04/06/2026
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እና የኢትዮጵያ አየር መንገድ አዲስ የቪዛ ዓለም አቀፍ የክፍያ ካርድ ይፋ አደረጉ
****
ማምሻውን በስካይ ላይት ሆቴል በተዘጋጀ መርሀ ግብር የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እና የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከቪዛ ኩባንያ ጋር በመተባበር ይፋ ያደረጉት የክፍያ ካርድ ደንበኞች በውጭ ሀገራት ቆይታቸው በቀላሉ ክፍያ እንዲፈጽሙ የሚያስችል ነው።
የኢትዮጵያ አየር መንገድ የሼባ ማይልስ አባላት የሆኑ መንገደኞች በሚደርሱበት ማንኛውም የዓለም መዳረሻ ካርዱን በሽያጭ መፈጸሚያ ማሽን (POS) ወይም ለኦንላይን ግብይት በሚጠቀሙበት ጊዜ ተጨማሪ የጉዞ ማይል ሽልማት እንደሚያስገኝላቸው ታውቋል፡፡