World Class Quality Award Organization

World Class Quality Award Organization award for an outstanding achievements that has saved the world and its peoples

10/05/2026

ግራንድ አፍሪካን የተቋማትና የአመራር ሽልማት ድርጅት፣ የማህበራዊ ሚዲያ ማኔጅመንት እና የዌብሳይት ግንባታ አገልግሎቶችን የሚሰጡ ብቁ ድርጅት ወይም ባለሙያዎችን ማሰራት ይፈልጋል።• የማህበራ...
08/05/2026

ግራንድ አፍሪካን የተቋማትና የአመራር ሽልማት ድርጅት፣ የማህበራዊ ሚዲያ ማኔጅመንት እና የዌብሳይት ግንባታ አገልግሎቶችን የሚሰጡ ብቁ ድርጅት ወይም ባለሙያዎችን ማሰራት ይፈልጋል።
• የማህበራዊ ሚዲያ ማኔጅመንት፡
o የድርጅታችንን የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች (Facebook, Instagram, LinkedIn, YouTube, TikTok) ማስተዳደር እና ይዘቶችን ማፍለቅ።
o የጥራት እና ወቅታዊ ይዘቶችን በማዘጋጀት የተጠቃሚዎችን ተሳትፎ ማሳደግ /Boosting/።
o የማህበራዊ ሚዲያ ማስታወቂያዎችን በማዘጋጀት እና በማስተዳደር የድርጅቱን ስም እና አገልግሎቶች ለሰፊው ህዝብ ማስተዋወቅ።
o የማህበራዊ ሚዲያ አጠቃቀምን በተመለከተ ወቅታዊ መረጃዎችን እና ግንዛቤዎችን በማቅረብ ድርጅቱ በዲጂታል ዓለም የበላይነቱን እንዲያገኝ ማስቻል።
• የዌብሳይት ግንባታ፡
o የድርጅታችንን የዌብሳይት ግንባታ እና ጥገና ማከናወን።
o የጥራት እና የተጠቃሚ-ተስማሚ ዌብሳይት በመገንባት የድርጅቱን አገልግሎቶች እና ሽልማቶችን ለሰፊው ህዝብ ማስተዋወቅ።
o የዌብሳይት አጠቃቀምን በተመለከተ ወቅታዊ መረጃዎችን እና ግንዛቤዎችን በማቅረብ ድርጅቱ በዲጂታል ዓለም የበላይነቱን እንዲያገኝ ማስቻል።
• ሌሎች መስፈርቶች፡
o ለግለሰቦች በዘርፉ ቢያንስ የሁለት ዓመት የስራ ልምድ ያለው። በተጨባጭ የሰሯቸውን የስራ ልምዶች ማቅረብ የሚችሉ፡፡
o ለስራው አፈጻጸም ፕሮፖዛል ሰርተው የሚያቀርቡ፡፡
o ለድርጅቶች ህጋዊ ፈቃድ ያላቸው፡፡ ቢሮና አድራሻ ያላቸው፡፡
o ለስራው ውል መዋዋል የሚችሉ፡፡
o የሰሯቸውን ስራዎች ናሙና የሚያቀርቡ፡፡
o ለስራው አፈጻጸም ፕሮፖዛል ሰርተው የሚያቀርቡ፡፡
ለተጨማሪ መረጃ በስራ ሰዓት በ0911-24 83 68 ደውለው ይጠይቁ፡፡









ማስታወቂያየአዲስ አበባ ከተማ ቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን ከተማ አስተዳደሩ በልዩ ትኩረት እየተገበረ ለሚገኝው መጠነ ሰፊ የቤት ልማት ፕሮግራም በግንባታው ዘርፍ ላይ የተሰማሩ እና መስፈርቱን የሚ...
07/05/2026

ማስታወቂያ

የአዲስ አበባ ከተማ ቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን ከተማ አስተዳደሩ በልዩ ትኩረት እየተገበረ ለሚገኝው መጠነ ሰፊ የቤት ልማት ፕሮግራም በግንባታው ዘርፍ ላይ የተሰማሩ እና መስፈርቱን የሚያሟሉ ስራ ተቋራጮችን አወዳድሮ ለማሰራት ይጋብዛል ፡፡

