ደሴ አምባ - ኃ.የተ የህብረት ስራ ማኃበራት የገንዘብ ቁጠባና ብድር ዩኒዬን

  • Home
  • Ethiopia
  • Dese
  • ደሴ አምባ - ኃ.የተ የህብረት ስራ ማኃበራት የገንዘብ ቁጠባና ብድር ዩኒዬን

ደሴ አምባ - ኃ.የተ የህብረት ስራ ማኃበራት የገንዘብ ቁጠባና ብድር ዩኒዬን Financial cooperatives are a backbones for our community development!!!
(1)

05/05/2026
✍️ሰላም የህ/ስራ ቤተሰቦች🙏🥰 👉ደሴ አምባ(ኃ.የተ) የህ/ሥ/ማ/የገንዘብ ቁጠባና ብድር ዩኒየን 16ኛ አመት መደበኛ ጠ/ጉባኤውን ጥር 30/2018 ዓ.ም አካሄደ። ዩኒየናችን በዕለተ ቅዳሜ ደ...
08/02/2026

✍️ሰላም የህ/ስራ ቤተሰቦች🙏🥰
👉ደሴ አምባ(ኃ.የተ) የህ/ሥ/ማ/የገንዘብ ቁጠባና ብድር ዩኒየን 16ኛ አመት መደበኛ ጠ/ጉባኤውን ጥር 30/2018 ዓ.ም አካሄደ። ዩኒየናችን በዕለተ ቅዳሜ ደሴ ከተማ አልማ የመሰብሰቢያ አዳራሽ አባላት፣ባለድርሻና አጋር አካላት በተገኙበት ጠቅላላ ጉባዔው በደማቅ ስነስርዓት ተካሂዷል።

👉ውድ የህብረት ስራ ቤተሰቦችና የዩኒየናችን አባላትእንደሚታወቀው ዩኒየናችን   የሁሉንም አባላት እና ደንበኞች ፍላጎት መሰረት ያደረገና የተሟላ አገልግሎት ለመስጠት ከመደበኛው የፋይናንስ አገ...
06/06/2025

👉ውድ የህብረት ስራ ቤተሰቦችና የዩኒየናችን አባላት
እንደሚታወቀው ዩኒየናችን የሁሉንም አባላት እና ደንበኞች ፍላጎት መሰረት ያደረገና የተሟላ አገልግሎት ለመስጠት ከመደበኛው የፋይናንስ አገልግሎት በተጨማሪ የወለድ አልባ ፋይናንስ አገልግሎት እየሰጠ ይገኛል።

👇👇👇
✍ ለመሆኑ ወለድ አልባ የፋይናንስ አገልግሎት ስንል ምን ማለታችን ነው??

🌹መሠረታዊ ፅንሰ ሃሳብ🌹

✍️ወለድ አልባ የፋይናንስ አገልግሎት ማለት :
✔️በአብዛኛው ከእምነት ጋር በተያያዘ ምክንያት ገንዘባቸው በአስተማማኝ ቦታ ያለምንም የወለድ ክፍያ እንዲቀመጥላቸው እና ከወለድ ውጪ የብድር አገልግሎት እንዲያገኙ የሚፈልጉ አካላት ከፋይናንስ ተቋሙ/ከዩኒየኑ የሚያገኙት የፋይናንስ አገልግሎት ሲሆን ይህንን አገልግሎት ተግባራዊ ለማድረግ የሚወጡ ወጪዎች እንዲሁም በሥራ ሂደት የሚመጡ ትርፍና ኪሳራዎች ሸሪዓው በሚፈቅደው መሠረት የሚስተናገዱበት አሰራር ነው።

