AhaduBank

AhaduBank we are committed to helping you achieve your financial goals with Inclusive Intermediation
(1)

ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች፤ እንኳን ለአረፋ በዓል አደረሳችሁ፡፡
27/05/2026

ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች፤ እንኳን ለአረፋ በዓል አደረሳችሁ፡፡

ውድ የአሐዱ፡ባንክ ቤተሰቦች!ባንካችን 105ኛ ቅርንጫፉን በአማራ ክልል፤ ሰሜን ወሎ ዞን፤ በቆቦ ከተማ "ቆቦ ቅርንጫፍ" በሚል ስያሜ በመክፈት፤ የባንክ አገልግሎት መስጠት መጀመሩን ስንገልጽል...
26/05/2026

ውድ የአሐዱ፡ባንክ ቤተሰቦች!

ባንካችን 105ኛ ቅርንጫፉን በአማራ ክልል፤ ሰሜን ወሎ ዞን፤ በቆቦ ከተማ "ቆቦ ቅርንጫፍ" በሚል ስያሜ በመክፈት፤ የባንክ አገልግሎት መስጠት መጀመሩን ስንገልጽልዎ በታላቅ ደስታ ነው፡፡

💼 We are Hiring👉Place of work: Addis Ababa👉Salary: As per the Bank’s ScaleRequired Quantity for each position: (One) 1👉I...
25/05/2026

💼 We are Hiring

👉Place of work: Addis Ababa
👉Salary: As per the Bank’s Scale
Required Quantity for each position: (One) 1
👉Interested and qualified applicants shall apply via the following link only
👉CLICK HERE (https://forms.gle/k7fgBaKwaZhC8Vhs7)
Application Deadline Date
May 30, 2026

Only Shortlisted Candidates will be communicated.
If you need more information, please call us on
📞+251-11-5-260-795

AHADU BANK
Inclusive Intermediation

ውድ የአሐዱ፡ ቤተሰብ“ፋይዳ ቁጥርዎን ከባንክ ሒሳብዎ እናስተሳስርልዎ” በሚል ሰበብ አጭበርባሪዎች ከፍተኛ ወንጀል ለመፈጸም እየተንቀሳቀሱ እንደሆነ ከሚደርሱን ጥቆማዎች ተረድተናል፡፡ ስለሆነም...
23/05/2026

ውድ የአሐዱ፡ ቤተሰብ
“ፋይዳ ቁጥርዎን ከባንክ ሒሳብዎ እናስተሳስርልዎ” በሚል ሰበብ አጭበርባሪዎች ከፍተኛ ወንጀል ለመፈጸም እየተንቀሳቀሱ እንደሆነ ከሚደርሱን ጥቆማዎች ተረድተናል፡፡ ስለሆነም ውድ ደንበኛችን ከመሰል መጭበርበር ራስዎን እና ቤተሰብዎን ለመጠበቅ እነዚህንና መሰል የጥንቃቄ እርምጃዎች እንዲወስዱ በጥብቅ እናሳስባለን፦
👉ምሥጢራዊ የባንክ መረጃዎትን ማለትም የምሥጢር ቁጥር (PIN)፣ የፋይዳ መለያ ቁጥርዎን፣ የፋይዳ ማረጋገጫ ኮድ (OTP)፣ የይለፍ ቃል (password) ወይም ሌሎች የደኅንነት መረጃዎችን ለማንም አያጋሩ፤
👉ፋይዳዎን ከባንክ ሒሳብዎ ጋር ለማስተሳሰር በአቅራቢያዎ በሚገኝ የባንካችን ቅርንጫፍ በአካል በመገኘት ወይም የባንካችንን የበይነ መረብ (Online) ማስተሳሰሪያ አማራጭ https://verifayda.ahadubank.com/ ብቻ ይጠቀሙ፤
👉በበይነ-መረብ (Online) ለማስተሳሰር በሚሞክሩበት ወቅት እገዛ ካስፈለግዎት፤ ከማያውቁት ወይም በሚገባ ከማያምኑት ሰው እርዳታ አይጠይቁ፤
👉አጠራጣሪ ሁኔታዎች ሲያጋጥምዎት ወይም የደኅንነት ሥጋት ሲኖርዎት በአቅራቢያዎ በሚገኝ አሐዱ፡ባንክ ቅርንጫፍ፣ በባንካችን የማኅበራዊ ሚዲያ ወይም በደንበኞች የጥሪ ማዕከል 694 በመደወል ሪፖርት ያድርጉ።

የሐራጅ ማስታወቂያ!
21/05/2026

የሐራጅ ማስታወቂያ!

