19/09/2023
ከታች የቀረበው ምስል ሲታይ ከጀርባው ያለውን ትርጉም መጀመርያ አይገባም ... (በድጋሚ ያስተውሉት !)
ድመቷ የእባብ ጅራት ከትንሽ ጉድጓድ ውስጥ ሲወጣ አይታ ድመቷ የአይጥ ጅራት መስሏት እስኪወጣ ድረስ ልትጎትተው ትታገላለች .... ይህ ፎቶ የታዋቂው ጣሊያናዊ ገላጭ ማርኮ ሜልግራቲ ነው።
የሥዕሉ ትርጉም፡- “ጉዳቱን ሳታውቅ ከማን ጋር እንደምትጫወት አታውቅም፤ ምክንያቱም ዛሬ ባለን እንደ ጠንክሮ መሥራት፣ ፈጣን መፍትሔዎች ሰጭነት ላይ ወዘተ ባሉ ባህርያት ተሞልተናል ይላል"።
ዛሬ በፈጣን እና በተጨናነቀ ህይወት የምናየው የእውነት ትንሽ ክፍል ማሳያ ይሆናል.... በተለይ ከጤና ጋር በተያያዘ ብዙዎች ሲሰቃዩ ፣ ተስፋን ሲያሳድዱ፣ ቀናት ሲቆጥሩ፣ የዓመት በዓል ቤተሰብ ደስታ ርቀው፣ በተለያዮ ዘመን አመጣሽ አንዳውም ሰው ሰራሽ በሚመስሉ በአንድ መልኩ ዘመኑ ረቀቀ፣ የህክምና ጥበብ በቴክኖሎጂ ተደገፈልን፣ ሙያተኞች በብዛት አስመረቅን እያልን በሌላ መልኩ እንደ #ካንሰር ፣ #ስኳር ፣ ደም ብዛት ፣ ልብ፣ ኩላሊት ... ታካሚዎች ብዛት ጨምሯል ፣ አዲስ አይነት ቫይረስ ዝርያ በየጊዜው አገኘን እንላለን ?!?
የጤና እክል ሁኔታዎችን እንደ አይጧ ጅራት መቁጠር ያለብን ጊዜ ላይ ደርሰናል ... አለበለዛ ከግድግዳው በስተጀርባ ያለው እውነተኛ አደገኛ እባብ በጭራሽ አናስተውለውም ።
ስለዚህ ለጤንነታችን ቅድሚያ እንስጥ ፣የጤና ሁኔታችንን በጭራሽ ችላ አንበል ።እንደ አይጥ ጅራት በመቁጠር ከኮብራ ጅራት ጋር አንጫወት ።
የጤና ህክምና ወጭ በአሁን ዘመን እጅግ ውድ ሆኗል ( is Very Expensive) በተለይ እንደ #ኢትዮጵያ ያሉ ደሀ አገራት ☠ ሊሆን ይችላል። በሀገሪቱ ውስጥ ላለው ከፍተኛ የጤና እንክብካቤ ዋጋ አስተዋጽኦ የሚያደርጉ ብዙ ምክንያቶች አሉ። የተወሰኑትም -
📌 አባካኝና የሙስና ሰንሰለት ሥርዓቶች፣
📌 የመድኃኒት ስርጭትና ተደራሽነት መርህ፣
📌 የሕክምና ባለሙያ ብቃት ፣ስነምግባር፣ ደመወዝ፣
📌 በትርፍ የሚመሩ የጤና አጠባበቅ ማዕከላት ቁጥጥር፣
📌 የሕክምና ልምምዶች ዓይነት ውስንነትና (ባህላዊ ህክምናን አማራጭ ማሳጣት )እና ከጤና ጋር የተያያዙ የተጋነነ ትርፍ ዋጋዎችን ሊጠቀሱ ይችላሉ።
ስለዚህ የጤና ሁኔታችንን እንንከባከብ፣ አመጋገባችንን እናስተካክል፣ አካላዊ ስፖርት እንቅስቃሴዎችን እናዘውትር እና ጤናማ እንሁን ... የመጀመርያ መፍትሄው ይህ ይመስላል፣ በአደገኛው እባብ ጭራ ከመጫወታችን በፊት።
#ጤና በዚህ ዘመን አዲስ ቅንጦት ነው...
cross with some modifications