A.A CITY GOVT BLG CON BUREAU

A.A CITY GOVT BLG CON BUREAU Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from A.A CITY GOVT BLG CON BUREAU, Addis Ababa.

nice
10/08/2020

nice

☞ የአቶ ሙስጠፌ ቀጭን ትእዛዝ...!
"ኢትዮጵያ የክርስትያኖች ብቻ መኖርያ በነበረችበት፥ ክርስትና ከቤተመንግስት እስከ መንደሮች በጥብቅ ተፅእኖ ስር ሀገሪቷን
በሚያስተዳድርበት፣ ስልጣኔ ባልነበረበት በድሮ ጊዜ # እስልምናን በሠላምና በክብር እንግድነት የተቀበሉት የኢትዮጵያ ክርስትያኖች ናቸው። ዛሬ የእኛ ትውልድ "ወርቅ ላበደረ ጠጠር" እንደሚባለው አባቶቻችንን በክብር የተቀበለውን ህዝብ በሰይፍ መግደል፣ የእምነት ቤቱን ማቃጠል በመንግስታችን በኩል በህግ
የሚያስጠይቅ ሲሆን በአላህ ፊት ደግሞ እጅግ አፀያፊ ተግባር ነው።
"እኔ ከአላህ የተላከውን የቅዱስ ቁርአን አስተምህሮ በመስጂድ ውስጥ የተማርሁት እስላም ማለት ሰላም መሆኑን ነው። አላህ
ወንጀልን ይፀየፋል፣ በቀልና ጥፋት ደግሞ ወንጀል ነው...።
ቀድሞ በእኛ ክልል ብዙ አብያተ ክርስትያናት በአክራሪ ኃይሎች ሲቃጠሉ በመላው ኢትዮጵያ የሚገኙ ክርስትያናት በመስጅዶችና በእስልምና ተከታዮች ላይ ምን አደረጉ? በአሁኑ ሰአት በአማራ
ክልል የተቃጠሉ መስጂዶችን ያቃጠሉ ክርስትያኖች ሳይሆኑ # የአክራሪ_እስልምና ክንፎች ናቸው። አላማውም በሀገራችን
የተፈጠረውን ሰላም ለማደፍረስ ና የኃይማኖት ፀብ በመፍጠር ሀገርን በማተራመስ የክፉዎችን ተልእኮ ለመፈፀም ሆን ተብሎ የታቀደ ነው።
ከዚህ በፊት በአማራ ክልል እኛ የምናውቀው በክልሉ ቤተክርስትያን ሲገነባ እስላሞች በገንዘብና በጉልበት ሲያግዙ፣ መስጂዶች ሲሰሩ
ደግሞ ክርስትያኖች በገንዘብና በጉልበት ሲያግዙ ነው። ክረስትያኖች ይህን ተግባር የሚፈፅሙበት ምንም አይነት ምክንያት የለም።
ስለሆነም ከዛሬ ጀምሮ በክልላችን ውስጥ በክርስትያኖችና በቤተ እምነታቸው ላይ የሚፈፀም ማንኛውም ጥቃት ቢኖር የመጀመርያ
ተጠያቂ የሚሆነው ይህ የክልላችን ከፍተኛ አመራር ነው።
ምክንያቱም ክልላችንን የሚያስተዳድረው መንግስት ሁሉም ነገር መዳፉ ውስጥ እንደሆነ ሁላችንም እናውቃለን።
ስለሆነም በክልላችን ውስጥ ማንኛውም አይነት ጸረ ሰላም እንቅስቃሴ ከተፈጠረ ተመጣጣኝ ና ቆራጥ እርምጃ በመውሰድ ወንጀለኞችን ማስተማር ተቀዳሚ ተግባራችን ይሆናል።
………
[[ የሶማሌ ክልል ርእሰ መስተዳድር አቶ ሙስጠፌ በዛሬው ዕለት ካቢኔያቸውን አስቸኳይ ስብሰባ ጠርተው በክልሉ የተፈጠረውን ሰላምና መረጋጋት ለማደፍረስ እየሰሩ ስላሉ አክራሪ ውኃብዮች በተመለከተ ካስተላለፉት ከረር ያለ መልእክት]

#ዘ ኢትዮጵያ
via-Ethio -press

Address

Addis Ababa

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when A.A CITY GOVT BLG CON BUREAU posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share