የስማርት ስልኮች ጥገና Smartphone Repair and Maintenance at GediTech Trading

  • Home
  • Ethiopia
  • Jijiga
  • የስማርት ስልኮች ጥገና Smartphone Repair and Maintenance at GediTech Trading

የስማርት ስልኮች ጥገና Smartphone Repair and Maintenance at GediTech Trading በዚህ ገጻችን --------- መረጃዎች ይቀርባሉ፡፡

28/08/2016

How much time do smartphone users spend doing different things?

22 percent dedicated to fun (videos, music, surf, games)
22 percent dedicated to instant messaging
22 percent dedicated to calls
10 percent dedicated to social networks
10 percent dedicated to emails

25/08/2016

ያገለገሉ የ አይፎን ስልኮችን ከመግዛትዎ በፊት ሊወስዷቸው የሚገቡ ጠቃሚ የጥንቃቄ እርምጃዎች፡፡
በመጀመሪያ ሊገዙ የሚፈልጉት የትኛው የአይፎን ሞዴል መሆኑን ጠንቅቀው ይወቁ፡፡ የios ቨርዥን ብቻ በማየት ሊሳሳቱ አይገባም፡፡ ለምሳሌ ምንም እንኳን በአይፎን 4ኤስ እና በአይፎን 5ኤስ መካከል ሰፊ ልዩነት ቢኖርም ሁለቱም ግን ለምሳሌ ios 7ን ሊጠቀሙ ይችላሉና፡፡ ሁልጊዜም ቢሆን በቅርብ የመጣው ሞዴል የተሻሉ ብዙ ጠቀሜታዎች ሊኖሩት እንደሚችሉ የታወቀ ነውና፡፡
ስልኩ ከዚህ በፊት በተጠቃሚው እጅ ምን ያል ጊዜ እንደቆየ ይጠይቁ፡፡ ሻጩ ዘንድ ለረጅም ጊዜ የቆየ ስልክ የአገልግሎት እድሜው ውስን መሆኑ አይቀርምና፡፡
የባትሪውን እድሜ ጠንቅቀው ይወቁ፡፡ በአጠቃላይ ከተገዛ ከአመት በላይ የሆነውን ባትሪ ባለበት ሁኔታ ከመግዛት መጠንቀቅ ይመከራል፡፡
የስልኩን አጠቃላይ ውጫዊ ገጽታ በትኩረት ያጥኑት፡፡ መልኩ አለመወየቡን፣ የተሰበረ ወይም የተሰነጠቀ፣ የዛገ ወይም የሻገተ ነገር አለመኖሩን ወዘተ…
ስልኩ አሁን ለሚገለገሉበት የቴሌኮም ሲምካርድ የተከፈተ መሆኑን ሲም ካርድዎን በማስገባትና በመፈተሸ ያረጋግጡ፡፡ ለምሳሌ ከዚህ በፊት በኤቲ እና ኤቲ ሲሰራ የነበረው አሁን ለምሳሌ በኢትዮ ቴሌኮም ሲምካርድ መስራት መቻሉን እርግጠኛ ይሁኑ፡፡
አክቲቬሽን ሎክ አክቲቭ አለመሆኑን እርግጠኛ ይሁኑ፡፡ ይህ ካልሆነ አፕል አይዲ ስለሚጠይቅዎት፡፡ አፕል አይዲውን ያላወቁት ወይም ሊያገኙት የማይችሉት ስልክ ከሆነ ደግሞ በእውነቱ የገዙት ስልክ ለመለዋወጫነት ካልሆነ ለምንም ሊያገለግል አይችልምና በተለይ በዚህ ጉዳይ ላይ ልዩ ጥንቃቄ ይውሰዱ፡፡
ምናልባትም ከአምራቹ ድርጅት የተሰጡ የዋስትና(waranty) ጉዳዮች ካሉና ጊዜያቸው ያለፈ ወይም ያላለፈ መሆኑንም በትኩረት ይመልከቱት፡፡
በመጨረሻም ጊዜዎንና መስዋእት በማድረግ እነዚህን ጠቃሚ ምክሮች ስላነበቡ እናመሰግናለን፡፡ ተጨማሪ አስተያየትና ምክር ካለዎም ማካፈልዎን አይዘንጉ

23/08/2016

Have you ever gave a thought on what the letters at the network signal mean?
For your information....

R = roaming as you found out
E = Edge, or 2g...its really slow but works in a pinch
3G = 3g...still slow but better than Edge
H = HSPA, its a form of 3G just a lot faster...this was considered 4g before true 4g
H+ = HSPA+, same as above just faster
LTE = 4g LTE. its the fastest of the bunch.

