Finot Saving and Credit Association

Finot Saving and Credit Association Finot saving and credit association provides saving and credit services in different products to help its members and the society.

and the most aim of the association is to participate in different big projects in the country.

13/06/2024
አልመን እንስራ !!!ፍኖት የገንዘብ ቁ/ገ/ብ/ህ/ስ/ማ አብረን ከሰራን የማንችለው ነገር የለም።
17/04/2023

አልመን እንስራ !!!
ፍኖት የገንዘብ ቁ/ገ/ብ/ህ/ስ/ማ
አብረን ከሰራን የማንችለው ነገር የለም።

23/03/2023
የፍኖት የገንዘብ ቁጠባና ብድር ኃላፊነቱ የተወሰነ መሠረታዊ ህብረት ስራ ማህበር የቴሌግራም ገፅ አባል እንድትሆኑ ተጋብዛችኋል ።
13/12/2022

የፍኖት የገንዘብ ቁጠባና ብድር ኃላፊነቱ የተወሰነ መሠረታዊ ህብረት ስራ ማህበር
የቴሌግራም ገፅ አባል እንድትሆኑ ተጋብዛችኋል ።

በቻይና ውስጥ እጅግ ባለጸጋ የሆነውና 39 ቢሊዮን ዶላር የሚገመት ሀብት እንዳለው የሚነገርለት “ጃክ ማ” እንዲህ ይላል፡-‘’ ገንዘብና ሙዝን ከዝንጀሮዎች ፊት ብታስቀምጥ ዝንጀሮዎች ሙዙን ይ...
13/11/2022

በቻይና ውስጥ እጅግ ባለጸጋ የሆነውና 39 ቢሊዮን ዶላር የሚገመት ሀብት እንዳለው የሚነገርለት “ጃክ ማ” እንዲህ ይላል፡-

‘’ ገንዘብና ሙዝን ከዝንጀሮዎች ፊት ብታስቀምጥ ዝንጀሮዎች ሙዙን ይመርጣሉ። ምክንያቱም ገንዘብ ብዙ ሙዝ እንደሚገዛ አያውቁም!

አብዛኛው ሰው ላይ ተመሳሳይ ሙከራ ብታደርጉና በአንድ የተወሰነ የግል ስራ (ቢዝነስ) እና በወር ደመወዝ መካከል ምርጫቸው ምን እንደሆነ ብትጠይቁ አብዛኛው ሰው ወርሃዊ ደመወዝ ያለው ስራን ይመርጣል። ምክንያቱም ትንሽም ቢሆን የግል ስራ (ቢዝነስ) ከወርሃዊ ደሞዝ የበለጠ ገቢ እንደሚያመጣ እና ህይወት የሚቀይረው ይህ እንደሆነ ስለማያውቁ ነው።

ሰዎችን ለድህነት ከሚዳርጉት ነገሮች አንዱ ከግል ስራ (ቢዝነስ) የሚመጡትን እድሎች ማየት አለመቻላቸው ነው።

ምክንያቱም በህይወት ዘመናቸው ሁሉ በትምህርት ቤቶች የሚማሩት ስራ ማለት ሁልጊዜ ለወርሃዊ ደመወዝ መስራት መሆኑን ነው። ለራሳቸው ከመስራት ይልቅ ለሌሎች መስራትን ብቸኛ አማራጭ እንደሆነ ተምረዋል!

እውነት ነው የወር ደሞዝ ከድህነት ይጠብቅሃል። ነገር ግን ሀብትን እንዳታገኝ ያደርግሃል።

በህይወቴ ከጠዋቱ 2 ሰአት እስከ 12 ሰአት የሚሰራ ተቀጣሪ ሰው ሀብታም ሆኖ አይቼ አላውቅም።’’

ፍኖት የጋራ መንገድ ነው!!!የፍኖት አባል በመሆን ነጋችን አብረን እንስራ ።
08/11/2022

ፍኖት የጋራ መንገድ ነው!!!
የፍኖት አባል በመሆን ነጋችን አብረን እንስራ ።

 #ቤተሰቦቻችን እንዴት አደራችሁ። #ጊዜ እንደዋዛ ያልፋል ዛሬ በፈረንጆች ጥቅምት 27/2022 ነው።ከሶስት ቀናት በኋላ ሕዳር 1 ይላሉ። #የሐበሻይቱ ምድር ኢትዮጵያ ምንም ከማንም አልተቀበለ...
27/10/2022

