Abay Stock Market

Abay Stock Market Abay Axion
የአትራፊ ባንኮችን፣ኢንሹራንሶችንና ሌሎች አክሲዮኖችን እናሻሽጣለን።
0940599595
0911248597

Abay Computers and Tech Solutions,
We are Are Importer and Whole Sellers of:
🖥 Desktop Computers
🖨 Office printers
💻 Laptop Computers
📲 0940599595
📲 0911248597
🌐 https://www.abaytechsolutions.com/

31/01/2026
Special FX Auction Notice!
26/12/2025

Special FX Auction Notice!

የዳሽን ባንክ አክስዮን ማህበር የምዝገባ ማስታወቂያ*****************************************በሰነደ ሙአለ ንዋይን ለህዝብ የማቅረብ እና ግብይት መመሪያ ቁጥር 1031/...
25/12/2025

የዳሽን ባንክ አክስዮን ማህበር የምዝገባ ማስታወቂያ
*****************************************
በሰነደ ሙአለ ንዋይን ለህዝብ የማቅረብ እና ግብይት መመሪያ ቁጥር 1031/2016 አንቀጽ 4 እና 29 ላይ በመመሪያው ወይም በካፒታል ገበያ አዋጅ ቁጥር 1248/2013 ከምዝገባ ነጻ ከተደረጉ ውጪ ያሉ ለህዝብ የሚቀርቡ ወይም የሚሸጡ ሰነደ ሙአለ ንዋዮች በኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ ባለስልጣን መመዝገብ ያለባቸው በመሆኑ እና መመሪያው ከመውጣቱ በፊት በህዝብ የተያዙ ሰነደ ሙአለ ንዋዮችም ባለስልጣኑ መመዝገብ ያለባቸው መሆኑ ተደንግጎ ይገኛል፡፡

በዚህም መሰረት ባለስልጣኑ በታህሳስ 15 ቀን 2018 ዓ.ም. የዳሽን ባንክ አክስዮን ማህበርን የምዝገባ መግለጫ ያጸደቀ ሲሆን በዚህም መሰረት፡

➡️ በነባር ባለአክስዮኖች ተይዘው ያሉ አስራ አራት ሚሊዮን ሶስት መቶ ሰላሳ ሰባት ሺህ (14,337,000) አክስዮኖችን፤ እንዲሁም

➡️ በያዙት አክስዮን ድርሻ ልክ ለነባር ባለአክስዮኖች እና/ወይም ነባር ባለአክስዮኖች ሳይገዙ ከቀሩ ለብቁ ኢንቨስተሮች/ ለህዝብ የሚቀርቡ ሁለት ሚሊየን ሁለት መቶ ስድስት ሺህ ዘጠኝ መቶ ስድስት (2,206,906) አክስዮኖችን የመዘገበ መሆኑን ለህብረተሰቡ ለማሳወቅ ይወዳል፡፡
ማሣሠቢያ:

ማስታወቂያው ሰነደ ሙአለ ንዋይ ለመሸጥ ወይም እንዲሸጡ ለማድረግ የቀረበ ጥሪ አለመሆኑ፤
ይህ ማስታወቂያ የወጣው ሰነደ ሙአለ ንዋዮች በባለስልጣኑ መመዝገባቸውን ለሕዝብ ለማሳወቅ ብቻ ሲሆን፤ ማንኛውንም ሰነደ ሙአለ ንዋዮች ለመሸጥ የቀረበ ጥያቄ ወይም እንዲሸጡ ለማድረግ የቀረበ ጥሪ ወይም ማስታወቂያ አይደለም።

በኢትዮጵያ ኢንሹራንስ ኢንዱስትሪው ውስጥ በርካታ ተግዳሮቶች ቢኖሩም፣ ሕብረት ኢንሹራንስ አ.ማ. በተጠናቀቀው በ2017 በጀት ዓመት ከግብር በፊት ከ1 ቢሊዮን ብር በላይ ትርፍ ማስመዝገቡን አ...
04/12/2025

