Food, Beverage and Pharmaceutical Industry Development Institute

Food, Beverage and Pharmaceutical Industry Development Institute Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Food, Beverage and Pharmaceutical Industry Development Institute, Addis Ababa.

15/12/2024
ድሪንክ ቴክ የተሰኘው ዓለም አቀፍ የንግድ ዓውደ ርዕይ ከሴፕቴምበር 11-15-2017 እንደሚካሄድ ተገለጸ፡፡ ዓውደ ርዕዩ በጀርመን ሙኒክ (ሜስ) ላይ የሚካሄድ ሲሆን የመጠጥና በፈሳሽ መልክ ...
06/02/2017

ድሪንክ ቴክ የተሰኘው ዓለም አቀፍ የንግድ ዓውደ ርዕይ ከሴፕቴምበር 11-15-2017 እንደሚካሄድ ተገለጸ፡፡ ዓውደ ርዕዩ በጀርመን ሙኒክ (ሜስ) ላይ የሚካሄድ ሲሆን የመጠጥና በፈሳሽ መልክ የሚወሰዱ የምግብ ዓይነቶች እንደሚቀርቡበት ተገልጸEል፡፡

የምግብ ፣መጠጥና ፋርማሲዩቲካል ኢንዱስትሪ ኢንስቲትዩትና የኢትዮጵያ ስጋና ወተት ኢንዱስትሪ ልማት ኢንድስቲትዩት ከኢትዮጵያ አየር መንግድ ጋር በመተባበር በተኪ ምርቶች ዙሪያ ከባለሀብቱ ጋር ...
02/02/2017

የምግብ ፣መጠጥና ፋርማሲዩቲካል ኢንዱስትሪ ኢንስቲትዩትና የኢትዮጵያ ስጋና ወተት ኢንዱስትሪ ልማት ኢንድስቲትዩት ከኢትዮጵያ አየር መንግድ ጋር በመተባበር በተኪ ምርቶች ዙሪያ ከባለሀብቱ ጋር ውይይት አደረጉ፡፡

21/01/2017

የዓለም የኤች.አይ.ቪ ኤድስ እና የጸረ-ጾታ ጥቃት ቀን ተከበረ
የምግብ፣ የመጠጥና የፋርማሲዩቲካል ኢንዱስትሪ ልማት ኢንስቲትዩት ሠራተኞች በዓለም አቀፍ ደረጃ 29ኛው የዓለም የኤች.አይ.ቪ/ኤድስ ቀን “አሁንም ትኩረት ኤች.አይ.ቪ/ኤድስን ለመከላከል” እና የጸረ-ጾታ ጥቃት ቀን በዓለም ለ25ኛ ጊዜ “በሴቶች ላይ የሚፈጸሙ የኃይል ጥቃቶችን በመከላከልና በማስቆም የዕድገትና የህዳሴ ለውጥ ዘላቂነት እናረጋግጥ!!” በሚሉ መሪ ሃሳቦች ህዳር 27 ቀን 2009 ዓ.ም በደብረ ዳሞ ሆቴል በድምቀት አከበሩ፡፡
በዕለቱ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የኢንስቲትዩቱ ም/ዋና ዳይሬክተር ረዳት ፕሮፌሰር መሣይ ወ/ማርያም በሽታውን በመከላከል እና በመቆጣጠር በተገኙት ስኬቶች መዘናጋት የለብንም ብለዋል፡፡ በፈቃደኝነት ላይ የተመሠረተ ምርመራ በማድረግም ራሳችንን አውቀን የቫይረሱን ስርጭት መግታት እንችላለን ብለዋል፡፡ ከዓለም ኤች.አይ.ቪ/ኤድስ ጋር በጋራ የተከበረውን የዓለም የጸረ ጾታ ጥቃት ቀንን አስመልክተውም በሴቶች ላይ እየተፈጸመ ያለውን የኃይል ጥቃት ለመከላከል ሁሉም ኃላፊነቱን ሊወጣ እንደሚገባም ጠቁመዋል፡፡

