Wolayita Sodo Page

Wolayita Sodo Page Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Wolayita Sodo Page, Sodo.

17/05/2026

Yadi Records

26/01/2025

Yana G Hisanu (Hanacho) ያና ጂ (ሀናቾ) New Ethiopan Music New Wolayita Music Wolayita Cultural Music 2025 (offical video)@Didigagamusic ...

09/11/2024

12/09/2024

Sisay Ukumo Yoo-Gifatta ሲሳይ ኡኩሞ ዮ ጊፋታ Wolaita S**o - Ethiopian Musicአዲስ የጊፋታ ሙዚቃ በያዲ ስቱዲዮ ...

23/08/2024

Tariku Gankisi Dishta Gina ታሪኩ ጋንካሲ ዲሽታግና Wolaita S**o - Ethiopian Musicበወላይታ ሶዶ አዘጋጅነት የተካሄደው 9ኛዉ የከተሞች ፎረም በወላይታ ሶዶ ሁለገብ ስታድየም ከ150 በላይ ከተሞች፣ የከተማዋ...

https://youtu.be/JIudYI0l49A
23/08/2024

https://youtu.be/JIudYI0l49A

Tariku Gankisi Dishta Gina ታሪኩ ጋንካሲ ዲሽታግና Wolaita S**o - Ethiopian Musicበወላይታ ሶዶ አዘጋጅነት የተካሄደው 9ኛዉ የከተሞች ፎረም በወላይታ ሶዶ ሁለገብ ስታድየም ከ150 በላይ ከተሞች፣ የከተማዋ...

የደቡቧ ፈርጥ ባለ ሰባት በር ወላይታ ሶዶሰባቱ በሮች 1. በበሌ ሃዋሳ-ታርጫ-ጅማ2. በአረካ -ሆሳዕና 3.በቦዲቲ -ሻሼመኔ 4.በዲምቱ-ሐዋሳ5.በሆብቻ-ዲላ6.በጠበላ ሁምቦ አርባምንጭ ጂንካ7....
11/04/2024

የደቡቧ ፈርጥ ባለ ሰባት በር ወላይታ ሶዶ

ሰባቱ በሮች
1. በበሌ ሃዋሳ-ታርጫ-ጅማ
2. በአረካ -ሆሳዕና
3.በቦዲቲ -ሻሼመኔ
4.በዲምቱ-ሐዋሳ
5.በሆብቻ-ዲላ
6.በጠበላ ሁምቦ አርባምንጭ ጂንካ
7.በገሱባ- ጎፋ ሳውላ

ለኑሮ፣ ለኢንቨስትመንት እና ለንግድ ምቹ የሆነችውን ወላይታ ሶዶን ይጎብኙ!

27/07/2023
ከንጉስ ስራዓት ጀምሮ እስከ ብልፅግና መንግስት የኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ መስራቾች እና መሪዎች ለምን የዎላይታ ተወላጆች ብቻ ሆኑ ❓የብሔራዊ ባንክ እና የህንጻው ድራፍት ዲዛይን ከዎላይታ ህዝ...
25/07/2023

ከንጉስ ስራዓት ጀምሮ እስከ ብልፅግና መንግስት የኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ መስራቾች እና መሪዎች ለምን የዎላይታ ተወላጆች ብቻ ሆኑ ❓

የብሔራዊ ባንክ እና የህንጻው ድራፍት ዲዛይን ከዎላይታ ህዝብ ባህላዊ ቤት ጋር ምን አገናኘው⁉️

ዎላይታነት ኢትዮጵያዊነትን ይገልጻል በማለት የመጀመሪያ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ገዥና መስራች የነበሩት ዶ/ር ምናሴ ለማ የመጀመሪያው የባንክ ህንጻ ድራፍት ዲዛይን ሰሰራ የሰጡት Concept design ጸድቆ ሃሳብ ተጨምሮ ጎልቶ እንድሰራ ታሪካዊ አሻራ ጥለዋል።

የዎላይታ ህዝብ በኢትዮጵያ ባንክ ጉልህ አሻራ የጣለና ለባንኩ ህንጻ ከፊትለፍት የጎጆ ቅርጽ እንድይዝ ያደረገና ለባንኩ መመሰረት የአንባሳውን ድርሻ የተወጣ በኢትዮጵያ ከመጀመሪያው ከንጉሱ ግዜ ጀምሮ እስከዛሬ ድረስ የማክሮ ኢኮኖሚ አማካሪ በመሆን ሃገርን ያገለገለ ኢኮኖሚስት ማህበረሰብ... #ዎላይታ!!