👉ይህ ወለድ አልባ የፋይናንስ አገልግሎት

ቅዱስ ቁርዓንንና የነብዩ መሀመድ (ሰለሏህ ዓለይሂ ወሰለም) አስተምህሮትን መሠረት በማድረግ የሸሪዓ ህግና ድንጋጌን ተከትሎ የሚሠራ ሲሆን በዋናነት ወለድ መቀበል፣ መክፈልና ተያያዥነት የሚኖራቸውን ሌሎች ክልከላዎችን የሚያካትት ሆኖ በመሠረታዊነትም የራሱ የሆኑ ቁልፍ መርሆዎችን ይከተላል፡፡ እነሱም፡-
1️⃣ ጥሬ ገንዘብ እውነተኛ ዋጋ የለውም፣
2️⃣ የንግድ ስጋትን መጋራት፣
3️⃣ ያለቀለት ምርት/ዕቃ/አገልግሎት ማቅረብ፣
4️⃣ በተበዳሪው ላይ ጫና የማያሳድር ስምምነት፣
5️⃣ ገንዘብን በሸሪዓ መር የሥራ መስክ ላይ ማዋል፣

✔️ እነዚህም መርሆዎች በህብረተሰቡ ውስጥ እኩልነትንና ፍትሃዊ የሀብት ተጠቃሚነትን እንዲሁም የምጣኔ ሃብት መረጋጋትን የሚያሰፍኑ ናቸው፡፡ በተጨማሪም የህብረተሰቡ የተጠቃሚነት መብት እንዲከበር እና ጎጂ በሆኑ ተግባራት (ለምሳሌ፡- በቁማር ተግባር፣ በአልኮል ንግድ፣በወሲብ ተግባር፣ የጦር መሳሪያ ግዥና ማምረት፣ ወዘተ የሥራ መስኮች) ላይ ገንዘብን ማዋል ወይም ኢንቨስት ማድረግን የሚከለክሉ ናቸው፡፡
........... ይቀጥላል።

✅ለበለጠ መረጃ
👇👇👇👇👇👇👇
🔰ስልክ
👉 09-11-68-95-00
👉 09-14-60-44-72
👉 033-312-65-44

Telegram group:-
👉@ https://t.me/DESSIE_AMBA_SACCOs_UNION
Telegram channel
👉@ t.me/DACSCCU
page ;
👉@ http://facebook.me/.amba.coops.saving.and.credit.union

★★★★★★★★★★★★★★

👉ሰላም የህብረት ስራ ቤተሰቦች በመቀጠልም ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች እንኳን ለኢደል-አደሀ( ለአረፋ) በዓል በሰላም አደረሳችሁ። መልካም በዓል !!👇👇👇👇👇👇👇Telegram group...
06/06/2025

👉ሰላም የህብረት ስራ ቤተሰቦች
በመቀጠልም ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች እንኳን ለኢደል-አደሀ( ለአረፋ) በዓል በሰላም አደረሳችሁ። መልካም በዓል !!
👇👇👇👇👇👇👇
Telegram group:-
👉@ https://t.me/DESSIE_AMBA_SACCOs_UNION
Telegram channel
👉@ t.me/DACSCCU
page ;
👉@ http://facebook.me/.amba.coops.saving.and.credit.union

********************

የተከበራችሁ የህ/ስ/ቤተሰቦች፤ የህብረት ስራ ሰላምታችን ይድረሳችሁ🙏🙏👉እንደሚታወቀው ዩኒየናችን የወለድ አልባ ፋይናንስ አገልግሎትን ለዓባላት ተደራሽ ለማድረግ ወደ ትግበራ በመግባት ሸሪዓውን...
29/05/2025

