14/05/2026
💫💫የራስን ዋጋ ማወቅ በህይወትህ ላይ ምን ያህል ተፅዕኖ እንዳለው ታውቃለህ???
በሕይወታችን ውስጥ በራሳችን ላይ ተስፋ የምንቆርጥባቸው፣ "እንደ ሌሎች አይደለሁም" ብለን የምናስብባቸውና በራሳችን የምናፍርባቸው ጊዜያት ይኖራሉ። ይህ ስሜት ልክ እንደ ከባድ ጭጋግ ውስጣችንን ይሸፍነዋል።
ብዙውን ጊዜ በራሳችን ላይ እንድንከፋ የሚያደርገን ራሳችንን ከሌሎች ጋር ማወዳደራችን ነው። የሌሎችን "ውጫዊ ስኬት" ከእኛ "ውስጣዊ ትግል" ጋር እናወዳድራለን።
ነገር ግን መዘንጋት የሌለብን፣ እያንዳንዱ ሰው የራሱ የሆነ የጨለማ ጊዜ አለው። ስህተት መስራት ማለት "አንተ ስህተት ነህ ማለት አይደለም። ውድቀት ትምህርት እንጂ መድረሻ አይደለም። ዛሬ ደካማ እንደሆንክ ቢሰማህ፣ ያ ደካማነት ለነገው ጥንካሬህ መሰረት ነው።
ትናንት የተሸነፍክበት ጉዳይ የዛሬውን አይገታውም።የሰዎች ትችት ያንተን ማንነት አይወስነውም። ራስህን ይቅር በል።
ፍጹም ለመሆን አትጣጣር/ሪ፤ ይልቁንም የተሻለ ሰው ለመሆን ሞክር/ሪ። ዛሬ በራስህ ላይ ያለህ ስሜት መጥፎ ቢሆንም፣ ነገ አዲስ ቀን ነው።
ፀሐይ በደመና ተሸፈነች ማለት ጠፋች ማለት አይደለም፤ ደመናው ሲገፈፍ በደመቀ ሁኔታ ትወጣለች። ያንተም ማንነት እንደዚሁ ነው። ይህ ጭጋግ ያልፋል፣ አንተ ግን ትቀጥላለህ ።
በርታ አንተ ከምታስበው በላይ ጠንካራ ነህ።
ሠናይ ምሽት👌