የአራዳ ክ/ከተማ ማዐጤመ ተቋም - Arada Sub City CBHI Scheme

የአራዳ ክ/ከተማ ማዐጤመ ተቋም - Arada Sub City CBHI Scheme ይህ የአራዳ ክ/ከተማ አስተዳደር የማኅበረሰብ ዐቀፍ ጤና መድ?

9060 አዲሱ የኢትዮጵያ ጤና መድህን አገልግሎት ነጻ የስልክ መስመር  መረጃ የመስጠት ስራ  ጀመረ።የኢትዮጵያ ጤና መድህን አገልግሎት ለህብረተሰቡ ስለ ጤና መድህን ጽንሰ ሀሳብ፣ ስለ ማህበራ...
01/02/2023

9060 አዲሱ የኢትዮጵያ ጤና መድህን አገልግሎት ነጻ የስልክ መስመር መረጃ የመስጠት ስራ ጀመረ።
የኢትዮጵያ ጤና መድህን አገልግሎት ለህብረተሰቡ ስለ ጤና መድህን ጽንሰ ሀሳብ፣ ስለ ማህበራዊ የጤና መድህን፣ ስለማህበረሰብ አቀፍ የጤና መድህን፣ ስለሚሰጡ አገልግሎቶች፣ስለ ጥቅም ማቀፍ እና ለሌሎች ለተመሳሳይ ጥያቄዎች መልስ የሚሰጥ ነጻ የስልክ መስመር 9060 በሶስት ቋንቋዎች አገልግሎት መስጠት ጀመረ።

የአራዳ ክ/ከተማ ማኅበረሰብ አቀፍ ጤና መድኅን አባላት የማፍራት ሥራ ዛሬ ህዳር 30/2015 ዓ/ም ተጠናቀቀ።94.6% (እጅግ በጣም ጥሩ)
09/12/2022

የአራዳ ክ/ከተማ ማኅበረሰብ አቀፍ ጤና መድኅን አባላት የማፍራት ሥራ ዛሬ ህዳር 30/2015 ዓ/ም ተጠናቀቀ።

94.6% (እጅግ በጣም ጥሩ)

08/12/2022
03/12/2022
የማዐጤመ መጨረሻው ቅዳሜ እንቅስቃሴዎች ➥የ2015 ዓ/ም የማዐጤመ አባላት የማፍራት ሥራ ዛሬ ቅዳሜም ተጠናክሮ ቀጥሎ ውሏል። ➥የሚቀጥሉት ተከታታይ 5 ቀናት ላይ እድሳትን ከ80% በላይ ለማድ...
03/12/2022

የማዐጤመ መጨረሻው ቅዳሜ እንቅስቃሴዎች
➥የ2015 ዓ/ም የማዐጤመ አባላት የማፍራት ሥራ ዛሬ ቅዳሜም ተጠናክሮ ቀጥሎ ውሏል።
➥የሚቀጥሉት ተከታታይ 5 ቀናት ላይ እድሳትን ከ80% በላይ ለማድረስ ሁሉም ጤና ጣቢያዎች የሞት ሽረት ትግል ላይ ይገኛሉ።
➥በሁሉም ጤና ጣቢያዎች የአባላት መረጃ እየተሞላ ወደ server አየተላከ ውሏል።

02/12/2022

የጤና መድህን አዲስ አባላት ማፍራትና የነባር እድሳት ህዳር 30/2015 ዓ.ም እንደሚያበቃ ተገለፀ፡፡

አራዳ ህዳር 22/2015 ዓ.ም

የአራዳ ክፍለ ከተማ ጤና ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ሔኖክ ጌታቸው በክፍለ ከተማው የጤና መድህን አዲስ አባላት ማፍራትና የነባር አባላት እድሳት ተግባርን ከመስከረም 15 እስከ አሁን እየተከናወነ መሆኑን ገልፀው ለነባር አባላት ተደጋጋሚ የአድሱ መልዕክት በባንክ፣ በስልክና በቅስቀሳ ተሰርቷል ብለዋል፡፡

እንደ ክፍለ ከተማ በተሰራ ሰፊ የቅስቀሳ ስራ ለነባር አባላት 70 % እድሳት የተደረገ ሲሆን 95% አዲስ አባል ማፍራት ተችሏል ያሉት አቶ ሔኖክ 500 ብር ከፍሎ የጤና መድህን አገልግሎት ተጠቃሚ በመሆን ከብዙ የህክምና ወጪ መዳን ይቻላል ሲሉ ተናግረዋል፡፡

አቶ ሔኖክ አያይዘውም የጤና መድህን እድሳትና አዲስ የመመዝገብ ስራ ከህዳር 30/2015 ዓ.ም በኃላ ስለማይቀጥል በቀሩት ቀናት የአገልግሎቱ ተጠቃሚ ሁኑ ሲሉ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡
ለበለጠ መረጃ
የፌስቡክ ገፃችንን ይወዳጁ ይከተሉ
https://www.facebook.com/aradasubcityofficialpage/
የቴሌግራም ገጻችንን ይቀላቀሉ
https://t.me/aradacommunication
የዩቲዩብ ቻናላችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ
https://youtube.com/channelመ/UC06NEZgnlM2eBE13Em9GuXQ
የትዊተር ገፃችንን ይከተሉ
https://twitter.com/arada_subcity...
የቲክቶክ አካውንታችንን ይከተሉ
https://www.tiktok.com/?_t=8X6SAvUTMYQ&_r=1

