ላዚዮ ቁጠባና ብድር ህብረት ሥራ ማህበር

ላዚዮ ቁጠባና ብድር ህብረት ሥራ ማህበር የላዚዮ ቁጠባና ብድር ህብረት ሥራ ማህበር በአባላቱ የ200 (ሁለ?

22/04/2026

በሀገራችን አሁን ላይ በየመንደሩ የምናገኛቸው የብድር እና ቁጠባ ማህበራት በኢኮኖሚያዊ ልማት ውስጥ ያላቸው ዋና ዋና ነጥቦች እና ሚናዎች በጥቂቱ የሚከተሉትን ይመስላሉ፡፡
1. የፋይናንስ ተደራሽነትን ማሳደግ - ዝቅተኛ ገቢ ላላቸው ሰዎች (ሴቶችን ጨምሮ) ባንክ የማይደርሳቸውን ክፍተት ይሞላሉ።
2. ድህነትን መቀነስ - ብድር በመስጠት ሰዎች ትንንሽ ንግዶችን እንዲጀምሩ፣ ግብርናን እንዲያሳድጉ እና ገቢን እንዲጨምሩ ያግዛሉ።
3. የአካባቢ ኢኮኖሚ ማጎልበት - የአባሎችን ቁጠባ በመሰብሰብ እና ወደ ብድር በመቀየር ገንዘቡ በአካባቢው ውስጥ እንዲዘዋወር ያደርጋሉ። ይህም የስራ እድል ይፈጥራል፣ ምርታማነትን ያሳድጋል።
#በከተማችን ጥቁር ውሀ ብቸኛው ጠንካራ የሆነው ላዚዮ ቁጠባና ብድር የህብረት ስራ ማህበር በርካቶችን ተጠቃሚ እያደረገ ይገኛል፡፡
#ብድር ወስደህ ምን ሰራህ? በቂ ቁጠባስ ታደርጋለህ?
#እንቆጥብ፣ እንበደር፣ ብድራችንን በአግባቡ እንመልስ!
#ላዚዮ አንድ ቤተሰብ!

20/06/2025

የ2017 ዓ.ም መገባደጃ ሰሞን ማስታወሻ

ከጥቂት ዓመታት በፊት በጥቂት ባለራዕዮች የተመሰረተው ላዚዮ ብድርና ቁጠባ ኅብረት ስራ ማህበር (ጥቁር ውሀ) ከዓመት ወደ ዓመት ከፍተኛ ዕድገትን እያስመዘገበ ይገኛል፡፡

በእነዚህ ዓመታት ውስጥ ማህበራችን በዋናነት በሶስት ግቦች ላይ ትኩረት በማድረግ ተንቀሳቅሷል፡፡

• የአባላትን ቁጥር ማሳደግ
• የማህበሩን የገንዘብ አቅም (Capital) ማሳደግ
• ለአባላት የብድር አገልግሎት መስጠት

በዚህ ዓመት መጀመሪያ (ቅዳሜ መስከረም 25) በተካሄደው ጠቅላላ ጉባዔ የ2016 ዓ.ም ስራ አፈፃፀም ሪፖርት እና የ2017 ዓ.ም ዕቅድ ውይይት መደረጉ ይታወሳል፡፡

በወቅቱ ቀርቦ የነበረው ሪፖርት እንዳመላከተው፤ በ2016 ዓ.ም የማህበሩን ካፒታል 3.5 ሚሊዮን ለማድረስ ታስቦ ከ3.6 ሚሊዮን በላይ ማድረስ ተችሎ ነበር። ለብድር አገልግሎት ፈላጊዎች እስከ 3 ሚሊዮን ብር ያህል የብድር አገልግሎት ለመስጠት ታቅዶ 2.9 ሚሊዮን ብር ለአባላት የብድር አገልግሎት መዋሉ ይታወቃል፡፡ ማህበሩ በሚሰጠው አገልግሎት ጠቅላላ ገቢ 369 ሺህ ማግኘት ችሏል። የማህበሩን ተቀማጭ ገንዘብም ወደ 135 ሺ ማሳደግ የተቻለበት ዓመት እንደነበር ይታወሳል፡፡ ለአባላቱም በአክሲዮን ድርሻቸው ልክ የ18 በመቶ ትርፍ ክፍፍል ተደርጓል። በዚህም 2016 ዓ.ም ከታቀደው አንፃር ስኬታማ ዓመት አሳልፎ ወደ 2017 ዓ.ም መሸጋገሩ ይታወሳል፡፡

