Small and Medium Enterprise Finance Project - SMEFP

Small and Medium Enterprise Finance Project - SMEFP The SMEFP aims to increase access to finance for SMEs in Ethiopia through:(a) providing credit lines

19/05/2023
10/04/2023
በኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ልማት ም/ዋና ዳይሬክተር የተመራው የልኡካን ቡድን በጣሊያን ሃገር የተያዩ ከተሞች ሲያካሂድ የነበረውን የስራ ጉብኝት አጠናቆ ወደሃገሩ ተመለሰ፡፡=============...
01/11/2022

በኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ልማት ም/ዋና ዳይሬክተር የተመራው የልኡካን ቡድን በጣሊያን ሃገር የተያዩ ከተሞች ሲያካሂድ የነበረውን የስራ ጉብኝት አጠናቆ ወደሃገሩ ተመለሰ፡፡
======================================
የክልል የዘርፉ አመራሮችን ያካተተው የልኡካን ቡድኑ በጉብኝቱ ማጠቃለያ ላይ በጣሊያን የኢትዮጵያ ኤምባሲ በመገኘት ለኤምባሲው የስራ ኃላፊዎች ገለጻ አድርጓል፡፡ በዚሁ ውይይት ላይ ኤምባሲውን በመወከል የተገኙት ዶ/ር ካባ ኡርጌሳ በኢንዱስትሪ ልማት ዘርፍ እንደጣሊያን ካሉ አውሮፓ ሃገራት ሃገራችን ኢትዮጵያ በርካታ ተሞክሮዎችን መቅሰም እንደምትችል ጠቁመው የልኡካን ቡድኑ የቀሰማቸውን ልምዶች በመቀመርና ወደተግባር በመቀየር ረገድ ተጨባጭ ስራዎችን ማከናወን ይጠበቅበታል ብለዋል፡፡
የኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ልማት ም/ዋና ዳይሬክተርና የልኡካን ቡድኑ መሪ አቶ አብዱልፈታ የሱፍ በበኩላቸው ከጉብኝቱ በተለይ የኢንዱስትሪ ክላስተሮችን በማደራጀት ረገድ የአንዱ ምርት ለሌላው ግብዓት እንዲሆኑ በማድረግ እርስ በእርስ ማስተሳሰር የግብዓት ማጓጓዣ ወጪንና ጊዜን በመቆጠብ ረገድ ያለውን ፋይዳ መገንዘባቸውን ገልጸው በምርት ጥራትና ተረፈ ምርትን መልሶ ጥቅም ላይ በማዋል በኩልም ጠቃሚ ልምድ ማግኘታቸውን ተናግረዋል፡፡
በመጨረሻም አቶ አብዱልፈታ የልኡካን ቡድኑ የተገኙትን ተሞክሮዎች ወደሃገራችን ወስደን በመተግበር ረገድ የኢትዮጵያ ኢንተርፕራዝ ልማት ከክልል የዘርፉ ተቋማት ጋር በመቀናጀት እንደሚሰራ ጠቅሰው በጣሊያን የኢትዮጵያ ኤምባሲ ጉዞውን ከማመቻቸት ጀምሮ ጉብኝቱ እስከሚጠናቀቅ ድረስ ላደረገላቸው የቅርብ ድጋፍ ምስጋና አቅርበዋል፡፡
ልኡካን ቡድኑ ጉብኝቱን አጠናቆ ሰኞ ጥቅምት 21 ቀን 2015 ዓ.ም ወደ አዲስ አበባ ተመልሷል፡፡

የኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ልማትና የዘርፉ የክልል ቢሮ ኃላፊዎች የአምራች ዘርፉን ለመደገፍ የሚያስችል ጉብኝት በጣሊያን ሃገር በማካሄድ ላይ ናቸው።በኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ልማት ም/ዋና ዳይሬ...
28/10/2022

የኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ልማትና የዘርፉ የክልል ቢሮ ኃላፊዎች የአምራች ዘርፉን ለመደገፍ የሚያስችል ጉብኝት በጣሊያን ሃገር በማካሄድ ላይ ናቸው።
በኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ልማት ም/ዋና ዳይሬክተር አቶ አብዱልፈታ የሱፍ የተመራና ዘርፉን የሚመሩ የክልል አመራሮች የተካተቱበት የልኡካን ቡድን በጣሊያን ሃገር የተለያዩ ከተሞች የሚገኙና በቆዳና ተያያዥ ምርቶች ላይ የተሰማሩ ኢንተርፕራይዞችን በመጎብኘት ላይ ናቸዉ።
በጣሊያን የአምራች ኢንዱስትሪ ማእከል በሆነችው የፖዶቫ ክልል ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎችን በማግኘት የልምድ ልውውጡን የጀመረው የልዑካን ቡድኑ በክልሉ ም/ፕሬዚዳንት ቪቺንዞ ጉታርዶ እና የክልሉ ም/ቤት ተወካይ ፖውሎ ቤርቶ ስለክልሉ አጠቃላይ ገጽታ በተለይም በአምራች ዘርፍ ስላለው ሁኔታ ገለጻ ተደርጎበታል።
የልዑካን ቡድኑ ባለፉት አራት ቀናት ቆይታው በቪቼንዛና ሳንታ ክሩስ ሶላርኖ ከተሞች የሚገኙ የቆዳ ማልፊያና ማለስለሻ እንዲሁም ከቆዳ ተረፈ ምርት የአፈር ማዳበሪያ ማምረቻ ኢንዱስትሪዎች የጎበኘና ውይይት ያካሄደ ሲሆን በቀጣይ ሶስት ቀናትም ተጨማሪ የልምድ ልውውጦችን እንደሚያደርግ ይጠበቃል።

ሚላን-ጣሊያን

Address

Addis Ababa

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Small and Medium Enterprise Finance Project - SMEFP posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share