በዛሬው ዕለት በአዲስ አበባ ጤና ቢሮ አመቻችነት ከድሬዳዋ ለልምድ ልውውጥ የመጡ የማዐጤመ አመራሮችን ➥ስለአራዳ ክ/ከተማ ማዐጤመ  ባንኪንግ ሲስተም አሠራር➥ስለአራዳ ክ/ከተማ የማዐጤመ አባላ...
28/11/2022

በዛሬው ዕለት በአዲስ አበባ ጤና ቢሮ አመቻችነት ከድሬዳዋ ለልምድ ልውውጥ የመጡ የማዐጤመ አመራሮችን

➥ስለአራዳ ክ/ከተማ ማዐጤመ ባንኪንግ ሲስተም አሠራር
➥ስለአራዳ ክ/ከተማ የማዐጤመ አባላት መረጃ አያያዝ እንዲሁም
➥የአባላት ማፍራት ጊዜን ስለማሳጠር ልምድ ሰጥተናል።
ስላገኙት ልምድም በጣም ተደስተው ሄደዋል። እኛም ደስ ብሎናል።

ቦታ ➥የአራዳ ክ/ከተማ ጤና ጽ/ቤት
➥በዓታ ጤና ጣቢያ

19/03/15 ዓ/ም

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የአራዳ ክ/ከተማ የማኅበረሰብ ዐቀፍ ጤና መድኀን ተቋም ቀደም ሲል ቤት ለቤት በመዞር በአደረጃጀቶች በኩል በደረሰኝ ሲሰበሰብ የነበረውን የገንዘብ አሰባሰብ ሥራ...
07/09/2022

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የአራዳ ክ/ከተማ የማኅበረሰብ ዐቀፍ ጤና መድኀን ተቋም ቀደም ሲል ቤት ለቤት በመዞር በአደረጃጀቶች በኩል በደረሰኝ ሲሰበሰብ የነበረውን የገንዘብ አሰባሰብ ሥራ በ2014 ዓ/ም ከገንዘብ ንክኪ ነፃ በማድረግ ሙሉ በሙሉ በባንክ ሲስተም ብቻ እንዲሆን በማድረግ ከፍተኛ የለውጥ ሥራን ሠርቷል።

ይህ አሠራር በጤና መድኅን የአሠራር ሥርዓት ብልሹ አሠራርን ከመቅረፉም ባሻገር ዘመናዊነትን የተላበሰ ነው።እንደ አራዳ ማዐጤመ ቀደምሲል ከኢትዮጵያ ጤና መድኅን አገልግሎት አአ ቅርንጫፍ በእምነት ተቀብሎ ከተጀመራቸው የአባላትን መረጃ የማዘመንና(CBHI Enrollment Appና) የቁርጥ ክፍያን(capitationን) ሥራ ሙሉበሙሉ ከመተግበር ባሻገር በአራዳ ክ/ከተማ ማዐጤመ ተቋም ባለቤትነት የተሠራ የለውጥ ሥራ ነው።

ሥራው ሲጀመር ማኅበረሰቡ አዲስ ሊሆንበት ስለሚችል የተለያዩ የግንዛቤ ማስጨበጫ ሥራዎችን በመሥራት እንዲሁም ከባንኮች ጋር የጋራ የውል ስምምነት ሰነድ በማዘጋጀት በቂ ዝግጅት ተደርጎበት የተሠራ ሥራ ነው።

ተሞክሮው ይበል የሚያስብል ሆኖ በመገኘቱ የአዲስ አበባ ክልል መስተዳደር ፐብሊክ ሰርቪስ ኃላፊ ወ/ሮ ሂክማ ኸይረዲን በተገኙበት በሙሉ ድምፅ ፀድቋል። በተለይም በአዲስ አበባ ጤና ቢሮ ማዐጤመ ዳይሬክቶሬት አመቻችነት ከአራዳ ክ/ከተማ ውጭ ባሉ 10ሩ ክ/ከተሞች ላይ እንዲሠፋ ከአራዳ ልምድ የተወሰደ ሲሆን አንዳንድ ክ/ከተሞች ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አዲስ አበባ ዲስትሪክቶች ጋር ውል እየተፈራረሙ ይገኛሉ።

ባንክ ሲስተሙ አባላቱ የቁጠባ ባህልን እንዲያዳብሩ ከማድረጉም በላይ የቅስቀሳ ሥራውንም ያቀለለ ሆኖ ተገኝቷል። እያንዳንዱ አባል ከጤና መድኅን ጋር በተያያዘ ቢያንስ በወር አንድ ጊዜ ይቆጥቡ የሚል አጭር የፅሁፍ መልዕክት እየደረሰው ይገኛል።