በ2017 ዓመትም የተለያዩ ዕቅዶች ታቅደው ለተግባራዊነቱ ጠንካራ እንቅስቃሴ እየተደረገ ይገኛል፡፡ ከማህበሩ ዕቅዶች መካከል የካፒታል አቅሙን 5 ሚሊዮን ማድረስ፣ እስከ 4 ሚሊዮን ብር የሚደርስ የብድር አገልግሎት መስጠት እና ጠቅላላ ገቢውን ግማሽ ሚሊዮን (500000) ብር ማድረስ የሚሉት ይገኙበታል፡፡

በዚህም መሰረት 2017 ዓ.ም ወደ መገባደጃው እየተቃረበ በመሆኑ ዕቅዱን ከግብ ለማድረስ በማህበሩ ሥራ አስፈፃሚ አባላት እና ጠቅላላ አባላት ከፍተኛ ርብርብ እየተደረገ ይገኛል፡፡

በመሆኑም ዕቅዱን ዕውን ለማድረግ አባላት የቁጠባ ግዴታን በወቅቱ መወጣት እና የብድር ተመላሾችን በተገቢው መንገድ መክፈል በእጅጉ አስፈላጊ መሆኑ ሊታወቅ ይገባል፡፡

ስራ አስፈፃሚ አባላትም በቁርጠኝነት መስራት፣ ክትትል ማድረግ እና አሰራሮችን ማዘመን ላይ በትኩረት ሊሰሩ ይገባል፡፡

ወሰናችን አድማስ ጥግ አረማመዳችን በጋራ ነው!
ላዚዮ ብድርና ቁጠባ ኅብረት ስራ ማህበር
(ጥቁር ውሀ)

11/10/2021

ከሶስት ዓመታት በፊት በጥቂት ባለራዕዮች የተመሰረተው ላዚዮ ብድርና ቁጠባ ኅብረት ስራ ማህበር (ጥቁር ውሀ) ከዓመት ወደ ዓመት ከፍተኛ ዕድገትን እያስመዘገበ ይገኛል፡፡

በእነዚህ ዓመታት ውስጥ ማህበራችን በዋናነት በሶስት ግቦች ላይ ትኩረት በማድረግ ተንቀሳቅሷል፡፡

• የአባላትን ቁጥር ማሳደግ
• የማህበሩን የገንዘብ አቅም (Capital) ማሳደግ
• ለአባላት የብድር አገልግሎት መስጠት

በእነዚህ የትኩረት ነጥቦች ላይ የተለያዩ እንቅስቃሴዎች ሲደረጉ ቆይተው አሁን ላይ የማህበራችን አባላት ቁጥር 63 መድረስ ችሏል፡፡

የማህበሩ መንቀሳቀሻ የገንዘብ አቅም ከ1 ነጥብ 1 ሚሊዮን ብር በላይ የደረሰ ሲሆን፤ ይህም አምና ከነበረው የግማሽ ሚሊዮን ብር ጋር ሲነፃፀር አመርቂ ውጤት የተገኘበት ሆኗል፡፡

በአንድ ዓመት የሥራ አፈፃፀሙ ብቻ 28 የማህበሩ አባላትን የብድር ተጠቃሚ ማድረግ የቻለው ማህበሩ፤ ለአንድ ግለሰብ እስከ አንድ መቶ ሺህ (100,000) ብር የብድር አገልግሎት የመስጠት አቅም ፈጥሯል፡፡