30/07/2016

Got any problem with your Smartphone? We are there at your service. Just remember to forward it to us! Let's learn a lot from each other.

26/07/2016

ጸረ-ዘራፊ ሶፍትዌሮች(Antitheft Softwares)
እንደልብ ወዳጅ የሚያቀርቡት ታማኝ አገልጋይዎ… ስማርት ስልክዎ ጠፋ እንበል….(ወይም ደግሞ አያድርገውና የስልክ ቀበኞች ሲሳይ ሆነ…)
ፈጥኖ ወደአእምሯችን የሚመጣው ጉዳይ ቢኖር ስልኩን ለመግዛት የከሰከስነው በሺዎች (አንዳንዴም በአስራሺዎች) የሚቆጠር ገንዘብ እንዲሁ ውሀ በልቶት መቅረቱ ሊሆን ይችላል፡፡ከዚህ ባላነሰ(ወይም በባሰ መልኩ) ስልኮቻችን ላይ ያለው የተለያየ አይነት ዳታ፣ መረጃ፣ ወይም ሌላ Sensitive Private Data በባእዳን እጅ የመግባቱ ነገር ይበልጡኑ አስጨናቂ ሊሆንብን ይችላል፡፡
በአንድሮይድም ሆነ በiOS ፕላትፎርሞች የጠፋ ስልክዎን መልሰው ለማግኘት የሚያስችሉ፣ በስልክዎ ውስጥ የሚገኘውን ዳታ በርቀት መቆጣጠር (Remote data management) ወይም ሙሉ በሙሉ መደምሰስ የሚያስችሉዎ የተለያዩ አፕሊኬሽኖች አሉ፡፡ እነዚህን አፕሊኬሽኖች Find my Phone tools ወይም Antitheft Software ብለን ልንጠራቸው እንችላለን፡፡
እነዚህ አፕሊኬሽኖች በተለያዩ መንገዶች የጠፋብንን ስልክ እንዲሁም ዳታችንን ጉዳይ መከታተል እንድንችል ያግዙናል፡፡
ስልካችን (ዘራፊው) ሊቆጣጠረው በማይችለው መልኩ የAlarm/siren ድምጽ እንዲያሰማ በማድረግ
GPS Location Tracking አክቲቬት በማድረግ ስልካችን የሚገኝበትን ስፍራ በመጠቆም
ስልካችን የኢንተርኔት Connection በሚገባለት ሰአት አስቀድመን ባዘጋጀነው አካውንት እንድንከታተል በማስቻል
ስልኩ ላይ ያለው ዳታ፣ በሚሞሪ ካርዱ ላይ ያለውን ጨምሮ ወደ ጎግል ወይም iCloud አካውንታችን እንዲገባ በማድረግ፤ ካልሆነም ደግሞ በማይመለከታቸው ሰዎች እጅ እንዳይገባ ሙሉ በሙሉ በመደምሰስ (Data wipeout)
ስልኩን ለያዘው ሰው የተለያዩ አይነት የማስጠንቀቂያ መልእክቶች እንዲደርሰው በማድረግ (የስልኩ ስክሪን ላይ ይህ ስልክ የጠፋ መሆኑን፣ በመሆኑ በሚሰጠው አድራሻ ሪፖርት እንዲያደርግ በማስጠንቀቅ ወዘተ)
ሌላ ያልተፈቀደለት ባእድ ሲም ካርድ በጠፋው ስልካችን በሚገባበት ጊዜ የአዲሱን ሲም ካርድ ቁጥር አስቀድመን ወዳዘጋጀነው ቁጥር በ Text Message እንዲደርሰን በማድረግ
ስልካችንን የያዘውን ሰው የድምጽ፣ የምስል እና የቪዲዮ ዳታዎች በሚስጥር በመቅረጽ ወደ ጎግል ወይም iCloud አካውንታችን እንዲገባ በማድረግ (Remote Listening)
ወዘተ ወዘተ….