#ቤተሰቦቻችን እንዴት አደራችሁ።
#ጊዜ እንደዋዛ ያልፋል ዛሬ በፈረንጆች ጥቅምት 27/2022 ነው።ከሶስት ቀናት በኋላ ሕዳር 1 ይላሉ።
#የሐበሻይቱ ምድር ኢትዮጵያ ምንም ከማንም አልተቀበለችም ከፈጣሪ ሁሉም ነገር ተችሩኣታል። እናም በራሱኣ አቆጣጠር ጥቅምት 17/2015 ነው
#የራሱኣ የዘመን አቆጣጠር አላት። ዘመኑን በወቅት ከፍላ ለወቅቶች ደግሞ ስያሜ ሰጥታ በወቅቶችም የሚከሰቱ ክስተቶችን እና በወቅቶች የሚገኙ ትሩፋቶችንም ጠንቅቃ ታውቃለች።

#አሁን ያለንበትን ወቅት ከመስከረም 26 በኋላ ያለውን ዘመነ ጽጌ ትለዋለች። አዝእርቶች ከአበባነት ወደ ፍሬነት የሚቀየሩበት ዘመን ለማለት ነው። ይህም የአበባ የፍሬ፣ወቅት እንደማለት ነው።
#አዝእርቶች ለመብቀል መበስበስ ይጠበቅባቸዋል። ለፍሬ ለመብቃት አስቸጋሪ የክረምቱን ቅዝቃዜ፣ ብርድ፣ ጎርፍ፣ ውሽንፍር በረዶ፣ማለፍ ይጠበቅባቸዋል። #ይህ ያለድካም ፍሬ እንደማይገኝ ጥሩ ማሳያ ነው።

#ውድ ቤተሰቦቻችን ለነገ ለምንተካቸው ትውልዶች ዛሬ ዋጋ መክፈል እና ለፍሬዎቻችን ፍሬን የሚያፈሩ ተቋማትን መስርቶ ስምን መትከል አስፈላጊ ነው።

#ፍኖት ለዘላቂ ልማት ለማህበረሰብ ተደራሽነት ሚናዋ እጅግ ከፍተኛ ነው። ብዙ ሀብታትን እየወለደች ትገኛለች።

#300 ብር እንዲህ ለትውልድ የምትሆን ፍሬ ማፍራት ከቻለች የበለጠ ብናሳድጋት ደግሞ ፍሬዋ እንዲሁ ብዙ ይሆናል።

እናም ከዛሬ እስከ ጥቅምት 30 መልእክታችን

በጥቅምት/2015 ፍሬን ሳናፈራ ሌላል ክረምት እንዳይመጣብን በጥቅምት ጥሩ ዘር እናፍራ እንላልን።

። የወሩ መሪ ቃላችን ነው።
ንቅናቄውን ተቀላቀሉ።

እኛ ፍኖቶች ነን፤"ተደጋግፈን ካሰብንበት እንደርሳለን "
24/10/2022

እኛ ፍኖቶች ነን፤
"ተደጋግፈን ካሰብንበት እንደርሳለን "

 ።በቀን 04/02/2015 በኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ በተካሄደ አመታዊ ስብሰባ በ2014 አመት አመርቂ ውጤት ያስመዘገቡ ተቋማት በየዘርፉ የሰርተፊኬት እና የዋንጫ ሽልማት በመስጠት እውቅና ...
15/10/2022


በቀን 04/02/2015 በኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ በተካሄደ አመታዊ ስብሰባ በ2014 አመት አመርቂ ውጤት ያስመዘገቡ ተቋማት በየዘርፉ የሰርተፊኬት እና የዋንጫ ሽልማት በመስጠት እውቅና ተሰጥቱኣል።

