Asbeza Trading PLC

Asbeza Trading PLC Known Ethiopian Business sight

07/03/2022
25/10/2019
27/03/2019

ለፓስፖርት አገልግሎት መሟላት ያለባቸው ቅድመ ሁኔታዎች
1. ለአዲስ ፓስፖርት ጠያቂዎች

1.1 እድሜያቸው ከ18 ዓመት በላይ የሆነ ጠያቂዎች
 የታደሰ የቀበሌ መታወቂያ ወይም፣
 አገልግሎት ጊዜው ያላለፈበት የመንግስት መ/ቤት መታወቂያ ወይም፣
 ውጭ አገር ነዋሪ ሆነው በሊሴፓሴ የገቡ ከሆነ ወደአገር በገቡ በ6 ወራት ጊዜ ውስጥ
ሊሴፓሴውን ይዘው በመቅረብ መስተናገድ ይችላሉ፡፡
1.2 እድሜያቸው ከ18 አመት በታች ለሆኑ አዲስ ፓስፖርት ጠያቂዎች
o ፓስፖርት ሲጠየቅ ህፃኑ በአካል መቅረብ አለበት፣
1.2.1 ወላጆች ይዘው ሲቀርቡ ማሟላት ያለባቸው
 እድሜው ከ6 ወር በታች ለሆነ ህፃን የሆስፒታል የልደት ማስረጃ በማቅረብ የሚስተናገዱ ሲሆን
ከ6 ወር በላይ ለሆናቸው ህፃናት በወሳ„ኩነቶች የተዘጋጀ የልደት ሰርተፊኬት ማቅረብ
ይኖርባቸዋል፣
 መጠኑ ¾ የሆነ የህፃኑ ሁለት ጉርድ ፎቶ ግራፍ፣
 የወላጅ የቀበሌ /የመንግስት መ/ቤት መታወቂያ ወይም ፓስፖርት/፣
ፓስፖርት ለመቀየር በሚቀርብ ጥያቄ መሟላት ያለባቸው ሁኔታዎች
እድሜያቸው ከ18 ዓመት በላይ ለሆኑ፣

1 የአገልግሎት ጊዜው ያበቃ ወይም ገጽቹ ያለቁ ፓስፖርት ለመቀየር o የቀድሞው ፓስፖርት ከነኮፒው ተያይዞ ሲቀርብ፣ 2 የጠፋ ወይም የተበላሸ ፓስፖርት ለመቀየር
- ፓስፖርቱ ከጠፋ የፖሊስ ማስረጃ ወይም ውጭ ሀገር የጠፋ ከሆነ የገቡበትን ሊሴፓሴ፣ - ፓስፖርቱ ከተበላሸ የተበላሸውን ፓስፖርት ከነኮፒው አያይዞ ማቅረብ፣ ያስፈልጋል።

3 ለፓስፖርት እርማት የሚያስፈልጉ ማስረጃዎች
- ስም ለመለወጥ የፍ/ቤት ማስረጃ፣
- ፓስፖርቱ እና ለእርማት የሚያስፈልጉ መረጃዎች (የልደት ሰርትፍኬት) ዋናው ከነኮፒው መቅረብ አለበት፣ - ከ18 አመት በታች ለሆኑ የፓስፖርት እድሳት ጠያቂዎች
- የህፃኑ ፓስፖርት ዋናው ከነኮፒው፣
- ለማስፈፀም የቀረበው አባት ከሆነ የአባት የቀበሌ መታወቂያ ወይም ፓስፖርት ወይም
የመንግስት መ/ቤት መታወቂያ፣
- እናት ከሆነች የህፃኑን የልደት ሰርትፍጄት፣ የእናት የቀበሌ መታወቂያ ወይም ፓስፖርት
ወይም የመንግስት መ/ቤት መታወቂያ፣ ማቅረብ ያስፈልጋል።
የህጻኑ የፓስፖርት አገልግሎት ጥያቄ ከወላጅ ውጭ በሞግዚት ፣ በተወካይ እና በጉዲፈቻ የቀረበ ከሆነ
የሞግዚትነት የውክልና የአሳዳጊነት ወይም ጉዲፈቻ አድራጊነት የተፈቀደበት ማስረጃ አግባብ ካለው
መንግስታዊ አካል ማቅረብ ያስፈልጋል።
ማሳሰቢያ፡-
- በጊዜያዊ መታወቂያ አገልግሎት አንሰጥም፣