በኢትዮጵያ ኢንሹራንስ ኢንዱስትሪው ውስጥ በርካታ ተግዳሮቶች ቢኖሩም፣ ሕብረት ኢንሹራንስ አ.ማ. በተጠናቀቀው በ2017 በጀት ዓመት ከግብር በፊት ከ1 ቢሊዮን ብር በላይ ትርፍ ማስመዝገቡን አስታውቋል።
#ካፒታል #ጋዜጣ

የዚህ የበጀት ዓመቱ አፈፃፀም ኩባንያዉ በታሪኩ የመጀመሪያው በቢሊዮን የሚቆጠር ትርፍ ያስመዘገበበት እንደሆነ አስታውቋል። ይህ የተነገረው ሕብረት ኢንሹራንስ ዛሬ ባካሄደው 31ኛ መደበኛ የባለአክሲዮኖች ጠቅላላ ጉባኤ ላይ ነዉ።

ኩባንያው ያስመዘገበው ይህ ስኬት ባለፈው ዓመት (በ2016) ከተመዘገበው 563 ሚሊዮን ብር ያልተጣራ ትርፍ ጋር ሲነፃፀር በ79.04% ጭማሪ ማሳየቱ ተመላክቷል።

ኩባንያው ከግብር በኋላ ያገኘው የተጣራ ትርፍም ብር 843 ሚሊዮን የደረሰ ሲሆን፣ ይህም አምና ከተገኘው ብር 470.955 ሚሊዮን ጋር ሲወዳደር የ79.03% ዕድገት ማስመዝገቡን በዓመታዊ ሪፖርቱ በዝርዝር አስቀምጧል።

የሕብረት ኢንሹራንስ የዳይሬክተሮች ቦርድ ሊቀመንበር የሆኑት አቶ ወንደሰን ተሾመ የ2017 በጀት ዓመት ሪፖርት ባቀረቡበት ወቅት እንደተናገሩት፣ ኩባንያው ከሕይወት ነክ፣ ሕይወት ነክ ካልሆነው (Non-Life) እና ከጀነራል ታካፉል የኢንሹራንስ ዘርፎች የሰበሰበው አጠቃላይ አረቦን ብር 2.75 ቢሊዮን ሆኗል።

ይህም አምና ከነበረው ብር 1.96 ቢሊዮን ጋር ሲነፃፀር የ40.31% ጠንካራ ዕድገት ማስመዝገቡን ሊቀመንበሩ ጠቁመዋል።

ከተሰበሰበው ጠቅላላ የአርቦን መጠን ዉስጥ 2.57 ቢሊዮን የሚሆነዉ ሕይወት ነክ ያልሆነ ኢንሹራንስ (Non-Life) ሲሆን ከ ሕይወት ኢንሹራንስ (Life) ደግሞ ከ142 ሚሊዮን ብር ገደማ መሆኑ ተገልጿል።

በተጨማሪም በተጠናቀቀው የበጀት ዓመት ከመድን ሥራ የተገኘው ጠቅላላ ገቢ ብር 2.33 ቢሊዮን የደረሰ ሲሆን ይህም ባለፈው ዓመት ከነበረው ጋር ሲነፃፀር የ32.20% ዕድገት እንዳለው ተመልክቷል።

ሕብረት ኢንሹራንስ ይህን ታሪካዊ ስኬት ያስመዘገበው በኢንሹራንስ ኢንዱስትሪው ውስጥ ያሉ በርካታ ተግዳሮቶችን ተቋቁሞ እንደሆነ የዳይሬክተሮች ቦርድ ሊቀመንበር አቶ ወንደሰን ተሾመ በሪፖርታቸው ገልጸዋል።

በዋናነትም፣ በተሽከርካሪዎች ኢንሹራንስ ላይ ተግባራዊ እየተደረገ ያለው ቁርጥ የዐረቦን ተመን ብሎም በኢንደስትሪው አልፎ አልፎ የሚታየው ስነ ምግባር የጎደለው የንግድ ስራ እንቅስቃሴ በዓመቱ ያጋጠሙ ተጨማሪ ፈተናዎች እንደነበሩ ተናግረዋል።

