ከ ፋይናንስ አለም / Finance world

ከ ፋይናንስ አለም / Finance world Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from ከ ፋይናንስ አለም / Finance world, Finance, Addis Ababa.

ለበዓለ ትንሳኤ በሰላም አደረሳችሁ እያልኩ በቅርቡ በተሻለ አቀራረብ በድጋሚ እንገናኛለን በድጋሚ መልካም በዓል
05/05/2024

ለበዓለ ትንሳኤ በሰላም አደረሳችሁ እያልኩ በቅርቡ በተሻለ አቀራረብ በድጋሚ እንገናኛለን በድጋሚ መልካም በዓል

Service charge/ የአገልግሎት ክፍያ • ሁሉም የሀገራችን ባንኮች ለደንበኞቻቸው በሚሰጡት መጠነ ሰፊ አገልግሎቶች ለሰጡት አገልግሎት የሚያስከፍሉት የአገልግሎት ታሪፍ ነው። ከነዚህም መ...
22/11/2023

Service charge/ የአገልግሎት ክፍያ

• ሁሉም የሀገራችን ባንኮች ለደንበኞቻቸው በሚሰጡት መጠነ ሰፊ አገልግሎቶች ለሰጡት አገልግሎት የሚያስከፍሉት የአገልግሎት ታሪፍ ነው። ከነዚህም መሐከል የATM አገልግሎት ስንጠቀም፣ Mobile banking transfer ስናደርግ ፣ Bank ststment ስናወጣ እና ተያያዥ አገልግሎቶችን ስናገኝ ባንኩ charge የሚያደርገን የክፍያ ስርዓት ነው።

• ለዛሬ ለመዳሰስ የምንሞክረው በተለምዶ ስሙ RTGS ወይንም ከአንደኛው ባንክ ወደ ሌላኛው ባንክ የሚደረግ የገንዘብ ልውውጥ ላይ የሚጣለውን የ Service charge መጠንን እናያለን።

• RTGS በባንኮች በኩል ያለውን Transaction ከማሳለጡ በተጨማሪ የደንበኞችን ጊዜ ከመቆጠብ አንፃር ጉልህ የሚባል አስተዋጽኦ አበርክቷል። ነገር ግን አብዛኛው ሰው ከግምት ውስጥ ማያስገባው ነገር ቢኖር የ service charge amount ነው። በ RTGS Transaction ወቅት 3 ባለድርሻ አካላት የመሪነቱን ሚና ይወስዳሉ። ከነዚህም መሐከል የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ፣ የሚያስተላልፈው ባንክ እና ገንዘብ የተላለፈላቸው ባንክ ናቸው።

• የ RTGS service charge ታሪፍ አቀማመጥ እምብዛም ግልጽ እና ምክንያታዊነቱም አሳማኝ አደለም። ብሔራዊ ባንክ ከእያንዳንዱ የ RTGS transaction የትኛውንም የገንዘብ መጠን ሊሆን ይችላል ከእያንዳንዱ Transaction 50 (ሃምሣ ) ብር ይቆርጣል ከዚህ በተጨማሪም የሚያስተላልፈው ባንክ 25 ( ሃያ አምስት )ብር በአጠቃላይ 75 ብር Charge ትደረጋላችሁ።

• ለምን??? ለምን መክፈል አስፈለገ ??? አንድ ሰው የራሱን ሀብት በፈለገው ሰአት እና ቦታ ቢያዘዋውር ይህን ያህል የተጋነነ የአገልግሎት ክፍያ ለምን መክፈል አስፈለገ። ብሔራዊ ባንክስ ተሳትፎው እምብዛም ግልጽ ባልሆነበት ሁኔታ በምን የህግ አግባብ ነው ይህን የአገልግሎት ታሪፍ ማግኘት የሚገባው???