በመሆኑም በገንዘብ ቁጠባና ብድር ካሉ 17 ማኅበራት ውስጥ ፍኖት #2ኛ በመውጣት የዋንጫ እና የሰርተፊኬት ተሸላሚ ሁኖ 2014ን አጠናቋል።

ውጤቱ የተሰጠው በየሩብ አመቱ በሚወሰዱ ከ10 በላይ መመዘኛዎች እና መመልመያ መስፈርቶች ሲሆን #1ኛ ደረጃ በመሆን ያጠናቀቀው ከ17 አመት በፊት የተመሰረት ህብረት ስራ ማህበር። ይህም ከፍኖት ጋር ሲነጻጸር ከ14 አመት ያላነሰ ልምድ ያለው ሲሆን ከፍኖት የምስረታ ጊዜ አንጻር ስንመለከተው የፍኖት ውጤት እጅግ የሚመሰገን ሂደት መሆኑን ያሳያል።

ይህ ውጤት የተመዘገበው በአመራሩ እና በሰራተኞቻችን የተጠናከረ ሥራ፣ በልበ ብርሃን እና ቅን ቤተሰቦቻችን የባለቤትነትና የእኔነት የስነ ልቦና ውቅር የድርሻችሁን በመወጣታችሁ በመሆኑ ህብረት ስራ ማኅበሩ ያመሰግናችኋል።

#ስለሆነም በ2014 አመት በታዩ ጠንካራ ጎኖች በመበርታት የታዩ ክፍተቶችን በመድፈን ያጋጠሙ ችግሮችን በመፍታት አሁን ካለንበት ደረጃ ቀዳሚ በመሆን አመርቂ ውጤት እንደምናስመዘግብ በ3ወራት ውስጥ የታየው አፈጻጸም አመላካች መሆኑን እንገልጻለን።

# የተከበራችሁ ውድ ቤተሰቦቻችን አሁን የጀመርነው እና ያስመዘገብነው ውጤት የህብረታዊ አንድነታችን ውጤት መሆኑን በመረዳት በመደጋገፍ እና በመተሳሰብ፣ አዳዲስ ቤተሰቦችን አባል በማድረግ፣ ወርሃዊ ቁጠባችንን በጊዜ በመቆጠብ፣ የፍላጎት ቁጠባዎችን በመቆጠብ፣ እጣችንን በማሳደግ እና በሙያችን አዳዲስ አሰራሮችን በመቅረጽ አንድነታችንን እና የጋራ እድገታችንን በማፋጠን የሕብረታዊ አንድነት ስኬትን እንድናረጋግጥ እና የድርሻችንን እንድንወጣ ከወዲሁ እየጠቆምን_በድጋሜ_እንኳን_ደስ_አላችሁ_እንላለን።

ፍኖት የገንዘብ ቁጠባና ብድር ኃ/የተ/ህብረት ስራ ማህበር።
#ተደጋግፈን ካሰብንበት እንደርሳለን።

የምትሰሩት ስራ ጉዳይ በአሁኑ ወቅት በስራ አለም ውስጥ ከተሰማራችሁና የወደፊት የስራ ቆይታችሁ ስኬታማና እድገት ያለበት እንዲሆን ከፈለጋችሁ ስለጉዳዩ ማሰብ ያለባችሁ ዛሬ ነው፡፡ ዛሬ አእምሯ...
10/10/2022

የምትሰሩት ስራ ጉዳይ

በአሁኑ ወቅት በስራ አለም ውስጥ ከተሰማራችሁና የወደፊት የስራ ቆይታችሁ ስኬታማና እድገት ያለበት እንዲሆን ከፈለጋችሁ ስለጉዳዩ ማሰብ ያለባችሁ ዛሬ ነው፡፡ ዛሬ አእምሯችሁን ተጠቅማችሁ ካላሰባችሁ፣ ነገ ስሜታችሁ መጨነቅና መዛባት ይጀምራል፡፡