በዕለቱም የቦሌ ክ/ከተማ የኤች.አይ.ቪ መከላከልና መቆጣጠር ሴክሪተሪያል ባለሙያ አቶ ገ/ህይወት በኤች.አይ.ቪ/ኤድስ መተላለፊያ መንገዶች፣ ያለዕድሜ ጋብቻ እና ተያያዥ ጉዳዮችን በስፋት ዳሰዋል፡፡ የጸረ ፆታ ጥቃት ቀንን አስመልክቶ ከሴቶችና ህጻናት ጉዳይ ሚኒስቴር በተጋባዥነት የመጡት ወ/ሮ ህሊና ላቀው በበኩላቸው የጸረ ጾታ ጥቃት ቀንን አስመልክተው ወቅታዊና ሰፋ ያለ ማብራሪያ ለውይይቱ ተሳታፊዎች አቅርበዋል፡፡ በተለይም የሴቶችን ጥቃት ለመከላከል መንግስት የተለያዩ እርምጃዎችን እየወሰደ ይገኛል ብለዋል፡፡ በተደራጀና ህዝባዊ ንቅናቄ ሊፈጥር በሚችል መልኩም የሴቶች ጥቃትን ለመከላከል ሁሉም በበኩሉ ጥረት ማድረግ እንዳለበትም ባለሙያዋ ጠቁመዋል፡፡

በውይይቱ ላይ የተሳተፉት የኢንስቲትዩቱ ሠራተኞች ልዩ ልዩ ጥያቄዎችንና ሀሳቦችን አንስተው ተወያይተዋል፡፡ ካነሷቸው ሀሳቦች ውስጥ የቫይረሱን ስርጭት ለመግታት እና በሴቶች ላይ እየተፈጸመ ያለውን የሀይል ጥቃት ለመቀነስ ጠንከር ያለ የግንዛቤ ማስጨበጫ ሥራ በመስራት የአመለካከት ለውጥ እንዲመጣ ማድረግ ይገባል ብለዋል፡፡

በተጨማሪም በሴቶች ላይ የሚፈጸመውን ጥቃት በተፈለገው መጠን መግታት ያልተቻለው የሚሰጠው ቅጣት ተመጣጣኝ ስላልሆነ ነው የሚል ሀሳብም አንስተዋል፡፡ ከተጋባዥ ባለሙያዎችም ምላሽ ተሰጥቶባቸዋል፡፡
የኤች.አይ.ቪ/ኤድስ ወረርሽኝ በዓለማችን መከሰቱ የታወቀው እ.ኤ.አ. 1982 ጀምሮ ሲሆን ከ39 ሚሊዮን የሚበልጡ ሰዎችን ለህልፈተ ህይወት እንደዳረገ ይታወቃል፡፡

21/01/2017

11 ኛው የብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች ቀን በድምቀት ተከበረ
የምግብ፣ የመጠጥና የፋርማሲዩቲካል ኢንዱስትሪ ልማት ኢንስቲትዩት እና የሥጋና ወተት ኢንዱስትሪ ልማት ኢንስቲትዩት ሠራተኞች በቢሾፍቱ ከተማ አዱላላ ሆቴል ህዳር 13/2009 ዓ.ም “ህገ መንግስታችን ለዴሞክራሲያዊ አንድነታችንና ለህዳሴያችን!” በሚል መሪ ቃል የብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች ቀንን በድምቀት አከበሩ፡፡

በበዓሉ ላይ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የስጋና፣ ወተት ኢንዱስትሪ ልማት ኢንስቲትዩት ዋ/ዳይሬክተር አቶ ኃይለ ሥላሴ ወረስ እንዳሉት የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች በከፈሉት እልህ አስጨራሽ ትግል በሀገራችን ዘላቂ ሰላም፣ ፈጣንና ቀጣይነት ያለው ልማት ማረጋገጥ ተችሏል ብለዋል፡፡
በዕለቱ የብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች ቀንን አስመልክቶ የውይይት ጽሁፍ ያቀረቡት የስጋና ወተት ኢንዱስትሪ ልማት ኢንስቲትዩት የኮርፖሬት ኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ደበሌ ለማ በበኩላቸው የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች ራሳቸውን በራሳቸው የማስተዳደር፤ ቋንቋቸውንና ባህላቸውን የማሳደግ፤ የመልማት እንዲሁም የራሳቸውን ዕድል በራስ የመወሰን መብት ዋስትና ያገኘው በህገ-መንግስቱ እንደሆነ አስረድተዋል፡፡ የተገኙትን ፍሬዎች ጠብቆ ለማቆየትም የጀመርነውን የህዳሴ ጉዞ አጠናክረን መቀጠል ይኖርብናል ብለዋል፡፡ በዕለቱ በዓሉን አስመልክቶ በህገ-መንግስት፣ ብዝሃነት፣ ልማት፣ ዲሞክራሲ የሚሉት በስፋት ተዳሰዋል፡፡