የሕብረት ኢንሹራንስ የ 2017 በጀት ዓመት ትርፍ 1 ቢሊዮን ብርን ተሻገረ!ድርጅቱ በበጀት ዓመቱ 1.08 ቢሊዮን ብር አትርፏል።ባንኩ በአንድ አክሲዮን 68.56% ትርፍ አስመዝግቧል።
04/12/2025

የሕብረት ኢንሹራንስ የ 2017 በጀት ዓመት ትርፍ 1 ቢሊዮን ብርን ተሻገረ!
ድርጅቱ በበጀት ዓመቱ 1.08 ቢሊዮን ብር አትርፏል።
ባንኩ በአንድ አክሲዮን 68.56% ትርፍ አስመዝግቧል።

አማራ ባንክ ከታክስ በፊት 654 ነጥብ 8 ሚሊየን ብር አተረፈ!*******አዲስ አበባ፣ ሕዳር 20፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) አማራ ባንክ በ2017 በጀት ዓመት ከታክስ በፊት 654 ነጥብ 8 ...
29/11/2025

አማራ ባንክ ከታክስ በፊት 654 ነጥብ 8 ሚሊየን ብር አተረፈ!
*******
አዲስ አበባ፣ ሕዳር 20፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) አማራ ባንክ በ2017 በጀት ዓመት ከታክስ በፊት 654 ነጥብ 8 ሚሊየን ብር ትርፍ አስመዘገበ።
የባንኩ አራተኛ ጠቅላላ መደበኛ ጉባኤ እየተካሄደ ይገኛል።
የባንኩ ዋና ስራ አስፈፃሚ ዮሐንስ አያሌው (ዶ/ር) በዚህ ወቅት÷ ባንኩ በበጀት ዓመቱ ከታክስ በፊት 654 ነጥብ 8 ሚሊየን ብር ትርፍ ማስመዝገቡንና ይህም ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር የ85 በመቶ ዕድገት እንዳለው ተናግረዋል።
በተጨማሪም የባንኩ አጠቃላይ ሀብት 43 ነጥብ 4 ቢሊየን ብር መድረሱንና ካለፈው ዓመት ጋር ሲነፃፀርም የ23 ነጥብ 2 በመቶ ዓመታዊ ዕድገት እንዳሳየ አመላክተዋል።
የባንኩ አጠቃላይ ተቀማጭ ገንዘብ በ26 በመቶ በማደግ ወደ 31 ነጥብ 5 ቢሊየን ብር ከፍ ብሏል ያሉት ዋና ስራ አስፈፃሚው÷ በበጀት ዓመቱ 70 ነጥብ 8 ሚሊየን ዶላር የውጭ ምንዛሪ ማግኘቱን ጠቁመዋል።
አጠቃላይ የባንኩ ካፒታል በ21 በመቶ በማደግ 8 ነጥብ 6 ቢሊየን ብር እንዲሁም የተከፈለ ካፒታሉ በ14 በመቶ በማደግ 7 ነጥብ 4 ቢሊየን ብር ደርሷልም ነው ያሉት።
በበጀት ዓመቱ አጠቃላይ የባንኩ ገቢ 5 ነጥብ 6 ቢሊየን ብር እንደደረሰና ከዚህም 80 በመቶው የሚሆነው ወለድ ነክ ከሆኑ የብድር ሥራዎች የተገኘ መሆኑን አስረድተዋል።
ይህም ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር የ29 በመቶ ዕድገት ማሳየቱ ተገልጿል።

ጋዜጣዊ መግለጫ | የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የሩብ ዓመት የውጭ ምንዛሪ ጨረታ መርሐ ግብር!
20/11/2025

ጋዜጣዊ መግለጫ | የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የሩብ ዓመት የውጭ ምንዛሪ ጨረታ መርሐ ግብር!