ባንካችን "ልደታ ማርያም" ቅርንጫፍ በድምቀት ተመረቀ!በማኅደረ ስብሐት ቅድስት ልደታ ማርያም እና ደብረ መድኃኒት መድኃኔ ዓለም ቤተ ክርስቲያን ሕንጻ ላይ የሚገኘው "ልደታ ማርያም" የተሰኘው...
18/05/2026

ባንካችን "ልደታ ማርያም" ቅርንጫፍ በድምቀት ተመረቀ!

በማኅደረ ስብሐት ቅድስት ልደታ ማርያም እና ደብረ መድኃኒት መድኃኔ ዓለም ቤተ ክርስቲያን ሕንጻ ላይ የሚገኘው "ልደታ ማርያም" የተሰኘው 104ኛው የባንካችን ቅርንጫፍ፤ ብፁዕ አቡነ ያዕቆብ (የሰሜን አሜሪካ÷ አትላንታ እና ጆርጂያ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ)÷ መልአከ ምሕረት ቆሞስ አባ ገብረ መድኅን (የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ዋና ሥራ አስኪያጅ)÷የመንበረ ፓትርያርክ የአገልግሎት ክፍል ኃላፊዎች÷የሀገረ ስብከት ሥራ አስኪያጆች÷የክፍላተ ከተማ ቤተ ክህነት ሥራ አስኪያጆች÷የአድባራት አስተዳዳሪዎች÷የባንካችን የዳይሬክተሮች ቦርድ አባላት÷የባንካችን ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ሙሉጌታ በዛ÷የባንካችን ከፍተኛ የሥራ አመራሮች እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በታደሙበት ግንቦት 08/2018 ዓ.ም በድምቀት ተመርቋል፡፡

ብፁዕ አቡነ ያዕቆብ (የሰሜን አሜሪካ÷ አትላንታ እና ጆርጂያ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ)፤ ኢትዮጵያ ፈጣሪን የሚፈሩ ሰዎች የሚገኙባት ሀገር ናት፤ አሐዱ፡ባንክም ፈጣሪን መፍራት ቀዳሚ ዕሴቱ ማድረጉ፤ በመልካም የአገልጋይነት ስሜት ነግዶ ለማትረፍ እና ለወገን ለመድረስ ያለመውን ዓላማ ያመለክታል በማለት አባታዊ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡

የማኅደረ ስብሐት ቅድስት ልደታ ለማርያም እና ደብረ መድኃኒት መድኃኔ ዓለም ቤተ ክርስቲያን ዋና አስተዳዳሪ የሆኑት መልአከ ስብሐት ቆሞስ አባ ገብረ ሥላሴ፤ አሐዱ፡ባንክ የተመሠረተበትን ዓላማ ስለማውቅ፤ በቤተ ክርስቲያናችን ሕንጻ ላይ ቅርንጫፍ በመክፈቱ እጅግ ደስ ብሎኛል፤ በትብብር ሠርተን አሐዱ፡ባንክን እናሳድገዋለን በማለት በአጽንኦት ተናግረዋል፡፡

የባንካችን ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ሙሉጌታ በዛ በበኩላቸው፤ ከብዙዎች ለብዙዎች በሚል መርሕ ተግባሩን እየከወነ የሚገኘው ባንካችን ለብዙዎች ለመድረስ እየተጋ መሆኑ ዛሬ በይፋ የተከፈተው 104ኛው "ልደታ ማርያም" ቅርንጫፍ ማሳያ ነው፤ ስለሆነም በትብብር በመሥራት ባንካችንን ወደ ሚፈለገው ውጤት ማድረስ ይጠበቅብናል በማለት ገልጸዋል::