የተከበራችሁ የህ/ስ/ቤተሰቦች፤ የህብረት ስራ ሰላምታችን ይድረሳችሁ🙏🙏

👉እንደሚታወቀው ዩኒየናችን የወለድ አልባ ፋይናንስ አገልግሎትን ለዓባላት ተደራሽ ለማድረግ ወደ ትግበራ በመግባት ሸሪዓውን በጠበቀ መልኩ ማለትም ሸሪዓ መር የቁጠባና ብድር አገልግሎት አየሰጠ ይገኛል።
ከዚሁ ጋር ተያይዞ በትላንትናው ዕለት ማለትም በ19/09/2017 ዓ.ም በወረባቦ ወረዳ ቢስቲማ ከተማ በወረዳው ህ/ስ/ማ/ማስ/ጽ/ቤት አስተባባሪነት በወረዳው ውስጥ ለተመረጡ የገንዘብ ቁጠባና ብድር ህ/ስ/ማህበራት የግንዛቤ ፈጠራ ስራና አገልግሎቱን በይፋ ማሰጀመሪያ መድረክ ተካሄዷል።
✍በዕለቱም የዩኒየናችን ቦርድ ሰብሳቢ አቶ ሲሳይ ከበደ አጠር ያለ የመክፈቻ ንግግር በማድረግ የፕሮግራሙን መጀመር በይፋ አብስረዋል።
👉በዚህ መድረክ የተገኙት አካላትም፦
✅ የደ/ወሎ ዞን የፋይናንስ ህ/ስራ ማህበራት አደራጅ ቡድን መሪ፤
✅ የዩኒየኑ አመራሮች፣ዋ/ስራ አሰኪያጅ፣ የዘርፉ ክፍል ኃላፊና የቅ/ፍ ሰራተኞች፤
✅የወረባቦ ወረዳ ህ/ስ/ማህበራት ማ/ጽ/ቤት ኃላፊና ባለሙያዎች፤
✅ የተመረጡና ቁጥራቸው 8 የሚደርሱ መሰ/ማህበራት አመራሮችና አባላት፤
✅ ከየማህበራቱ የተመረጡ የሸሪዓ አማካሪ ቦርዶች፤
✅ እና ሌሎችም የተገኙበት ደስ የሚል መድረክም ነበር።

👉ዋና ስራ አስኪያጁ አጠቃላይ ተቋሟዊ ገፅታና የወለድ አልባ ፋይናንስን ምንነት ዙሪያ በቂ ገለፃ ካደረጉ በኋላ ሀሳቦችና ጥያቄዎች ከመድረኩ አየተነሱ በሳልና አስተማሪ ውይይትም ተደርጓል።

✍በመቀጠልም ደሴ አምባ ዩኒየን በወለድ ምክንያት ከፋይናንስ ስርዓቱ ለራቀው ሰፊው የማህበረሰብ ክፍል መፍትሄ ይዞ የመጣ መሆኑን ተሳታፊ አመራሮችና አማካሪ ቦርዶች ገልፀዋል።

➡️ በመጨረሻም የዞኑ የፋይ/ህ/ስ/አደ/ቡድን መሪ አቶ ደረጀ መንግስቱ የቀጣይ አቅጣጫ በማስቀመጥ ፕሮግራሙ ባማረ ሁኔታ ተጠናቋል።
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
👉ለበለጠ መረጃ
09-11-68-95-00
09-14-60-44-72
✍️
Telegram group:-
👉@ https://t.me/DESSIE_AMBA_SACCOs_UNION
Telegram channel 👉@
t.me/DACSCCU
page ;
👉@ http://facebook.me/.amba.coops.saving.and.credit.union