Bunna Bankየቡና ባንክ አክሲዮን ማህበር የዳይሬክተሮች ቦርድ የባንኩን የተከፈለ ካፒታል በ2022 ዓ.ም. መጨረሻ (እ.ኤ.አ 2030) ወደ 20 ቢሊዮን ብር ለማሳደግ የሚያስችል ስትራቴጂ...
20/11/2025

Bunna Bank
የቡና ባንክ አክሲዮን ማህበር የዳይሬክተሮች ቦርድ የባንኩን የተከፈለ ካፒታል በ2022 ዓ.ም. መጨረሻ (እ.ኤ.አ 2030) ወደ 20 ቢሊዮን ብር ለማሳደግ የሚያስችል ስትራቴጂካዊ ዕቅድ አዘጋጅቶ ለባለአክሲዮኖች ጠቅላላ ጉባዔ የውሳኔ ሃሳብ ሊያቀርብ መሆኑ ተገልጿል።
ይህ ዕቅድ ባንኩን በቀጣይ 5 ዓመታት ውስጥ በኢትዮጵያ ከሚገኙ ሦስት ቀዳሚ የፋይናንስ ተቋማት ተርታ ለማሰለፍ የሚያስችል ነው።
የቦርዱ የተከፈለ ካፒታል የማሳደጊያ ዕቅድ በመጪው ቅዳሜ ህዳር 13 ቀን 2018 ዓ.ም. በሚያደርገዉ 16ኛዉ የባለአክስዮኖች መደበኛና 7ኛዉ አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባኤ ላይ ቀርቦ ይፀድቃል ተብሎ ይጠበቃል።
ባንኩ ካፒታልን ማሳደግ ያስፈለገበት ዋነኛው ምክንያት፣ ዛሬ ካፒታልን ማሳደግ የሕግ ግዴታን የመወጣት ጉዳይ ብቻ ሳይሆን፣ የህልውና እና የላቀ ተወዳዳሪነት ጉዳይ መሆኑን መገንዘብ ነዉ ሲል ቦርዱ አስታውቋል።
በስትራቴጂክ እቅዱ ላይ ካፒታል ጋዜጣ ለመመልከት እንደቻለው ፤ ብሔራዊ ባንክ ከዚህ የሒሳብ ዓመት ጀምሮ ተግባራዊ እንዲሆን ያጸደቀውና ባንኮች ለሌሎች ስጋቶችም በቂ መተማመኛ የሚሆን ጠቅላላ ካፒታል እንዲይዙ የሚያስገድድ አዲስና ጥብቅ መመሪያ ባንኩ ካፒታሉን እንዲያሳድግ ያስፈለገበት ቀዳሚዉ ምክንያት እንደሆነ በዝርዝር አስቀምጧል።
በተጨማሪም መንግሥት የባንክ ዘርፉን ለውጭ ባንኮች ክፍት ማድረጉን ተከትሎ የሚመጣውን ከፍተኛ ውድድር መቋቋም ለመቻይ ይህ ዉሳኔ በእጅጉ አስፈላጊ መሆኑን አፅንኦት በመስጠት አብራርቷል።
ቦርዱ ፤ ባንኩ የረጅም ጊዜ ስትራቴጂካዊ ዕቅዱን ለማሳካት እና በተለይ የብድር አቅርቦት አቅሙን በዘላቂነት ለማስፋት የሚያስችል ጠንካራና አስተማማኝ የካፒታል መሰረት መገንባት ወሳኝ እንደሆነ ገልጿል።
የቡና ባንክ የአምስት ዓመት ስትራቴጂካዊ የካፒታል ማሳደጊያ ዕቅድ ፤ ደንበኞች የሚፈልጉትን ዘመናዊ እና ፈጣን የዲጂታል አገልግሎት ለመስጠት በቴክኖሎጂ ላይ ከፍተኛ መዋዕለ ንዋይ ማፍሰስ እና በውጭ ምንዛሪ አሠራር ላይ የታየውን ለውጥ እና ሊኖር የሚችለውን የዋጋ መስተካከል ተፅዕኖ ለመቋቋም ጠንካራ ካፒታል መኖሩ ወሳኝ እንደሆነ አመልክቷል።
የዚህ ዕቅድ መጽደቅና መተግበር ለባለአክሲዮኖች የላቀ ጥቅም እንደሚሰጥ የገለፀው ቦርዱ ከነዚህም መካከል የባንኩ አጠቃላይ ትርፍ ከሚጨመረው የአክሲዮን ብዛት በበለጠ ፍጥነት እንዲያድግ በማድረግ በአንድ አክሲዮን የሚገኘው ትርፍ (EPS) በዘላቂነት እንዲያድግ ይረዳል ብሏል።
በተጨማሪም የተሻለ የትርፍ ድርሻ (DPS) እንዲከፈል ማስቻል እና ባንኩ በራሱ ጥንካሬ እንዲቆም ስለሚያደርገው ወደ ፊት ከመንግስት ወይም ከብሔራዊ ባንክ በሚመጣ ‘በግድ የመዋሃድ’ ጫና ስጋት ውስጥ እንዳይገባ መከላከል እንደሚቻል ለባለአክሲዮኑ የአዲሱን እቅድ ያለውን ፋይዳ አስረድቷል።
ባንኩ፤ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ያስቀመጠውን የ5 ቢሊዮን ብር የተከፈለ ካፒታል የማሟላት ግዴታ ከተሰጠው የጊዜ ገደብ አንድ ዓመት ቀድሞ ማሳካቱን አስታውቋል።
​የቡና ባንክ የ 2016 በጀት ዓመት ሪፖርት እንደሚያመለክተው፣ የቡና ባንክ የተከፈለ ካፒታል በ549.2 ሚሊዮን ብር በማደግ አጠቃላይ 4.83 ቢሊዮን ብር ደርሶ ነበር።
እንደ ሪፖርቱ ከሆነ ከተመሰረተ 16 ዓመታትን ያስቆጠረው ባንኩ፣ ከ14,000 በላይ ባለአክሲዮኖችን ያሉት ሲሆን በመላው አገሪቱ በሚገኙ 474 ቅርንጫፎቹም ከ4,100 በላይ ቋሚ ሠራተኞችን በመቅጠር የስራ እድል መፍጠር መቻሉ ተመላክቷል።
Via