በዚህም መነሻ

1. ለስራ ተቋራጮች ምዝገባ መሟላት
ያለባቸው መረጃዎች፡-

ሀ) የታደሰ የንግድ ፍቃድ ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሰርተፍኬት ፣ የታደሰ የብቃት ማረጋገጫ ምዝገባ ሰርተፍኬት እና የአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ ስለመመዝገቡ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል፤

 በምዝገባው ወቅት የሰነዶቹን ዋና እና አንድ የማይመለስ ቅጂ በአካል የሚቀርብ ሆኖ የስራ ተቋራጩ የበላይ ኃላፊ ባለቤት ወይም ህጋዊ ውክልና ያለው ተወካይ ፊርማ እና የድርጅቱ ህጋዊ ማህተም በማድረግ ማቅረብ ይጠበቅበታል፡፡

2. ደረጃ 1 እና 2 (ህንፃ (BC) እና ጠቅላላ ስራ ተቋራጭ(GC)) እንዲሁም ደረጃ- 3 (ጠቅላላ ስራ ተቋራጭ (GC)) የብቃት ማረጋገጫ ያላቸው በግንባታው ዘርፍ ላይ የተሰማሩ ስራ ተቋራጮች ተሳታፊ መሆን ይችላሉ

3. ከዓርብ ሚያዝያ 30 ቀን 2018 ዓ/ም ከጠዋቱ 2፡30 ጀምሮ ቅዳሜን ጨምሮ ለ5 (አምስት) ተከታታይ የስራ ቀናት ( እስከ ዕሮብ ግንቦት 5 ቀን 2018 ዓ/ም ከሰዓት እስከ 11፡30)) በአካል በመቅረብ በኮርፖሬሽኑ 11ኛ ወለል በሚገኝ አዳራሽ ላይ ምዝገባ በማድረግ መረጃዎቹ መሟላታቸው በመዝጋቢው ሲረጋገጥ ለዚሁ የተዘጋጀ የቴክኒካል ሰነድ መግዛት ይቻላል፤

4. ተገቢውን ሰነድ በማቅረብ የምዝገባ ሂደቱን በሚገባ ያሟላ ስራ ተቋራጮችን በተመለከተ ምዝገባው በተጠናቀቀ በ 24 ሰዓት ውስጥ ግንቦት 6 ቀን 2018 ዓ/ም በተቋሙ ማህበራዊ ድህረ ገጽ እና በኮርፖሬሽኑ የማስታወቂያ ቦርድ 11ኛ ወለል የሚለጠፍ ይሆናል፡፡

5. ስራ ተቋራጮች የቅድመ ምዝገባ ውጤት ከታወቀበት ቀን ቅዳሜን ጨምሮ በአስር (10) ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ አንድ ኦርጅናል እና ሁለት ቅጂ የቴክኒካል ፕሮፖዛላችሁን ለዚሁ በተዘጋጀ ሳጥን እስከ ቀን ግንቦት 18 ቀን 2018 ዓ/ም ከሰዓት 10፡00 ድረስ ብቻ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡

6. ስራ ተቋራጮች ለምዝገባ እና ለቴክኒካል ሰነድ ግዢ
የማይመለስ ብር

ለደረጃ 1 ...........ብር 7500
ለደረጃ 2 .......... ብር 6500
ለደረጃ 3 ...........ብር 5500 መክፈል ይጠበቅባቸዋል፡፡

አድራሻ

 ቂርቆስ ክ/ተማ ወረዳ 01
ባምቢስ አከባቢ ግሪክ ት/ቤት ፊት ለፊት በሚገኘው
የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት አስተዳደር ህንፃ ላይ ፦

ለተጨማሪ የመረጃ አማራጭ፦
https://linktr.ee/aahdc

የቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን ኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት

ሚያዝያ 29 ቀን 2018 ዓ/ም

ሊያመልጥዎ የማይገባ ታላቅ የገለጻና ውይይት መድረክ!             *****************የኢትዮጵያ ሳይንስ አካዳሚ ወቅታዊና ሀገራዊ ፋይዳ ባላቸው ጉዳዮች ላይ ሳይንሳዊ ውይይቶችን...
06/05/2026

ሊያመልጥዎ የማይገባ ታላቅ የገለጻና ውይይት መድረክ!
*****************
የኢትዮጵያ ሳይንስ አካዳሚ ወቅታዊና ሀገራዊ ፋይዳ ባላቸው ጉዳዮች ላይ ሳይንሳዊ ውይይቶችን የማካሄድ ተልዕኮውን መሠረት በማድረግ “የገጠር ትራንስፎርሜሽን በኢትዮጵያ: ከግብርና ወደ መዋቅራዊ ሽግግር ትልም’’ በሚል ርዕስ የገለጻና ውይይት መርሐግብ አዘጋጅቷል።