Financial literacy እስከሌላችሁ ድረስ የFinance ተቋማት እና የታክስ ህጎች እናንተ ለማደህየት ቆርጠው የተነሱ ናቸዉ ....... ይቀጥላል

27/07/2023
  Business [  ] ይህ ሁለተኛው የቢዝነስ አይነት ሲሆን ይህ የቢዝነስ አይነት ከመጀመሪያው የቢዝነስ መመስረቻ መንገድ ብዙም የተለየ አይደለም። በዚህ የቢዝነስ ስርዓት ውስጥ ሁለት እና...
25/07/2023

Business

[ ] ይህ ሁለተኛው የቢዝነስ አይነት ሲሆን ይህ የቢዝነስ አይነት ከመጀመሪያው የቢዝነስ መመስረቻ መንገድ ብዙም የተለየ አይደለም። በዚህ የቢዝነስ ስርዓት ውስጥ ሁለት እና ከ ሁለት በላይ በሆኑ ሰዎች የሚመሰረት ሲሆን እነዚህም partner በመባል ይታወቃሉ የቢዝነሱ መስራች እና ባለቤት እነሱ ናቸው።

[ ] እነዚህ partner ቢዝነሱን ከመጀመራቸው በፊት partnership agreement ይፈርማሉ። በዚህ ስምምነት ውስጥ የእያንዳንዳቸው partner መብት እና ግዴታ እንዲሁም የትርፍና ኪሳራ ክፍፍልን ግልፅና ቀላል በሆነ ቋንቋ የያዘ ሲሆን ይህም የሆነበት ምክንያት በኅላ ሊፈጠር የሚችለው አለመግባባት ታሳቢ በማድረግ ነው።

[ ] partnership Business ያለው ጠቀሜታ

• partnership business ከ solproprietar Business አንፃር የተሻለ capital መሰብሰብ ይችላል ምክንያቱም ከአንድ ሠው ይልቅ ሁለት ሠው የተሻለ capital raise ማድረግ ስለሚችል ነው።

• የተለያዩ personal skill ያላቸው ግለሰቦች ውህደት ስለሚሆን Effective and efficient resources utilization ያደርጋሉ በዚህም የተነሳ objective በቀላሉ ያሳኩታል።

• የመንግስት ህግና ደምቦች ተግዳሮት አይሆኑም ይህ ማለት ሁለት ሰዎች ከተስማሙ በቀላሉ መመስረት ይችላሉ።

[ ] ይህ በእንዲህ እያለ የተለያዩ እንከኖችን በውስጡ ይዟል ከነዚህም መሐል

• በቢዝነሱ ላይ ለሚወሰኑ የ financial ሆነ Operational ዉሳኔዎች የጋራ የሆነ ስምምነት ያስፈልጋል ስለሆነም አንድ ግለሰብ ይሆናል ብሎ ያመነበትን ውሳኔ ያለ ማንም ጣልቃ ገብነት Exercise ማድረግ አይችልም

• ቢዝነሱ የመቀጠል እና ያለመቀጠል ወይም የ Going concern assumotion የሚወሰነው እንደ አዲስ በሚገቡና በሚወጡት የሚወሰን ነው ሚሆነው።

[ ] ከሞላ ጎደል partnership እንደዚህ ያለውን ፀባይ የተላበሱ ሲሆን ይህ ቢዝነስ በሀገራችን እምብዛም ያልተለመደ እና አስፈላጊነቱም ጎልቶ የማይታይ ነው........

  proprietorship business በቢዝነስ ዓለም ሶስት አይነት የቢዝነስ ማቋቋሚያ መንገዶች አሉ እነዚህም sole proprietorship , partnership እና corporation...
26/05/2023

proprietorship business

በቢዝነስ ዓለም ሶስት አይነት የቢዝነስ ማቋቋሚያ መንገዶች አሉ እነዚህም sole proprietorship , partnership እና corporation ሲሆኑ እነዚህ አንድን ቢዝነስ form ስናደርግ የምንጠቀማቸው ናቸው። ሶስቱም የየራሳቸው የሆነ ባህሪ መስፈር ብሎም የህግ ማዕቀፍ አለባቸው። ለዛሬ የ sole proprietorship business ምንነትን እናያለን።

ይህ የቢዝነስ አይነት በቀላሉ በአንድ የሚመሠረት እንዲሁም በሀገራችን በብዛት የሚተገበር የቢዝነስ አካሄድ ነው ።

sols proprietorship የተለያዩ ጠቀሜታ ያለው ሲሆን ከነዚህም መካከል:

[ ] በቀላሉ መመስረት መቻሉ: እንደዚ አይነት ቢዝነስ በምናቋቁምበት ጊዜ በመንግሥት የተደነገጉት ህግ እና አዋጆች አስቸጋሪ አይደሉም ስለዚህ ማንኛውም ሠው በቀላሉ ሊመሠርተው ይችላል።

[ ] Interest conflict አይኖርም: እንደሚታወቀው የድርጅቱ መስራች አንድ ሰው ስለሆነ በባለቤቶች መሀከል የሚኖር የጥቅም ግጭት አይኖርም።

[ ] tax benefit: ቢዝነሱ በህግ ማቀፍ የሰውነት ከለላ ( legal personality ) ስለሌለው ከ business income tax ነፃ ነው ስለዚህ dual taxation አይኖርም የድርጅቱ ባለቤት ብቻ personal income tax ይከፍላል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ የተለያዩ ክፍተቶች ይስተዋላሉ ከነዚህም መሀከል:

[ ] Limited life: የቢዝነሱ የመቀጠል ያለመቀጠል ሁኔታ የሚወሰነው በባለቤቱ ጤንነት ላይ ነው። ባለቤቱ ከሞት ወይም ከታመመ business የሚሰራ ሰው ስለሌለ ይዘጋል።

[ ] difficult to contribute huge capital: በሀገራችን አባባል ከአንድ ብርቱ ሁለት መዳኒቱ ይባላል።የድርጅቱ ባለቤት ለቢዝነሱ የሚየስፈልገውን ማንኛውንም አይነት capital ከራሱ በማውጣት ይሸፍናል capital sources አንድ ሰው ስለሆነ ብዙ ገንዘብ ለመሰብሰብ አስቸጋሪ ነው ሚሆነው።

[ ] unlimited liability: ቢዝነሱ እዳውን መክፈል ባይችል የቢዝነሱ ባለቤት የሆኑ ንብረቶች ተሸጠው የቢዝነሱን ዕዳ እንዲከፈል ህግ ያስገድደዋል።

[ ] High risk: ማንኛውንም ትርፍ ሆነ ኪሳራ ቢያጋጥመ ሀላፊነት የሚወስደው የድርጅቱ ባለቤት ብቻ ነው ለምሳሌ ቢዝነሱ 100,000 ብር ቢያተርፍ ሙሉ በሙሉ ለባለቤቱ ገቢ ይደረጋል በተመሳሳይ ኪሳራም ሲያጋጥም ሙሉ በሙሉ በባለቤቱ የሚሸፈን ይሆናል።

[ ] እንደዚ አይነቱ ቢዝነስ በሀገራችን በተለምዶ በአከባቢያችን በሚገኙ ሱቆች ላይ ይስተዋላል ። በቀጣይ በ partnership business ላይ እንመለሳለን ቸር ቆዩልኝ.......

✅የወረቀት ገንዘብ ከምን ይሰራል?የብር ኖትን ለመጀመሪያ ጊዜ እ.አ.አ በ1914 ይፋ ያደረገችው እንግሊዝ እንደሆነች ይነገራል፡፡ ይሁን እንጂ አንዳንድ ጥናታዊ ጽሁፎች እንደሚያወሱት ቻይናውያ...
19/05/2023

✅የወረቀት ገንዘብ ከምን ይሰራል?

የብር ኖትን ለመጀመሪያ ጊዜ እ.አ.አ በ1914 ይፋ ያደረገችው እንግሊዝ እንደሆነች ይነገራል፡፡ ይሁን እንጂ አንዳንድ ጥናታዊ ጽሁፎች እንደሚያወሱት ቻይናውያን እ.አ.አ በ900 አካባቢ እንደጀመሩት ታሪክ ይነግረናል፡፡

ለመሆኑ ገንዘብ በኪስዎ ሲይዙ ከምን እንደሚሰራ አስብው ያውቃሉ? አዲስ የብር ኖት በእጅዎ ይዘዉ አሽትተውስ ያውቃሉ? እንግዲያዉስ ያ ሽታ የጥጥ ሽታ ነው፡፡

