26/11/2024
ለሁለተኛ ጊዜ የተጠራ የጠቅላላ ጉባኤ ሰብሰባ ጥሪ!! ህዳር 7 ቀን 2017 ዓ.ም የተጠራው የጠቅላላ ጉባዔ ስብሰባ በአዋጁ መሠረት ስብሰባውን ለማከናወን የሚያስችል የተሰብሳቢ ቁጥር ስላልምላ ስብሰባውን ማከናወን ስላልተቻለ በአዋጁ መሠረት ይህ ለ2ኛ ጊዜ ስብሰባ ለማድረግ የተላለፈ የስብሰባ ጥሪ ነው።
ውድ የአማራጭ አባላት እሁድ ህዳር 22/2017 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡30 መገናኛ ፓናሮማ ሆቴል አጠገብ ቶታል ማደያ ጊቢ ውስጥ ባለው በቫምዳስ ሲኒማ የጠቅላላ ጉባኤ ስብሰባ ላይ እንዲገኙ ተጋብዘዋል።
የጠቅላላ ጉባኤው አጀንዳዎች
=======================
1,የማህበሩን የኦዲት የስራ ሪፖርት ማዳመጥ።
2. በማህበሩ ቀጣይ ህልውና ላይ (ስለማህበሩ ማፍረስና ማጠናከር) ላይ ውሳኔ ማሳለፍ
ማሳሰቢያ፦
=======
1. በስብሰባው ላይ መገኘት የማትችሉ አባላት
ከስብሰባው አምስት ቀን በፊት በስልክ ወይም
በአካል ቢሮ በመቅረብ የተወካይ ስም
ማስመዝገብ ይቻላል።
2. ለስብሰባው ስትመጡ ማንነታችሁን የሚገልጽ
መታወቂያ ወይም ፓስፖርት ይዛችሁ
እንድትገኙ እናሳስባለን።
3. የግል ማህደራችሁን ለማደራጀት ፎቶና
መታወቂያ ያልሰጣችሁ አባላት 2ጉርድ ፎቶና
መታወቂያ ኮፒ እንዲሁም ክፍያ
የፈፀማችሁባቸው ደረሰኞች ካሉ ይዛችሁ
በመምጣት እንድትተባበሩን በአክብሮት
እንጠይቃለን።
የስብሰባው ቦታ
ከ22 ወደ መገናኛ በሚወስደው መንገድ ለም ሆቴል ድልድዩን እንዳለፋችሁ ያለው ቶታል ነዳጅ ማደያ ጊቢ ውስጥ ቫምዳስ ሲኒማ ።
ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት
+251 911714355 +251911267622
የስራ አመራር ቦርድ፦
ማሳሰቢያ ፦ ለሁለተኛ ጊዜ የተጠራ ሰብሰባ በመሆኑ ማንኛውም ውሳኔ በዕለቱ በተገኙት አባላት የሚፀድቅ መሆኑን እናሳውቃለን።