20/01/2026
ሲቢኢ ኮኔክት ዲጂታል ዋሌት (CBE Connect Digital Wallet) የተሰኘ የፋይናንስ አገልግሎት መስጫ ከውጭ ሀገር ገንዘብ ለመላክ የሚያስችል አዲስ ቀላል መተግበሪያ ስራ ጀምሯል።
ሲቢኢ ኮኔክት ዲጂታል ዋሌት ለደንበኞች ምን አዲስ ነገር ይዞ መጣ ?
*******************
• ሲቢኢ ኮኔክት ዲጂታል ዋሌት በውጭ ሀገር ገንዘብን በቀላሉ ለማስተላለፍ የሚያስችል በኢትዮጵያ ውስጥ ለመጀመሪያ ጊዜ የበለጸገ ሀገር በቀል የቴክኖሎጂ መሰረተ ልማት በመሆኑ፤ የሀገራችንን የውጭ ምንዛሬ ማግኛ ዘዴን ያስፋፋል፡፡
• ሲቢኢ ኮኔክት ዲጂታል ዋሌት ማንኛውም ሀገር ከሚገኝ ግለሰብ߹ ዋሌት ኦፕሬተር ߹ሕጋዊ ገንዘብ አስተላላፊ ተቋም ጋር በቀጥታ ጥምረት በመፍጠር፤ ከውጭ ሀገር በቀላሉ ገንዘብ በነፃ መላክ የሚያስችል መተግበሪያ ነው፡፡
• በውጭ ሀገር ሕጋዊ ወኪል በመሆን ገንዘብ የሚያስተላልፉ ተቋማት መተግበሪያውን በመጠቀም፤ በቀላሉ በፈለጉበት ወቅት ፤ የፈለጉትን የገንዘብ መጠን ለብዙ ሰዎች ወደ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሒሳብ እንዲሁም ወደ ሌሎች የኢትዮጵያ ባንኮች ሒሳብ ገንዘብ ማስተላለፍ ያስችላቸዋል፡፡
• ለኢትዮጵያ ዳያስፖራ አባላት ድንበር ተሻጋሪ የሆነ ፤በቅጽበት የገንዘብ የሚላክበት መተግበሪያ ከመሆኑ በተጨማሪ፤የውጭ ምንዛሪ እንዲሁም ፤የቤት እና መኪና ብድር አገልግሎቶችን እንዲያገኙ ያስችላል፡፡
• ሲቢኢ ኮኔክት ዲጂታል ዋሌት በደንበኞች ዘንድ የውጪ ሐዋላ መላክ በቀላሉ እና ያለምንም ክፍያ ለማከናወን የሚያስችል፤ የውጪ ሀገር የመገበያያ ገንዘቦችን ለመላላክ እና ወደ ብር ለመመንዘር እንዲሁም በብር ሒሳብ በኢትዮጵያ ውስጥ በቀጥታ ለመጠቀም ያስችላል፡፡
• ሲቢኢ ኮኔክት ዲጂታል ዋሌት ዓለም አቀፍ የክፍያ ካርዶችን (ቪዛ ካርድ እና ማስተርካርድ) በመጠቀም በነፃ ገንዘብ በቀላሉ ወደ ሀገር ቤት መላክ እንዲሁም ማስቀመጥ ያስችላል፡፡
• ሲቢኢ ኮኔክት ዲጂታል ዋሌት ሌሎች ተጨማሪ አገልግሎቶችን በመተግበሪያው አማካኝነት ማግኘት የሚያስችል ሲሆን፤ ለአጠቃቀም ቀላል፤ ደህንነቱም የተጠበቀ፤ ለደንበኞች አስተማማኝ አገልግሎት የሚሰጥ አዲስ የዲጂታል ዋሌት መተግበሪ ነው፡፡
መተግበሪያውን ስልክዎ ላይ ለመጫን
አንድሮይድ https://play.google.com/store/apps/details?id=com.eaglelionsystems.connectethiopia&hl=en
አይፎን https://apps.apple.com/us/app/cbe-connect/id6753888802