በዕለቱም የኢትዮጵያ ግብርና ትራንስፎርሜሽን ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ማንደፍሮ ንጉሤ ሰፊ ገለጻ የሚያደርጉ ሲሆን፣ በኢትዮጵያ ሳይንስ አካዳሚ ፕሬዝዳንት በፕሮፌሰር በላይ ካሳ አወያይነት ውይይቱ ይመራል።

ስለሆነም የዘርፉ ባለሙያዎች፣ ጋዜጠኞችና ጥሪ የተደረገላችሁ እንግዶች በሙሉ በተጠቀሰው ቀንና ሰዓት በአካል በመገኘት በውይይቱ ላይ እንድትሳተፉ በአክብሮት ተጋብዘዋል።
መርሐ-ግብሩ፦
🗓ቀን፦ ነገ ሐሙስ ሚያዝያ 29 ቀን 2016 ዓ.ም
⏰ሰዓት፦ ከቀኑ 10፡00 ሰዓት ጀምሮ
📍ቦታ፦ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ፣ 5 ኪሎ ካምፓስ (AAiT) አዳራሽ
በአካል መገኘት ለማትችሉ በዙም (Zoom) ወይም በፖስተሩ ላይ ያለውን QR code በመጠቀም መከታተል ትችላላችሁ፦
የZoom አድራሻ፦
🔗Link: https://us06web.zoom.us/j/87449049928?
pwd=o6WgdwZJsmMK88hbsRVDGf8aIOs6ZH.1
💡Meeting ID: 874 4904 9928
🗝Passcode: 378609

05/05/2026

04/05/2026

                                 ቀን 19/08/ 2018 ዓ.ምበዚህ ማስታወቂያ የሚቀጠሩ ሰራተኞች የግራንድ አፍሪካን የተቋማትና አመራር ሽልማት ድርጅት እናየወርልድ ክላስ ...
27/04/2026



ቀን 19/08/ 2018 ዓ.ም
በዚህ ማስታወቂያ የሚቀጠሩ ሰራተኞች የግራንድ አፍሪካን የተቋማትና አመራር ሽልማት ድርጅት እና
የወርልድ ክላስ የጥራት ሽልማት ድርጅት ስራዎችን በዋና መስሪያ ቤት ደረጃ የሚሰሩ ይሆናሉ፡፡
1. የምዘና ዘርፍ ሥራ አስኪያጅ
የት/ት ደረጃ፡- PH.D in any field የ15 ዓመት የስራ ልምድ ያላቸው፡፡ ደሞዝ፡- 40,500 ብር
የት/ት ደረጃ፡- PH.D in any field የ8 ዓመት የስራ ልምድ ያላቸው፡፡ ደሞዝ፡- 35,500 ብር
የስራው ጊዜ፡- የሙሉ ጊዜ ቋሚ ሰራተኛ እድሜ፡- ከ35 - 60 ብዛት፡-1 ፆታ፡- አይለይም
2. የቅርንጫፍ ስራ አስኪያጅ
የት/ት ደረጃ፡- በሥራ አመራር መስኮች በመጀመሪያ ዲግሪ የተመረቁ የ5 ዓመት የስራ ልምድ ያላቸው፡፡ ደሞዝ :- 30,500 ብር
በሥራ አመራር መስኮች በሁለተኛ ዲግሪ የተመረቁ የ3 ዓመት የስራ ልምድ ያላቸው፡፡ ደሞዝ:-35,500 ብር
ከፍተኛ የኮምፒውተር ጽሁፍ ችሎታ ያላቸው፡፡
እድሜ፡- ከ30 - 45 ብዛት፡- 4 ፆታ፡- አይለይም
3. የጥራት ሽልማት ምዘና ሙያተኛ :-
የጤና ፣ የአምራች ኢንዱስትሪ ፣ የትምህርት ፣ ለግብር ፣ ለአገልግሎት ሰጪ እና የንግድ ዘርፎች፡፡
ተፈላጊ የቋሚ ሰራተኛ ብዛት፡-18
ተፈላጊ የ2 ወራት የኮንትራት ሰራተኞች ብዛት፡-17