- ማንኛውም ባለጉዳይ የሚያቀርበው ሰነድ ህጋዊ እና ስርዝ ድልዝ የሌለው መሆን አለበት፣
- በተጭበረበረ ሰነድ ለመስተናገድ መሞከር በህግ ያስጠይቃል፡፡
ለግንዛቤዎ
1. በተደጋጋሚ ወደ ውጭ የሚመላለሱ በመሆኑ ምክንያት የፓስፖርቶ ገጾች ከፓስፖርቱ የአገልግሎት
ጊዜ በፊት ቢያልቅብዎ ባለ 64 ገጽ ፓስፖርት በአገልግሎት ላይ ያዋልን ስለሆነ መጠየቅ ይችላሉ።
2 ፓስፖርት በአስቸኳይ ለማግኘት የሚያስገድድ ሁኔታ ቢገጥሞት ተጨማሪ የአገልግሎት ክፍያ
እንዲሁም ከዚህ በታች የተመለከቱትን ማሟላት የጠበቅበታል፦
 ለህክምና ከሆነ የሕክምና ማስረጃ
 የውጭ የትምህርት ዕድል ያገኙ የጀመሩት ፕሮሰስ የሚያሳይና የተምህርት ማስረጃ
 ለመንግስት ስራ ክሆነ የመስሪያቤቱ ደብዳቤና የመ/ቤት መታወቅያ
 የውጭ አገር ኗሪ ከሆኑ መኖሪያ ፍቃድ ወይም ቪዛ
 ለDV ደርሶት ፕሮሶስ የጀመሩ
 ኢምባሲ ቀጠሮ ካላቸው የኢምባሲ ቀጠሮ ማቅረብ የሚችሉ ከሆኑ
 መንግስታዊ ባልሆኑ ድርጅቶች የሚሰሩ የድርጅቱ መታውቅያና የሚሄዱበት ምክንያት የሚገልጽ
ደብዳቤ ካቀረቡ፣
ነጋዴ ክሆኑ
o የከፈሉበት LC
o የታደሰ ንግድ ፍቃድ
o ውል ያላቸው ከሆኑ ቅድሚያ መስተናገድ ይችላሉ።
3. መንግስት ወደ መካከለኛው ምስራቅ የሚደረገው ሕገወጥ ስደት በማስቆም ሕጋዊ የውጭ አገር የስራ
ስምሪት ለማጠናከር ቁጥጥር እና ክትትል እያደረገ እንደሚገኝ ይታወቃል።

በመሆኑም ፓስፖርት ለማውጣት ወደ ኢሚግሬሽንና ዜግነት ጉዳይ ዋና መምሪያ አገልግሎት
መስጪያ ማእከላት ለምትመጡ ዜጎች የሚከተሉት ቅድመ ሁኔታዎች መሟላት
ይተበቅባቸዋል፦
ዕድሜያቸው ከ18 እስከ 55 ዓመት ለሆኑ ዜጎች ላይ ከተዘረዘሩት መስፈርቶች(ምሳሌ የቀበሌ መታወቅያ)
በተጨማሪ፦
 የመንስግት ሰራትኛ መሆናቸው የመ/ቤት መታወቅያ
 ነጋዴ ከሆኑ የታደሰ ንግድ ፍቃድ
 በግል ድርጅት ተቀጣሪ ከሆኑ የመ/ቤቱ ደብዳቤና መታወቅያ
 መንግስታዊ በልሆኑ ድርጅቶች (NGO) ተቀጣሪ ከሆኑ የድርጅቱ ደብዳቤና መታወቅያ
 ለህክምና ለሚሄዱ የሕክምና ማስረጃ
 ለትምህርት ለሚሔዱ የተጻጻፉበት ማስረጀ
 ለጉብኝት ከሆኑ የግብዣ ደብዳቤ
4. በሕጋዊ መንገድ ለሰራ ወደ ውጭ አገር የሚሄድ ማንኛውም ሰራተኛ ከዚህ በታች የተመለከቱትን ማሟላት የጠበቅበታል፦
ሀ) ቢያንስ የስምንተኛ ክፍል ትምህርት ያጠናቀቀ፣ እና
ለ) በሚቀጠርበት የሥራ መስክ አግባብ ካለው የምዘና ማዕከል (ቴክኒክና ሙያ) የሙያ ብቃት ማረጋገጫ
ማስረጃ የያዘ፣ መሆን አለበት፡፡
ሐ) ዕድሜው ከ21 ዓመት በላይ የሆነ፣
መ) የጤና ምርመራ ያደረገ መሆን እንዳአበት ይደነግጋል።


2. አዲስ አበባ ከሚገኘው የዋና መምሪያው ጽሕፈት ቤት በተጨማሪ ከዚህ ቀጥሎ በተገለጹት
ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤቶችና እንዲሁም በውጭ ሀገራት በሚገኙ የኢትዮጵያ ሚሲዮኖች ማግኘት
ይችላሉ።
1 ሀዋሳ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት
2 ደሴ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት
3 ድሬዳዋ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት
4 ባህርዳር ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት
5 መቐለ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት
6 ጅማ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት
7. ጅግጅጋ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት
8. ሳመራ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት
9. አዳማ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት

ለበለጠ መረጃ ወይም ለቅሬታ አድራሻችን
ነጻ ስልክ 8133
መደበኛ ስልክ 0111560167 ወይም 0118287216
website www.immigration.gov.et


Face book, MDINA Ethiopia
ኢሜይል support@ immigration.gov.et
ፖስታ 5741

Address

Addis Abeba, Sweden, Lund
Addis Ababa
139720

Opening Hours

Monday 08:00 - 17:00
Friday 08:00 - 17:00

Telephone

+251930439396

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Asbeza Trading PLC posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Asbeza Trading PLC:

Share