በተጨማሪም በተሞክሮው ዙሪያ በኢትዮጵያ ጤና መድኅን አገልግሎት ጋባዥነት ከተለያዩ ክልሎች ለመጡ የማኅበረሰብ ዐቀፍ ጤና መድኅን ተወካዮችና ባለድርሻ አካላት ሀገራዊ ስለሚሆንበት መንገድ ስለተሞክሮው ግንዛቤ ተሰጥቶ ውይይት ተደርጎበታል።

ሥራውን ያግዝ ዘንድ የእያንዳንዱን አባል የመዋጮ ተመን ሳይንሳዊ በሆነ መንገድ የሚያሰላ ዳታ ቤዝ ተዘጋጅቶ በጤና ተቋማት የማዐጤመ ባለሙያዎች እና የባንክ ኦፊሰሮች በኩል በከፍተኛ ሁኔታ ጥቅም ላይ እንዲውል ተደርጓል። ለ2015 ዓ/ም ደግሞ ከዳታቤዙ በመነሳት ሥራውን የበለጠ ለማቀላጠፍ እና ጥራት እንዲኖረው ለማስቻል "online" የማድረግ ሥራዎች በመጠናቀቅ ላይ ናቸው።

https://www.facebook.com/cbhiarada

በአራዳ ክ/ከተማ አስተዳደር ጤና ፅ/ቤት የማኅበረሰብ ዐቀፍ ጤና መድኅን ሥራ ሂደት ለጤና ጣቢያ የማዐጤመ ባለሙያዎች እና ሜዲካል ዳይሬክተሮች የ 3 ቀናት ግንዛቤ ማስጨበጫ ትምህርት ተሰጠ።➾...
04/09/2022

በአራዳ ክ/ከተማ አስተዳደር ጤና ፅ/ቤት የማኅበረሰብ ዐቀፍ ጤና መድኅን ሥራ ሂደት ለጤና ጣቢያ የማዐጤመ ባለሙያዎች እና ሜዲካል ዳይሬክተሮች የ 3 ቀናት ግንዛቤ ማስጨበጫ ትምህርት ተሰጠ።
➾የማኅበረሰብ ዐቀፍ ጤና መድኅን ምንነት
➾የክሊኒካል ኦዲት አሠራር
➾የአባላት ዲጂታል መረጃ አያያዝ
➾የቁርጥ ክፍያ አተገባበር እና
➾የባንኪንግ ሲስተም አሠራር አርዕስቶቹ ነበሩ።

ሠራተኞችን ተጠቃሚ የሚያደርግ ጤና መድኅን አገልግሎት ሊጀመር ነው ሰኔ 2/2014 (ዋልታ) የመንግሥት፣ የግል ተቋማትና መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ሠራተኞችን ተጠቃሚ የሚያደርግ የማኅበራዊ ...
22/07/2022

ሠራተኞችን ተጠቃሚ የሚያደርግ ጤና መድኅን አገልግሎት ሊጀመር ነው

ሰኔ 2/2014 (ዋልታ) የመንግሥት፣ የግል ተቋማትና መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ሠራተኞችን ተጠቃሚ የሚያደርግ የማኅበራዊ ጤና መድኅን አገልግሎት በሚቀጥለው ዓመት እንደሚጀመር ተገለጸ።

በኢትዮጵያ በየዓመቱ ለጤና አገልግሎት ከ127 ቢሊዮን ብር በላይ ወጪ እንደሚደረግ ተነግሯል፡፡

በ2015 ዓ.ም ተግባራዊ የሚሆነውን የማኅበራዊ ጤና መድኅን አገልግሎት አስመልክቶ ከባለድርሻ አካላት ጋር የምክክር መድረክ በአዳማ እየተካሄደ ነው።

አርሶ አደሮች፣ አርብቶ አደሮችና ዝቅተኛ ገቢ ያላቸው የኅብረተሰብ ክፍሎችን ተጠቃሚ የሚያደርግ የማኅበረሰብ ዐቀፍ የጤና መድኅን አገልግሎት ከጀመረ 10 ዓመታት አስቆጥሯል።

የኢትዮጵያ ጤና መድኅን አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ፍሬሕይወት አበበ ሠራተኞችን ተጠቃሚ የሚያደርግ ጤና መድኅን ከ2015 ዓ.ም ጀምሮ ተግባራዊ እንደሚሆን ማስታወቃቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

አገልግሎቱን ተግባራዊ ማድረግ የሚያስችል የሕግ ማዕቀፍ መዘጋጀቱንና በማዕቀፉ አማካኝነት ሠራተኞችና የሚሠሩበት ተቋም ዓመታዊ የጤና መድኅን መዋጮ በቅርቡ እንደሚወሰን ተናግረዋል።

ምንጭ ፦ ዋልታ ቴቪ

Address

Adwa Street
Addis Ababa
1000

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when የአራዳ ክ/ከተማ ማዐጤመ ተቋም - Arada Sub City CBHI Scheme posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to የአራዳ ክ/ከተማ ማዐጤመ ተቋም - Arada Sub City CBHI Scheme:

Share