**************************************************************

24/05/2025

የገጠር መሬት ባለይዞታነት በኢትዮጵያ ህግ
መግቢያ
አብዛኛው የኢትዮጵያ ማህበረሰብ በግብርና ሥራ የሚተዳደር ሲሆን ግብርና ደግሞ የሀገሪቱ የጀርባ አጥንት ነው። የግብርና ሥራን ለማከናወን መሬት በጣም አስፈላጊና ዋናው ሲሆን በኢትዮጵያ ህገ-መንግስት መሰረት የገጠርም ሆነ የከተማ መሬት ባለቤትነት የመንግስትና የህዝብ እንደሆነ ተቀምጧል። የህዝብ ቁጥር እየጨመረ መምጣቱ የመሬት ሀብት እያነሰ እንዲመጣ ያደረገው በመሆኑ የገጠር መሬትን ለማስተዳደርና ለመቆጣጠር እንዲያመች እራሱን የቻለ ህግ ማውጣት የግድ ይላል። የገጠር መሬትን በሚመለከት ከዚህ በፊት የተለያዩ ህጎች የወጡ ሲሆን ከሀገሪቱ አሁናዊ ሁኔታ በመነሳት ያለፉትን አዋጆች በመሻር በ2016 ዓ.ም አዲስ የገጠር መሬት አስተዳደርና አጠቃቀም አዋጅ በህዝብ በተወካዮች ምክር ቤት ፀድቆ በሥራ ላይ ውሏል፡፡
በመሆኑም ለኀብረትስራ ማህበራት በተለይም ለገንዘብ ቁጠባና ብድር ኀብረት ስራ ማህበራት አባላት የነበረውን የረዥም ጊዜ ጥያቄ የሆነውን በአዋጅ ምላሽ እንዲያገኝ ተደርጓል፡፡
ስለሆነም የማስፈፀሚያ መመሪያ እስከ ሚወጣ ድረስ አዋጁ ላይ ለኀብረት ስራ ማህበራት የሚገልፀውን አንቀጽ ከዚህ በታች እንደሚከተለው ነው፡፡
የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ መንገስት የገጠር መሬት አስተዳደርና አጠቃቀም አዋጅ ቁጥር 1324/16
አንቀጽ 15፡ በይዞታ የመጠቀም መብትን ለብድር ዋስትና ስለማስያዝ
1. የገጠር መሬት ባለይዞታ የመጠቀም መብቱን በየክልሉ በሚወጡ ህጎች ለሚወሰን የጊዜ ገደብ ለፋይናነስ ተቋማት ለብድር ዋስትና ማስያዝ ይችላል፡፡
2. የገጠር መሬትን የመጠቀም መብትን በመጠቀም አበዳሪዎች የሚሰጡት የብድር መጠን የተበዳሪዎን ዕቅዶች ሊያሳካ የሚችል እንዲሆን የመሬቱን እምቅ አቅም ከፍተኛ ጣሪያ መሰረት ማድረግ አለባቸው፡፡
3. የገጠር መሬት ባለይዞታ የመጠቀም መብቱን ሌላ ሰው ከፋይናንስ ተቋማት ለሚበደረው ብድር ዋስትና ማስያዝ ይችላል፡፡
4. አበዳሪና ተበዳሪ የብድር መመለሻ ጊዜንና ብድር በሙሉ ወይም በከፊል ባይመለስ አበዳሪ መሬቱን ሊይዝ የሚችልበትን የጊዜ ገደብ በግልፅ በውላቸው ላይ ማስቀመጥ አለባቸው፡፡
5. ብድር ባለመመለሱ ምክኒያት የአበዳሪው በዋስትና የያዘውን መሬት የመጠቀም መብት ከ10 ዓመት ሊበልጥ አይችልም፡፡
6. ተበዳሪ በውላቸው በተጠቀሰው ጊዜ ብድሩን ያልከፈለ ከሆነ አበዳሪ በሙሉ ለተጠቀሰው ጊዜ ያህል ብቻ በመሬቱ የመጠቀም ፣የማከራየት ወይም ለጋራ አራሽ የመስጠት መብት አለው፡፡
7. አበዳሪ ዕዳው ባለመከፈሉ በውሉ በተቀመጠው የጊዜ ገደብ በዋስትና የያዘውን መሬት በመጠቀም ከአበዳሪው ገንዘብ የበለጠ ጥቅም ቢያገኝ ተበዳሪ ከዚህ የመጠየቅ መብት የለውም ፡፡
8. ብድሩ በከፊል ባልተከፈለ ጊዜ የአበዳሪውበመሬቱ ላይ ያለው የመጠቀም መብትና የአከፋፈል ሁኔታ ያልተከፈለውን ብድር ታሳቢ ማድረግ አለበት፡፡
9. አበዳሪ ዕዳው ባለመከፈሉ በዋስትና የያዘውን መሬት በመጠቀም ከአበዳሪው ገንዘብ ያነሰ ጥቅም ቢያገኝ መሬቱን በውሉ ከተቀመጠው የጊዜ ገደብ በላይ ለመያዝ ወይም የተበዳሪውን ሌላ ንበረት በመያዝ ለዕዳው ማስፈፀሚያ ለማዋል አይችልመ፡፡
10. ማንኛውም የማስያዣ ውል በፁሑፍ መደረግና በክልል ስልጣን በተሰጠው የወረዳ ፣ልዩ ወረዳ እና ከተማ አስተዳደር ተቋም ቀርቦ መረጋገጥ እና መመዝገብ አለበት፡፡
11. ከላይ ተደነገገው እንደተጠበቀ ሆኖአበዳሪና ተበዳሪ ስለሚኖራቸው ዝርዝር መብትና ግዴታ በየክልሉ በሚወጡ ሕጎች ይወሰናል ፡፡
12. በአበዳሪና በተበዳሪ መካከል የዋስትና የመሬት የመተቀም መብትን በሚመለከት ለሚነሱ ማናቸውም ክርክር በእርቅ ወይም ስልጣን ባለው መደበኛ ፍ/ቤት ቀርቦ መወሰን አለበት፡፡
ማሳሰቢያ
ይህን አዋጅ መሰረት ያደረገ ለአንቀጽ 15 የአብክመ ኀብረት ስራ ማህበራት ማስፋፊያ ባለስልጣን ከመሬት ቢሮ ጋር በጋር በመነጋገር ሊያሰራ የሚችል ለገንዘብ ቁጠባና ብድር ኀብረት ስራ ማህበራት የብድር መመሪያ ላይ ተካቶ የአሰራር መመሪያ የሚወጣ እና የሚተገበር ይሆናል፡፡እስከዚየው ድረስ በትዕግስት መጠበቅ ነው፡፡