የመዛኞች የስራ መደቦች ተፈላጊ ብቃቶች

#የመጀመሪያ ዲግሪ ላለቸው በተመረቁበት ሙያ የ10 ዓመታት የስራ ልምድ ያላቸው፡፡ የመነሻ ደሞዝ፡- 30,500 ብር
#በዘርፋቸው ማስተርስ ዲግሪ ያላቸው እና በተማሩበት ሙያ የ5 ዓመት የስራ ልምድ ያላቸው፡፡ የመነሻ ደሞዝ፡- 35,500 ብር
.D in any field እና በተማሩበት ሙያ የ5 ዓመት የስራ ልምድ ያላቸው፡፡ የመነሻ ደሞዝ፡- 40,500 ብር
.D in any field እና በተማሩበት ሙያ የ15 ዓመት የስራ ልምድ ያላቸው፡፡ የመነሻ ደሞዝ፡- 45,500 ብር
#ከፍተኛ የእንግሊዘኛ ማንበብና ተንትኖ መፃፍ ችሎታ ያላቸው፡፡
#እድሜ፡- ከ30-65 ፆታ፡- አይለይም
ከፍተኛ የኮምፒውተር ጽሁፍ ችሎታ ያላቸውና የምዘና ስራዎች በላፕቶፕ መስራትና ማቅረብ የሚችሉ፡፡
የምዘና ስራ ዘርፍ አመ ልካቾች በድርጅታችችን ለዘርፉ የተዘጋጀውን ስልጠና መውሰድ ግዴታ ሲሆን ለስልጠናውም በስልጠናው ሒደት ተቋማችን የሚከፍላችሁ ክፍያ አይኖርም ከሰልጣኞቹም ክፍያ አይቀበልም፡፡
ከስልጠናው በኋላ ፈተና የምንሰጥ ሲሆን የላቀ ውጤት ያመጡት በያመለከቱበት ደረጃ ይቀጠራሉ፡፡

4. የሽልማት እጩ ምልመላ የመስክ ሰራተኛ
የትምህርት ደረጃ፡- በማንኛውም ሙያ በመጀመሪያ ዲግሪ የተመረቁ፡፡ ደሞዝ:- 20.500 ብር
ዲፕሎማ እና 10/12ኛ ክፍል ላጠናቀቁት የ2 ዓመታት የተፃፈ የስራ ልምድ ያላቸው፡፡ ደሞዝ:- 16.500 ብር
ከፍተኛ የንግግርና የማስረዳት ችሎታቸው ያላቸው፡፡
ብዛት፡- 42 እድሜ፡- ከ25 - 45 ፆታ፡- ወንድ

5. የሰው ኃይል ምልመላና ስልጠና ሰራተኛ
የት/ት ደረጃ፡- በተዛማጅ መስኮች በመጀመሪያ ዲግሪ የተመረቁ፡፡ የስራ ልምድ፡- 5 ዓመት የስራ ልምድ ደሞዝ:- 25,500 ብር
የት/ት ደረጃ፡- በተዛማጅ መስኮች በመጀመሪያ ዲግሪ የተመረቁ፡፡ የስራ ልምድ፡- 2 ዓመት የስራ ልምድ ደሞዝ:- 20,500 ብር
የት/ት ደረጃ፡- በቴክኒክና ሙያ በተዛማጅ መስኮች በደረጀ 3/4 የተመረቁ፡፡ የስራ ልምድ፡-1 ዓመት የስራ ልምድ ደሞዝ:- 17,500 ብር
እድሜ፡-ከ28-45 ብዛት፡-2
ፆታ፡-አይለይም

6. የቪዲዮ ኢዲቲንግ እና የግራፊክስ የሙያተኛ
የትምህርት ደረጃ፡- በዘርፉ የሰለጠኑና በተግባር መስራት የሚችሉ የስራ ናሙና ማቅረብ የሚችሉ፡፡
ደሞዝ:- 25,500 ብር እድሜ፡- ከ25-40 ብዛት፡- 2 ፆታ፡- አይለይም
የስራው ጊዜ፡- የሙሉ ጊዜ ሰራተኛ