ማህበራችን እስከ አሁን የተጓዘበት ሁኔታ ከዕቅድ በላይ ስኬት ያስመዘገበበት ሆኗል፡፡

አባላት የቁጠባ እና የአክስዮን ድርሻቸውን እያሳደጉ መምጣታቸው ትልቅ ውጤት እያስገኘ መሆኑ ሊሰመርበት ይገባል፡፡

የአባላት ተጠቃሚነት እየተረጋገጠ በመምጣቱ የቁጠባ እና ብድር ግንዛቤ ማደጉ ተስትውሏል፡፡

በቴክኖሎጂ የታገዘው የመረጃ ልውውጥ እና ፈጣን አገልግሎት የማህበራችን መለያ መሆኑ በጉልህ የታየ ነው፡፡

በዚያው መጠን ለወደፊቱ ፈጣን ጉዟችን እንቅፋት ሊሆኑ የሚችሉ እና በቶሎ ሊስተካከሉ የሚገቡ ክፍተቶች ተስተውለዋል፡፡

ወርሀዊ ቁጠባ ለማስገባት የሚታዩ መዘግየቶች፣ ዝቅተኛውን የቁጠባ መጠን እንደ ግዴታ በመውሰድ ቁጠባን አለማሳደግ፣ ቸልተኝነት እና የተነሳሽነት ማነስ ሊቀረፉ የሚገባቸው የአንዳንድ አባላት ድክመቶች ናቸው፡፡

ማህበራችን ከፊቱ በርካታ መልካም አጋጣሚዎች እየጠበቁት ሲሆን በያዝነው ዓመት በከፍተኛ ሁኔታ ውጤታማ ሊያደርገው የሚችል እና ተተግባሪ ዕቅድ በማዘጋጀት ወደ እንቅስቃሴ ገብቷል፡፡

ለዕቅዱ ስኬት የሚረዱ አንዳንድ የህገ ደንብ ማሻሻያዎችን ያደረገ ሲሆን አጠቃላይ ዕቅዶችን እና የተሸሻሉ ህገ ደንቦችን እንደ አስፈላጊነቱ በተከታታይ ጽሑፎች ለአባላት የምናሳውቅ ይሆናል፡፡

ወሰናችን አድማስ ጥግ አረማመዳችን በጋራ ነው!
ላዚዮ ብድርና ቁጠባ ኅብረት ስራ ማህበር
(ጥቁር ውሀ)

የላዚዮ ቁጠባና ብድር ህብረት ሥራ ማህበር መስራች አባል የሆኑት የአቶ ሙሉ ግርማይ ወላጅ እናት ከዚህ ዓለም በሞት በመለየታቸው የተሰማንን ጥልቅ ሀዘን እንገልፃለን።ፈጣሪ ነፍሳቸውን በአፀደ ...
04/04/2021

የላዚዮ ቁጠባና ብድር ህብረት ሥራ ማህበር መስራች አባል የሆኑት የአቶ ሙሉ ግርማይ ወላጅ እናት ከዚህ ዓለም በሞት በመለየታቸው የተሰማንን ጥልቅ ሀዘን እንገልፃለን።

ፈጣሪ ነፍሳቸውን በአፀደ ገነት ያኑርልን። ለቤተሰቦቻቸው፣ ለወዳጅ ዘመዶቻቸው መፅናናትን ይስጥልን።

27/10/2020

የተከበራችሁ የማህበራችን አባላት!

በመስከረሙ ጉባዔ ከተንሸራሸሩ ሀሳቦች መካከል ማህበራችን በዋናነት የገንዘብ አቅሙን የማሳደግ ሁኔታ ላይ ትኩረት ሊያደርግ ይገባል የሚለው አንዱ መሆኑ ይታወሳል።

1ኛ. ማህበራችን ወርሀዊ መዋጯቸው ከፍተኛ
የሆኑ አባላት ስላሉት እንጂ አባላት
ዝቅተኛውን ወርሀዊ መዋጮ ብቻ
እየከፈሉ መጓዛቸው የማህበሩን የስኬት
ጉዞ ረጅም ማድረጉ አይቀርም።

ስለሆነም የአባላትን አቅም በማገናዘብ
እና አባላትን በማወያየት 300 ብር
ቢደረግም አባላት ወርሀዊ ቁጠባቸው
ከዚህ ከፍ እንዲል ሊበረታቱ ይገባል።

(በቋሚነት በየወሩ ከፍተኛ የቁጠባ ገንዘብ
ገቢ የሚያደርጉ አባላት መመስገን ይገባቸዋል)

2ኛ.ለአባላትም ሆነ ለማህበሩ የገንዘብ መጠን
ማደግ የአክሲዮን ግዢው ላይ በከፍተኛ
ሁኔታ መረባረብ ይኖርብናል። ማህበራችን
ለአባላት የብድር አገልግሎት በመስጠት
በከፍተኛ ሁኔታ ተጠቃሚ እያደረገ የመጣ
ሲሆን ከዚህ በኋላም በተጠናከረ ሁኔታ
ለማስቀጠል የአክሲዮን ግዢዎቹ ከፍ እያሉ
መሄድ ይኖርባቸል። ጥቅምት 30
ከመድረሱ በፊት በርካቶች ግዢ እየፈፀሙ
ነው፤ ያልገዛን ካለን ግን የመጨረሻዋ ቀን
ከመድረሷ በፊት መግዛት ይኖርብናል።

ወሰናችን አድማስ ጥግ፤ አረማመዳችን በጋራ ነው!

