Wotaro BALTA DANA-Personal Blogger

18/02/2026

28/03/2025

"ሚስቶች ከባሎቻቸው የሚጠሏቸው 7 ነገሮች"
( አባቶች በትዳር ሕይወት ውስጥ ላሉ ለወንድ ልጆቻቸው የመከሯቸው ምክር መሰረት አድርጎ የተዘጋጀ ጽሑፍ ነው።)
1. ፍቅሩን የማይገልጥ ባል፤
ልጄ መቼም ሚስትህን ስታገባት ተገደህ አይደለም ፡፡ ከብዙ ሚሊዮን ሴቶች መሐል ወደህና ፈቅደህ ነው ያገባሐት ወደህና ፈቅደህ ከሆነ ደግሞ ያገባሃት ልብህ ውስጥ ያለውን በማውጣት እወድሻለሁ በላት፡፡
ልጄ ብዙ ጊዜ ወንዶች ሚስቴን እወድሻለሁ አፈቅርሻለሁ ብላት ሌላ ነገር ይሰማት ይሆናል? ወይም ይህ ክብሬ ይቀንስብኛል ብለው ያስባሉ። አንተ ግን እንደዚህ አትበል፤ ከአምላክህ ቀጥሎ ክብርህ እርሷ ናት፤ ለርሷም አንተው ነህ፡፡
ልጄ ታዲያ እወድሻለሁ አፈቅርሻለሁ በል ስለተባልክ ብቻ ሳይሆን በእርግጥም ስለምትወዳት ስለምታፈቅራት ነው ማለት ያለብህ እርሱማ ፊልምም ቲያትርም ላይ እኮ ሳይወዱ እወድሻለሁ ሳያፈቅሩ አፈቅርሻለሁ ይላሉ። አንተ ግን እየሰራህ ያለኸው እውነተኛ ትዳርን ቤትን እንጂ ቲያትር አይደለምና እንደ ቲያትሩ በሽምደዳ ሳይሆን ከልብህ ልትለው ይገባል።
ልጄ ምን መሰለህ በውስጥህ የሌለውን ፍቅር ለማለት ብትሞክር ያ ማታለል ነውና ፣ በራስ ላይ የከፋ የስነልቦና ችግር የሚፈጥርብህ ስለሆነ አትበለው፤ እኔ እያልኩህ ያለሁት የተደበቀውን እውነተኛ ፍቅርህን ግለጠው ነው።
በመፅሐፍ ቅዱስም በመጽሐፈ ምሳሌ 27:5 "ከተደበቀ ፍቅር የተገለጠ ዘለፋ ይሻላል… " ይላል አየህ! ፍቅርህን ልትገልጽላት ከሚገባው አንዷ ሚስትህ ናት፤ ባል ለሚስቱ ፍቅሩን ሊደብቅ አይገባውም ሊገልጠው ይገባል፤ ከተደበቀ ፍቅር የተገለጠ ዘለፋ ይሻላል ማለቱን ስታስተውል ፍቅርን መደበቅ አለመግለጽ ምን ያህል ከተገለጠ ዘለፋ እንኳን የከፋ እንደሆነ ነው የተናገረው፤
ስለዚህ ልጄ ሆይ ሚስቶች ሁሌም ቢሆን መወደዳቸውን በንግግርና በድርጊት እንድታረጋግጥላቸው ይፈልጋሉ ፍቅርህን በደንብ ግለጸው አትደብቀው፤
2. የማይረዳቸው ባልን
ልጄ በትዳር ሕይወት ውስጥ ቁልፉና ወሳኙ ነገር ሚስትህ የምትልህንና የምትፈልገውን ነገር መረዳት መቻልህ ነው፡፡ በተለይም የወንድና ሴት ፍላጎት እንደ አፈጣጠራቸው ይለያያልና ነገሮችን በእርሷ በኩል ሆነህ ልታያቸው ይገባል። ሚስትህ የምትናገረውን የምትፈልገውንና የምታደርገውን ነገር ካልተረዳህ ሌላ ሊረዳት የሚችል ሰው ያገኘች ቀን በቀላሉ ልትሸነፍ ትችላለችና ተጠንቀቅ፤
