25/12/2025
የዳሽን ባንክ አክስዮን ማህበር የምዝገባ ማስታወቂያ
*********
በሰነደ ሙአለ ንዋይን ለህዝብ የማቅረብ እና ግብይት መመሪያ ቁጥር 1031/2016 አንቀጽ 4 እና 29 ላይ በመመሪያው ወይም በካፒታል ገበያ አዋጅ ቁጥር 1248/2013 ከምዝገባ ነጻ ከተደረጉ ውጪ ያሉ ለህዝብ የሚቀርቡ ወይም የሚሸጡ ሰነደ ሙአለ ንዋዮች በኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ ባለስልጣን መመዝገብ ያለባቸው በመሆኑ እና መመሪያው ከመውጣቱ በፊት በህዝብ የተያዙ ሰነደ ሙአለ ንዋዮችም ባለስልጣኑ መመዝገብ ያለባቸው መሆኑ ተደንግጎ ይገኛል፡፡
በዚህም መሰረት ባለስልጣኑ በታህሳስ 15 ቀን 2018 ዓ.ም. የዳሽን ባንክ አክስዮን ማህበርን የምዝገባ መግለጫ ያጸደቀ ሲሆን በዚህም መሰረት፡
➡️ በነባር ባለአክስዮኖች ተይዘው ያሉ አስራ አራት ሚሊዮን ሶስት መቶ ሰላሳ ሰባት ሺህ (14,337,000) አክስዮኖችን፤ እንዲሁም
➡️ በያዙት አክስዮን ድርሻ ልክ ለነባር ባለአክስዮኖች እና/ወይም ነባር ባለአክስዮኖች ሳይገዙ ከቀሩ ለብቁ ኢንቨስተሮች/ ለህዝብ የሚቀርቡ ሁለት ሚሊየን ሁለት መቶ ስድስት ሺህ ዘጠኝ መቶ ስድስት (2,206,906) አክስዮኖችን የመዘገበ መሆኑን ለህብረተሰቡ ለማሳወቅ ይወዳል፡፡
ማሣሠቢያ:
ማስታወቂያው ሰነደ ሙአለ ንዋይ ለመሸጥ ወይም እንዲሸጡ ለማድረግ የቀረበ ጥሪ አለመሆኑ፤
ይህ ማስታወቂያ የወጣው ሰነደ ሙአለ ንዋዮች በባለስልጣኑ መመዝገባቸውን ለሕዝብ ለማሳወቅ ብቻ ሲሆን፤ ማንኛውንም ሰነደ ሙአለ ንዋዮች ለመሸጥ የቀረበ ጥያቄ ወይም እንዲሸጡ ለማድረግ የቀረበ ጥሪ ወይም ማስታወቂያ አይደለም።
#ዳሸንባንክ