05/10/2020

ውድ የማህበራችን አባላት!

እንደሚታወቀው ማህበራችን ጠቅላላ ጉባዔውን መስከረም 16 ቀን 2013 ዓ.ም ማድረጉ ይታወሳል።

በጉባዔውም የተለያዩ ሀሳቦች የተንሸራሸሩ ሲሆን የማህበራችን የአፈፃፀም ሁኔታ በበጎ መልኩ የተነሳ ከመሆኑም በላይ የአባላቱም ተሳትፎ ያደገበት መሆኑ ተመልክቷል።

ከዚህ በላይ የላቀ ደረጃ ላይ ለመድረስም የማህበራችንን የገንዘብ አቅም ማሳደግ በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ምክክር ተደርጓል።

በመሆኑም ከያዝነው ወር ጀምሮ አባላት ዝቅተኛውን የቁጠባ የገንዘብ መጠን 300 ብር እያስገቡ ሲሆን እስከ ጥቅምት 30 ቀን 2013 ዓ.ም በሚቆየው የአክሲዮን ሽያጭ ተጠቃሚ ለመሆንም አክሲዮን እየገዙ ይገኛሉ።

እርስዎም የቁጠባ የገንዘብ መጠንዎን በማሳደግ እና እስከ ጥቅምት 30 የሚቆየውን አክሲዮን በመግዛት ተጠቃሚ ይሁኑ፤ ለማህበራችን የገንዘብ አቅም መጎልበትም አስዋፅዖ ያድርጉ።

ላዚዮ(ጥቁር ውሃ)Lazio finance የሚል በቴሌግራም የመወያያ ቻናል የተከፈተ በመሆኑ ሀሳብዎን እንዲያጋሩም ተጋብዘዋል።

መድረሻች አድማስ ጥግ፤
አረማመዳችን በጋራ ነው!

26/09/2020

የFB መስመር ላይ ያላችሁ የማህበራችን አባላት ለበዓሉ እንኳን አደረሳችሁ እያልን ዛሬ ከጠዋቱ 3:00 ጀምሮ በማህራችን የ2012 ዓ.ም አፈፃፀም እና የ2013 ዓ.ም የጉዞ አቅጣጫ ላይ እንመክራለን።

ቦታው አዲሱ ሰፈር እነአክሊሉ እሸቱ (ዳማ) ጊቢ ነው። ሁለችሁም እንድትገኙ ተጋብዛችኋል።

የተከበራችሁ የማህራችን አባላት!ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የአንተ፣ የአንቺ፣ የእኔ፣ የቤተሰቦቻችን እና የትውልዳችን የጋራ ውጤት ነው። ውጤቱን በአይናችን እስክናየው ድረስ እንቅልፍ አንተ...
25/06/2020

የተከበራችሁ የማህራችን አባላት!

ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የአንተ፣ የአንቺ፣ የእኔ፣ የቤተሰቦቻችን እና የትውልዳችን የጋራ ውጤት ነው። ውጤቱን በአይናችን እስክናየው ድረስ እንቅልፍ አንተኛም፤ የኢትዮጵያችን የተስፋ ችቦ ነውና! እባክዎ ባሉበት እና በቻሉት መንገድ ድምፅዎን ያሰሙ!

ይህ ስለ ፖለቲካ አይደለም፤ ስለ ሐይማኖት አይደለም፤ ስለ ብሔርም አይደለም ... ለመጪው ትውልድ ስለምናስተላልፈው ሀገራዊ ቅርስ እንጂ!

ዓባይ የእኛ የሁላችን ነው!