ልጄ ማንም ሰው ፍፁም ስላልሆነ ባለቤትህም ጥፋት ልትሰራ ትችላለች፡፡ ችግሯን በመረዳት ይቅርታ የማታደርግላት ከሆነ ትጠላሃለችና ተረዳት ነገሮችን ከራስህ መንገድ ብቻ ሳይሆን በእርሷም ቦታ ሆነህ ለመመልከት ሞክር።
3. በቂ ጊዜ የማይሰጣቸው ባል፤
ልጄ መጽሐፍ ቅዱስ በኦሪት ዘዳግም 24:5 ላይ እንዲህ ይላል " አዲስ ሚስትም ያገባ ሰው ወደ ጦርነት አይሒድ፤ ነገርም አይጫኑበት፤ ነገር ግን አንድ ዓመት በፈቃዱ በቤቱ ይቀመጥ፤ የወሰዳትንም ሚስቱ ደስ ያሰኛት።" ይላል ይህ ቃል እንደሚያስረዳን ባል ለሚስቱ በቂ ጊዜ ሊሰጣት እንደሚገባ ነው። ጊዜ ስትሰጣት ግን ሚስትህን ደስ ልታሰኛት መሆን አለበት እንጂ ልትጨቀጭቃት መሆን የለበትም፤ ቃሉም ሚስቱንም ደስ ያሰኛት ነው የሚለው፤ ይህም ማለቱ ባል ሁልጊዜ ለሚስቱ ለቤተሰቦቹ ደስታ መድከም እንዳለበት ሲነግረን ነው።
ልጄ ይህንኑ የእግዚአብሔርን ቃል አክብረህ ሚስትህ በቂ የሆነ ጊዜ ከባሏ ካንተ ማግኘትን ትሻለችና የምትወያይበት፣ ፕሮግራም ይዛችሁ አብረኻት የምትዝናናበት፣ ዕቅድህን ነጻና ግልፅ በሆነ መንገድ የምታዋይበት ጊዜ በሚገባ ስጣት፤ ለእሷና ለልጆችህ ያልሆነ ጊዜ ለማንም ሊሆን አይችልምና ለእነሱ በምትሰጠው ጊዜ አትሰስት፤
4. አምባገነን ባል (እኔ ያልኩት ብቻ ይሁን ባይ)፤
ልጄ "አምባገነን ባልና አምባገነን ንጉስ አንድ ናቸው ሁለቱም እኔ ያልኩት ብቻ ይሁን ነው የሚሉት፤ ሲባል አልሰማህምን?
አየህ ልጄ አምባገነን ባል ማለት ሚስቱን ልጆቹን የማያዳምጥ እነርሱ የሚጠይቁትን የማይፈጽም፤ እኔ ያልኩት ይሁን ብቻ የሚል፤ እምቢታን የሚያበዛ ቤቱን ሚስቱን ልጆቹን በፍቅር ሳይሆን በኃይል የሚገዛ ባል ማለት ነው።
ልጄ አንተም ብዙውን ጊዜ ባለቤትህም ሆኑ ልጆችህ በሚጠይቁህ ነገር ላይ አይሆንም/እምቢታን ካስለመድካቸውና እኔ ያልኩት ብቻ ይሁን ባይ ከሆንክባቸው አንተን መሸሻቸው እውን ነው፡፡ ምክንያቱም ሌላም ጊዜ መጠየቅ ቢፈልጉ እንኳ እሺ አይለንም የሚል ግምት ስለሚኖራቸው የጨለመ አመለካከትን ያዳብራሉ፡፡
ልጄ ምንም እንኳን መጽሐፍ ቅዱስ " ወንድ የሴት ራስ ነው" ቢል አንተም እኔ ራስ በመባሌ የበላይ ነኝ አትበል ምክንያቱም "ሚስት የባሏ ዘውድ ነች" ተብሏልና ያለ ሚስትህ ንጉስ፣ ያለ ሚስትህ አባወራ፣ ያለ ሚስትህ አባት፣ ያለ ሚስትህ ባል ልትባል አትችልምና ሚስትህን አክብራት አዳምጣት፤ ምንም ራስ ብቶትሆን ያለርሷ ንግስና እንደሌለ ልታውቅ ይገባል፤