21/05/2025
እንኳን ደስ አላችሁ!ደሴዎች ደሴ አምባ አለላችሁሠላም የህ/ስራ ቤተሰቦች  ዛሬ በርግጠኝነት ደሴ ላይ  የቤት ባለቤት መሆን ይቻላል።        በህብረት ስራ ማሀበራት ጥላ ስር ነጋቸዉን የተ...
04/05/2025

እንኳን ደስ አላችሁ!
ደሴዎች ደሴ አምባ አለላችሁ

ሠላም የህ/ስራ ቤተሰቦች ዛሬ በርግጠኝነት ደሴ ላይ የቤት ባለቤት መሆን ይቻላል።
በህብረት ስራ ማሀበራት ጥላ ስር
ነጋቸዉን የተሻለ ለማድረግ የሚታትሩ ወገኖቻቸው ከመበደር ባሻገር የባንክ ባለቤት ሆነው ጭምር ቤታቸውን መገንባት ይችላሉ።
በመኖሪያ ቤት ህብረት ስራ ማሀበራት ሁለገብ አገልግሎት በመስጠት ማንም የፋይናንስ ተቋም ከጎኑ ሊቆም በማይችል መልኩ ተጨባጭ አገ/ት በመስጠት ደሴ ከተማ፣ደ/ዙሪያ፣ ኮ/ቻ፣ ደላንታ፣ኩታበር፣፣ወረባቦ፣አልብኮ... ከዩኒየናችን ፈዋሽ አገልግሎት አግኝተው የቦታና የቤት ባለቤት ሆነዋል።
ዛሬ ለሁለተኛ ዙር ተራው የደሴ ከተማ ሆኗል በጥቅሉ በህ/ስ/ማሀበራት ተደራጅተው ወይም ለመደራጀት ፍላጎት ኖሮ የአቅም ማሳያ/ቅድመ ቁጠባ ጭምር የሌላቸውን እንዲሁም የካሳ ክፍያ ገንዘብ እጥረት የገጠማቸውንና ለግንባታ የሚውል በቂ የብድር አቅርቦት በማመቻቸት በርካቶችን የቦታና የቤት ባለቤት ማድረግ የዘወትር ተግባራችን መሆኑ ይታወቃል።
ህ/ስ/ማሀበራት ለማኝ ሳይሆኑ የሠፊ ሀብት ባለቤቶችና የፋይናንስ ተቋማት የደም ስር ጭምር ናቸው።
በደሴ አምባ የህብረት ስራ ማሀበራት ጀምበር አትጠልቅም
በዩኒየናችን የትኛውም የፋይናንስ ተቋም በማያደርጉት መልኩ የትኛውም ቁጠባ ወለድ የገቢ ግብር አይቆረጥበትም፣ ለሚሰጠው ብድር ባለቤትነትን በተግባር የሚያሳይና ዝቅተኛ ወለድ በማስከፈል ያበድራል፣ ከሚያገኘው መጠነኛ አመታዊ ትርፍ ላይ ለአባል ህ/ስ/ማሀበራት በገዙት እጣ ብዛትና ቆይታ መሰረት አድርጎ የትርፍ ክፍፍል ይሰጣል፣ ተበዳሪወች ወይም የትዳር አጋሮቻቸው የሞት አደጋ ካጋጠማቸው የተበደሩትን እዳ ከነወለዱ ሰርዞ በተጨማሪ ለሟች ቤተሰብ የቀብር ማስፈጸሚያ ጥሬ ብር ይከፍላል/የብድር ህይወት መድህን አገ/ት ይሰጣል ሌላም...
እናም የደሴ ከተማ እና አካባቢው ኗሪወች ይህን እድል ተጠቅማችሁ የቤት ባለቤት ትሆኑ ዘንድ ተጋብዛችኋል።
አድራሻ ደሴ ከተማ አልማ ህንጻ ሁለተኛ ፎቅ ባለው የዩኒየኑ ዋና ጽ/ቤት ይምጡ የቤተሰብ አቀባበልና ልዩ መስተንግዶ ይጠብቃችኋል።
ይህን መልእክት ከእርስዎ ባሻገር ለሌሎች ወገኖቻችን ሸር በማድረግ የቤት ባለቤት እንዲሆኑ እፎይታ እንዲሰማቸው ያድርጉ።
በህብረት ስራ ቤታችን ይሰራ!