የብር ኖት ወረቀት በየዕለቱ ከምንጠቀማቸው ወረቀቶች የተለየ ነው፡፡ የብር ወረቀት የሚሰራው ከጥጥ ነው ይህም የሚሆንበት ምክንያት በጣም ረዥም ጊዜ እንዲቆይ እና በቀላሉ እንዳይቀደድ ያደርገዋል:: አንድ የአሜሪካ ዶላር 4000 ጊዜ ያክል ሳይቀደድ መተጣጠፍ ይችላል፡፡ ለመጀመሪያ ጊዜ ወረቀትን ከጥጥ የሰሩትም አሜሪካኖች ናቸው፡፡

የወረቀት ገንዘብ አሰራር ሂደቶች

1. ከፍተኛ መጠን ያለዉን ጥጥ ትልቅ እና ግዙፍ ድስት ዉስጥ በማስገባት በከፍተኛ ሙቀት ውስጥ ለሁለት ሰአት ተጨቁኖ ድስቱ ዉስጥ ይቆያል፡፡ በመቀጠልም ትልቅ የመዋኛ ገንዳ በሚያክል ገንዳ ዉስጥ በማስገባት በዉሃ በጣም ነጭ እና ጽዱ እስከሚሆን ይታጠባል፡፡

2. በመቀጠልም ግዙፍ ማዋሃጃ ዉስጥ ገብቶ ይቦካል ያም ለስላሳ እንዲሆን ያደርገዋል፡፡ በተጨማሪም እንዳይኮረጅና በፎርጂድ እንዳይሰራም ያደርገዋል፡፡

3. በመቀጠል የተቦካው እርጥብ እንዳለ በኖቱ ልክ ሆኖ ይዘጋጃል፤እንደየሃገሩ የኖት መጠኑ ይለያያል፡፡

4. ከዛም ነጩ ወረቀት ቀለም እንዲያገኝ ይደረጋል የኖቶቹም የቁጥር መጠን ይለያል፤ የሃገሩ ስም ይጻፋል፤ፎቶዎችም ይጨመሩበታል፡፡

5. የብር ኖትን ልዩና እንዳይኮረጅ ከሚያደርጉ ዋና ነገሮች የደህንነት ክሮች የሚባሉት ሲሆኑ አብረቅራቂም ናቸው፡፡

እያንዳንዱ ክሮች ላይ ጥቃቅን ቁጥሮች ያሉት ሲሆን የእያንዳንዱ የብር መጠን ላይ ያሉት ቁጥሮች የተለያዩ ናቸው፡፡ እነዚህም ቁጥሮች ትክክለኛን ብር በሚለይ መሳሪያ የሚታዩ ሲሆን ለመኮረጅ የሚሞክሩ ሰዎች ይህንን ቁጥር የሚያሳይ መሳሪያ የላቸዉም፡፡

6. በመቀጠልም ዉሃዊ ምልክቶች ይጨመራሉ ያም ማለት ኖቱ ላይ ያለዉን ስዕል ብርሃን ላይ ሲሆን እንዲታይ የሚያደርገው ምስል ማለት ነው፡፡

7. በመቀጠልም ወረቀቱ እንዲደርቅ ይደረጋል ይህም ለብር ብቻ በተዘጋጀ ምድጃ ዉስጥ ነው፡፡

8. በመቀጠልም ማተሚያው ከብር ላይ ያለዉን እርጥበት ሙሉ በሙሉ በመንቀሳቀስ ያስወግደዋል፡፡

9. በመቀጠልም ገንዘቡ ታትሞ ለሚመለከተው አካል ይደርሳል........ቸር ቆዩልኝ

 #ደሞዛችሁን ምን ያህል ታውቁታላችሁ አሁናዊ የኢትዮጵያ የግብር መጠን (tax rate) በመጠቀም ወርሃዊ ደሞዛችንን በቀላሉ መስራት እንችላለን። ወርሃዊ ገቢ              %      ...
16/05/2023

#ደሞዛችሁን ምን ያህል ታውቁታላችሁ

አሁናዊ የኢትዮጵያ የግብር መጠን (tax rate) በመጠቀም ወርሃዊ ደሞዛችንን በቀላሉ መስራት እንችላለን።

ወርሃዊ ገቢ % ተቀናሽ

0-600 0 0

601-1650 10% 60

1651-3200 15% 142.50

3201 -5250 20% 302.50

5251-7800 25% 565

7801-10,900 30% 955

10,900- በላይ 35% 1500

ለምሳሌ: Mr y የ 7,400 ብር ደሞዝተኛ ሲሆን ግን ይህ 7,400 ሙሉ በሙሉ በእጁ አይደርሰውም የተለያዩ ተቀናሾች ይደረጋሉ ከተቀናሾች ውስጥ ዋነኛውን ቦታ የሚወስደው ግብር ነዉ። ግብርን ከደሞዝ እንዴት ማስላት እንችላለን?