ልጄ ሚስትህ አካልህ አንተም አካሏ ነህና ልትመጋገቡ ልትደጋገፉ ይገባል አካላችን ቆሞ የሚሔደው ስለተደጋገፈ መሆኑን አትዘንጋ፤
ልጄ ይህን ሁሉ ስልህ ግን ሁሉንም ነገር እሺ በላት እያልኩህ አይደለም። ይህማ ከሆነ እንደ አክአብ መጨረሻህ አያምርም፤ እያልኩህ ያለሁት ሚስትህ የጠየቀችህን ነገር አይሆንም ከማለትህ በፊት ደጋግመህ ለማሰብ ሞክር፡፡ እንቢ የምትል ከሆነ እንቢ አላደርገውም በማለት ሳይሆን ለምን እንዳልካት ለሁለታችሁም ጥቅም እንደሆነ በግልጽ ልትገልጽላት ልታስረዳት ይገባል ነው፤ ይህን ስታደርግም ሚስትህን ቢያንስ ከጭንቀትና የተለያዩ ነገሮችን እያሰበች ከመጠራጠር ታሳርፋታለህና እንቢ ስትል አሳማኝ ምክንያትህን መግለጽህን ልመድ። በሆነውም ባልሆነውም ነገር አምባገነን ባል አትሁን፤ እምቢታን አታብዛ፤
5. የማያዳምጣት ባል
ልጄ አንድ ነገር ተረዳ ማዳመጥና መስማት ይለያያል፤ መስማት ጆሮ መስጠትን ብቻ ነው የሚጠይቀው፤ ማዳመጥ ግን ጆሮንም ልብንም ነው የሚፈልገው፤ ስለዚህ ልጄ ሚስትህን አዳምጣት ስልህ ጆሮህንም ልብህንም ስጣት ማለቴ ነው።
ልጄ ሚስትህ ከልቡ እየሰማኝ ነው ብላ የተናገረችውን ቁም ነገር አንተ እንዳልሰማኻት ብታውቅ ምንኛ ሊያማትና ባለቤቷ አብሯት እንዳልነበር ስትረዳ እንደሚሰማት መገመት ትችላለህ ፡፡ ይህ ደግሞ ለርሷ ቦታ እንደማትሰጣት ሊሰማት ይችላል፡፡ በሌላ አነጋገር የምታመጪው ሀሳብ፣ ወሬ የትም የሚገባ አይደለም እንዳልክባት ትቆጥረዋለችና በደንብ አድምጣት እየተከታተልካት ለመሆኑም የምልክት ቋንቋ አሳያት፣ ከዛም ባለፈ ያለችውን በትክክል ለመረዳት ደግመህ በሌላ ቋንቋ ንገራት፡፡ ስለዚህ የምልህ ከጆሮ በዘለለ ባለቤትህን ከልብህ ልታዳምጣት ይገባል ነው፡፡
6. ፍቅርና ርህራሄን የማያሳይ/የማይገልጥ ባል፤
ልጄ እንዲህ የሚል አንድ አባባል አለ "የጋብቻ ሰንሰለት ከባድ በመሆኑ የሚሸከሙት ሁለት ሰዎች ይፈልጋል አንዳንዴም ሶስት" ይህም የትዳር ሕይወት ተረዳድተው ተጋግዘው አንተ ትብስ አንቺ ትብሽ አየተባባሉ ካልተሳሰቡ ካለተረዳዱ በቀር ሸክሙ ከባድ መሆኑን የሚገልጥ ቃል ነው። ስለዚህ ለትዳር አጋርህ ለሚስትህ ፍቅርን ርሕራሔን ልታሳያት ይገባል።
ልጄ ጋብቻን ከሚያጠናክሩትና ውጤታማ ከሚያደርጉ ጉዳዮች መካከል አንዳችን