📱የማንኛዉንም ባንክ የሞባይል ባንኪንግ  መተግበሪያ በመጠቀም በተለያዩ  የግብይት ቦታዎች ላይ የሚያገኙትን የአሐዱ QR ኮድን እስካን በማድረግ ክፍያዎትን በቀላሉ ይፈፅሙ። ለበለጠ መረጃ ወደ...
18/05/2026

📱የማንኛዉንም ባንክ የሞባይል ባንኪንግ መተግበሪያ በመጠቀም በተለያዩ የግብይት ቦታዎች ላይ የሚያገኙትን የአሐዱ QR ኮድን እስካን በማድረግ ክፍያዎትን በቀላሉ ይፈፅሙ።

ለበለጠ መረጃ ወደ 694 ነፃ የስልክ መስመር ይደዉሉ።

አሐዱ፡ባንክ
ከብዙዎች ለብዙዎች!

📱የማንኛዉንም ባንክ የሞባይል ባንኪንግ  መተግበሪያ በመጠቀም በተለያዩ  የግብይት ቦታዎች ላይ የሚያገኙትን የአሐዱ QR ኮድን እስካን በማድረግ ክፍያዎትን በቀላሉ ይፈጽሙ። ለበለጠ መረጃ ወደ...
13/05/2026

📱የማንኛዉንም ባንክ የሞባይል ባንኪንግ መተግበሪያ በመጠቀም በተለያዩ የግብይት ቦታዎች ላይ የሚያገኙትን የአሐዱ QR ኮድን እስካን በማድረግ ክፍያዎትን በቀላሉ ይፈጽሙ።

ለበለጠ መረጃ ወደ 694 ነፃ የስልክ መስመር ይደዉሉ።

💼 We are Hiring👉Place of work: Addis Ababa(Head Office) 👉Salary: As per the Bank’s ScaleRequired Quantity for each posit...
11/05/2026

💼 We are Hiring

👉Place of work: Addis Ababa(Head Office)
👉Salary: As per the Bank’s Scale
Required Quantity for each position: (One) 1
👉Interested and qualified applicants shall apply via the following link only
👉CLICK HERE (https://forms.gle/QM9AJqpENir82UK59)
Application Deadline Date
May, 16, 2026

Only Shortlisted Candidates will be communicated.
If you need more information, please call us on
📞+251-11-5-260-795

AHADU BANK
Inclusive Intermediation

💼 We are Hiring👉Place of work: Addis Ababa(Head Office) 👉Salary: As per the Bank’s ScaleRequired Quantity for each posit...
08/05/2026

💼 We are Hiring

👉Place of work: Addis Ababa(Head Office)
👉Salary: As per the Bank’s Scale
Required Quantity for each position: (One) 1
👉Interested and qualified applicants shall apply via the following link only
👉CLICK HERE (https://forms.gle/k7fgBaKwaZhC8Vhs7)
Application Deadline Date
May, 13 2026

Only Shortlisted Candidates will be communicated.
If you need more information, please call us on
📞+251-11-5-260-795

AHADU BANK
Inclusive Intermediation

⚠️የጥንቃቄ መልዕክት በሀገራችን የዲጂታል ባንኪንግ እና የማኅበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚዎች ቁጥር መጨመሩን እንደ ምቹ አጋጣሚ በመጠቀም፣ አጭበርባሪዎች የተለያዩ አሳሳች ስልቶችን በመቀየስ የደንበኞ...
07/05/2026