7. የ ISO አሰልጣኝ እና የጥናትና ምርምር ሙያተኛ
#የት/ት ደረጃ፡- PH.D IN RELATED FIELD የ10 ዓመት የስራ ልምድ ያላቸው፡፡ደሞዝ፡-55,500 ብር
# የት/ት ደረጃ፡-ማስተርስ ዲግሪ ያላቸውና ደሞዝ፡- 40,500 ብር
በተለያዩ የ ISO ዘርፎች የማሰልጠንና ሲስተም የመዘርጋት የ4 ዓመት የስራ ልምድ ያላቸው፡፡
በQUALITY MANAGEMENT SYSTEM DEVELOPMENT AND IMPLEMENTATION እና
QUALITY MANAGEMENT SYSTEM AUDIT እና በሌሎችም የISO መስኮች ስልጠና የወሰዱና ሰርተፊኬት ያላቸው፣
የስራው ጊዜ፡- የሙሉ ጊዜ ሰራተኛ እድሜ፡- ከ30-65 ብዛት፡- 2 ፆታ፡- አይለይም

8. የስራ አመራር ፣ የንግድ ስራ እና ስትራቴጂ አሰልጣኝ ፣
የት/ት ደረጃ፡- PH.D IN RELATED FIELD የ10 ዓመት የስራ ልምድ ያላቸው፡፡ ስትራቴጀክ ፕላን መቅረፅ የሚችሉ!
የአመራርና የቢዝነስ ስልጠናዎች የመስጠት ልምድ ያላቸው ፣ አሰልጣኝ ለመሆን የሚያበቃቸውን ፕሮፖዛል ሰርተው የሚያቀርቡ!
ደሞዝ፡- 60,500 ብር እድሜ፡- ከ35-60 ብዛት፡-1 የስራው ጊዜ፡- የሙሉ ጊዜ ሰራተኛ ፆታ፡- አይለይም

9. የደንበኞች አገልግሎት / ጀማሪ / ከፍተኛ/
የት/ት ደረጃ፡- በማንኛውም ሙያ በመጀመሪያ ዲግሪ የተመረቁ፡፡ ጥሩ የኮምፒውተር ችሎታ ያላቸው፡፡ የንግግር ችሎታቸው ከፍተኛ፡፡
ደሞዝ:- 30,000 ብር የስራ ልምድ፡- የ4 ዓመታት ቀጥተኛ የስራ ልምድ ፆታ፡- አይለይም እድሜ፡- ከ30-45 ብዛት፡- 2

10. የሒሳብ ሰራተኛ / አካውንታንት
የት/ት ደረጃ፡- በአካውንቲንግ በደረጃ ሶስትና ከዛም በላይ የተመረቁ፡፡ ብዛት፡- 1
ደሞዝ:- 20,500 ብር እድሜ፡- ከ25-45 ፆታ፡- አይለይም የስራ ልምድ፡- የ4 ዓመታት ቀጥተኛ የስራ ልምድ

11. የገበያ ጥናትና ሽያጭ ባለሙያ
የት/ት ደረጃ፡- በማርኬቲንግ በመጀመሪያ ዲግሪ የተመረቁ፡፡ በተለያዩ ተቋማት የገበያና የንግድ ትስስር ላይ የሚሰሩ፡፡
ደሞዝ:- 25,500 ብር የስራ ልምድ፡- የ4 ዓመታት ቀጥተኛ የስራ ልምድ እድሜ፡- ከ30-45 ብዛት፡- 2 ፆታ፡- አይለይም

12. የመጽሔት ዝግጅት ሙያተኛ
የት/ት ደረጃ፡- በተዛማጅ መስኮች በመጀመሪያ ዲግሪ እና የ2 ዓመት የስራ ልምድ ያላቸው፡፡
አማርኛ እና እንግሊዝኛ እጅግ በጥሩ ሁኔታ የሚናገሩ፣ የስነ-ጽሁፍ ችሎታ ያላቸውና የጽሁፍ አርትኦት ብቃት ያላቸው፣
ደሞዝ:- 25,500 ብር እድሜ፡- ከ30-45 ብዛት፡- 2 ፆታ፡- አይለይም የስራው ጊዜ፡- የሙሉ ጊዜ ሰራተኛ

13. የዌብ ሳይት እና ማህበራዊ ሚዲያ ሙያተኛ
የትምህርት ደረጃ፡- በማንኛውም ሙያ በመጀመሪያ ዲግሪ የተመረቁ፡፡ የስራ ልምድ ያላቸው፡፡
ደሞዝ፡- 30,500 ብር እድሜ፡- ከ25-40 ብዛት፡- 2 ፆታ፡- አይለይም