በአዲሲቷ ኢትዮጵያ አንድ የኢኮኖሚና የፖለቲካ ማህበረሰብ ለመፍጠር የህዳሴ መሠረት የሆነውንና የሀገራችን ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች የሉዓላዊነት መገለጫ የሆነውን ሕገ መንግስታችንን እንደ ዓይናችን ብሌን በመጠበቅ የዴሞክራሲያዊ ስርዓት ግንባታ ሂደታችንንና መልካም አስተዳደርን የማስፈን ትግላችንን አጠናክረን መቀጠል አለብን ሲሉም አክለዋል፡፡

ከበዓሉ ታዳሚዎች የተለያዩ ሀሳቦችና ጥያቄዎች ተነስተዋል፡፡ ለተነሱት ሀሳቦችና ጥያቄዎች ከአመራሮች ማብራሪያ ተሰጥቶባቸዋል፡፡
በእለቱም የበዓሉን ታዳሚዎች ዘና ያደረገ የጥያቄና መልስ ውድድርም ተካሂዷል፡፡ በውድድሩም አሸናፊ ለሆኑት ከምግብ፣ ከመጠጥና ከፋርማሲዩቲካል ኢንዱስትሪ ልማት ኢንስቲትዩት ም/ዋና እና የተቋሙ ዋና አስተባባሪ ከአቶ ሰለሞን ታደለ እጅ ሽልማት ተቀብለዋል፡፡

ህዳር 29 የኢትዮጵያ ብሄሮች፣ ብሄረሰቦችና ህዝቦች ቀን ተብሎ በሀገር አቀፍ ደረጃ በድምቀት እንዲከበር የተወሰነው የፌዴሬሽን ምክር ቤት ሚያዚያ 21 ቀን 1998 ዓ.ም ባካሄደው ሶስተኛው የፓርላማ ዘመን አንደኛ አመት ሁለተኛ መደበኛ ስብሰባ ላይ ነበር።

21/01/2017

በፋርማሲዩቲካልስ ምርቶች አያያዝ ዙሪያ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጠ
የምግብ፣ የመጠጥና የፋርማሲዩቲካል ኢንዱስትሪ ልማት ኢንስቲትዩት፣ ሳይኖ ኢትዮጵ አሶሲየት(አፍሪካ) ኃ/የተ/የግ/ኩባንያ እና ካዲላ ፋርማሲዩቲካልስ(ኢትዮጵያ) ኃ.የተ.የግ.ኩባንያ በጋራ ያዘጋጁት የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ ለኢትዮጵያ አየር መንገድ የካርጐ ባለሙያዎች ታህሳሥ 6/2ዐዐ9 ዓ.ም በሳይኖ ኢትዮጵ አሶሲየት(አፍሪካ) ኃ/የተ/የግ/ኩባንያ መድኃኒት ፋብሪካ ቅጥር ግቢ ውስጥ የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ ተካሄደ፡፡

