Condominuim Market in Addis Ababa

Condominuim Market in Addis Ababa condominium sale and brokerage in Addis Ababaአጠቃላይ የኮንዶሚንየም ቤቶች ሽያጭ? condominium sale & buy in Addis Ababa

የጋራ መኖርያ ቤቶችን በሚያስተዳድሩ ማህበራት ላይ አስገዳጅ የዲጂታል ክፍያ ስርዐት እየዘረጋ ያለው 'እፎይ ፕላስ' የተባለው የግል ድርጅት ውዝግብ አስነሳ አሰራሩ አዲስ አበባ በሚገኙ በሁሉም...
30/05/2026

የጋራ መኖርያ ቤቶችን በሚያስተዳድሩ ማህበራት ላይ አስገዳጅ የዲጂታል ክፍያ ስርዐት እየዘረጋ ያለው 'እፎይ ፕላስ' የተባለው የግል ድርጅት ውዝግብ አስነሳ

አሰራሩ አዲስ አበባ በሚገኙ በሁሉም ኮንዶሚኒየሞች እና አፓርትመንቶች ላይ ተግባራዊ እንዲሆን የታቀደ ሲሆን የጋራ መኖርያ ማህበራት ይህንን አሰራር ካልተቀበሉ የባንክ ሂሳባቸው እንደሚታገድ ክፍለ ከተሞች እያስጠነቀቁ ይገኛሉ
https://bit.ly/4nL0s4x

27/05/2026

Mechare condominium sale

48 sqm
2nd floor
1 bedroom
5.8 million
0913587955

https://bit.ly/4nL0s4x

20/05/2026
በአዲስ አበባ በተከራዮች ላይ የኪራይ ጭማሪ እየተደረገ መሆኑ ተጠቆመ  !በአዲሰ አበባ ባለፉት 2 ዓመታት የነበሩ የኪራይ ውሎች መጠናቀቅን ተከትሎ ከ50 እስከ 100 በመቶ የሚደርስ የኪራይ ...
20/05/2026

በአዲስ አበባ በተከራዮች ላይ የኪራይ ጭማሪ እየተደረገ መሆኑ ተጠቆመ !

በአዲሰ አበባ ባለፉት 2 ዓመታት የነበሩ የኪራይ ውሎች መጠናቀቅን ተከትሎ ከ50 እስከ 100 በመቶ የሚደርስ የኪራይ ጭማሪ በተከራዮች ላይ እየተደረገ መሆኑን የኢትዮጵያ ሸማቾች መብት ተቆርቋሪ ድርጅት አስታወቀ ።

በአዲስ አበባ ለሁለት ዓመት ተጥሎ ሲተገበር የቆየው የኪራይ ውል ሊጠናቀቅ ጥቂት ጊዜያት ቀርቶታል።

ይህን ተከትሎ በአሁኑ ወቅት በከተማዋ በቤቶች ላይ እጅግ ከፍተኛ የተጋነነ የዋጋ ጭማሪ እየተደረገ መሆኑን ለማወቅ ተችሏል። ይህ ሁኔታ አስቀድሞ በኑሮ ውድነትና በዋጋ ግሽበት ክፉኛ እየተማረረ ለሚገኘው ማኅበረሰብ ተጨማሪ ከባድ ጫና ፈጥሯል።

የኢትዮጵያ ሸማቾች መብት ተቆርቋሪ ድርጅት ባወጣው መግለጫ ፥ " በኢትዮጵያ እየታየ ያለው የዋጋ ግሽበት እና የኑሮ ውድነት በህብረተሰቡ ላይ እያሳደረ ያለውን ጫናና በመሰረታዊ ሸቀጦች ላይ በየቀኑ ሰማይ እየነካ የሄደው የዋጋ ንረት የሸማቹን የመግዛት አቅም በእጅጉ አዳክሞታል፤ ለዚህም መፍትሄ ሊሰጠው ይገባል " ብሏል።

በተለይ ባለፉት 2 ዓመታት የነበሩ የኪራይ ውሎች መጠናቀቅን ተከትሎ ከ50 እስከ 100 በመቶ የሚደርስ የኪራይ ጭማሪ በተከራዮች እየተደረገ ነው ይህንንም አረጋግጫለሁ ሲል አሳውቋል።

የሸማቹ የመግዛት አቅም መዳከም ደግሞ አጠቃላይ ሀገራዊ ኢኮኖሚውን አቀዝቅዞታል፤ በተጨማሪም በነዳጅ አቅርቦት፣ ስርጭት፣ እጥረትና የዋጋ ጭማሪ ደግሞ ችግሩን አባብሶታል ብሏል።