⚠️የጥንቃቄ መልዕክት

በሀገራችን የዲጂታል ባንኪንግ እና የማኅበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚዎች ቁጥር መጨመሩን እንደ ምቹ አጋጣሚ በመጠቀም፣ አጭበርባሪዎች የተለያዩ አሳሳች ስልቶችን በመቀየስ የደንበኞችን ምሥጢራዊ መረጃ ለመስረቅና ተገቢ ያልሆነ የገንዘብ ዝውውር ለማስፈጸም የሚደረጉ ሙከራዎች እየተበራከቱ ይገኛሉ።
በመሆኑም ውድ የአሐዱ፡ባንክ ቤተሰቦች፤ ከዲጂታል ባንኪንግ አገልግሎት ጋር በተያያዘ በአሐዱ፡ባንክ ወይም በቅርብ ወዳጅ ዘመድዎ ስም በማስመሰል የሐሰተኛ ስልክ ጥሪዎች፣ አጭር የጽሑፍ መልዕክቶች (SMS) ፣ የኢሜል ወይም የማኅበራዊ ሚዲያ መልዕክቶችን በመላክ የግል መረጃዎን ለመውሰድና ለማጭበርበር የሚሞክሩ ግለሰቦች ስላሉ ተገቢውን ጥንቃቄ እንዲያደርጉ እናሳስባለን።
ራስዎን ከማንኛውም የማታለል/የማጭበርበር ተግባር ለመጠበቅ የሚከተሉትን የጥንቃቄ እርምጃዎች ይውሰዱ፡-
👉ምሥጢራዊ መረጃዎትን ማለትም የምሥጢር ቁጥር( PIN)፣ የይለፍ ቃል( password)፣ የአንድ ጊዜ ማረጋገጫ ኮድ (OTP) ወይም ሌሎች የደኅንነት መረጃዎችን ለማንም አያጋሩ። ባንካችን አሐዱ በፍጹም የደንበኞቹን የግል መረጃዎችን በስልክም ሆነ በማኅበራዊ ሚዲያ አይጠይቅም።
👉በአጭር የጽሑፍ መልዕክት (SMS)፣ በኢሜል ወይም በማኅበራዊ ሚዲያ የሚላኩ አጠራጣሪ ማስፈንጠሪያዎችን (Links) በፍጹም አይክፈቱ። የባንካችንን የሞባይል ባንኪንግ ወይም ሌሎች መተግበሪያዎችን ከትክክለኛ ምንጮች (Play Store ወይም App Store) ብቻ ያውርዱ።
👉ስልክዎ፣ ኤቲኤም ካርድዎ ወይም የባንክ አገልግሎት የሚጠቀሙበት መሣሪያ ቢጠፋ ወይም ቢሰረቅ፤ በአቅራቢያዎ ወደ ሚገኝ የአሐዱ፡ባንክ ቅርንጫፍ በአካል በመቅረብ ወይም በደንበኞች የጥሪ ማዕከላችን (694) በመደወል በፍጥነት ያሳውቁ.
👉በጓደኛ ወይም በቅርብ ዘመድዎ ስም በጽሑፍ መልዕክት፣ በማኅበራዊ ሚዲያ (Telegram, WhatsApp, Facebook) ወይም በኢሜል የሚላኩ የገንዘብ መጠየቂያ መልዕክቶችን ትክክለኛነት ሳያረጋግጡ ምንም ዓይነት የገንዘብ ዝውውር አይፈጽሙ።
👉ለሞባይል ባንኪንግ እና ለኤቲኤም ካርድዎ ጠንካራ የይለፍ ቃል እንዲሁም የጣት ወይም የፊት አሻራ (biometrics) ማረጋገጫ ይጠቀሙ። በተጨማሪም የስልክዎን ኦፕሬቲንግ ሲስተም እና የባንክ መተግበሪያዎን በየጊዜው ያዘምኑ።
የሒሳብዎን ወይም የዎሌትዎን ቀሪ መጠንና የግብይት ታሪክ (Transaction History) በየጊዜው በመከታተል፣ ያልተፈቀዱ የገንዘብ ዝውውሮች አለመኖራቸውን ያረጋግጡ።
ማንኛውንም አጠራጣሪ ሁኔታዎች ሲያጋጥምዎት ወይም የደኅንነት ስጋት ሲኖርዎት መረጃ ከመስጠት ተቆጥበው በአቅራቢያዎ በሚገኝ ቅርንጫፍ፣ በባንካችን የማኅበራዊ ሚዲያ ወይም በደንበኞች የጥሪ ማዕከል 694 በመደወል ሪፖርት ያድርጉ።

Address

Bole Road, Africa Avenue
Addis Ababa
32757

Opening Hours

Monday 08:30 - 18:30
Tuesday 08:30 - 18:30
Wednesday 08:30 - 18:30
Thursday 08:30 - 18:30
Friday 08:30 - 18:30
Saturday 08:30 - 12:00

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when AhaduBank posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to AhaduBank:

Share