ለአንድ አገር እጅግ ታማኝና በንጽህናቸውና በዘርፉ እውቀት የተመሰከረላቸው ዜጎች ከሚፈለግባቸው ተቋማት አንዱ የገንዘብ ተቋም ነው። የአገሪቱ የገንዘብና ኢኮኖሚ ሥርዓትን በአስተማማኝ ሁኔታ ቀጥ አድርጎ ለማቆም ብሔራዊ ባንክ ወሳኝ ነው ። ዎላይታ ካፈራቻቸው በብቃታቸው የተመሰከረላቸው ዜጎች መካከል በሶስት መንግሰታት የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ገዥ የነበሩ የትውልድ አራያወችን እነሆ ።

1. የተከበሩ ዶ/ር ምናሴ ለማ

የመጀመሪያው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ገዥ
--------------------------------------------------
በአጸ ሐይለ ስላሴ ዘመነ መንግስት ኢትዮጵያችንን በዲኘሎማትነት ያገለገሉ በፈረንሳይና በግብፅ አምባሳደር የነበሩ እንዲሁም የመጀመሪያው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ገዥ በመሆን ያገለገሉ የመጀመሪያው ኢትዮጵያዊ ኢኮኖሚት ነበሩ። ዶ/ር ምናሴ ከሰራቸው ሥራዎች አንዱ የመጀመሪው የኢትዮጵያ ባንክ ህንጻ የዎላይታ ባህላዊ ቤት (Concept drawing) በመስጠትና የባንኩን የመመሰረቻ ሰነድ ያዘጋጁ ዛሬ ላይ የቀድሞ ህንጻውን ጨምሮ በየክፍለ ሃገሩ ለሚሰራው ህንጻ አውደ ጥናት ላይ ዎላይታነት ኢትዮጵያዊነትን ይገልጻል በማለት የሰጠው Concept design ጸድቆ ሃሳብ ተጨምሮ ጎልቶ እንድሰራ ታሪካዊ አሻራ የጣለ ጀግና ነው።

2. የተከሩ አቶ ለገሰ ሞታ

በደረግ ዘመነ መንግሰት የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ም ገዥ በመሆን ያገለገሉ ለኢትዮጵያ ዘመናዊ የባንክ አሰራር መሠረት የጣሉ ስሆን የደቡብ ምዕራብ ምዕራብ የመጀመሪያው ድስትርክት ሥራ አስክያጅ ሆኖ ስያገለግሉ ቆይተው በራሽያ ሃገር በቀሰሙት ትምህርት ፖለቲካንና ኢኮኖሚውን በማቻቻል ብሔራዊ ባንክ ገዥ በመሆን አገልግለዋል።

ከሶቭየት ህብረት ጋር በመናበብ ገንዘብ የማተምና የማሠራጨት፣ የሀገሪቱን የውጭ ምንዛሪ ማስተዳደር፣ የገንዘብ ፖሊሲ የማውጣትና የመተግበር ኃላፊነት በመውሰድ ስሰራ ቆይተው በ1985 ዓ/ም የጦርነቱ መሰናበቻ እና ህገ መንግስት ማሻሻያ ስደረግ የኢትዮጵያንና የኤርትራን አካፍልና የኛንም ድርሻ ጨምረ ለኤርተራ ገንዘቡን በአስቸኳይ አስተላልፍ የሚል መልዕክት ስተላለፍ እኔ እያለው ሃገረ ተካፍላ ማየት አልፈልግም የእናት ሃገር ገንዘብ ለሻዕቢያ አልሰጥም በማለቱ የመግደል ሙከራ ሲደረግበት ሃገር ለቆ ወደ አሜሪካ ገብተዋል።