‼️ያልተከፈሉ የዘመን ባንክ አክሲዮኖችን ለመክፈል/ለመሸጥ የመጨረሻ  1 ቀን ቀረው‼️ሐሙስ ሕዳር 11 ብቻ ❗️******👉🏼ያልተከፈለ አክሲዮን ላላችሁ የዘመን ባንክ ባለአክሲዮኖች የተላለፈ ...
19/11/2025

‼️ያልተከፈሉ የዘመን ባንክ አክሲዮኖችን ለመክፈል/ለመሸጥ የመጨረሻ 1 ቀን ቀረው‼️
ሐሙስ ሕዳር 11 ብቻ ❗️
******
👉🏼ያልተከፈለ አክሲዮን ላላችሁ የዘመን ባንክ ባለአክሲዮኖች የተላለፈ መልዕክት፡
"ዉድ የዘመን ባንክ ባለአክሲዮኖች
የኢትዮጵያ የካፒታል ገበያ ባለስልጣን የሰነደ ሙዓለ ንዋይን ለህዝብ የማቅረብ እና የግብይት መመሪያዉ በሚደነግገዉ መሰረት አክሲዮኖችን ለሽያጭ ያወጡ ድርጅቶች መመሪያዉ ከመዉጣቱ በፊት የሸጧቸዉን አክሲዮኖች ባለሰልጣን መ/ቤቱ እስከ ህዳር 16 ቀን 2018 ዓ.ም የማስመዝገብ ግዴታ እንዳለባቸዉ ማሳወቁ ይታወሳል፡፡
በዚህም መሰረት ጥቅምት 01 ቀን 2018 ዓ.ም. በተደረገው የባለአክሲዮኖች 12ኛ አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባኤ ላይ በተሰጠዉ ማሳሰብያ መሰረት ቀነገደቡ ከመጠናቀቁ በፊት ተፈርመዉ ክፍያ ያልተከፈለባቸዉን አክሲዮኖች እስከ ህዳር 11 ቀን 2018 ዓ.ም ድረስ ቀሪ ክፍያ በመክፈል አክሲዮኖቹ መመዝገብ እንዲችሉ እንዲያደርጉ እናሳስባለን፡፡
ዘመን ባንክ አ.ማ"

