14/01/2022
እንኳን በደህና መጣችሁ!!
በሲዳማ ብ/ክ/መ የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን የክቡር ጠቅላይ ሚኒስቴር ዶ/ር አብይ አህመድ ጥሪ ተቀብላችሁ ከተለያዩ የአለም ሀገራት ወደ ሀገራችሁ የመጣችሁ ትውልዴ ኢትዮጵያውያንና የዲያስፖራ ማህበረሰብ፤ እንኳን ደህና መጣችሁ!
እያለ ግብርናን ለማዘመን ትልቅ ፋይዳ ያለውን የይርጋዓለም የተቀናጀ ግብርና ኢንዱስትሪ ፓርክ እንድትጎበኙ ሲጋብዝ ታላቅ ደስታ ይሰማዋል!
በፓርኩ ውስጥ በግልም ሆነ በቡድን ኢንቨስት ለማድረግ ለሚትፈልጉ በቡና፣ በአትክልትና ፍራፍሬ፣ በሰብልና ጥራጥሬ በማር፤ በወተትና እንስሳት ተዋጽኦ፣ በዶሮና እንቁላል፣ በቀርከሃና ደን ውጤቶች፣ በሁሉም ዘርፎች ከእኛ ጋር እንዲትሰሩ እድሉን አመቻችተንሎታል፡፡
በዚህ አጋጣሚ በቅርቡ ወደ ገበያ የተቀላቀሉ የወተት ማቀነባበሪያ፣ የአቮካዶ ዘይት፣ ቡናና ማር በአጭር ጊዜ ተወዳጅ የሆኑ የሀገር በቀል ኩባኒያዎቻችን ምርቶች በዚሁ ፓርክ የተመረቱ በመሆናቸው ኩራት ይሰማናል!
በተጨማሪም በበንሳ ዳዬ መካከለኛ ፓርክም ተመሳሳይ አገልግሎቶችን ለመስጠት የተዘጋጀን በመሆኑ ለሚፈልጉ ባለሀብቶች በቂ ድጋፍ ለማድረግ ዝግጁ መሆናችንን እንገልጻለን፡፡
በሌላ መልኩ በይርጋዓለም ኢንዱስትሪ ፓርክ ውስጥ የገበያ ማዕከል፣ የመዝናኛ ስፍራ፣ ለስልጠና ቢሉ ለልጆችዎ የትምህርት ቤት ማቆያ በቂ ስፍራዎች አሉን፡፡ ለስብሰባ ፣ለሰርግና ለልደት ምቹ አዳራሾችን በተመጣጣኝ ዋጋ ጥራቱን በጠበቀ የምግብና የትራንስፖርት አገልግሎቶችን ለማቅረብ በቂ ዝግጅት አድርገናል፡፡
በዚህ አጋጣሚ በካፌና ሬስቶራንት፤ ለሱፐር ማርኬትና መሰል አገልግሎቶች መሰማራት ለምትፈልጉ ባለሀብቶች ፓርኩ ጥሪ እያቀረበ፤
ኑ! ሀገራችንን አብረን እናልማ በሲዳማ ብ/ክ/መ የኢ/ፓ/ል/ ኮርፖሬሽን!!
አድራሻችን ሃዋሳ፤ ፒያሳ አዋሽ ህንጻ 6ኛ ፎቅ
በይርጋለም፡- ይርጋለም ኢንዱስትሪ ፓርክ አስተዳደር ህንጻ ዋና ስራ አስኪያጅ ቢሮ
በበንሳ፡- በንሳ ዳዬ መካከለኛ ኢንዱስትሪ ፓርክ፤
ስልክ በ0932189283/0979784863 ወይም 046 212 7977 ላይ ይደውሉ!