በስተመጨረሽ ለብዙ ዘመናት Bank of America ላይ የቦርድ አባልና የባንኩ አማካሪ በመሆን ስያገለግሉ ቆይተው ጡረታ ወተው በክብር በአሜሪካ ሃገር እየኖሩ ይገኛሉ።

3. የተከበሩ አቶ ተክለወለድ አጥናፉ

ላለፉት 23 አመታት የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ገዥ የነበሩ፤ የኢትዮጵያ ኢኮ

 !! ደቡብ ኢትዮጵያ አስደናቂ ከተማ!!የካዎ ጦና  ምድር  ወላይታ ሶዶ!!✅ዘመናዊቷ ወላይታ "የካዎ ጦና" ከተማ እንደ ጨረቃ ደምቃለች  እንደፀሐይ ወጥታለች እንደ ጽገረዳ አበባ ፈክታለች። ...
15/07/2023

!!

ደቡብ ኢትዮጵያ አስደናቂ ከተማ!!የካዎ ጦና ምድር ወላይታ ሶዶ!!✅

ዘመናዊቷ ወላይታ "የካዎ ጦና" ከተማ እንደ ጨረቃ ደምቃለች እንደፀሐይ ወጥታለች እንደ ጽገረዳ አበባ ፈክታለች።

ወላይታ ሶዶ ከተማ የሚትተዳደረው በራሱ በጀት ነው። በክልሉም ትልቁ ግብር ከፋይ እና ከፍተኛ የገቢ የሚሰበሰቢባት ከተማ ናት።

የከተማው ስፋት17,000 ሄክታር በላይ በሆነ ቦታ ላይ 1(አንድ)ሚሊዮን የሚጠጉ ከተለያዩ ብሔረሰቦች የተውጣጡ ነዋሪ ህዝቦች አሏት። በተፈጥሮ አምራ እና ተውባ በልምላሜ ያገጠች ከተማ ናት።

ወላይታ ሶዶ 7 ዋና መግቢያና መውጫ በሮች፣ 4 ራዲዮ ጣቢያዎች ዉጌታ፣ኤፍ ኤም 96.6 ፣ፋና ኤፍ ኤም 99.9 እንዲሁም የክልሉ ትምህርት ጽ/ቤት ሬዲዮ ጣቢያ እንዲሁም
በከተማዋ 2 የቴሌቭዥን ጣቢያዎች ማለትም ወላይታ ቲቪ እና ደቡብ ቲቪ ያላት ለክልሉ ትልቁ ከተማ ናት

የንጉሱ ምድር ምርጥ ከተማ ለነዋሪዎቿ እና ለተጠቃሚዎቿዋ ቀላል መንገዶች (አስፋልት እና ኮብልስቶን)፣ ምርጥ የውሃ እና የፍሳሽ ማስወገጃ ዘዴዎች፣ ስድስት ክፍት የህዝብ ገበያዎች፣ በርካታ ወቅታዊ ሆቴሎች፣ የመዝናኛ ቦታዎች እና የገበያ ማዕከሎች በዘመናዊ የመንገድ መብራቶች አብለጭልጨው ምድራዊ ገነት የሆነች ከተማ ናት።

የወላይታ ሶዶ ከተማ የተላያዮ 7(ሰባት)የባንክ ዲስትሪክቶች ፣ የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ማዕከል፣ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ዋና ማዕከል፣ የኢትዮጵያ መንገዶች ባለስልጣን እና የደቡብ ገጠር መንገዶች ባለስልጣን እና በርካታ የመንግስት እና የግል ባንኮች ያሏት የኢኮኖሚ ምንጭ የሆነች ከተማ ናት።

ይህች ከተማ ትልቅ የነዳጅ መጋዘን፣ ከአስራ አምስት በላይ ማደያዎች፣ ብዙ የዱቄት እና የዳቦ ፋብሪካ፣ ትልቅ የእህል መጋዘን እና ከ25 በላይ የባንክ ቅርንጫፎች ያላት ይህች ከተማ ዘመናዊ እና በኢኮኖሚያዊ ትስስር የበለጸገች ከተማ ናት።