ለሌላኛችን የምናሳየው ፍቅርና ርህራሄ መሆኑን ልትገነዘበው ይገባል፤ ንግግርህ ሁልግዜ የተመጠነና ከቁጣ የራቀ ይሁን፤ አንድ ነገር ፈልገህ ስትጠይቃት ወይም እንድትፈጽምልህ ከፈለግክ በንግግርህ መሐል እባክሽን፣ አመሰግናለሁ የኔ ቆንጆ፤ የሚሉና የመሳሰሉ የአድናቆትና የፍቅር ቃላትን መጠቀምህን አትርሳ፡፡
ልጄ ቢቻል ደግሞ እርሷን ብቻ የምትጠራበት ስም ቢኖርህ ጥሩ ነው፤ ሚስትህ ባንተ ላይ ትልቅ ስፍራ እንዳላት የምትገነዘበው በምትለውና በምታደርገው ላይ በመመርኮዝ ነው፡፡ አንዳንዶች ከተጋቡ በኋላ ይህን ነገር ይዘነጋሉ አንተ ግን እንደነርሱ አትሁን፤ ወደ ቤትህ ስትገባ እንኳን ምን ቢደክምህ፣ በደጅም ተበሳጭተህ ብትመጣ፣ ጉንጯን፣ ከንፈሯን አሊያም ግንባሯ ላይ በመሳም ለእርሷ ያለህን መሰጠትና ፍቅርህን ልትገልጽላት ይገባል።
7. በቤት ውስጥ ሥራን የማያግዝና ኃላፊነትን የማይጋራት ባል፤
ልጄ እንዳንተ የተማሩ ፈረንጆች አንድ ደስ የሚል አባባል አላቸው " Love Is Not Feeling Love Is Doing " ወደ አማርኛ ሲተረጎም "ፍቅር ስሜት አይደለም ፍቅር ድርጊት ነው" እንደማለት ነው።
የአባባሉ ዋነኛ መልእክት ሚስትህን በአፍህ በቃላት እወድሻለሁ አፈቅርሻለሁ ማለቱ ብቻ ሳይሆን ለሚስትህ በቤት ውስጥ ስራ በማገዝ የቤት ውስጥ ሐላፊነቱን በመጋራትም ፍቅርህን በተግባርም ልትገልጽላት ይገባል ማለታቸው ነው።
ልጄ ሚስትህ ካንተ በጣም ከምትሻቸው ነገሮች መካከል አንዱ የቤት ውስጥ ኃላፊነትን መጋራት ላይ ነው፡፡ በተለይም በዚህ በእናንተ ዘመን ሁለታችሁም ሰራተኞች እንደመሆናችሁ ቤት ስትገቡ ይደክማችኋል፡፡ ይህን ከግምት በማስገባት በቤት ውስጥ የስራ ክፍፍል ልታደርጉ ይገባል፤
ልጆችን በመንከባከብ በኩል ኃላፊነት የማይሰማህ ከሆነ ሚስትህ ልትማረርና ልትነጫነጭ ትችላለች፣ ሁሉም የጋራ ፍሬዎቻችሁ እንደመሆናቸው በጋራ ልትንከባከቧቸው የግድ ይላል፡፡ እቤት ውስጥ የሚሰሩ ማናቸውንም ነገሮች እርሷ እስክትልህ ድረስ መጠበቅ የለብህም፡፡
ልጄ ትዳርህ የዘላለም ፤ የፍቅር፤ የሰላም እንዲሆንልህ ከፈለግክ ከእነዚህ ሚስትህ ከምትጠላቸው ነገሮች ተቆጠብ ራቅ። በመጨረሻም አንድ ነገር ልበልህ " የተሳካ ትዳር የሚገኘው ትክክለኛውን አጋር በማግኘት ብቻ ሳይሆን ትክክለኛውን አጋር ሆኖ በመገኘትም ነው፤" የሚለውን አባባል እንዳትረሳብኝ ለዘላለም በልብህ አኑረው፤