14. የህግ ሙያተኛ / የድርጅቱ የህግ ክፍል ረዳትና ዋና የሚሰሩ/
የትምህርት ደረጃ፡- በህግ በመጀመሪያ ዲግሪ የተመረቁ፡፡ ከሁለት ዓመት በላይ የስራ ልምድ ያላቸው::
ደሞዝ:- 25,500 ብር ብዛት፡- 1 ፆታ፡- አይለይም እድሜ፡- ከ30–50 የስራ ልምድ፡- የ4 ዓመታት ቀጥተኛ የስራ ልምድ

15. ጀማሪ የስልክ ኦፕሬተር እና እንግዳ አቀባበል ሰራተኛ
የትምህርት ደረጃ፡- 10ኛ ወይም 12ኛ ክፍል ያጠናቀቁ ወይም /የቴ/ሙያ ዲፕሎማ ያላቸው
ደሞዝ:- 14,500 ብር እድሜ፡- ከ24 - 45 ብዛት፡- 12 ፆታ፡- ሴት

16. ከፍተኛ የስልክ ኦፕሬተር እና እንግዳ አቀባበል ሰራተኛ
የትምህርት ደረጃ፡- በማንኛውም ሙያ በመጀመሪያ ዲግሪ የተመረቁ፡፡
ደሞዝ:- 17,500 ብር እድሜ፡- ከ27 - 45 ብዛት፡- 10 ፆታ፡- ሴት

# ለማመልከት ስትመጡም ሆነ በስራ ወቅት የድርጅቱ አለባበስ መመሪያ ፡-
#ለሴቶች፡- ስርአት ያለው የሴቶች አለባበስ ቀሚስ ወይም ጨርቅ ኮትና ሱሪ ያሟሉ፡፡
#ለወንዶች፡- ሸሚዝ ፣ ክራቫት ፣ ጨርቅ ሱሪና ኮት ቆዳ ጫማ በአጭር የተስተካከለ ፀጉርና ፂም ግዴታ ነው፡፡
#ማሳሰቢያ ፡- አመልካቾች የት/ት ማስረጃችሁን ከ10/12ኛ ክፍል ጀምሮ እና ተዛማጅ ማስረጃችሁን ኦሪጂናል እና ኮፒ ይዘው ይቅረቡ፡፡
CV ፣ ማመልከቻና ለቅጥር ለማለፍ ይጠቅመኛል ያሉትን ማስረጃ የማይመለስ ፎቶ ኮፒ በአካል ቢሮ በማቅረብ አመልክቱ፡፡
አመልካቾች ብሔራዊ መታወቂያ ካርድ ፣ የመንግስት ድርጅት ሰራተኛ የሆነ ተያዥ ያስፈልጋችኋል፡፡
የማታና የእረፍት ቀናት ትምህርት ያላቸውና በሌሎች ተቋማት በስራ ላይ ያሉትን አንቀጥርም፡፡
#የመመዝገቢያ ጊዜ:- 19 / 08 / 2018 ዓ.ም እስከ 20 / 09 / 2018 ዓ.ም ድረስ
#አድራሻ፡- ቦሌ መድሃኒያለም ኢድናሞል አካባቢ / አለምነሽ ፕላዛ 8ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 801
#ለተጨማሪ መረጃ :- 0966 – 00 85 85 /
0966 – 72 7070

https://t.me/worldclassqualityawardethiopia

24/04/2026

ተቀጥራችሁ የምትሰሩ ሰራተኞች ሁሉ ልታውቁት የሚገባ
: አዲስ የሰበር አቋም!
🔑🔑🔑🔑🔑
ለ5 ተከታታይ ቀናት ያለፈቃድ ከስራ የቀረ ሰራተኛ
ያለማስጠንቀቂያ ከስራ መሰናበት ያለበት ስለመሆኑ
በ7 ዳኞች የተሰጠ ትርጉም!