03/06/2020

የተከበራችሁ የማህበራችን አባላት፤ ለአባላት የበለጠ ምቹ ሁኔታን ለመፍጠር ይረዳ ዘንድ ማህበራችን ሌላኛውን የባንክ ደብተር በዳሽን ባንክ አማካኝነት አግኝቷል።

ከንግድ ባንክ በተጨማሪ አዲስ የተከፈተውን የዳሽን ባንክ የቁጠባ ሂሳብ በአማራጭነት መጠቀም እንደሚቻል በደስታ እንገልፃለን፡፡

የቁጠባ ሂሳብ ቁጥር:- 5088182683011

ከዚህ በተጨማሪ ማህበራችን በ2013 ዓ.ም አዲስ የአክሲዮን ሽያጭ ስለሚኖረው የተሻለ ትርፍ ተከፋይ እንዲሆኑ ከወዲሁ መግዛት የሚችሉ መሆኑን እንገልፃለን፡፡

አረማመዳን በጋራ ወሰናችን አድማስ ጥግ ነው!

ርቀታችንን እንጠብቅ፤ እጃችንን በሚገባ እንታጠብ፤ ማስክ እንጠቀም!

09/04/2020

ውድ የፔጃችን ተከታታዮች!

ለረጅም ጊዜያት መረጃዎችን ወደ እናንተ ሳናደርስ በመቆየታችን ይቅርታ እየጠየቅን ከዛሬ ጀምሮ ማህበራችን ያለበትን ደረጃ የሚመለከቱ መረጃዎችን የምናስተላልፍ መሆኑን እንገልፃለን፡፡

የፌስ ቡክ ፔጃችንን ለሚያውቋቸው ሰዎች ሼር በማድረግ እና ላይክ እንዲያደርጉ በመጋበዝ የበኩላችሁን እንድትወጡ አደራ እንላለን፡፡

አስር በሆኑ አባላት የተመሰረተው የላዚዮ ቁጠባና ብድር አክሲዮን ማህበር እነሆ አሁን ላይ ወደ 43 የሚጠጉ አባሎችን በመያዝ ወደ 3 መቶ ሺህ ብር የካፒታል ገንዘብ ያለው ማህበር ለመሆን በቅቷል፡፡


የመካከለኛ ጊዜ የማህበሩ አላማ የአባላትን የቁጠባ ባህል ማሳደግ እና የማህበሩ አባላትን የብድር ተጠቃሚ ማድረግ ሲሆን የአባላቱን ቁጥር እያሳደገ መሄድም የማህበሩ አንዱ እና እጅግ አስፈላጊው ስራ ነው፡፡

ማህበራችን የተመሰረተበትን አላማ እያሳካ በተለይም ለበርካታ የብድር ተጠቃሚዎች ብድር እየሰጠ ሲሆን በቀጣይም አባላት የቁጠባ መጠናቸውን እያሳደጉ እንዲሄዱ እና አዳዲስ አባላትን ወደ ማህበራችን እንዲያመጡ መልዕክታችንን እናስተላልፋለን፡፡

ውድ የማህበራችን አባላት!

ዓለም የገጠማት የኮሮና ቫይረስ ስርጭቱን እያሰፋ እንደሆነ በመገንዘብ ራሳችሁን፣ ቤተሰባችሁን እና የአካባቢያችሁን ነዋሪዎች ከበሽታው እንድትታደጉ አደራ እንላለን፡፡

አካላዊ ርቀታችሁን ጠብቁ፣ እጃችሁን በሳሙና ታጠቡ፣ ከሰዎች ጋር ንክኪ እንዳይኖራችሁ ተጠንቀቁ፣ ብትችሉ ከቤት ላለመውጣት ሞክሩ የሚለው የማህበራችን መልዕክት ነው፡፡

ፈጣሪ ሀገራችንን እና ህዝባችንን ይጠብቅ!

29/09/2019

የተከበራችሁ የማህበራችን አባላት ዛሬ እሁድ 11 ሰዓት ላይ ማህበራችን ጉባዔውን እንደሚካሄድ ይታወቃል።

ቦታውም ማሪያም ቤተክርስቲያን ፊት ለፊት ወደ አዲሱ ሰፈር በሚወስደው መንገድ ላይ በሚገኘው ደሜ ግሮሰሪ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡

Address

የገንዘብ ተቋም
Awassa
2010

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when ላዚዮ ቁጠባና ብድር ህብረት ሥራ ማህበር posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share