ያልተከፈሉ የዘመን ባንክ አክሲዮኖችን እንገዛለን።
ይደውሉልን:
+251911248597
+251940599595
Greetings,
We buy Subscribed Zemen bank shares,
call us:
+251911248597
+251940599595

ለዘመን ባንክ ባለአክሲዮኖች የተላለፈ መልዕክት፡"ዉድ የዘመን ባንክ ባለአክሲዮኖችየኢትዮጵያ የካፒታል ገበያ ባለስልጣን የሰነደ ሙዓለ ንዋይን ለህዝብ የማቅረብ እና የግብይት መመሪያዉ በሚደነግ...
13/11/2025

ለዘመን ባንክ ባለአክሲዮኖች የተላለፈ መልዕክት፡
"ዉድ የዘመን ባንክ ባለአክሲዮኖች
የኢትዮጵያ የካፒታል ገበያ ባለስልጣን የሰነደ ሙዓለ ንዋይን ለህዝብ የማቅረብ እና የግብይት መመሪያዉ በሚደነግገዉ መሰረት አክሲዮኖችን ለሽያጭ ያወጡ ድርጅቶች መመሪያዉ ከመዉጣቱ በፊት የሸጧቸዉን አክሲዮኖች ባለሰልጣን መ/ቤቱ እስከ ህዳር 16 ቀን 2018 ዓ.ም የማስመዝገብ ግዴታ እንዳለባቸዉ ማሳወቁ ይታወሳል፡፡
በዚህም መሰረት ጥቅምት 01 ቀን 2018 ዓ.ም. በተደረገው የባለአክሲዮኖች 12ኛ አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባኤ ላይ በተሰጠዉ ማሳሰብያ መሰረት ቀነገደቡ ከመጠናቀቁ በፊት ተፈርመዉ ክፍያ ያልተከፈለባቸዉን አክሲዮኖች እስከ ህዳር 11 ቀን 2018 ዓ.ም ድረስ ቀሪ ክፍያ በመክፈል አክሲዮኖቹ መመዝገብ እንዲችሉ እንዲያደርጉ እናሳስባለን፡፡
ዘመን ባንክ አ.ማ"
Zemen Bank S.C.
ያልተከፈሉ የዘመን ባንክ አክሲዮኖችን እንገዛለን።
ይደውሉልን:
+251911248597
+251940599595
Greetings,
We buy Subscribed Zemen bank shares,
call us:
+251911248597
094 059 9595

አንበሳ ኢንተርናሽናል ባንክ ከታክስ በፊት ብር 1.8 ቢሊየን ትርፍ አስመዘገበ============================የአንድ አክሲዮን የትርፍ ድርሻ ብር 423.82 (42.3 በመቶ) ሆኗ...
04/11/2025