1. ሰበር በ7 ዳኞች መጋቢት 28 ቀን 2018 ዓ.ም በሰ/መ/ቁ 271726 የተሰጠው አስገዳጅ ትርጉም ከዚህ በፊት በሰ/መ/ቁ 249795 ሰራተኛው ለተከታታይ 5 ቀናት ቢቀር እንኳን ከስራ ለቀረበት ለእያንዳንዱ ቀን አሰሪ ማስጠንቀቂያ ሳይሰጥ የስራ ውልን ማቋረጥ እንደማይችል ተይዞ የነበረውን የሰበር አቋም የቀየረ ብሎም በሰራተኞች የስራ ደህንነት ላይ አሉታዊ ውጤት የሚኖረው ነው፡፡

2. ሰበር በ7 ዳኞቹ በያዘው አዲስ አቋሙ ሰራተኛ ያለፈቃድ ለ5 ተከታታይ ቀን ከቀረ ያለማስጠንቀቂያ ማሰናበትን የሚፈቅድ ይዘት በአዋጅ 1156 ላይ የለም ብሏል ፡፡

3. ይህ አዲስ አቋም የአንቀጽ 27 (1)(ለ) ይዘት በዚህ አዋጅ ከተመለከቱ እረፍቶችና ልዩ ልዩ ፈቃዶች ውጭ የጽኁፍ ማስጠንቀቂያ እየተሰጠው በስድስት ወር ውስጥ ለ5 ቀናት ከስራ መቅረት ለአሰሪው የስራ ውልን ያለማስጠንቀቂያ ለማቋረጥ ያስችለዋል የሚል ነው።

ነገር ግን የዚህ አንቀፅ ይዘት በግልፅ የሚያመለክተው አሰሪው የሰራተኛውን ከስራ መቅረት ለስራ ስንብት መነሻ ሊያደርግ የሚችለው ሰራተኛውን ለማረም የፅሁፍ ማስጠንቀቂያ ከሰጠ በኋላ ስለመሆኑ ብቻ ነው።

ከዚህ አንጻር የጽኁፍ ማስጠንቀቂያ ሳይደርሰው ከስራ ቀርቷል በሚል የስራ ውልን ያለማስጠንቀቂያ ለማሰናበት የህግ መሰረት አለ ወይ? የሚለው ትልቅ ጥያቄ ነው፡፡

4. የሰበር ሰሚ ችሎቱ በ7 ዳኞች አዲስ ለሰጠው አስገዳጅ ትርጉም መነሻ ያደረጋቸው አመክንዮዎች የሚከተሉት ናቸው፡-

4.1. በአንቀጽ 27 (1)(ለ) ሰራተኛው በተከታታይ ለ5 ቀናትና ከዚያ በላይ ለሆነ ጊዜ ፈቃድም ሆነ እረፍት ሳይሰጠው ከስራ ቢቀር አሰሪው የስራ ውሉን ያለ ማስጠንቀቂያ ከማቋረጡ በፊት ለሰራተኛው የጽኁፍ ማስጠንቀቂያ መስጠት አስገዳጅ ቅድመ ሁኔታ ስለመሆኑ አይደነገግም፡፡ (የ7 ዳኞች አዲስ አቋም)

4.2. በአዋጁ አንቀጽ 27(1)(2) ላይ የተመለከተው የጽኁፍ ማስጠንቀቂያ ሰራተኛው ያለፈቃድ ከስራ ከቀረ በኋላ ወደ ስራው ሲመጣ ለወደፊት ተመሳሳይ ጥፋት እንዳፈጽም ተገልጾ የሚሰጥ ማስጠንቀቂያ እንደመሆኑ መጠን ለ5 እና ተከታታይ ያለ ፈቃድ ለቀረ ሰራተኛ ጥፋቱን እንዳይደግም በመግለጽ ሰራተኛው ከስራ ለቀረበት ለእያንዳንዱ ቀን በአንቀጽ (27)(1)(ለ) ላይ የተመለከተውን ማስጠንቀቂያ መስጠት የሚቻል አይደለም፡፡

ለዚህ ድምዳሜ ምክንያት በሚል የተሰጠው ደሞ ሰራተኛው ከ5 ተከታታይ ቀናት በላይ ከቀረ በኋላ ሰራተኛውን አግኝቶ ያለፈቃድ ከስራ ከመቅረት ጥፋቱ እንዲታረም አስሪው የጽኁፍ ማስጠንቀቂያ ለመስጠት አሰሪው እድል ሊያገኝ አይችልምና የሚል ነው፡፡

