Ethio Crypto 433

Ethio Crypto 433 Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Ethio Crypto 433, Currency exchange, Ethiopian, Addis Ababa.

Airdrop ምንድነው ?➡️airdrop በክሪፕቶ ከረንሲ አለም የተለያዩ አዲስ ቶክኖች ወይም ኮይኖች ወደ ክሪፕቶ ከረንሲ ለመቀላቀል የራሳቸውን ፕሮጀክት ሲያዘጋጁ list ከመደረጋቸው ወይም ...
13/11/2024

Airdrop ምንድነው ?

➡️airdrop በክሪፕቶ ከረንሲ አለም የተለያዩ አዲስ ቶክኖች ወይም ኮይኖች ወደ ክሪፕቶ ከረንሲ ለመቀላቀል የራሳቸውን ፕሮጀክት ሲያዘጋጁ list ከመደረጋቸው ወይም ገበያውን ከመቀላቀላቸው በፊት ለተጠቃሚዎች በነፃ የሚሰጡበት መንገድ airdrop ይባላል ። airdrop ከዚህ ባለፈ ሌላኛው አላማው ተጠቃሚዎችን ማብዛት እንዲሁም ነባር የክሪፕቶከረንሲ ነባር ተጠቃሚዎችን ለመሸለም አዲስ ተጠቃሚዎችን ለማምጣት ይጠቀሙበታል ።

airdrop ምን ጥቅም አለው ?

➡️airdrop 90% የሚሆኑት free project ናቸው ይህም የተለያዩ ነፃ ቶክኖችን ለማግኘት ፣ በክሪፕቶከረንሲ ላይ ያለንን እውቀት ለማዳበር ወዘተ ጥቅሞች አሉት ። airdrop ያለምንም ወጪ የተለያዩ taskዎችን በመስራት የተዘጋጀውን የ coin airdrop መጠቀም እንችላለን airdrop የመሳካት እድሉ 50/50 በመሆኑ ወጪ የማይጠይቁ የ airdrop projectዎችን መሞከር አይከፋም ።

airdrop ለመጠቀም ምን ያስፈልጋል ?

➡️airdrop ለመጠቀም የተለያዩ የ airdrop project Join ማድረግ ያስፈልጋል በተጨማሪም በ airdrop ላይ የተወሰነ እውቀት ሊኖረን ይገባል ስለተዘጋጀው የ airdrop የተለያዩ የሶሻል ሚዲያ ገፆችን በማየት መረጃዎችን መሰብሰብ አስፈላጊ ነገር ነው

airdrop እውነት ነው ወይስ ውሸት ?

➡️የትኛውም airdrop 100% አይባልም ይህ ማለት የመሳካት እድሉ 50/50 ነው ግን የተዘጋጀው airdrop ያዘጋጀው ድርጅት የመሳካት እድሉ ላይ ልዩነት ያመጣል እንደምሳሌነት በቴሌግራም የተዘጋጀውን notcoin መመልከት እንችላለን ይህ project list በተደረገው TON ቶክን የሚታገዝ እንዲሁም ከቴሌግራም ጋር ተያያዥነት ያለው የ airdrop project ነው ይህም የመሳካት እድሉን ከፍ ያደርገዋል

💸P2P ምንድነው ?➡️P2P ማለት peer to peer ሲሆን ይህም ሲብራራ binance ላይ የሚገኙ የክሪፕቶከረንሲ ንግድ ተጠቃሚዎች ያላቸውን መሸጥ እንዲሁም የሌላቸውን የሚገዙበት መንገድ ...
13/11/2024

💸P2P ምንድነው ?

➡️P2P ማለት peer to peer ሲሆን ይህም ሲብራራ binance ላይ የሚገኙ የክሪፕቶከረንሲ ንግድ ተጠቃሚዎች ያላቸውን መሸጥ እንዲሁም የሌላቸውን የሚገዙበት መንገድ ነው ። P2P ያለማንም ሶስተኛ ወገን ሻጭ እና ገዢ እርስ በእርሳቸው ተገናኝተው የሚገበያዩበት platform ነው ።

✅ P2P ምን ጠቀሜታዎች አሉት ?

📌P2P ወይም ደሞ peer to peer ለሰዎች የፈለጉትን የክሪፕቶ ከረንሲ ልውውጥ ለመፈፀም ይረዳል እንዲሁም እንደ ኢትዮጵያ ላሉ ሀገራት የዶላር አቅርቦትን ለማግኘት ቀላሉ መንገድ ነው ''የዋጋው መወደድ እንዳለ ሆኖ'' ይህ እንዳለ ሆኖ ከP2P ገዝተን በምናገኘው ዶላር የተለያዩ online payment መፈፀም እንችላለን እንምሳሌነት ከ Amazon እቃዎችን order ለማድረግ የተለያዩ የኮሌጅ fee ለክፈል መጠቀም እንችላለን ።

P2P እንዴት መጠቀም እንችላለን ❕

➡️P2P ለመጠቀም በመጀመሪያ verify የሆነ የ binance አካውንት ሊኖራችሁ ይገባል verify ለማድረግ የራሳችን የሆነ national id ወይም passport መጠቀም እንችላለን ። በተጨማሪም መዘንጋት የሌለባችሁ ነገር verify የምታደርጉበት national id ወይም passport ግዴታ የራሳችሁ ሊሆን ይገባል ምክንያቱም በ P2P ዶላር ለመግዛትም ሆነ ለመሸጥ የምትጠቀሙት የክፍያ መንገድ verify በተደረገበት የፓስፖርት ባለቤት ስም ነው ስለዚህ ለመግዛትም ሆነ ለመሸጥ የምትጠቀሙበት የባንክ አካውንት ስም እና verify የሚደረግበት የፖስፖርት ባለቤት ስም ተመሳሳይ መሆን አለበት ።
ካልሆነ በ binance ህግ መሰረት 3rd party ወይም ሶስተኛ ወገን ተጠቃሚ ትሆናላችሁ ያ ደሞ risk አለው ።

➡️P2P risk አለው ወይ ?