ወላይታ ሶዶ 4 ዋና ጤና ጣቢያዎች፣ የመንግስት ሆስፒታል (ኦቶና)፣ በአለም አቀፍ ደረጃ የሚታወቅ ልዩ ሆስፒታል (ሶዶ ክርስቲያን)፣ ዘመናዊ የግል ሆስፒታሎች እና በርካታ ዘመናዊ የግል ክሊኒኮች አሏት።

ትልቅ የእንስሳት ምርምር ማዕከል፣ የአፈር ምርምር ጣቢያ እና የገጠር ግብርና እና ቴክኖሎጂ ማስተላለፊያ ማዕከልን ጨምሮ በሶዶ ከተማው ውስጥ ይገኛሉ።

በተጨማሪም ይህ ዘመናዊ ከተማ 10 ሁለተኛ ደረጃ እና መሰናዶ ትምህርት ቤቶች (6 መንግስት ፣ 4 የግል) ፣ ትልቅ የመንግስት ዩኒቨርሲቲ (WSU) ፣ 2 ፖሊ ቴክኒክ እና ሙያ ኮሌጆች ፣ ትልቅ ግብርና ኮሌጅ ፣ ከ 15 በላይ እውቅና ያላቸው የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት (ኮሌጆች) እንዲሁም ልዩ አዳሪ ትምህርት ቤት (ሊቃ) እና ብዙ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤቶች አሏት።

ከዚህም ባሻገር፣ ከአከባቢው አልፎ በዓለም አቀፍ ደረጃቸውን የጠበቁ ምሁራንን የምታፈራ ከተማ ናት።

!

የሚጨበጥ የሚዳሰስ የህያው ታሪክ ባለቤት -ዎላይታ ህዝብ የዎላይታ ባህላዊ ሙዚየምን በጨረፍታ፦ በታዋቂው ጀርመን ዶቼቬሌ ሚዲያ 👇በዎላይታው ሙዚየሙ ከሚገኙ የሚዳሰሱ ቅርሶች መካከል አንዱ ማህ...
15/07/2023

የሚጨበጥ የሚዳሰስ የህያው ታሪክ ባለቤት -ዎላይታ ህዝብ

የዎላይታ ባህላዊ ሙዚየምን በጨረፍታ፦ በታዋቂው ጀርመን ዶቼቬሌ ሚዲያ 👇

በዎላይታው ሙዚየሙ ከሚገኙ የሚዳሰሱ ቅርሶች መካከል አንዱ ማህበረሰቡ በወቅቱ ይገለገልበት የነበረው የመገበያያ ገንዘብ ነው፡፡ ይህ ከብረት የተሠራውና “ማርጯ“ የሚል መጠሪ ያላው የመገበያያ ገንዘብ እስከ ቀይ ባህር ድረስ ለንግድ ልውውጥ ያገለግል እንደነበር በበርካታ የውጭ አገር ተጓዦች ተፅፎ እንደሚገኝ አቶ እያሱ ጠቅሰዋል፡፡

በዎላይታ ሶዶ ከተማ የሚገኘው የዎላይታ ባህላዊ ሙዚየም ገዘፍ ያለና በባህላዊ የጎጆ ንድፍ የተገነባ ሰፊ የትዕይንት ማሳያ አለው ፡፡ ዙሪያው በአገር በቀል እጽዋቶችና ዛፎች የተሸፈነ ነው ፡፡ አቶ እያሱ ገጃቦ በዎላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ የአገር በቀል ዕውቀት ጥናት ተቋም ውስጥ የባህል፣ የቅርስና የታሪክ ተመራማሪ ናቸው።

የዎላይታ ብሄር ባህላዊ የአኗኗር ዘይቤ ከመኖሪያ ጎጆው ውጪያዊ ገጽታ ይጀምራል የሚሉት አቶ እያሱ “ ዎላይታ በመኖሪያው አካባቢ የሚገኘውን ቦታ ዝም ብሎ አይተውም፡፡ እያንድንዱ ለምግብ እና ለመድሃኒትነት የሚያገለግሉ አገር በቀል እፅዋቶችንና ዛፎችን በመኖሪያ ጎጆው ዙሪያ ይተክላል፡፡ በዚህ ሙዚየምም ይህን ነባር ጠቃሚ ልማድ ለማሳየት ተሞክሯል“ ብለዋል፡፡