4.3. ከዚህም ባሻገር የጥፋት ተግባሩን እየቀጠለ ያለንና ገና ወደ ስራ ገበታው ያልተመለሰን ሰራተኛን ጥፋቱን እንዳይደግም ወይም ለወደፊቱ ከጥፋቱ እንዲታረም ተገልጾ የጽኁፍ ማስጠንቀቂያ (Warning in writing) እንዲሰጠው አሰሪውን ማስገደድ ከስረ አመክንዩ (logic) አኳያ ሲታይም አሳማኝነት ያለው አይደለም፡፤ የሚቻል አይደለም የሚለውን ነጥብ አንስተዋል፡፡

4.4. በተጨማሪም ለተከታታይ 5 ቀናት ያለ በቂ ምክንያት ከስራ መቅረት ሌላ ምንም አይነት ቅድመ ሁኔታ ሳይኖር አሰሪው ያለማስጠንቀቂያ የስራ ውልን እንዲያቋርጥ የሚያስችለው ስለመሆኑ አዋጅ ቁጥር 1156/2011 ከመታወጁ በፊት በስራ ላይ በነበረው አዋጅ ቁጥር 377/1996 አንቀጽ 27(1)(ለ) በግልጽ ተደንግጎ የሚገኝ ነው አዋጅ 1156/2011 ለ5 ተከታታይ የስራ ቀናት ስለቀረ ሰራተኛ ሊኖው ስለሚገባ ውጤት ምንም አይልም የሚለውንም አንስተዋል፡፡

4.5. በሌላ በኩል ህጉ ግልጽነት ሲጎድለው ጠቅላላን የህጉን ይዘትና አቀራረጽ መሰረት በማድረግ ክፍተቱን በትርጉም መሙላት አስፈላጊ ስለመሆኑ አንስተው፡፡ የአዋጅ 1156 አንዱ አላማ አሰሪና ሰራተኛ የጋራ ራእይ ኖሯቸው ለድርጅቱ ምርታማነት እንዲሰሩ ስለመሆኑ ሰራተኛ የስራ ሰአትና የስራ ዲሲፒሊን አክብሮ ስራውን የመሰይሰራ ከሆነ አሰሪው ተወዳዳሪ ሊሆን አይችልም የሚለውም ለአዲሱ የ7 ዳኞች የሰበር አቋም ሌላ መነሻ ሆኗል፡፡

4.6. በመጨረሻም ሰበር የ1156ን የረቂቅ ህጉን አጭር ማብራሪያና ሀተታ ዘምክንያት ለአዲስ አቋሙ መነሻ ማድረጉ ተመልክቷል፡፡

5. እነኚህን ከላይ የተመለከቱትን ምክንያቶችን በመዘርዘር በሰ/መ/ቁ 249795 ሰበር ይዞት የነበረውን ሰራተኛው በተከታታይ ከ5 ቀናት በላይ ለሆነ ጊዜ ቢቀር እንኳን አሰሪው ሰራተኛው ከስራ ለቀረበት ለእያንዳንዱ ቀን ማስጠንቀቂያ ሳይሰጥ የስራ ውልን ማቋረጥ እንደማይችል ሰጥቶ የነበረውን አስገዳጅ ትርጉም ለውጦ በ7 ዳኞች መጋቢት 28 ቀን 2018 ዓ.ም በሰ/መ/ቁ 271726 በሰጠው አዲስ አስገዳጅ ትርጉም መሰረት የአዋጅ ቁጥር 1156/2011 አንቀጽ 27/1/ለ ድንጋጌ ሰራተኛው በዚሁ አዋጅ ከተመለከቱ እረፍቶችና ልዩ ልዩ ፈቃዶች ውጪ ለአምስት ተከታታይ የስራ ቀናትና ከዚያ በላይ ለሆነ ጊዜ ከስራ ላይ ከቀረ የጽሁፍ ማስጠንቀቂያ መስጠት ሳያስፈልግ የስራው ውልን ያለ ማስጠንቀቂያ ማቋረጥ ይችላል የሚል አቋም ወስዷል፡፡

ስለሆነም ሰራተኞች ይህን አዲስ የሰበር 7 ዳኞች አስገዳጅ ትርጉም መገንዘብና መጠንቀቅ ያስፈልጋቸዋል።

Legal Eagles Law Firm LLP Seble Asefa #ጠበቃ #ሕግምክር #ጠበቃሰብለአሰፋ

Address

Djibouti Street
Addis Ababa

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when World Class Quality Award Organization posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to World Class Quality Award Organization:

Share