በስራው አለም ውስጥ በቆያችሁ ቁጥር በሁለት መልኩ ማደግ አለባችሁ፡- 1) በገንዘብ ብቃት፣ 2) በአእምሮ እድገት

1. የገንዘብ ብቃት
የሚከፈላችሁ ክፍያ አናሳ እንደሆነ ካሰባችሁ፣ ለስራው ካላችሁ ብቃት አንጻር እየተከፈላችሁ ሊሆን ስለሚችል ብቃታችሁን የምትጨምሩበትን መንገድ ፈልጉ፡፡ ብቁ ሆናችሁ መስሪያ ቤቱ የመክፈል ባህሉ ወይም አቅሙ አናሳ ሆኖ ካገኛችሁት ደግሞ፣ የመስሪያ ቤቱን አሰራር ለማስቀየር ከመታገል ወይም ከመነጫነጭ ይልቅ የስራ መስካችሁን መቀየር ቀለል እንደሚል አትዘንጉ፡፡

2. የአእምሮ እድገት
የስራው ጸባይ አእምሮን የሚያሰራ፣ የሚሞግትና የሚያሳድግ ከመሆን ይልቅ ድግግሞሽ የሞላው ከሆነ፣ ምንም እንኳን ገንዘብን ብታኙበትም ከዘመኑ ጋር አብሮ የሚራመድ የአእምሮ እድገት እንደማይኖራችሁ አትዘንጉ፡፡ በስራው ለመቆየት ከፈለጋችሁ፣ በግላችሁ የምታድጉበትን ሌላ መንገድ መፈለግ አለባችሁ፡፡ ያንን ማድረግ ካልቻላችሁ ግን የሚሞግት፣ አእምሮን የሚያሰራና የሚያሳድጋችሁን ስራ ወደመፈለግ ማዘንበል ወሳኝ ነው፡፡

እድሜያችሁ በጨመረ ቁጥር ቤተሰብን ከመመስረት የሚመጣ ሃላፊነትና የተለያዩ ፍላጎቶች መጨመር ሁኔታዎች አብረው ስለሚመጡ ካለማቋረጥ የማደጋችሁን ጉዳይ በሚገባ አስቡበት፡፡

ምንጭ:-ዶክተር እዮብ ማሞ

04/10/2022

በኢኮኖሚ ራስን መቻል ብዙ ነገሮችን ማሻሻል ወይም ማስተካከል ይቻላል ።
የኢኮኖሚ ነፃነታችን ካወጅን መማር ፣መሰልጠን ፣የበጎ አድራጎት ስራ መስራት ፣ማህበራዊ ኃላፊነታችን መወጣት እና የምንፈልገውን ለመሆን የውስጥ ፍላጎት ካለን የሚገድበን ጉዳይ አይኖርም ።በተለይ ይህ ዘመን ጠንካራ ተወዳዳሪ ለመሆን በመጀመሪያ የኢኮኖሚ መሠረታችን መስመር ማስያዝ አስፈላጊ ብቻ ሳይሆን መሠረታዊ ጥያቄያችን ነው።
ጠንካራ የኢኮኖሚ መሠረት ያላቸው አገሮች ሆነ ግለሰቦች ተደማጭ እና ተፅዕኖ ፈጣሪ የሆኑት በመጀመሪያ ድህነት የሚባል አዋራጅ ተግባርን ማሸነፍ ስለቻሉ ነው።
እኛ ዛሬ በወር የምናገኘው ደመወዝ ብዙ ከሆነ ከምናገኘው ደመወዝ የተወሰነውን በመቆጠብ ለራሳችን እንኳ በቂ ነገር አለን ብለን የምናስብ ከሆነ በመቆጠብ ሌሎች በመበደር ስራ እንዲሰሩ ብናደርግ መልካም ተግባር ይሆናል ።
ሲሆን በወር ተቀጥረን ከምናገኘው ደመወዝ በተጨማሪ ገቢ እንዲኖረን መስራት ካልሆነ ግን ለሌሎች የስራ እድል መፈጠር የምንችል መሆኑን በመረዳት የፍኖት አባል እና ለሌሎችም አቻ ተቋማት አባል በመሆን በምንችለው መልኩ ለአገራችን የስራ አጥነት ችግር እና የኢኮኖሚ ደካማነት በመቆጠብ የድርሻችን መወጣት መቻል መለማመድ አለብን እንላለን ።

Address

Addis Ababa

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Finot Saving and Credit Association posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share