10/08/2022
የደቡብ ምእራብ ህዝቦች ምክር ቤት ቤቱ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል መንግስት የ2015 በጀት አመት 11ቢሊየን 33 ሚሊየን 665 ሺህ 9 መቶ 67 ብር ከ 93 ሳንቲም ሆኖ የቀረበውን የበጀት አዋጅ አጸደቀ ።
*** *** ***
የመንግስት ውስን ሀብትን ከብክነት በመከላከል ለታለመለት ዓላማ እንዲውል ትኩረት ሊደረግ እንደሚገባ ተገልጿል ።
በ2015 በጀት ዓመት በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልላዊ መንግሥት ለሚከናወኑ ሥራዎችና
አገልግልቶች የሚያስፈልገውን በጀት አጽድቆ ከበጀት ዓመቱ መጀመሪያ ወቅት ጀምሮ ሥራ ላይ ማዋል አስፈላጊ መሆኑን የክልሉ ፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ወሰነች ቶማስ ገልጸዋል ።
ከማንኛውም የገቢ ምንጭ የተገኘውን ገቢ በክልሉ ለሚገኙ ዞኖችና የክልል ማዕከላት ከፋፍሎ በጀታቸውን ለመመደብ ቀመርና ሌሎች መመዘኛዎችን መሰረት በማድረግ መሠራቱንም ኃላፊዋ ገልጸዋል ።
በክልሉ የሚገኙ ዞኖች ከክልሉ በቀመር ያገኙትን ሀብት በስራቸው ላሉ ወረዳዎችና የከተማ አስተዳደሮች ፍትሀዊ በሆነ መልኩ የቀመር አሰራርና ሌሎች መመዘኛዎችን መሠረት በማድረግ በማከፋፈል ያልተማከለውን የፋይናንስ አስተዳዳር ተግባራዊ ማድረግ እንዳለባቸው ወ/ሮ ወሰነች ቶማስ ገልጸዋል ።
በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልላዊ መንግሥት ከሐምሌ 01/2014 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ሰኔ 30/2015 ዓ.ም በሚፈጸመው አንድ የበጀት ዓመት ጊዜ ውስጥ ከክልሉ መንግስት ከሚሰበሰበው ገቢ ፣ከፌደራል መንግስት ድጎማ እና ከሌሎች የገቢ ምንጮች የሚሰበሰበውን ገቢ በተመለከተ
1.ከፌደራል መንግስት ግምጃ ቤት 6,400,400,905
2.የዉጭ ዕርዳታ 38,564,62.93
3.ዘላቂ ልማት ግቦች 434,765,330
4 ከክልል ገቢ 4,159,935,112
በጠቅላላዉ የፌደራል መንግስት ድጎማና የክልሉ ገቢ ድምር 11,033,665,967.93 (አስራ አንድ ቢሊየን ሰላሳ ሦስት ሚሊየን ስድስት መቶ ስልሳ አምስት ሺህ ዘጠኝ መቶ ስልሳ ሰባት ከዘጠና ሶስት ሳንቲም) ሆኖ ቀርቧል።
ከአጠቃላይ በጀትም
1.ለክልል ማዕከል 2,156,495,403.93
2.ለዞኖች ጥቅል በጀት 8 ,877,170,564,00
3.ለክልላዊ ፕሮግራም 401,561,424.50
4.ለዘላቂ ልማት ግቦች ማስፈፀሚያ 434,765,330
5.ለክልሉ መጠባበቂያ በጀት 70,000,000
ጠቅላላ 11,033,665,967.93
(አስራ አንድ ቢሊየን ሰላሳ ሦስት ሚሊየን ስድስት መቶ ስልሳ አምስት ሺህ ዘጠኝ መቶ ስልሳ ሰባት ከዘጠና ሶስት ሳንቲም)መሆኑን ኃላፊዋ አቅርበዋል ።
በ2015 በጀት ዓመት ለዞኖች የተደለደለውን የቢሮ ኃላፊዋ ወ/ሮ ወሰነች ቶማስ አብራርተዋል ።
በዚህም መሠረት:_
ሀ/ካፋ ዞን 3,084,609,615.39
ለ/ቤንች ሸኮ ዞን 1,872,257,564.10
ሐ/ዳውሮ ዞን 1,786,400,664.85
መ/ሸካ ዞን 915,994,423.89
ሠ/ምዕራብ ኦሞ ዞን 733,614,847.20
ረ/ኮንታ ዞን 484,293,448.58
ሆኖ መደልደሉን ወ/ሮ ወሰነች ቶማስ ለምክርቤቱ አብራርተዋል ።
የቀረበው የ2015 በጀት ዓመት ረቂቅ አዋጅ የምክርቤት አባላት መክረውበት በሙሉ ድምጽ አጽድቀዉታል ።