

የማሕበራችን ተወካይ አቶ ዮሰን ተሠማ በበኩላቸዉ የባንካችን ሠራተኞች እርስ በርሳቸው እንዲተዋወቁ እና ግንኙነታቸውን እንዲያጠናክሩ በማድረግ፣ የባንካችንን የመሪነት ሚና ማሳየት እና ባንኩን ማስተዋወቅ እንዲሁም ሰራተኞች ጤንነታቸውን እንዲጠብቁ ፣ የቡድን ስራን ይበልጥ እንዲያጎለብት የማድረግ ዓላማ አድርጎ የተዘጋጀ መሆኑን ለዚህም ማሕበራችን ትኩረት አድርጎ እየሠራ መሆኑን ገልፀዋል፡፡ በተጨማሪም የሪጅኑ ሠራተኞች ይህንን የስፖርት እንቅስቃሴ እንደ አጋጣሚ በመጠቀም ባንካችንን በማስተዋወቅ፣ ጤንነታቸዉን በመጠበቅ፣ አንድነታቸዉን በማጠናከር የባንካችንን ትርፋማነት እና እድገት ማስቀጠል እንዳለባቸዉ የአደራ መልክት አስተላልፈዋል፡፡

በዕለቱ ከተደረጉ የተለያዩ ስፖርታዊ እንቅስቃሴዎች ዉስጥ በሪጅኑ ስር ከሚገኙ ዲስትሪክቶች መካከል በባህር ዳር እና በደብረ ማርቆስ ዲስትሪክት መካከል በተደረገዉ የእግር ኳስ ግጥሚያ ደብረ ማርቆስ ዲስትሪክት ባህር ዳር ዲስትሪክትን 3 ለ 2 ማሸነፍ ችሏል፡፡

ይህ የባንካችን ሠራተኞች ስፖርታዊ ፌስትቫል ከአዲስ አበባ ዉጪ ባሉ ሪጅኖች ሲካሄድ የመጀመሪያ ጊዜ ቢሆንም በሠራተኞች መካከል አንድነት እንዲሁም የእርስ በእርስ ትዉዉቅን ለመፍጠር ትልቅ ጠቀሜታ ያለዉ መሆኑን የዉስጥ ስፖርታዊ ዉድድር አዘጋጅ ኮሚቴ ገልጿል፡፡ በመጨረሻም የስፖርት ፌስትቫሉ በቀጣይም በቀሪ ሪጅኖች በድምቀት የሚካሄድ ይሆናል፡፡

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሠራተኞች ማሕበር
በአንድነት ለተሻለ ህይወት እንተጋለን!

Telegram https://t.me/CBETUOfficial
Facebook https://www.facebook.com/TradeUnion2018
Website https://cbetradeunion.org
ስልክ ቁጥር፡- 0906570000 ዘወትር በሥራ ሰዓት
ይደዉሉ

እንኳን ለ85ኛው የአርበኞች የድል በዓል መታሰቢያ በሰላም አደረሳችሁ!የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሠራተኞች ማሕበርበአንድነት ለተሻለ ህይወት እንተጋለን!Telegram https://t.me/CBETU...
05/05/2026

እንኳን ለ85ኛው የአርበኞች የድል በዓል መታሰቢያ በሰላም አደረሳችሁ!

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሠራተኞች ማሕበር
በአንድነት ለተሻለ ህይወት እንተጋለን!

Telegram https://t.me/CBETUOfficial
Facebook https://www.facebook.com/TradeUnion2018
Website https://cbetradeunion.org
ስልክ ቁጥር፡- 0906570000 ዘወትር በሥራ ሰዓት
ይደዉሉ

02/05/2026

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በያዝነው በጀት ዓመት ዘጠኝ ወራት 54.5 ቢሊዮን ብር ያልተጣራ ትርፍ ማስመዝገቡን አስታወቀ ።
*****
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በ2025/26 በጀት ዓመት ዘጠኝ ወራት ውስጥ 54.5 ቢሊዮን ብር ያልተጣራ ትርፍ ማስመዝገቡን የባንካችን ፕሬዚዳንት አቶ አቤ ሳኖ ተናገሩ። የባንካችን የሦስተኛ ሩብ ዓመት የሥራ አፈጻጸሙ በገመገመበት ወቅት አቶ አቤ እንደተናገሩት፣ የባንካችን የሀብት መጠን ወደ 2.87 ትሪሊዮን ብር አድጓል።

በዘጠኙ ወራት ከፍተኛ ገቢ መሰብሰቡን ያነሱት አቶ አቤ ባንካችን ከገቢው ጋር የሚመጣጠን የወጪ አጠቃቀም እንዲኖረው ማድረግ እንደሚገባም አሳስበዋል።

አቶ አቤ በግምገማው ማጠቃለያ ላይ ባስተላለፉት መልዕክት፣ ባንካችን የበጀት ዓመቱን ዕቅድ በስኬት ለማጠናቀቅና ቀጣይነት ያለው ዕድገት ለማስመዝገብ መላው የማኔጅመንት አባላትና ሠራተኞች በተቀናጀ መልኩ ከፍተኛ ርብርብ እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርበዋል።

እንኳን ለዓለም አቀፍ የላብ አደሮች ቀን (ሜይ ዴይ) በሰላም አደረሳችሁ!የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሠራተኞች ማሕበርበአንድነት ለተሻለ ህይወት እንተጋለን!Telegram https://t.me/CBE...
30/04/2026

እንኳን ለዓለም አቀፍ የላብ አደሮች ቀን (ሜይ ዴይ) በሰላም አደረሳችሁ!

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሠራተኞች ማሕበር
በአንድነት ለተሻለ ህይወት እንተጋለን!

Telegram https://t.me/CBETUOfficial
Facebook https://www.facebook.com/TradeUnion2018
Website https://cbetradeunion.org
ስልክ ቁጥር፡- 0906570000 ዘወትር በሥራ ሰዓት
ይደዉሉ

Address

Addis Ababa
2176

Opening Hours

Monday 08:00 - 16:30
Tuesday 08:00 - 16:30
Wednesday 08:00 - 17:00
Thursday 08:00 - 17:00
Friday 08:00 - 16:30
Saturday 08:00 - 18:00

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Commercial Bank of Ethiopia Trade Union posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Commercial Bank of Ethiopia Trade Union:

Share