25/07/2016

ውድ የዚህ ገጽ አባላት፡ ስለስማርት ስልኮች ቴክኒካዊ ጥያቄዎች ቢኖሩዎ፣ ተጨማሪ ማብራሪያና ሞያዊ ገለጻ ቢያሻዎ፣ ስማርት ስልክዎ ቢበላሽና ምን ማድረግ፣ ወዴት መሄድ እንዳለብዎ ግራ ከተጋቡ ወዘተ… ጥያቄዎችዎን በዚህ ገጽ ላይ ፖስት በማድረግ አስፈላጊውን ምላሽና ምክር በማቅረብ ልናገለግልዎ ተዘጋጅተናል፡፡
በተጨማሪም አዲስ የስማርት ስልክ መግዛት ወይም መሸጥ ቢያሻዎ መልእክትዎን በዚህ ገጽ ላይ ያለገደብ ፖስት በማድረግ መረጃዎችን መለዋወጥ ይችላሉ፡፡

24/07/2016

ሀምሌ 17 ቀን 2008 ዓ/ም
የሶፍትዌር ችግር ማለት ምን ማለት ነው?
ከሚከተሉት አንደኛው ወይም ሁሉም ችግሮች በአይፎን ወይም የአንድሮይድ ስልክዎ ላይ ተከስተው ያውቃሉ?
ስልክዎ በራሱ ጊዜ እየበራ ይጠፋል፣ ወይም Involuntary Restart ያደርጋል
ስልኩ ሙሉ በሙሉ አይነሳም Dead Phone ይሆናል
ከጫኗቸው አፕሊኬሽኖች የተወሰኑቱ ተለይተው ያለመስራት ወይም የመዘግየትና ስታክ የማድረግ ችግር ያሳያሉ
በአጠቃላይ ስልክዎ እጅግ በጣም ቀርፋፋ ይሆናል ( በእርግጥ አንዳንድ ጊዜ ይህ አይነቱ ችግር በስልካችን ላይ በጣም ብዙ አፕሊኬሽኖችና ዳታዎችን በመያዝ ምክንያት ከሚሞሪ መጣበብም የተነሳ ሊከሰት ይችላል) ወይም የአንድሮይድ ወይም የአፕል ሎጎ ላይ Stack ያደርጋል
ለስልክዎ ያስገቡት የፓተርን ፓስወርድ ጠፍቶዎታል፣ ወይም User Locked ሆኗል
የኔትወርክ መዘጋት(Carrier Network Locked )፣
ከሚከተሉት አንደኛውን መልእክት ይሰጥዎታል SIM not Valid, Wrong SIM, Contact SP (Service Provider), Unknown SIM, Phone Restricted ወዘተ…
እና ሌሎችም
እነዚህን የመሳሰሉ ችግሮች በሚከሰቱበት ጊዜ ስልኩ የሶፍትዌር ችግር አለው ማለት ነው፡፡ በዚህ ጊዜ ከዚህ በታች የሚከተሉት መፍትሄዎች ችግሩን ሙሉ በሙሉ በመቅረፍ እፎይታ ይሰጡዎታል ማለት ነው
ማሳሰቢያ፡
ማንኛውንም የሶፍትዌርም ሆነ የሀርድዌር ጥገና ከመከወናችን በፊት data backup ማድረግ ወይም ያሉንን ዳታዎችና መረጃዎች ወደሌላ ሚዲየም (ወደሌላ ፍላሽ ሚሞሪ ወይም ወደ ኮምፒውተር ወይም ወደጎግል ወይም አይክላውድ አካውንት) ማዛወር ይኖርብናል፡፡ ይህን ማድረግ በጥገናው ሂደት ለሚደርስ የዳታ መጥፋት ሁነኛ መፍትሄ ይሆናል፡፡
ለአንድሮይድ ስልኮች
Hard Reset or Factory Reset ማድረግ
Format ማድረግ በዚህም ችግሩ ካልተፈታ በ Stock Firmware Flash ማድረግ
Unlocking, Android Rooting ማድረግ (User, Network Provider or Carrier etc… )
እና ሌሎችም
ለአይፎን ስልኮች
በቅርብ ጊዜ የ iTunes Software Restore ማድረግ
ቀደም ብለው በነበሩት የአይፎን ስልኮች ላይ የተለያዩ የ Jailbreaking ሶፍትዌሮች በመጠቀም የኔትወርክ ክልከላውን ሰብሮ ማለፍ
እና ሌሎችም
በድጋሚ ማንኛውንም የሶፍትዌርም ሆነ የሀርድዌር ጥገና ከመከወናችን በፊት data backup ማድረግ በፍጹም በፍጹም እንዳይዘነጉ፡፡

23/07/2016

Address

Bishoftu Debrezeit
Jijiga
254

Telephone

+251913267053

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when የስማርት ስልኮች ጥገና Smartphone Repair and Maintenance at GediTech Trading posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to የስማርት ስልኮች ጥገና Smartphone Repair and Maintenance at GediTech Trading:

Share