የድርጅቱ መስራችና ዋና ዳይሬክተር አቶ ቁምላቸው አበበ ለሸገር ኤፍ ኤም 102.1 ሬድዮ ጣቢያ በሰጡት ቃል፤ ድርጅቱ በአዲስ አበባ የተለያዩ አካባቢዎች ጥናት ማድረጉንና ለኪራይ ንረቱ አሉታዊ አስተዋጽኦ ያደረጉ ሁኔታዎች መታዘቡን እንዲሁም ጭማሪም መደረጉን መመልከቱን ገልጸዋል።

አብዛኛው ተከራይ ዝቅተኛ ገቢ ያለው በመሆኑ ካለው የኑሮ ውድነት ጋራ ተደምሮ በተለይ የመኖሪያ ቤት ጉዳይ ከኢኮኖሚና የተረጋጋ ማህበረሰብ ከመገንባት አንጻር አስተዋጽኦ ስላለው ልዩ ትኩረት ይሻል ማህበረሰቡ ላይ ምስቅልቅል እየፈጠረ ነው " ሲሉ ተናግረዋል፡፡

በሌላ በኩል በአከራዮች ላይ የተጣለው ከፍተኛ የታክስ መጠን፣ አከራዮች ይህንኑ ታክስ ወደ ተከራዩ እንዲያስተላልፉ እና ከውል ውጭ ተጨማሪ ክፍያ እንዲጠይቁ ምክንያት ሆኗል ያሉ ሲሆን ለዚህም ከመንግስት መፍትሄ ይፈልጋል ብለዋል።

ድርጅቱ መንግስትና የሚመለከታቸው አካላት ፦
- የኑሮ ውድነቱን፣
-የዋጋ ግሽበቱን፣
- የነዳጅ ዋጋ ጭማሬውንና እጥረቱ በማዕቀፍ ለመፍታት እንዲያስችል ከዚህ በላይ የተቀናጀ ርብርብ እንዲያደርጉ አሳስቧል፡፡

የቤት ኪራይ ውድነትን ለመከላከል ምን መፍትሄ አለ ?

ድርጅቱ፣ መንግስት በህገ-መንግስቱ በተደነገገው መሰረት አቅም በፈቀደ መጠን ለሁሉም ኢትዮጵያውያን መኖሪያ ቤት እንዲኖራቸው የማድረግ የፖሊሲ ዓላማና ኃላፊነት አለበት ብሏል።

የመኖሪያ ቤት አቅርቦት መሠረታዊ የሰብዓዊ መብት ጉዳይ በመሆኑ አቅርቦቱን ለማሟላት ከሚደረገው ጥረት ጎን ለጎን በከተሞች ያለውን የቤት ኪራይ ዋጋ የማኅበረሰቡን የመግዛት አቅም ያገናዘበና ተመጣጣኝ እንዲሆን የማድረግ፣ የመቆጣጠርና የማስተዳደር ሕጋዊ ግዴታን ሊወጣ እንደሚገባ አመልክቷል።

ይህ አስፈላጊ ጣልቃ ገብነት የአከራዮችንና የተከራዮችን መሠረታዊ መብቶችና ጥቅሞች ሚዛኑን በጠበቀ መልኩ ለማስተናገድ የሚያስችል ግልጽነትና ተጠያቂነት ያለው አሠራር ለመዘርጋት ወሳኝ እንደሆነ ገልጿል።

ከተማ አስተዳደሩ ምን አለ ?

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፣ የሁለት ዓመት የቤት ኪራይ ውሉ በመጪው ሰኔ 30/2018 ዓ.ም የሚያበቃ መሆኑን ገልጿል። ይህን አስመልክቶ ጥናት እያስጠና መሆኑን ተናግሯል።

በጥናቱ መሰረት የኪራይ ዋጋ ባለበት እንደሚቀጥል፣ አሊያም ባለው የገበያ ዋጋ መሰረት የሚጨምር ወይም የሚቀንስ መሆኑን ለማህበረሰቡ ያሳውቃል።

ሸገር ኤፍ ኤም 102 .1
Condoaddis.etsecurities.com

09/05/2026

Enjoy the videos and music you love, upload original content, and share it all with friends, family, and the world on YouTube.

Adresse

Addis Ababa
Democratic Republic Of The
1000

Notifications

Soyez le premier à savoir et laissez-nous vous envoyer un courriel lorsque Condominuim Market in Addis Ababa publie des nouvelles et des promotions. Votre adresse e-mail ne sera pas utilisée à d'autres fins, et vous pouvez vous désabonner à tout moment.

Contacter L'entreprise

Envoyer un message à Condominuim Market in Addis Ababa:

Partager