የግንዛቤ ማስጨበጫ የውይይት መድረኩን የከፈቱት የምርት ክፍል ኃላፊ አቶ ሸጋው አደራው ናቸው፡፡ በመክፈቻ ንግግራቸውም በመድኃኒት አመራረት፣ አያያዝ፣ አቀማመጥና መልካም አመራረት ምን ይመስላል በሚል ርዕስ ሰፊ ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡ የግንዛቤ ማስጨበጫው ዋና ዓላማም መድኃኒትና የመድኃኒት መሥሪያ ጥሬ እቃዎች፣ የህክምና መገልገያ መሣሪያዎች ከቦታ ቦታ በሚዘዋወሩበት ጊዜ የሚደርስባቸውን ጉዳት ለማስቀረት የታለመ ነው ብለዋል፡፡
በዚህ ረገድ የምግብ፣ የመጠጥና የፋርማሲዩቲካል ኢንዱስትሪ ልማት ኢንስቲትዩት የፋርማሲዩቲካል ዘርፍን ለመደገፍ ባለሙያዎችን መድቦ እየተንቀሳቀሰ ይገኛል፡፡ ይህም የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ ሲፈጠር ትልቅ ትኩረት ተሰጥቶት ነው፡፡ ይኽም በመሆኑ በኢትዮጵያ አየር መንገድ ያሉ ባለሙያዎችም በመድኃኒት አያያዝ፣ አቀማመጥና አጓጓዝ፣ ዙሪያ ከፍተኛ ትኩረት መስጠት እንዳለባቸው አሳስበዋል፡፡

አቶ ሸጋው አያይዘውም መድኃኒት ከሰው ህይወት ጋር በጥብቅ የሚያያዝ ነው፡፡ በመሆኑም የመድኃኒቶች አያያዝ ላይ ከፍተኛ ትኩረት ስለሚሻ ጥንቃቄ ሊደረግ ይገባል ብለዋል፡፡ መድኃኒቶች የአያያዝ፣ የአቀማመጥና የአጓጓዝ ችግር ካለባቸው በቀላሉ ለብልሽት ይዳረጋሉ ይኸውም በህብረተሰቡ ጤና ላይ ከፍተኛ ጉዳት ያደርሳሉ፡፡

የካዲላ ፋርማሲዩቲካልስ(ኢትዮጵያ) ኃ.የተ.የግ.ኩባንያ የምርት ክፍል ኃላፊ አቶ አባይነህ ጥላዬ በበኩላቸው መድኃኒቶች በባህሪያቸው ከቦታ ቦታ በሚጓጓዙበት ጊዜ ከአያያዝ ጉድለት የተነሳ በቀላሉ ይበላሻሉ፡፡ በዚህ ረገድ በኢትዮጵያ አየር መንገድ በኩል የፋርማሲዩቲካልስ ውጤቶችን ለይቶ በጥንቃቄ ከመያዝ አኳያ ከፍተኛ ክፍተት ስለሚታይ አየር መንገዱ ለችግሩ አፋጣኝ እልባት ሊሰጥ ይገባል ብለዋል፡፡ ከዚህ ችግር ጋር በተያያዘም በዓለም ላይ በሰው ልጆች ህይወት ላይ የተከሰቱ ከፍተኛ የአካል ጉዳቶችንና ሞትን እያነሱ ስለችግሩ አሳሳቢነት በምሳሌ አስረድተዋል፡፡


በሌላ በኩል የኢትዮጵያ አየር መንገድ የሽያጭ ክፍል ባለሙያ አቶ ዳዊት ተስፋዬ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ካርጎ ክፍል የተለያዩ እቃዎችን በአንድ ጊዜ በብዛት ስለሚያስተናግድ አንዳንድ ችግርች ሊፈጠሩ ይችላሉ፡፡ በቀጣይ ግን ዘመናዊ በሆነ መልኩ በርካታ ቁሳቁሶችን በአንድ ጊዜ ማስተናገድ የሚችል መጋዘን ገንብቶ ወደ ስራ እንደሚገባ ገልጸዋል፡፡ ግንባታውም በዚህ ስድስት ወር ውስጥ ተጠናቆ ወደ ስራ እንደሚገባ አስረድተዋል፡፡ ግንባታውም ሲጠናቀቅ አሁን በመድኃኒትና በሌሎች ቁሳቁሶች አያያዝ ላይ የሚስተዋለውን ችግር ለመቅረፍ ያስችላል ብለዋል፡፡