አንበሳ ኢንተርናሽናል ባንክ ከታክስ በፊት ብር 1.8 ቢሊየን ትርፍ አስመዘገበ
============================
የአንድ አክሲዮን የትርፍ ድርሻ ብር 423.82 (42.3 በመቶ) ሆኗል
በአሁኑ ሰዓት የባንኩ የተከፈለ ካፒታል ብር 5.8 ቢሊየን ደርሷል
(ጥቅምት 22 ቀን 2018 ዓ.ም.) አንበሳ ኢንተርናሽናል ባንክ በ2017 በጀት ዓመት ከታክስ በፊት 1.8 ቢሊየን ብር ትርፍ ያገኘ ሲሆን አፈጻጸሙም ካለፈው ዓመት ጋር ሲነጻጸር የ94 በመቶ እድገት ማሳየቱ ቅዳሜ ጥቅምት 22 ቀን 2018 ዓ.ም በሸራተን ሆቴል በተካሄደው የባንኩ 21ኛ መደበኛ እና 7ኛ ድንገተኛ የባለአክሲዮኖች ዓመታዊ ጠቅላላ ጉባዔ ላይ ተገለጸ፡፡ ከዚህም በተጨማሪ ከአንድ አክሲዮን የተገኘ የትርፍ ድርሻ ብር 423.82 ወይም 42.3 በመቶ በመሆን ከፍተኛ እድገት ማሳየቱ ተገልጿል፡፡
ይህ አመርቂ አፈፃፀም የባንኩን ጥንካሬ አጉልቶ የሚያሳይና ለቀጣይ የላቀ ስኬት መንደርደሪያ እንደሆነ የባንኩ የዲሬክተሮች ቦርድ ሰብሳቢ አቶ አለም አስፋው የተናገሩ ሲሆን የባንኩን የተከፈለ ካፒታል አቅም ብር 5.8 ቢሊየን በላይ በማድረስ በብሔራዊ ባንክ ከተቀመጠው ዝቅተኛ መስፈርት ከፍ ማድረግ መቻሉን ገልጸዋል።
ባንኩ በበጀት ዓመቱ ስድስት ቢሊየን ብር ብድር የሰጠ ሲሆን ከብድር ክፍያዎች ብር 5.2 ቢሊየን መሰብሰብ ችሏል። በሂሳብ ዓመቱ ማብቂያ ላይ የባንኩ አጠቃላይ የብድር መጠን ብር 36.2 ቢሊየን ሆኖ ሲመዘገብ ባንኩ ኢንቨስት ያደረገበት የግምጃ ቤት ሰነድ እና የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ቦንድ ግዥ ብር 4.1 ቢሊየን ደርሷል።
የባንኩ አጠቃላይ ሃብት ብር 54 ቢሊየን ሲደርስ የባንኩ ዕዳ ደግሞ ብር 47.5 ቢልየን ሆኗል። ከዚህ ባሻገር የባንኩ አጠቃላይ የካፒታልና መጠባበቂያ ክምችት ብር 6.5 ቢሊየን ደርሷል። በሀብት ማሰባሰብ ረገድ ባንኩ በበጀት ዓመቱ ብር 8.3 ቢሊየን ተቀማጭ ገንዘብ ማሰባሰቡን እና አጠቃላይ የተቀማጭ ገንዘብ መጠኑን ብር 44 ቢሊየን ማድረስ መቻሉን ሰብሳቢው የገለጹ ሲሆን አፈጻጸሙም ካለፈው ዓመት አንጻር የ25 በመቶ እድገት ማሳየቱን ጠቁመዋል፡፡ ከዚህ በተጨማሪም ባንኩ ካለፈው ዓመት ጋር ሲነጻጸር ከፍተኛ እድገት ያለው የውጭ ምንዛሪ ማሰባሰብ መቻሉ ተነግሯል።
በቅርንጫፍ እና በዲጂታል የባንክ አገልግሎት ተደራሽነትን ከማጎልበት አንጻር በርካታ ስራዎች የተከናወኑ ሲሆን ከዚሁ ጋር ተያይዞ ሰፊ የደንበኞች መሰረት በመፍጠር ባንኩ ከ2.4 ሚሊየን በላይ ደንበኞችን ማፍራት ችሏል፡፡
