28/03/2023
የሐዘን መግለጫ
የእናት ባንክ የዳይሬክተሮች ቦርድ፣ የሥራ አመራር አባላትና ሠራተኞች በእማሆይ ፅጌ ማርያም ገብሩ ህልፈተ ህይወት የተሰማንን ጥልቅ ሀዘን እየገለጽን ለቤተሰቦቻቸው፣ ለወዳጅ ዘመድና ለመላው ኢትዮጵያውያን መጽናናትን እንመኛለን።
ቀዳሚ የኢትዮጲያዊ የቫዬሊን እና ፒያኖ አቀናባሪ እማሆይ ፅጌ ማርያም የኢትዮጵያ ክላሲካል ሙዚቃዎች እናት ተብለው ይጠሩ ነበር ፡፡ ባንካችን እማሆይ ፅጌ ማርያም ገብሩ ለማህበረሰቡ ያደረጉትን አሰተዋጽኦ ግምት ውስጥ በማስገባት አዲስ አበባ ሀይሌ ጋርመንት አካባቢ የሚገኘውን ቅርንጫፋችንን በስማቸው መሰየማችን የሚታወስ ነው።
ማን እንደ እናት!