➡️P2P ትክክለኛ ሻጭ እና ገዢዎች እንዳሉት ሁሉ scammer (ሌቦችም ይገኙበታል) ስለዚህ የምንገዛው ወይም የምንሸጥለትን ሰው ለይተን ማወቅ አለብን እንዴት ማወቅ እንችላለን ? binance የራሱ የሆነ የ feedback platform አለው ይህ ማለት አንድ ሰው ለሚሰራው ስራ ከተጠቃሚዎቹ የሚያገኘው ምላሽ አለ ያ ምላሽ public የሆነ ሲሆን ጥሩም ሆነ መጥፎ የተሰጠው feedback በፊት ለፊት ገፁ ላይ ይታያል ያንን በመመልከት እንዲሁም ያከናወናቸው ንግድ ብዛት ፣ ከፈፀማቸው ሽያጭ ወይም ግዢ ስንቱን በትክክለኛ መንገድ እንደጨረሰ ፣ እንዲሁም በፐርሰንት ምን ያክል የተአማኒነት ደረጃ እንዳለው በማየት እራሳችንን ከሌቦች መጠበቅ እንችላለን ። ✅

👉 binance ምንድነው ?binance በክሪፕቶከረንሲ ላይ የሚሰራ በእለታዊ የንግድ ልውውጥ በክርፒቶ ከረንሲ የምንዛሬ ልውውጥን የሚሰራ አለምአቀፍ ኩባንያ ነው ። binance 2017 በቻይ...
13/11/2024

👉 binance ምንድነው ?

binance በክሪፕቶከረንሲ ላይ የሚሰራ በእለታዊ የንግድ ልውውጥ በክርፒቶ ከረንሲ የምንዛሬ ልውውጥን የሚሰራ አለምአቀፍ ኩባንያ ነው ። binance 2017 በቻይና ውስጥ የንግድ ሶፍትዌርን በፈጠረው ቻንግፔንግ ዣኦ ነው የተመሰረተው ። ሆኖም የቻይና መንግስት ክሪፕቶከረንሲ ኩባንያዎች ላይ ገደብ በመጣሉ ወደ ጃፓን ሊዘዋወር ችሏል በአሁን ሰአት binance በ ዩናይትድ ስቴት ይገኛል ።

👉 የ binance ጠቀሜታ ምንድነው ?

binance የተለያዩ ነጋዴዎችን (trader) ምንዛሬዎችን እንዲሰሩ እንዲሸጡ እና እንዲለዋወጡ የሚያስችል ቀዳሚ የ 𝕔𝕣𝕪𝕡𝕥𝕠𝕔𝕦𝕣𝕣𝕖𝕟𝕔𝕪 ኩባንያ ነው ። እንዲሁም በ 𝕔𝕣𝕪𝕡𝕥𝕠𝕔𝕦𝕣𝕣𝕖𝕟𝕔𝕪 ላይ የሚገኙ የተለያዩ ኮይኖችን exchange ለማድረግ ይረዳል ለምሳሌነት ያክል በአለም አቀፍ ደረጃ ከፍተኛ ተደራሽነትን ያተረፈው ቢትኮይን መጥቀስ ይቻላል ። በ binance ላይ የሚገኝ የ usdt ( የዶላር) balance ልክ እንደ ቢትኮይን እንዳሉ የ 𝕔𝕣𝕪𝕡𝕥𝕠𝕔𝕦𝕣𝕣𝕖𝕟𝕔𝕪 ኮይኖች እንድንቀይር ይረዳናል ። በብዛት በኢትዮጵያ የዶላር ግብይትን ለማድረግ እንጠቀምበታለን

👉 Binance ኢትዮጵያ ሆነን እንዴት እንጠቀማለን ?

binance በአለም አቀፍ ደረጃ እገዳ ከጣሉ አንድ አንድ ሀገሮች ውጪ በሁሉም ሀገር መጠቀም ይቻላል የሚያስፈልገን (email or phone number ) እንዲሁም national id or passport ነው በኢትዮጵያ ለምንገኝ የታደሰ ፓስፖርት ብንጠቀም የተሻለ ነው ። ከላይ እንደጠቀስኩት ኢትዮጵያ ላይ በብዛት ለዶላር ግብይት ነው የምንጠቀመው ለማንኛውም የውጪ payment ዶላር በ binance ላይ ከሚገኘው P2P platform በመግዛት መጠቀም ይቻላል በ P2P platform ገዢዎችም ሆነ ሻጮች ኢትዮጵያዊ በመሆናቸው የምንጠቀመው የክፍያ መንገድ የሀገር ውስጥ ባንኮችን በመሆኑ የፈለግነውን ክፍያ ለመፈፀም ቀላል ይሆንልናል ።

ይህ ቻናል ከ ዜሮ ተነስተን እንዴት ክሪፕቶ እና ኤር ድሮፖችን መስራት እንዳለብን የምንማማርበት የፌስቡክ ገፃችን ይሆናል :: ከ4-3-3 ክሪፕቶ ጋር  መልካም ቆይታ !
13/11/2024

ይህ ቻናል ከ ዜሮ ተነስተን እንዴት ክሪፕቶ እና ኤር ድሮፖችን መስራት እንዳለብን የምንማማርበት የፌስቡክ ገፃችን ይሆናል :: ከ4-3-3 ክሪፕቶ ጋር መልካም ቆይታ !

Address

Ethiopian
Addis Ababa

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Ethio Crypto 433 posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share