Abiy Ahmed usually takes advantage of speeches to his army to distill subtle messages for his rivals in the region. Howe...
20/09/2024

Abiy Ahmed usually takes advantage of speeches to his army to distill subtle messages for his rivals in the region. However, there was no need to read between the lines on Sunday, September 8, when he presided over a military tribute in Addis Ababa. The Ethiopian prime minister reiterated that his country "won't negotiate with anyone on Ethiopia's sovereignty and dignity" and demanded "nationalist patriotism" from its population in order to resist the "foreign powers" he accuses of wanting to "destabilize the region."
=========================================

The country's quest for a port on the Red Sea has greatly destabilized the Horn of Africa. In return, its neighbors are engaged in a dangerous military escalation.

14/07/2024

ስለ መጽሐፍ ቅዱስ ምን ያህል ያውቃሉ..?

❖ የመጀመሪያው መጽሐፍ ቅዱስ የተፃፈው በእብራይስጥ፣ በአረማይክ እና በኮይኔ ግሪክ ቋንቋዎች ነው።

❖ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ
• 66 መጽሐፍት
• 1,189 ምዕራፎች
• 31,173 አንቀፆች
• 810,697 ቃላት
• 3,566,480 ፊደላት ይገኛሉ።

❖ በጣም ረጅሙ መጽሐፍ- መዝሙረ ዳዊት ሲሆን
• በጣም አጭሩ መጽሐፍ- ሶስተኛ ዮሐንስ
• በጣም ረጅሙ ምዕራፍ- መዝሙረ ዳዊት 119
• አጭሩ ምዕራፍ መዝሙረ ዳዊት 117 ነው።

❖ የመጽሐፍ ቅዱስ አማካይ ስፍራ መዝሙረ ዳዊት 118:8 ነው።

❖በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የብዙ ሰዎች መጠሪያ የሆነው ስም ዘካሪያስ ነው።

❖ ብዙ ጊዜ ተደጋግሞ የተጠቀሰው ስም "ዳዊት" ሲሆን 1008 ጊዜ ተጠቅሷል። በመቀጠልም ኢየሱስ 973 ጊዜ፤ ሙሴ 829 ጊዜ ተጠቅሰዋል።

❖ ሙሉው መጽሐፍ ቅዱስ እና የትንቢተ ኢሳይያስ መጽሐፍ አስደናቂ መመሳሰል አላቸው።
ይኸውም፦
• መጽሐፍ ቅዱስ 66 መጽሐፍ ሲኖሩት ትንቢተ ኢሳይያስ 66 ምዕራፎች አሉት።

• የመጀመሪያው 39 የመጽሐፍ ቅዱስ መጻሕፍት የሚተርኩት ስለ እስራኤል ህዝብ ነው። እንደዚሁም የመጀመሪያው የትንቢተ ኢሳይያስ 39 ምዕራፎች የሚተርኩት ስለ እስራኤል ህዝቦች ነው።

• የመጨረሻው 27 የመጽሐፍት ቅዱስ መጻህፍት የሚያስተምሩት ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ ሲሆን፤ እንደዚሁም የመጨረሻዎቹ 27 የትንቢተ ኢሳይያስ ምዕራፎች የሚተርኩት ስለ ክርስቶስ መምጣት ነው።

❖ መጽሐፍ ቅዱስ ተፅፎ ያለቀው በ1600 ዓመታት የጊዜ ልዩነት ውስጥ ሲሆን ይህም ከ1500 ዓመተ ዓለም እስከ 100 ዓመተ ምህረት ድረስ ያለውን ዘመን ያጠቃልላል።

❖ መጽሐፍ ቅዱስ በእግዚአብሔር ተልከው ቅዱሳን ሰዎች በመንፈስ ቅዱስ ተነድተው የጻፉት መጽሐፍ ነው።( 2ጴጥ 1:21)