ከዋስትና ማስያዣ ነጻ በሆነው “አለኝታ” ዲጂታል ብድር ባንኩ ከ5,000 በላይ ደንበኞችን ተጠቃሚ ያደረገ ሲሆን የትምህርት ቤት ክፍያ እና የህብረት ስራ ማህበራት የገንዘብ ልውውጥን የሚያሳልጡ ስርአቶችን ስራ ላይ በማዋል በርካታ ደንበኞችን ተጠቃሚ ማድረግ ችሏል፡፡
በተጨማሪም ከኢትዮቴሌኮም፣ ከሳፋሪኮም፣ ከሳንቲም-ፔይ እና ሌሎች የፊንቴክ ኩባንያዎች ጋር ስትራቴጂካዊ አጋርነት በመፍጠር የባንኩን ተደራሽነት ይበልጥ በማስፋት የደንበኞችን ፍላጎት በማሟላት ረገድ ምቹ ተግባራት ተከናውነዋል።
በሂሳብ ዓመቱ ከተከናወኑ ጉልህ ተግባራት አንዱ 'አል-ነጃሺ' የተሰኘ የሼሪአ መርሆችን የጠበቀ ከወለድ ነፃ የባንክ አገልግሎት መጀመሩ ሲሆን በአሁኑ ሠዓት በትግራይ - መቀሌ፣ በአፋር - ሎጊያ እና በአዲስ አበባ - ቤቴል ከወለድ ነጻ የባንክ አገልግሎት ብቻ የሚሰጡ ቅርንጫፎች ተከፍተው አገልግሎት ሲሰጡ በሁሉም የባንኩ ቅርንጫፎች ይኽው አገልግሎት እየተሰጠ ይገኛል፡፡
የባንኩ የሰው ሃይል ወደ 6,888 ሲያድግ ከነዚህ መካከል 50% ያህሉ በቋሚ ቅጥር የስራ መደቦች ላይ ይገኛሉ። በበጀት ዓመቱ ብቻ ለ348 አዲስ ሰራተኞች የስራ እድል የተፈጠረ ሲሆን በተለያየ ምክንያት ስራቸውን የሚለቁ ሰዎች ምጣኔ ከ4.5 በመቶ እንዳይበልጥ ማድረግ ተችሏል። በተጨማሪም የሰራተኞችን ክህሎት ለማሳደግ እና ቅልጥፍናቸውን ለማጎልበት በዘርፈ ብዙ የሙያ መስኮች ላይ ያተኮሩ የስልጠና መርሃ ግብሮች ላይ ከፍተኛ ኢንቨስትመንት ተደርጓል በውጤቱም የተረጋጋ የስራ አካባቢ ለመፍጠር አስችሏል፡፡
አንበሳ ኢንተርናሽናል ባንክ በህብረተሰቡ ላይ በጎ ተጽዕኖ ለመፍጠር በትጋት እየሰራ የሚገኝ ሲሆን በበጀት ዓመቱ የተለያዩ የማህበረሰብ ልማት ላይ ያተኮሩ ስራዎችን ለመደገፍ 9.3 ሚሊዮን ብር ድጋፍ አድርጓል። በተጨማሪም በማህበረሰብ ልማት ዙሪያ ንቁ ተሳትፎ ለሚያደርጉ የሲቪክ ማህበራትና ተቋማት 5.1 ሚሊዮን ብር ስፖንሰር አድርጓል።
አንበሳ ኢንተርናሽናል ባንክ
By

የብርሃን ባንክ የ 2017 በጀት ዓመት አፈፃፀም********Gross Profit: 2.5 BillionEPS: 54.7%Total Asset: 58.9 Billion*****ምንጭ፡'Berhan Bank ...
30/10/2025

የብርሃን ባንክ የ 2017 በጀት ዓመት አፈፃፀም
********
Gross Profit: 2.5 Billion
EPS: 54.7%
Total Asset: 58.9 Billion
*****
ምንጭ፡'Berhan Bank S.C. 2024-25 Annual Report'

Address

Legehar
Addis Ababa
7856

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Abay Stock Market posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Abay Stock Market:

Share