👇👇👇👇👇👇
ለበለጠ መረጃ
☎️ 033-312-65-44
09-11-68-95-00
09-14-60-44-72 ✍️
ቢሮ-አድራሻ:- ደሴ ከተማ መናፈሻ አልማ ህንጻ 2ኛ ፎቅ

Telegram group:-
👉@ https://t.me/DESSIE_AMBA_SACCOs_UNION
Telegram channel @
t.me/DACSCCU

page ;
👉@ http://facebook.me/.amba.coops.saving.and.credit.union

****************************

***************************

29/04/2025

#የ

.የተ_የህብረት_ስራ_ማኃበራት_የገንዘብ_ቁጠባና_ብድር_ዩኒዬን


#ደሴ




👉ሰላም የህብረት ስራ ማሀበራት ቤተሰቦች🙏🙏❤
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
✍️ዩኒዬናችን የሚሰራቸው ዋና ዋና ተግባራት፡-👇
✔️1⃣ የቁጠባ አገልግሎት
✔️2⃣ የብድር አገልግሎት
✔️3⃣ ወለድ አልባ የፋይናንስ አግልግሎት (Non Interest Bearing Finance _NIB Service)
✔️4⃣ የብድር መድህን/ኢንሹራንስ ሽፋን አግልግሎት
✔️5⃣ ተካፉል/ተዓውኒ አገልግሎት
✔️6⃣ ለአባላት የስልጠና መስጠት
✔️7⃣ለአባላት የሂሳብ አያያዝ ድጋፍ ማድረግ
✔️8⃣ የድርጅቶችና ተቋማትን የአስተዳድሩልኝ ገንዘብ ማስተዳደር
✔️9⃣ እና ሌሎች ተግባራት

👇👇👇👇👇👇
ለበለጠ መረጃ
☎️ 033-312-65-44
09-11-68-95-00
09-14-60-44-72 ✍️
ቢሮ-አድራሻ:- ደሴ ከተማ መናፈሻ አልማ ህንጻ 2ኛ ፎቅ

Telegram group:-
👉@ https://t.me/DESSIE_AMBA_SACCOs_UNION
Telegram channel @
t.me/DACSCCU

page ;
👉@ http://facebook.me/.amba.coops.saving.and.credit.union

****************************

***************************

Address

Menafesha, A. D. A Building, 2nd Floor, No. 8
Dese

Opening Hours

Friday 11:30 - 13:30
Saturday 09:00 - 17:00
Sunday 00:00 - 12:00

Telephone

+251911689500

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when ደሴ አምባ - ኃ.የተ የህብረት ስራ ማኃበራት የገንዘብ ቁጠባና ብድር ዩኒዬን posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to ደሴ አምባ - ኃ.የተ የህብረት ስራ ማኃበራት የገንዘብ ቁጠባና ብድር ዩኒዬን:

Share