❖ በመጽሐፍ ቅዱሳችን ውስጥ 49 የምግብ ዓይነቶች ተጠቅሰዋል፤ በተለይ "ጨው" 30 ጊዜ ተጠቅሷል።

❖ ከቤት እንሰሳት መካከል ስሟ ያልተጠቀሰ እንሰሳ
"ድመት" ብቻ ናት።
ውሻ 14 ጊዜ ተጠቅሷል።

❖ በመጽሐፍ ቅዱስ ታሪክ ውስጥ እራሳቸውን በራሳቸው ያጠፉ ሰዎች ሰባት ሲሆኑ
እነርሱም፦ 1. አቤሜሌክ 2. ሳምሶን 3. ሳዖል 4. የሳዖል ወታደር 5. አኪጦፌል 6. ዚምራ 7. ይሁዳ ናቸው።

❖ በመጽሐፍ ቅዱሳችን ውስጥ
ስለ ፀሎት 400 ጊዜ
ስለ እምነት 500 ጊዜ
ስለ ገንዘብና ሐብት ደግሞ 2,000 ጊዜ ተፅፏል። መጽሐፍ ቅዱስ ገንዘብን መውደድ የኃጢአት ሁሉ ስር ነው ይለዋል።

❖ መጽሐፍ ቅዱስ ለመጀመሪያ ጊዜ ወደ እንግሊዝኛ የተተረጎመው በ 1388 ዓ.ም ነው።

,
..✍️

Try your best, please CLICK TO GET MONEY  Creative KFC Bitcoin Center Bitcoin & Crypto Online Edge Swadesh Online Make Y...
21/06/2024

Try your best, please CLICK TO GET MONEY
Creative KFC Bitcoin Center Bitcoin & Crypto Online Edge Swadesh Online Make You Feel Better EverMerge Everlyne Osero Nuso

Millions of people trust MoneyEasily who play games, complete tasks, share their opinions in exchange for rewards. Be social and make money online with MoneyEasily.

20/06/2024

ሚኒስትሪ ተፈታኙ የዕድሜ ባለጸጋ
*************

በ87 አመታቸው የ6ኛ ክፍል ሚኒስትሪ ፈተና እየተቀበሉ ያሉት የዕድሜ ባለጸጋ ተማሪ ማሞ ጋንገርሺ መነጋገሪያ ሆነዋል።

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ኣሪ ዞን ደቡብ ኣሪ ወረዳ ቲኪ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤት የመጀመሪያውን 6ኛ ክፍል ሚኒስትሪ ዞናዊ ፈተና እየወሰዱ የሚገኙት አባት መነጋገሪያ ሆነዋል።

ተማሪ ማሞ ጋንጋርሺ የ16 ልጆች እና 36 የልጅ ልጆች እንዲሁም 2 የልጅ ልጅ ልጆችን ያዩ ዕድሜ ጠገብ አባት መሆናቸውን ከአሪ ዞን ኮሙኒኬሽን የተገኘው መረጃ ያመላክታል።

ለመማር ዕድሜ ያልገደባቸው ተማሪ ማሞ 87 አመት የሆናቸው ሲሆን ለትውልዱ ትምህርት ለመማር መቼም ቢሆን ጊዜው አይረፍድም የሚለውን መልዕክት ማስተላለፍ ችለዋል።

02/06/2024

22/03/2024

ሽንኩርት በ45 ብር፣ አንደኛ ደረጃ ቲማቲም በ12 ብር ብቻ ሌሎች አትክልትና ፍራፍሮ በገበሬ ዋጋ በአዲስ አበባ እየሸጥን እንገኛለን ስትል በረከት ገበሬዋ ገለፀች። በተለይ የጋራ መኖሪያ ቤቶች፣ መስሪያ ቤቶች በብዛት የምትፈልጉ ባላችሁበት ያለ ምንም ተጨማሪ ዋጋ ይዘን እንመጣለን ብላለች።

***
በቴሌግራም መረጃ ማቅረብ ጀምረናል ተከተሉን
https://t.me/fastmereja
https://t.me/fastmereja

Address

Addis Ababa, Hayahulet Area Behind Elsa Kolo
Addis Ababa
1000

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Wotaro BALTA DANA-Personal Blogger posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Wotaro BALTA DANA-Personal Blogger:

Share