ወርሃዊ ደሞዝ x የግብር መጠን( percent )-ተቀናሽ

7,400 x 25% - 565

= 1,850- 565

=1,285

# ይህ ግን የጡረታ ተቀናሽ እና የተለያዩ ጥቅማጥቅሞችን ያላገናዘበ ነው። በሌላ ምሳሌ እንመለስበታለን......... ቸር ቆዩልኝ

 #ኢትዮጵያ እና የግብር ስርአት ኢትዮጵያ ከቀደምት ጊዚያት ጀምሮ በተለያዪ መንገዶች ስትተገብር ኖራለች። ዘመናዊ የ tax system የጀመረው በአለም ጦርነት ወቅት ሲሆን ይህም ለጦርነት የ...
12/05/2023

#ኢትዮጵያ እና የግብር ስርአት

ኢትዮጵያ ከቀደምት ጊዚያት ጀምሮ በተለያዪ መንገዶች ስትተገብር ኖራለች። ዘመናዊ የ tax system የጀመረው በአለም ጦርነት ወቅት ሲሆን ይህም ለጦርነት የሚውል ገንዘብ አጥሯቸው ስለነበር እሱን በማሰብ ከሀገሪቱ ዜጎች በግዴታ ለመሠብሰብ ታቅዶ ነበር።

በጊዜው ብዙ ተቀባይነት ባያገኝም በኋላ ከሀብታሞች ተሰብስቦ ድሆችን ተጠቃሚ የሚያደርግ አሰራር በሚል በተደረገው ቅስቀሳ በ lower level income በሚገኘው ማህበረሰብ ውስጥ ተቀባይነት አግኝቷል።

# ከፍተኛ ግብር ከፋይ ማን ነው?

በዘመናዊ አለም ውስጥ ለመንግስ እንደ ዋነኛ የገቢ ምንጭ ሆኖ በማገልገል ግብር አይተኬ ሚና ይጫወታል። ግብር ከሠራተኞች ደሞዝ (employee income tax ), ከ businsss ተቋማት ,VAT, በተለያዩ System ከዜጎች በግዴታ የሚሰበሰብበት መንገድ ነው።

አብዛኛው የግብር ገቢ ከሠራተኞች የሚሰበሰብ ነው ይህ ማለት ከሀብታሞች ተሰብስቦ ለድሀው ማህበረሰብ የሚተላለፍ ነው ሚለውን ሀሳብ ከ ፕሮፓጋንዳ የዘለለ እውነታ የለውም። እስቲ በምሳሌ አንመልከት

# እኩል አመታዊ ገቢ የሚያገኙ ደሞዝተኛ Mr x እና business enterprise Y እናነፃፅራቸው

Mr x ዓመታዊ ገቢ 132,000 ወርሃዊ(11,000) tax rate 35% =46,200 -1800(deduction ) ለመንግሥት የሚደርሰው 28,200 ቀሪ 103,800 ዓመታዊ ወጪ 100,00 saving =3,800

Business y ዓመታዊ ገቢ 132,000 ወጪ 100,000 ቀሪ 32,000 tax rate 30%= 9,600 saving = 22,400

በግብር ህግ መሠረት ደሞዝተኞች ወጪ ከማድረጋቸው በፊት ነው ግብር የሚከፍሉት ከዛም የተረፈውን ለወጪ እና ለቁጠባ ይጠቀሙበታል። businsss ተቋማት ግን የፈለገውን ካወጣ በኋላ ከቀሪው ግብር ይከፍላል ለዚህም ነው ከደሞዝተኞች ያነሰ የሚከፍሉት።