የዎላይታው የባህል ፣የቅርስና የታሪክ ተመራማሪው አቶ እያሱ እንደሚሉት ዎላይታ ለረጅም ጊዜ በጥንታዊ የመንግስት ሥረዓት ሲመራ ነው የቆየው፡፡ የመንግሥታዊ አስተዳደር ልማድ ከቀደሙት አባቶች የአስተዳደር ዘዬ የተቀዳ እንደነበር አቶ እያሱ ይናገራሉ፡፡ ህዝቡ በሦስት ሥርወ መንግሥታት ከካዎ ቢቶ እስከ ካዎ ጦና ድረስ በ52 በላይ ነገስታቶች ሲተዳደር እንደነበር የታሪክ ድርሳናት ያሳያሉ፡፡

በወቅቱ በሥረወ መንግሥታቱ መካከል ይከናወን የነበረው የሥልጣን ቅብብሎሽ ግን መመዘኛው ሌላ ሳይሆን ነገስታቱና መንግሥታቸው ለህዝቡ ምን ሠሩ የሚለው እንደነበር አቶ እያሱ አስረድተዋል።

በዎላይታው ሙዚየሙ ከሚገኙ የሚዳሰሱ ቅርሶች መካከል አንዱ ማህበረሰቡ በወቅቱ ይገለገልበት የነበረው የመገበያያ ገንዘብ ነው ፡፡ ይህ ከብረት የተሠራውና “ማርጯ“ የሚል መጠሪ ያላው የመገበያያ ገንዘብ እስከ ቀይ ባህር ድረስ ለንግድ ልውውጥ ያገለግል እንደነበር በበርካታ የውጭ አገር ተጓዦች ተፅፎ እንደሚገኝ አቶ እያሱ ጠቅሰዋል፡፡

በመዚየሙ ለእይታ ከቀረቡት ባህላዊ ቁሶች መካከል የብሄሩ ባህላዊ የሙዚቃ መሣሪያዎች ሌላው የተመልካቹን ቀልብ የሚስቡ ናቸው፡፡ በየመልካቸው ተሰድረው የሚገኙት የሙዚቃ መሣሪያዎች ምን አይነት አገልግሎት አላቸው ለሚለው አቶ እያሱ ሲያብራሩ “ለምሳሌ ዲንኬ እና ጨቻ ዘዬ የተባሉት የትንፋሽ መሳሪያዎች ለደስታ እና ለሀዘን ያገለግላሉ፡፡

በተለይ ደግሞ ነገሪታ የተባለው የምት ከበሮ ለቤተ መንግሥት ሥራ ያገለግል ነበር፡፡ ለምሳሌ ነገሬታው ሦስት ጊዜ ከተመታ በቤተ መንግሥት ግቢ ለቅሶ መኖሩን፤ አራት ጊዜ ከተመታ ደግሞ ሹመት እንዳለ ለህዝቡ መልዕክት ይተላለፍበት ነበር “ ብለዋል፡፡

የዎላይታ ማህበረሰብ በታታሪ ሠራተኝነቱ በቀዳሚነት ይጠቀሳል። ዛሬ ላይ የሚገኘው ትውልድ በተለያዩ የአገሪቱ አካባቢዎች በወዙና በላቡ አገር ሲያቀና ማየት የተለመደም፤ የሚታይም እውነት ነው፡፡ ይህ የታታሪነት ባህል ታዲያ ታሪካዊ ዳራ አለው ይላሉ የዎላይታ፣ የቅርስና የታሪክ ተመራማሪው አቶ እያሱ፡፡

በጥንታዊ የዎላይታ ሥረዓት አንድ የማህበረሰቡ አባል በልፋቱ ሠርቶና ደክሞ በርካታ ቁጥር የላቸው ከብቶችን ማርባት ከቻለ ንጉሱ ፊት ቀርቦ ባህላዊ ማዕረግ ይሰጠው እንደነበር አቶ እያሱ ይናገራሉ።

ከዎላይታ ብሄር ነ

Address

Sodo

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Wolayita Sodo Page posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share