የምግብ፣ የመጠጥና የፋርማሲዩቲካል ኢንዱስትሪ ልማት ኢንስቲትዩት የኢንዱስትሪያል ፋርማሲ ተመራማሪ አቶ ፍፁም አድነው በበኩላቸው የፋርማሲዩቲካልስ ዘርፍ የመንግስት ቀጥተኛ ድጋፍ ከሚያስፈልጋቸው ውስጥ አንዱ መሆኑን ጠቅሰው ኢንስቲትዩቱም በዘርፉ የሚታየውን ችግር ለመፍታት ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በቅርበት እየሰራ ይገኛል ብለዋል፡፡ በቀጣይም የፋርማሲዩቲካል ፋብሪካዎች የኢትዮጵያ አየር መንገድ የካርጐ ክፍል የፋርማሲዩቲካልስ ውጤቶች አያያዝ፣ አቀማመጥና አጓጓዝ ላይ ጉብኝት ለማድረግ እቅድ እንዳለው ገልጸዋል፡፡ የመድኃኒት ፋብሪካዎችና የኢትዮጵያ አየር መንገድ የጋራ እቅድ አቅደው ቢንቀሳቀሱ ጥሩ ውጤት እንደሚያመጡ አሳስበዋል፡፡

ከውይይቱ በኋላ የኢንስቲትዩቱ ሠራተኞችና የኢትዮጵያ አየር መንገድ የካርጎ ባለሙያዎች ፋብሪካዎቹን ጎብኝተዋል፡፡

የመጀመሪያው ዙር የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ መስከረም 19/2009 ዓ.ም መካሄዱ ይታወሳል፡፡

21/01/2017

የሁለቱ ተቋማት ሠራተኞች ጥልቅ ተሃድሶ አካሄዱ
የምግብ፣ የመጠጥ፣ የፋርማሲዩቲካል እና የሥጋና ወተት ኢንዱስትሪ ልማት ኢንስቲትዩት ሠራተኞች በቢሾፍቱ ከተማ በብሔራዊ የእንስሳት ህክምና ኢንስቲትዩትና በፒራሚድ ሪዞርት ከጥር 1 እስከ ጥር 8 ድረስ “በፐብሊክ ሰርቪሱ የነቃና የተደራጀ ተሳትፎ የህዳሴ ግቦቻችን ዕውን ይሆናሉ!” በሚል መሪ ቃል ውይይትና ጥልቅ ተሀድሶ አካሄዱ፡፡

በውይይት መድረኩ በመገኘት የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዲኤታ ክቡር ዶ/ር መብርሃቱ መለስ የመንግስት ሠራተኛው ጥልቅ ተሃድሶ በማድረግ መታደስ እንዳለበት ገልጸዋል፡፡ አያይዘውም በጥልቀት የመታደስ ንቅናቄውን በፐብሊክ ሰርቪሱ የምንተገብርበት ማስፈጸሚያ ዕቅድን አስመልክቶ ብቁና ውጤታማ ፐብሊክ ሰርቪስ ለማፍራትና የሀገራችንን ህዳሴ ለማፋጠን ሁሉም መረባረብ እንዳለበትም አሳስበዋል፡፡
በተጨማሪም የኢንደስትሪው ዘርፍ የሚጠበቅበትን ያህል ስላላደገ ሠራተኛው በጥልቅ በመታደስ ያለውን ችግር በመለየት በጥልቅ ተሃድሶው ራሱን ፈትሾ ዘርፉን ለማሳደግ በየተሰማራበት መስክ በቅንነት ለማገልገል ቁርጠኛ መሆን ያስፈልጋል ብለዋል፡፡

በተከታታይ ለ 5 ቀናት በተደረጉት የጥልቅ ተሃድሶ የውይይት መድረኮች በመንግስት ምንነት፣ አስፈላጊነትና ባህሪ ዙሪያ የሚነሱ ጥያቄዎችና የፐብሊክ ሰርቪሱ ሁኔታ፤ የመንግስትን ሚና የሚጠይቁ ሁኔታዎች፤ ሊበራላዊ ወይስ ልማታዊ መንግስት ለኢትዮጵያ፤ ልማታዊ ዴሞክራሲያዊ መንግስት በኢትዮጵያ፤ የሪፎርም መሣሪያዎች አጠቃቀምና አተገባበር ላይ የሚታይ ዳተኝነት፤ የለውጥ ሠራዊት ግንባታ፤ የአሠራር የአደረጃጀት ሥርዓቱ የአፈጻጸም ጉድለት እና ሌሎች የውይይት ርዕሶችን በማንሳት ሠራተኛው በሰፊው ተወያይቶባቸዋል፡፡