በአጠቃላይ የዓለም የፋይናንስ ስርአት በአብዛኛው በሚባል መልኩ ለታችኛው ማህበረሰብ ክፍል ጠቃሚ ሲሆን አይስተዋልም

" ተቀጣሪ ሳይሆን የራሳችሁን business መገንባት ላይ አተኩሩ"

  ክፍል 2  || part 2 BitCoin ለመጀሪያ ጊዜ define የተደረገው 31 October 2008 እ.ኤ.አ ሲሆን bit እና coin ከሚሉ ሁለት ቃላት ነው የተወሰደው shorter co...
22/04/2023

ክፍል 2 || part 2

BitCoin ለመጀሪያ ጊዜ define የተደረገው 31 October 2008 እ.ኤ.አ ሲሆን bit እና coin ከሚሉ ሁለት ቃላት ነው የተወሰደው shorter coin እሚል ይዘትም ነበረው፡፡

➲ የBitcoin አለካክ፡

◽️ Bitcoin Units፦ BTC, XBT አርገን በአጭሩ መፃፍ ይቻላል፡፡
Millibitcoin እንዲሁም satoshi (sat) bitcoin በሰራው ስም የተሰየው እነዚህ የ Bitcoin ትንንሽ unit ሲሆኑ
1 satoshi = 0.00000001 bitcoin
1 millibitcoin = 0.001 bitcoin ነው፡፡

🆔 የ bitcoin Domain name "bitcoin.org"18 August 2008G.Cተመዘገበ፡፡
⛏⛏ bitcoin ለመጀመሪያ ጊዜ mine ያረገው እራሱ satoshi nakomoto ሲሆን ለመጀመሪያ ጊዜ 🛄 bitcoin የተቀበለው ወይም የመጀመሪያውን transaction የፈፀመው cypherpunk Hal finney ይህ ሰው የመጀመሪያውን reusable proof of work system (RPOW)creator በ2004 G.cfinney የ bitcoin software download አደረገ በመቀጠልም ከ nakomoto 10 bitcoin ተቀበለ ከሱ በመቀጠል wei dai የ bitcoin predecessor b-money creator እና Nick szabo,creator of bitcoin predecessor bit gold እነዚህ የ bitcoin transaction ለመጀመሪያ ጊዜ የፈፀሙ ሰዎች ናቸው፡፡

🔊🔉 Nakomoto 1 million bit coin እንዳለው ይፋ አርጓል ፡፡

✅Block chain public ledger ሲሆን የተለያዩ transactionኖች ሲፈፀሙ record ያደርጋል ይህን የሚያደርገው ደግሞ Network communicating node በመጠቀም ነው፡፡

🌐 network node transaction ሲፈፀም validate በማድረግ ወደ ሌላ network node ያስተላልፋል፡፡ በዚህም block chain ተግባራዊ ይደረጋል፡፡

💢 በአጭሩ block chain distributed database system ሲሆን ይህም centralized የሆነውነ ስርአት ይቀይረዋል አንድ ሰው ሳይሆን ብዙ ሰው እንዲቆጣጠረው ያረጋል ይህ ጥቅሙ ገንዘብ በአንድ ሰው እንዳይጭበረበር ይረዳል፡፡

🔄 transaction ማለት በአጭሩ ግብይት ማረግ ወይም ገንዘብ መለዋወጥ ማለት ነው፡፡

🆔 ownership በ block chain system bitcoin በ bitcoin address ይመዘገባል፡፡ እናም አንድ ሰው የ bitcoin address ሲኖረው 2 key 🔑 ይሰጠዋል
እነሱም፦ public and private key ናቸው፡፡

👩‍👩‍👧‍👧👨‍👨‍👧‍👦 public key 🔑 ማለት አንድ ሰው bitcoin ሊልክልን ሲፈልግ የምንሰጠው የ account መለያ ቁጥር ማለት ነው፡፡ ለምሳሌ እኛ አንድ ሰው በ Facebook friend request ሊልክልን ሲፈልግ የምንሰጠው መለያ የሆነውን አድራሻ ነው እንጂ password አይደለም ያ መለያ አድራሻችን public key ብለን እንውሰደው፡፡

Address

Addis Ababa

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when ከ ፋይናንስ አለም / Finance world posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share

Category