በውይይቱ ላይ የተሳተፉት ሠራተኞች የተለያዩ ሀሳቦችንና ጥያቄዎችን አንስተዋል፡፡ ከእነዚህም ውስጥ የሀገሪቱን ህዳሴ እውን ለማድረግና ያጋጠሙ የመልካም አስተዳደር ችግሮችን ከመሠረቱ ለመፍታት ከበላይ አመራር አካላት ጀምሮ ጥልቅ ተሃድሶ መደረጉ ወሳኝ መሆኑን፤ በሀገሪቱ እየተመዘገበ ያለው ስኬትም ሆነ ውድቀት ሠራተኛውን በቀጥታ የሚመለከት በመሆኑ የጥልቅ ተሃድሶው ውይይት ወደ ሠራተኛው እንዲወርድ መደረጉ ሰራተኛው ራሱን እንዲፈትሽና ለለውጥ እንዲነሳ ያግዛል ብለዋል፤
ውይይቱ በሠራተኛው ላይ የሚስተዋለውን የአሰራር ክፍተት በግልጽ በማውጣት ለህብረተሰቡ ጥያቄ ተገቢውን ምላሽ ለመስጠትና የሠራተኛውን የሥራ ተነሳሽነት ለማሳደግ ጠቃሚ መሆኑንም አንስተዋል፤ ለተመሳሳይ የስራ መደብ በተለያዩ መ/ቤቶች የተለያየ ክፍያ መሆኑ ሠራተኛው ባለበት ተረጋግቶ መስራት አልቻለም ስለሆነም መንግስት እስካሁን ይህንን ያላስተካከለበት ምክንያቱ ቢገለጽ፤ ስራችንን ከመስራት ይልቅ ሪፖርት በመጻፍና በማቀናበር ነው የምንውለው፤ ከአመራሩ እስከ ፈጻሚው ኪራይ ሰብሳቢነት በመኖሩ ይህንን ሲቪል ሰርቫንቱ እንዴት ሊታገለው ይችላል? አመራሩ በአንድ ቦታ ጥፋት ሲገኝበት የማያዳግም እርምጃ እንደመውሰድ ወደ ሌላ ቦታ ተዛውሮ እንዲሰራ ይደረጋል ይህ እንዴት ያታያል? ሰነዱ ላይ በ25 ዓመታት የመጡትን ለውጦችና ያጋጠሙ ችግሮችን ለውይይት መቅረብ አልነበረበትም ወይ?
በውይይቱ መጨረሻ ሠራተኞች በመልካም አስተዳደርና በአገልግሎት አሰጣጥ ላይ የለዩዋቸውን ችግሮች የጋራ በማድረግ የችግሩን ባለቤት የመለየትና ከአመራሩ እስከ ፈጻሚው በሂስ ግለሂስ መድረክ እንዲያልፍ ተደርጓል፡፡
የሁለቱ ተቋማት የበላይ አመራሮች በግምገማው ወቅት የግምገማውን ሪፖርት ለተሰብሳቢው አቅርበዋል፡፡ ከበላይ አመራሮች አስተያየትም ተሰጥቶበል፡፡
በመጨረሻም ባለ አስራ አራት ነጥብ የአቋም መግለጫ በማውጣት የውይይቱ ፍጻሜ ሆኗል፡፡

አምራች ኢንዱስትሪዎች ከኢትዮጵያ አየር መንገድ የስራ ኃላፊዎች ጋር ውይይት አደረጉ፡፡የፋርማሱዩቲካል አምራች ኢንዱስትሪዎች የጭነት  አገልግሎት አሰጣጥ ፈጣን፣ ቀልጣፋና ዓለም አቀፍ ደረጃውን...
02/09/2016

አምራች ኢንዱስትሪዎች ከኢትዮጵያ አየር መንገድ የስራ ኃላፊዎች ጋር ውይይት አደረጉ፡፡
የፋርማሱዩቲካል አምራች ኢንዱስትሪዎች የጭነት አገልግሎት አሰጣጥ ፈጣን፣ ቀልጣፋና ዓለም አቀፍ ደረጃውን የጠበቀ ለማድረግ በዘርፉ የተሰማሩ ማኑፋክቸረር ከኢትዮጵያ አየር መንገድ የስራ ኃላፊዎች ጋር ነሐሴ 25 ቀን 2008 ዓ.ም ውይይት አደረጉ፡፡
ውይይቱን የመሩት በኢትዮጵያ አየር መንገድ የዓለም ዓቀፍ የካርጎ ሽያጭና አገልግሎት ዳይሬክተር አቶ ብርሐኑ ካሳ እንደገለፁት አየር መንገዱ ዓለም አቀፍ ደረጃወን የጠበቀና ዘመናዊ የጭነት አገልግሎት ለመስጠት ሰፊ ስራዎችን በመስራት የአገልግሎት አሰጣጡም ከጊዜ ወደጊዜ እየተሸሻለ ነው፡፡ ዳይሬክተሩ አያይዘውም አንዳንድ ጊዜ በሰው ጉልበት የሚሰሩ የጭነት አገልግሎቶችንና በመጋዝን አካባቢ የሚስተዋሉ መጨናነቅን ሙሉ ለሙሉ የሚፈታ ማስፋፊያ እየተደረገ ነው፡፡ በተለይም በኤክስፖርት ላይ የተሰማሩ አምራች ኢንዱስትሪዎች ቅድሚያ የጭነት አገልግሎት እንዲያገኙ የሚደረግበት እድል እንደተመቻቸ አመላክተው በየጊዜው ከአምራች ኢንዱስትሪው ጋር በቅርበት ለመስራት የሚያስችል ወርክ ሾፕ መስከረም 26 ቀን 2009 ዓ.ም መዘጋጀቱን ጠቁመዋል፡፡ በዘርፉ የተሰማሩ አምራች ኢንዱስትሪዎች ኢንዲሳተፉ ጥሪ ተደርጎላቸዋል፡፡
በውይይቱ ላይ የተሳተፉት የምግብ የመጠጥና የፋርማሲዩቲካል ኢንዱስትሪ ልማት ኢንስቲትዩት ም/ዋና ዳይሬክተር ረዳት ፕሮፌሰር መሳይ ወ/ማሪያም በበኩላቸው የፋርማሲዩቲካል ኢንዱስትሪ ምርቶች በባህሪያቸው ለየት ያሉና ከፍተኛ ጥንቃቄ የሚፈልጉ ስለሆነ አየር መንገዱ ትኩረት ሰጥቶ እንዲሰራበት ጠቁመዋል፡፡ የጭነት አገልግሎቱን ለመስጠትና ምርቶቹ የሚቀመጡበትን ቦታ ለመምረጥ የምርቶችን ባህሪ ማወቅ ስለሚጠይቅ ግንዛቤን ለማሳደግ ከአየር መንገዱ ጋር በቅንጅት የሚሰራበትን ስርዓት በመዘርጋተና በመተባበር ስልጠና ኢንስቲትዩቱ እንደሚሰራ አረጋግጠዋል፡፡

በፋርማሲቲዩካል ንዕስ ዘርፍ ከቻይና ሀገር ከመጡ ልዑካን ጋር በመድሃኒት ቁጥጥርና አስተዳደር፣አሰራር እና በኢንቨስትመንት አፈጻጸምና ዕድሎች የተገኙ ተሞክሮዎች ላይ ከጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ጋር...
25/08/2016

በፋርማሲቲዩካል ንዕስ ዘርፍ ከቻይና ሀገር ከመጡ ልዑካን ጋር በመድሃኒት ቁጥጥርና አስተዳደር፣አሰራር እና በኢንቨስትመንት አፈጻጸምና ዕድሎች የተገኙ ተሞክሮዎች ላይ ከጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ጋር በመተባበር የተደረገ የልምድ ልውውጥ፣

Address

Addis Ababa
46883

Telephone

+251116394177

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Food, Beverage and Pharmaceutical Industry Development Institute posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Food, Beverage and Pharmaceutical Industry Development Institute:

Share